Sunday, January 12, 2014

ማገዶ!

January 12, 2014
… አንተ ምን አለብህ ሁልጊዜም ነዲድ ነህ
ለኋላህ ተከታይ ቋያና ሀዲድ ነህ።
ትኩስነት ዕዳ ….
የማገዶ ፍዳ ….
 ከሥርጉተ ሥላሴ
እውነት ለመናገር ከዬካቲት በፊት በአጭር ጊዜ ላልመለስ ወስኜ ነበር። ብቻ እንዲህ ሆነላችሁ … ተክዤ ቆዬሁ። አፍጥጬም አዬሁት። ባለፉት ሳምንታት ዘሀበሻ ላይ የአንድነት ልዩ ጉባኤ ውጤትን ጀመርኩት። መጀመር ነበረብኝና ውስጤን አናጋርኩት – የግድ። የአዲሱን የአንድነት ልዩ ጉባኤ ተመራጮችን ዝርዝር አዬሁት። አቶ ሸፍጠኛው ሂደት …. አንተ ምን አለብህ ቀልድ። ዬደላህ! መለስህ መላስህ ግራጫ ያሰኛኃል …. ዛሬም አዲስ ትወና ይዘህ ከች … አታካች።‹‹ከእስረኞች ሁሉ ህገ-መንግስታዊ መብቴ ተጥሶ ዘመድ አዝማድ እና ጓደኛ እንዳይጠይቀኝ የተደረኩት እኔ ነኝ››
እርግጥ በሂደቱ  የቀድሞ የአንድነት ምክትል ሊቀመንበር እሩቅ አሳቢው እስረኛው አቶ አንዱአለም አራጌ በጣም እንደ ተደሰተ ዘሀበሻ ላይም አንብቢያለሁ። በሌላ በኩልም ትናንትና በ07.01.2014 ዝርዝር መረጃ ስለመርጫው ሂደት „ከቃሌ ሩም“ አዳምጫለሁ። የቃሌ ሩም ከአቶ ሃብታሙ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ እንደ አዳመጥኩት ከሆነ ምርጫው ዲሞክራሲ እንደ ነበረ ብቻ ሳይሆን አዲሱ አመራር በቃሊቲ እስር ቤት ከአቶ አንዱአለም አራጌ ጋር የነበረውን ቆይታ ምን ይመስል እንደነበርም በዝርዝር ተገንዝቤያለሁ። ያንገበገበኝ ጥቄ ይነሳል በማለት ጓጉቼም ነበር። የሆነ ሆኖ „አቶ አንዱአለም አራጌ  ዘግይቶ ሊታይ የሚገባው የአማራሩ ጥንካሬ ከ15 ዓመት በፊት መቅደሙ እንደ አስደሰተው ከደቡብ አፍሪካ የነፃነት ትግል ጋር በንጽጽር ሲያው በጣምም እንደተደነቀ ተስፋም እንደጣለበት“ ነበር አቶ ሃብታሙ የገለጹት። መልካም ነው …


ሻምበል ጉታ ዲንቃ፤ ጊዜውን ጠብቆ ይነጋል (ፕ/ር መስፍን ወልደ-ማርያም)

January 11, 2014ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
በአሁኑ ጊዜ ወያኔ ሰውን እያፈረሰ፣ ማህበረሰብን እያፈረሰ ሰማይ-ጠቀስ ሕንጻዎችን በሚሠራበት ጊዜ፣ ከትናንት ወዲያ የሰዎችን ቤቶች አፍርሶ ትናንት የመኪና መንገድ ከሠራ በኋላ ዛሬ መንገዱን አፍርሶ የባቡር መንገድ እየተሠራ አዲስ አበባ በትራፊክ መጨናነቅ መኪና መንዳት አደገኛ በሆነበት ጊዜ፣ ዛሬ ባለሥልጣኖች የሚሠሩት ጠፍቶአቸው የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ የሚባለውን በአማካሪዎች ከሞሉት በኋላ ለሚኒስትሮችም አማካሪ መሾም በተጀመረበት ጊዜ፣ ዛሬ በሳኡዲ አረብያ ኢትዮጵያውያን እንደአደገኛ አውሬ እየታደኑ በሚደበደቡበት፣ በሚታሰሩበት፣ በሚደፈሩበትና በሚገደሉበት ጊዜ፣ ዛሬ በኬንያና በዩጋንዳ እንዲሁም በእሥራኤል ኢትዮጵያውያንን የማንገላታት ዝንባሌዎች በሚታዩበት ጊዜ፣ ዛሬ ኢትዮጵያውያን ከስዊድን እስከአውስትራልያ እየተሰበሰቡ በመጮህ ለማይሰሟቸው ሁሉ አቤቱታቸውን በሚያቀርቡበት ጊዜ፣ ዛሬ በተለያዩ አገሮች በኢትዮጵያውያን ላይ በሚፈጸመው ጥቃትና በደል፣ አለሁላችሁ የሚል መንግሥት በሌለበት ጊዜ —- ዛሬ ታሪካዊትዋ ኢትዮጵያ፣ ራሳቸውን የሚያከብሩና ኩራት ራታችን የሚሉት ኢትዮጵያውያን አልቀው ለሆድ በየሰው አገር መሰደድ ባህል በሆነበት ጊዜ፣ ዛሬ ዶር. በድሉ ዋቅጅራ ስለኢትዮጵያና ስለኢትዮጵያውያን ውርደት ደጋግሞ የነፍሱን ኡኡታ ባሰማበት ጊዜ በድንገት አንገታችንን ቀና አድርጎ ኩራታችንን ሊያስጎነጨን የሞከረ ሰው ተገኘ! ኢትዮጵያ ሁሌም የተአምር አገር ነች።Capitain Guta Dinka an Ethiopian soldier, responsible for Madiba's safety during his stay
በታላቁ ሰው በኔልሰን ማንዴላ እረፍት ምክንያት አንድ ተደብቆ የኖረ ክቡር ኢትዮጵያዊ ብቅ አለ፤ ማንዴላ ለሥልጠና በኢትዮጵያ በነበረበት ጊዜ ምናልባትም እንግሊዞች ማንዴላን ሊያስገድሉ ከጠባቂዎቹ አንዱ የነበረውን ወታደር በገንዘብ ገዝተው ዓላማቸውን ለመፈጸም አቅደው ነበር፤ ወታደሩ ገንዘቡን ከተቀበለ በኋላ ሀሳቡን ለውጦ ገንዘቡን ለአለቃው ሰጠ፤ ማንዴላ ከሞት ተረፈ፤ አንድ ተራ ኢትዮጵያዊ ራሱንና አገሩን የሚያስከብር ሥራ ሲሠራ የሚኮሰኩሳቸው ባለሥልጣኖች ለእነሱ የማይተላለፍ ክብር በመሆኑ ተዳፍኖ እንዲኖር አደረጉት፤ እነሱ ሞተው ወይም ተሰድደው ሲያልቁ የተዳፈነው ምሥጢር ብቅ አለ፤ ባለሥልጣኖቹ ሸልመውት ይሆናል፤ ግን አላከበሩትም፤ ሻምበል ጉታን ያከበረው የማንዴላ ሞት ነው፤ የሚያሳዝነው ማንዴላ ይህንