Saturday, June 15, 2013

አገር በቤተሰብ ስትዘረፍ ኢህአዴግ የት ነበር?

ምህረት ገ/መድህን ገ/የስ
ትርሃስ ገ/መድህን ገ/የስ
ሀብቶም ገ/መድህን ገ/የስ
ኬኬ ኃ/የተ/የግ/ማ
ኢንተር ኮንቲነንታል ሆቴል
አዲስ የልብ ህክምና ክሊኒክ
ምፍአም ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ነፃ ትራንስፖርት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ዎው ትራንዚት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ኤምዲ ትራንዚት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ዲ ኤች ሲሚክስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

አገር በቤተሰብ ስትዘረፍ ኢህአዴግ የት ነበር?

Posted: June 15, 2013 in Uncategorized
0
“አዲስ አበባ የተገተሩት ህንጻዎችስ?”Image
በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ባለስልጣናት፣ ባለሃብት፣ ደላሎችና ባለድርጅቶች በልጆቻቸውና በቤተሰቦቻቸው ስም “ዘርፈው አስቀመጡት” የተባለው ንብረታቸውና የባንክ ሂሳባቸው መታገዱ ታወቀ። የዜናውን ይፋ መሆን ተከትሎ አዲስ አበባን ያጥለቀለቋት ህንጻዎችና የንግድ ድርጅቶች ጉዳይ ለምን ዝም ተባሉ የሚል ጥያቄ እየተሰነዘረ ነው።


Wednesday, June 12, 2013

አስቸጋሪው ነገር አገርን መገንባት ነው!!

አስቸጋሪው ነገር አገርን መገንባት ነው!!

(ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ)

ወያኔን ማስወገድ አይደለም የሚያስቸግረው፤

 

 building

አስቸጋሪው ነገር አገርን መገንባት ነው !!

“We are just leaving barbarism and are still entirely at the beginning. The French, however have already gone a piece of the way and have a century`s lead in every respect.” Friedrich the Great II to Wilhelm of Prussia

ትንሽማሟሺያ ፤”ከብርሃን ልክፍት”

ትንሽማሟሺያ ፤”ከብርሃን ልክፍት”

268970_538199819551757_896179330_nትንሽማሟሺያ ፤”ከብርሃን ልክፍት”
ድሮ ከቁርስ በፊት የሚበላ ሟሟሽያ የሚባል ምግብ ነበር፡፡ ከዛ ዋናው ቁርስ ከዛ ምሳ ከዛ ደግሞ ከእራት በፊት መክሰስ ከዛ እራት፡፡ እንዲህ ሲኖር ሲኖር ሲኖር ታጋዮቹ መጡ እና የኢትዮጵያ ህዝብ በቀን ሶስቴ እንዲበላ እናደርጋለን አሉ፡፡ እውነትም እቅዱ በጣም ስለተሳካ ማሟሽያም ጠፋች መክሰስም ጠፋች እራትም የት እንደደረሰች እነጃላቷ ቁምሳ እና ምራት ተጀመሩ፡፡ ቁምሳ ቁርስ እና ምሳን በማዳቀል ወደ አምስት ሰዓት አካባቢ የሚበላ ሲሆን ቁምራ ደግሞ ምሳ እና እራትን አዳቅሎ ወደ አስራ አንድ ሰዓት አካባቢ ይበላል፡፡ ከዛ ሰላም አሳድረኝ ብሎ ለጥ ነው፡፡




ጉድ በል ሰላሌ 2

Untitled-2
ጉድ በል ሰላሌ 2
ልክ እሁድ ነግቶ ሰኞ ሲመጣ አንዲት ማስታወሻ ለዘመዶቼ ከትቤ ነበር፡፡ ማስታወሻዋ ብዙ ምላሾችን አምጥታለች፡፡ በሌላ አባባል ገበያዋ ደርቷል ማለት ነው፡፡ በመጀመሪያ ገበያዋን ያደሯትን ሁሉ ምስጋና ላቀርብ ይገባኛል፡፡ የመከራችሁኝ፣ የተቆጣችሁኝ፣ ያመሰገናችሁኝ፣ እንኳንስ ሌላው ቀርቶ ሙልጭ አድርጋችሁ የሰደባችሁኝ ሁሉ ለኔው ብላችሁ እንደሆነ እረዳለሁ፡፡ እንዲሁም የቤተዘመድ ስድብ ከምርቃት እኩል ነው ባዬ “ገለቶማ” እላለሁ፡፡


መንግሥት ሕዝቡ ለአገሩ ዘብ እንዲቆም ጥሪ አቀረበ

መንግሥት ሕዝቡ ለአገሩ ዘብ እንዲቆም ጥሪ አቀረበ


872ede1c1b32b96ba8500685aaa6a3f8_L
የግብፅ ፖለቲከኞች ከአፍራሽ ድርጊታቸው ይቆጠቡ ብሏል
የግብፅ ፕሬዚዳንት፣ ጠቅላይ ሚኒስትርና ሌሎች የአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት ባለፈው ሰኞ በተካሄደው ብሔራዊ የናይል ኮንፈረንስ ላይ ታላቁን የህዳሴ ግድብ በተመለከተ በተንፀባረቀው አፍራሽ መልዕክት የተበሳጨው የኢትዮጵያ መንግሥት፣ “ሕዝቡ ለአገሩ ዘብ እንዲቆም” ሲል ጥሪ አቀረበ፡፡ የግብፅ ፖለቲከኞችም ከአፍራሽ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስቧል፡፡



ወያኔ በሁመራ ከአርበኞች ጋር መዋጋቱን አመነ

ወያኔ በሁመራ ከአርበኞች ጋር መዋጋቱን አመነEthiopian People Patriotic Front fighters

June 12, 2013 ECADF – ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር “ነበልባል” በመባል የሚታወቀው ባብዛኛው በወጣቶች የተገነባው ተዋጊ ሀይል በሁመራ አካባቢ 35ኛውን የወያኔ ክፍለጦርና ሚሊሻዎችን ገጥሞ አንጸባራቂ ድል እንደተቀናጀ አስታውቆ ነበር። ዜናውን ለመመልከት እዚህ ይጫኑ።
ቁስለኞቹን እና የተገደሉ ወታደሮቹን ሲያሸሽ የከረመው ወያኔ ከሶስት ሳምንታት በሗላ አርበኞችን ገደልኩ… ብሎ ዜና ሰርቶ ለቋል።
በሁመራ አካባቢ የተደረገውን የአርበኞቹን የውጊያ ውሎ የግንባሩ ሬድዮ በበኩሉ እንደሚከተለው ዘግቦታል፣
“35ኛው የወያኔ ክፍለጦር አባላት አዳዲስ ኦራል መኪና በመንዳትና አዳዲስ ዩኒፎርም በመልበስ አስፈሪ የጦር ሀይል ይመስሉ ነበር… ይሁንና ያን ሁሉ ኩራት እና መመጻደቅ ግንቦት 24 ቀን ነበልባሉ አርበኛ ውሀ ቸልሶበታል.. አዳዲሶቹ ኦራል መኪኖችም የወያኔዎቹን ቁስለኛና ሟች ወታደሮች ሲያጓጉዙ ሰንብተዋል።”
እንደ ሬድዮው ዘገባ የጎንደር ነዋሪዎች በአርበኞቹ የወጊያ ብቃትና ጀግንነት እጅግ ተደንቀዋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ሬድዮ ዘገባን ያዳምጡ።
2. EPPF ሬድዮ (ሰኔ 1 – 2005)
Stopped
Play Pause
Stop
Next»
«Prev
HIDE PLAYLIST

Tuesday, June 11, 2013

የሃይማኖት አባቶችና የሰብአዊ መብት ድርጅቶች የካናዳ ፓርላማ አባላት በተሳተፉበት ውይይት ለሃገራችን ችግሮች አማራጭ አቀረቡ

የሃይማኖት አባቶችና የሰብአዊ መብት ድርጅቶች የካናዳ ፓርላማ አባላት በተሳተፉበት ውይይት ለሃገራችን ችግሮች አማራጭ አቀረቡ


የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) አባል የሆነው የኢትዮጵያ ፖለቲካ እስረኞች አንድነት ኮሚቴ (SOCEPP Canada) ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል የካናዳ ዋና ጽህፈት ቤት በመተባበር በኦታዋ (ካናዳ) ጁን 4 ቀን 2013 ያካሄደው የአንድ ቀን ውይይት በተሳካ ሁኔታ መደምደሙን ሸንጎ ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫ አስታወቀ።
Read more:http://www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2013/06/ottawa-conference-report-june42013-revised.pdf

ዶ/ር መራራ ጉዲና “ለእኛ እንቢ የተባለው ሰልፍ እንዴት ለእነርሱ ለሰማያዊዎቹ መሆኑ ነው ተፈቀደ?”

ዶ/ር መራራ ጉዲና “ለእኛ እንቢ የተባለው ሰልፍ እንዴት ለእነርሱ ለሰማያዊዎቹ መሆኑ ነው ተፈቀደ?”


የሰማያዊው ፓርቲ ሰልፍ ሰሞኑን አነጋጋሪ ሆኖዋል፤ ገናም አነጋጋሪነቱም ይቀጥላል። መድረክን በተለይም ደግሞ ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ እና ዶ/ር መራራ ጉዲና የሰጡትን አስተያየት በተመለከተ የምጽፈውን ነገር አሰበኩኝ እና ብዕሬ ልተፋብኝ የምትችውን የቃላት ውርጅብኝ በመፍራት ላልፋቸው ወደድኩኝ…. ቢያንስ እነዚህ ሰዎች ስለእኔ እና ስለራሳቸው ሲሉ ደክመዋል እና እግዚአብሔር ድካማችሁን ይቁጠርላችሁ፣ በቁማችሁ ኢትዮጵያ ነጻ ወጥታ ለማየት ያድላችሁ በማለት ለመመረቅ እወዳለሁኝ። ደግሞ በተለያዮ ጊዜአት የሚያነሱዋቸውን አተያየት በተመለከተ ሰምቶ እንዳልሰማ ቅር ተሰኝቶ ቅር እንዳልተሰኘ በመሆን ዝም ብሎ ማለፉንም አልወደድኩትምና የማደርገውን አሰብኩኝ ለጥቂት ጊዜም….ምን ላድርግ ይሆን? በማለት እያሰብኩ…እያወረድኩኝ… እያጠነጠንኩኝ ሳለ በአንድ ወቅት በአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ ተማሪ እያለሁኝ ዶ/ር መራራ ጉዲና ስለ ግል ሕይወታቸው ፣ ስለ ቤተሰባቸው እና ስለ አጠቃላይ ስለ መላው እምነታቸው ከተወሰንን የዮኒቨርስቲው ተማሪዎች ጋር በመሆን አዘውትረው መኪናቸውን ከሚያቆሙበት ስፍራ ሄደን የተለያዮ ጥያቄዎችን ጠይቀናቸው…. ዶ/ር መራራ ግልጽ እና ተግባቢ ሰውን አቅራቢ የሆኑ ሰው ናቸው እናም በወቅቱ ለጥያቄዎቻችን ሁሉ ያገኘነውን ምላሽ አልረሳውም….. አንዳንዱ ምላሻቸው በተለይ ቤተሰብን፣ ትዳር እና ልጆችን በተመለከተ የዶ/ር መራራ መስዋዕትነት ትልቅ መሆኑን አስገንዝቦኝ ነበረና ነው። ምንም እንኳን አሁን ሰማያዊዎቹን በተመለከተ የሰጣችሁት አተያየት ባልስማማም እናንትን ከልቤ ማክበሬን በመግለጽ ወደ ፍሬ ነገሬ ወይ ወደ ፍሬ ከርስኪዮ ልግባ ( በቅንፍ ለእኔ ፍሬ ነገር የሆነው ለሌላው ፍሬ ከርስኪ ቢሆንስ ብዮ ነው)።



የሰማያዊ ፓርቲ ተስፋ

የሰማያዊ ፓርቲ ተስፋ

June 11, 2013ከታክሎ ተሾመ
ወያኔ / ኢሕአዴግ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረበት ቀን ጀምሮ በአገርና በሕዝብ ላይ የሚደርሰው እልቂት ከፍተኛ ስለመሆኑ ነጋሪ የሚያስፈልግ አይመስለኝም።  የከፋፍለህ ግዛውን ይትባህል ለማስወገድም ሆነ እድሜውን ለማስቀጠል  በደጋፊና  በተቃዋሚ  መካከል ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ ትግል ተካሂዷል።  በዘር ላይ የተመሰረተ አገዛዝ ዛሬም ሆነ  ነገ  እልቂትን ይጋብዛል፤ እየታየ ያለውም እልቂት ነው።


ውጭም ሆነ አገር ውስጥ ድርጅት መሰረትን ያሉት  የትግል ስልታቸውም ሆነ ጥንካሬያቸው አንድነትን የተላበሰ ባለመሆኑ ከራሳቸው ፍጆታ ውጭ ለሕዝብ የሚጠቅም ሥራ  እየሰሩ አለመሆናቸው  በየጊዜው እየታየ ነው። በየጊዜው ሥማቸውንና መልካቸውን እየቀየሩ የሚወለዱ ድርጅቶችና ስቪክ ማኅበር ስብስቦች የሕዝቡ ትግል እንዲወሳሰብና አንድ ወጥ እንዳይሆን  አድርጐታል።
The long youth march to freedom and dignity has begun in Ethiopia. It is beautiful.
በቅርቡ ወጣቱን ማዕከል ያደረገ ሰማያዊ ፓርቲ የተባለው ወጣቱን በማደራጀት ሥር-ነቀል ለውጥ ለማምጣት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል። በመሆኑም  ሰማያዊ ፓርቲ ከዚህ ቀደም እንደ አሸን ከፈሉ ድርጅቶች በተሻለ ሁኔታ የትግል ስልት የተከተለ ይመስላል።

ኢትዮጵያ በቀረርቶ ተደናግጣ ለሰከንድ የግድብ ግንባታዋን አታቆምም – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ኢትዮጵያ በቀረርቶ ተደናግጣ ለሰከንድ የግድብ ግንባታዋን አታቆምም – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

969694_588045714550673_1440883208_n
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን አስመልክቶ የግብፅ አንዳንድ ባለስልጣናት ፣ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና የተለያዩ ማህበራት ሀላፊዎች ሲያካሂዱ የከረሙትን አፍራሽ ፕሮፖጋንዳ በተመከለተ ዛሬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ሰጥቷል ።


ሚኒስቴሩ በመግለጫው ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ ያላትን ገንቢ አቋም ገልፃ ነገር ግን በግብፅ በኩል የአገሪቱን አቋም በኢትዮጵያ የግብፅ አምባሳደርን ከአንዴም ሁለት ጊዜ ጠርታ መጠየቋንና ለግብፅ መንግስት ጥያቄ ማቅረቧን ያስታውሳል ።

“የአባይ ግድብ የህይወትና ሞት ጉዳይ ነው” የግብፅ ጠቅላይ ሚንስትር

“የአባይ ግድብ የህይወትና ሞት ጉዳይ ነው” የግብፅ ጠቅላይ ሚንስትር

ካለፉት ጥቂት ሳምንታት ወዲህ ከሃገራችን፣በምስራቅና ሰሜን አፍሪካ እስከ መካከለኛው ምስራቅ ድረስ የሚሰማው የጂኦ– ፖለቲካ ትኩሳት በዓባይ ወንዝ ተፋሰስ ልማት ላይ ያተኮረ መሆኑ ለሁላችንም ግልጽ ነው:: በተለይ ደግሞ  ወያኔ “ታላቁን የህዳሴ ግድብ” ግንባታ በማካሄድ ረገድ የወንዙን ተፈጥሮአዊ አቅጣጫ ማስቀየሩን በፕሮፖጋንዳ ማሽኖቹ እንደ “ትልቅ ድል” መለፈፍ ከጀመረ በኋላ የግብጽ መንግስትና ህዝቧን አስቆጥቷል፣ የወታደራዊና ፖለቲካዊ ብቀላና ጥቃት እርምጃ አማራጮችም በኢትዮጵያ ላይ ለመውሰድ ምክክሩ ተጧጡፏል::

Ethiopian dam “a matter of life or death”: PM

Prime Minister Hisham Qandil discusses Egypt's options in dealing with the Ethiopian Renaissance Dam during a speech to the Shura Council on Monday (Photo Cabinet handout)
The Ethiopian Renaissance Dam will negatively affect Egypt’s share of water from the Nile River and compromise the electricity it generates from it, Prime Minister Hesham Qandil announced on Monday.
Qandil called the water crisis “a matter of life or death” and a “high-level national security issue” in an 

Monday, June 10, 2013

ዜና በጨዋታ፤ የፍትህ ሳምንት በኢትዮጵያ ተቀበረ (ተከበረ ማለቴ)

ETHIOPIA AFRICAN UNION MEETING
ዜና በጨዋታ፤ የፍትህ ሳምንት በኢትዮጵያ ተቀበረ (ተከበረ ማለቴ)
በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ዳኞች፣ የፍርድ ቤት ሰራተኞች፣ የማረሚያ ቤት ፖሊሶች እና የፍትህ ሚኒስቴር ሰራተኞች በመሆን ከሜክሲኮ አደባባይ እስከ ልደታ ፍርድ ቤት በፖሊስ ማርሽ ታጅበው ስለ ፍትህ እየዘመሩ የፍትህ ሳምንት አከባበርን አንድ ብለው ጀመሩ፡፡


ወቅታዊው የአባይ ወንዝ ዲፖሎማሲ፣ ፖለቲካዊ ብዥታውና እንደምታው

ወቅታዊው የአባይ ወንዝ ዲፖሎማሲ፣ ፖለቲካዊ ብዥታውና እንደምታው


ዶ/ር ዘላለም ተክሉ – 06/10/2013
መግቢያ
ካለፉት ጥቂት ሳምንታት ወዲህ ከሃገራችን፣በምስራቅና ሰሜን አፍሪካ እስከ መካከለኛው ምስራቅ ድረስ የሚሰማው የጂኦ ፖለቲካ ትኩሳት በዓባይ ወንዝ ተፋሰስ ልማት ላይ ያተኮረ መሆኑ ለሁላችንም ግልጽ ነው:: በተለይ ደግሞ  ወያኔ “ታላቁን የህዳሴ ግድብ” ግንባታ በማካሄድ ረገድ የወንዙን ተፈጥሮአዊ አቅጣጫ ማስቀየሩን በፕሮፖጋንዳ ማሽኖቹ እንደ “ትልቅ ድል” መለፈፍ ከጀመረ በኋላ የግብጽ መንግስትና ህዝቧን አስቆጥቷል፣ የወታደራዊና ፖለቲካዊ ብቀላና ጥቃት እርምጃ አማራጮችም በኢትዮጵያ ላይ ለመውሰድ ምክክሩ ተጧጡፏል:: በኢትዮጵያ በኩልም ገዢው መንግስት ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም በአንድ በኩል ግብጽ ልማታችንን ልታሰናክል እየጣረች ነው፣ተቀዋሚዎችም የግብጽ ተባባሪ እየሆኑ ነው ብሎ በማላከክ እየተፋፋመ የመጣውን የህዝብ የለውጥ ንቅናቄ ለማርገብ እያሴር ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ የግብጽን መንግስት ግድቡን በተመለከተ “Win –Win Diplomacy” እንደሚከተል በመደጋገም እየተለማመጠ ይገኛል::Rile river facts and information in Amharic
የእኔን ትኩረት የሳበው በተለይ ከአገዛዙ በቀጥታም  ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ተጠቃሚ በሆኑትና በየዋህነት ድጋፋቸውን የሚገልጹት (ከሊቅ እስከ ደቂቅ ያሉ) ወገኖቻችን ዓባይን በተመለከተ “Win –Win” የተባለውን ዲፕሎማሲያዊ አማራጭ ግብጽ ጦርነትም ከመረጠች ድባቅ እናደርጋታለን ከሚል ስሜት ጋር እየደበላለቁ መጠቀም እንደፋሽን አይሉት እንደልማድ በስፋት መያያዛቸው ነው::.

አቶ ኦባንግ ለአቶ ለኃይለማርያም ግልጽ ደብዳቤ ላኩ (ለማሰር መጣድፍ እንደማያዋጣ አስጠነቀቁ)

አቶ ኦባንግ ለአቶ ለኃይለማርያም ግልጽ ደብዳቤ ላኩ (ለማሰር መጣድፍ እንደማያዋጣ አስጠነቀቁ)http://ethiopia.ecadf.netdna-cdn.com/Amharic/wp-content/uploads/2013/05/obang1-620x310.jpg


ባለፈው እሁድ በሰማያዊ ፓርቲ የተጠራውንና በሰላም የተጠናቀቀውን ሰላማዊ ሰልፍ በማስመልከት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ለጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ ግልጽ ደብዳቤ ላኩ፡፡ በደብዳቤው ላይ ኢህአዴግ ሰልፈኞቹንም ሆነ የፓርቲውን አመራሮች ለማሠር የሚያደርገውን ሃሳብ ከመፈጸም እንዲቆጠብ ማስጠንቀቂያ ልከዋል፡፡
አቶ ኦባንግ በደብዳቤያቸው ላይ በርካታ ጉዳዮችን የዳሰሱ ሲሆን በቅድሚያ ግን ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ሠልፉን በመፍቀዳቸው ሊመሰገኑ እንደሚገባ ጠቅሰዋል፡፡ ይህንንም በማድረግ ከቀድሞው መሪ መለስ እንደሚለዩና ምናልባትም ህዝብን ለማዳመጥ ፍላጎት እንዳላቸው ጠቋሚ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ምክንያቱንም ሲያስረዱ መለስ በእንደዚህ ዓይነቱ ሠልፈኞች ላይ የህወሓት አልሞ ተኳሾች ተኩስ በመክፈት እንዲገደሉ ማድረገቸውና የፓርቲ አመራሮችን ማሳሰራቸውን እንደ ማስረጃ ጠቅሰዋል፡፡


የሕግ ማዕቀፍ ለናይል ፖለቲካ ምኑ ነው? (ክፍል ፪)

የሕግ ማዕቀፍ ለናይል ፖለቲካ ምኑ ነው? (ክፍል ፪)


በሚኪያስ በቀለ
(ማስገንዘቢያ፤ በዚህ ጽሑፍ ላይ የተገለጹት ቀኖች፣ ወሮች እና ዓመተ ምኅረቶች በሙሉ በኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር ናቸው፡፡)
የተፋሰስ ውኃ የሕግ መርሖች እና አፈጻጸማቸው
የናይል ተፋሰስ ካለበት የከረመ የውኃ ፖለቲካ ግጭት በተጨማሪ የተፋሰስ ውኃ የሕግ ማዕቀፎች ላይ የተገለጹ መሠረታዊ የሕግ መርሆች ለአፈፃፀም አስቸጋሪ እንደሆኑ የተለያዩ የሕግ ልሒቃን ይገልጻሉ፡፡ ከእነዚህ የተፋሰስ ውኃ የሕግ መርሖች ውስጥ ዋነኞቹ በምክንያዊ እና በዕኩልነት የመጠቀም መርሕ (Reasonable and Equitable utilization) እና ሌሎች ተፋሰሶችን ያለመጉዳት መርሕ (No Harm/Appretiable Harm) ናቸው፡፡ZONE 9
በምክንያዊ እና በእኩሌታ የመጠቀም መርሕ (Reasonable and Equitable utilization) በተባበሩት መንግሥታት በ1997 ላይ በወጣው የዓለም አቀፍ ስምምነት (UN Convention on the Law of the Non-navigational Uses of International Watercourses) አንቀጽ 5 ላይ ተገልጾአል፡፡ እንዲሁም በአዲሱ የናይል ተፋሰስ የሕግ ማዕቀፍ ክፍል 2 አንቀጽ 4 ላይ ተደንግጓል፡፡

የአባይ ኢትዮ-ግብጽ ጦርነት ወይንስ የነፃነት ትግላችን!

የአባይ ኢትዮ-ግብጽ ጦርነት ወይንስ የነፃነት ትግላችን!

(ግርማ ሞገስ)nile_basin_countries
አምባገነኖች ስልጣናቸውን ለማጠባበቅ አጋጣሚውን ሁሉ ይጠቀማሉ። ሰሞኑን የአባይን ግድብ አስታከው አምባገነኖቹ ህውሃት/ኢህአዴግ እና የግብጽ መንግስት መምታት የጀመሩት የጦርነት ከበሮም ከዚህ የተለየ አይደለም። የህዝባቸውን ብሄራዊ ክብር ስሜት ተቆጣጥረው የዲሞክራሲ ኃይሎችን ለማዳከም እና ስልጣናቸውን ለመጠጋገን የሚያደርጉት ድራማ ነው። ኢትዮ-ግብጽ ጦርነት አይቀሬ አይደለም። የግብጽ ዴሞክራሲ ኃይሎች ወደ ጦርነት አይሄዱም። የኢትዮጵያ ሰላማዊ ትግል ወታደር አይኑን ከነፃነት ትግሉ መንቀል የለበትም።



Part 2 Ethiopian Muslims community in South Africa show their solidarity with the Ethiopian Mus...


የዳውድ ኢብሣ ኦነግ ለተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ የጻፈው ደብዳቤ አማርኛ ትርጉም

ሰሞኑን ለድረገፆች የላክኋትን አንዲት ትርጉም ቢጤ ተመርኩዘው ብዙዎች ሲቆራቆሱባት ታዘብኩ፡፡ የኢሣቱ ልጅ ተክሌ የሚላት http://www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2013/06/dawd-ibsa.jpgነገር ትዝ አለችኝና በዚህ አጋጣሚ እሷን አስታውሼ ወደድኩለት፤ በቀጥታ ላልጠቅሰው እችላለሁ – የምጽፈው ነገር አቧራ ካላስነሳ የጻፍኩ አይመስለኝም – ይላል ልጅ ተክሌ፤ እውነቱን ነው፡፡ እየበሉ እየጠጡ ዝም… የሚባለው የመደሰቻ ድግስ ብሂል እንኳን መብላት መጠጣታቸው ስለሚታይ ነው፡፡ የአንድ ጽሑፍ መነበብና አለመነበብ የሚለካው ደግሞ እንደዚህ ዓይነት ሰላማዊ ውርክብ ሲታይ ነው፡፡ በነገር መነታረክ መጥፎ አይደለም፤ ከብዙ ተጨቃጫቂ መካከል አንድና ሁለት የሚማማር ሰው ማግኘት ቀላል አይደለምና፡፡ ፍሬና ገለባ ከሚለይባቸው መንገዶችም አንዱ ይሄኛው ነው፡፡ ‹ከአነጋገር ይፈረዳል፤ከአያያዝ ይቀደዳል› እንደምንል፡፡ ዛሬ ደግሞ በ‹ጠዓመኒ ድግመኒ› የትግርኛ ብሂል መሠረት አንዲት ነገር ተርጉሜ ማስነበብን ወደድኩ፡፡ የዛሬው ወደአማርኛ በከፊል የተመለሰ ጽሑፍ ቀደም ሲል ከድረ ገፅ ያወረድኩትና ለክፉ ቀን ሳይሆነኝ አይቀርም ብዬ እንዳይዘነጋኝ በ‹ሾርት ከት› የኮምቡጦሬ ደስክቶፕ ላይ ያኖርኩት አንድ አስደናቂ የኦነግ ደብዳቤ ነው፡፡ የደብዳቤ መለያውን ፍርማት(head letter) በኦሮምኛ፣ በዐረብኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች ያዘጋጀው ይህ ግምባር የጌቶቹንና የጃዝ ባዮቹን የኤሪዎች ትግርኛ – የኛም ነው ለነገሩ – አለመጨመሩ ገርሞኛል፡፡ (ሰዎች እየተጃጃሉ የማያስፈልግ ግጭት ውስጥ የሚዘፈቁት እኮ ቋንቋን ልክ እንደ አንድ የምርት መገልገያ መሣሪያ ወይም ልክ እንደሸሚዝና ከናቴራ ከመቁጠር አልፈው በዘር ሐረግ ባሕርያዊ ውርስ ከአባት ወደ ልጅ እንደሚተላለፍ ትልቅ ቁም ነገር እየቆጠሩ 


ሥነ ልቦናዊ ቀውስ በመግባታቸው ነው – እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በዚህም ላይ እመለስበ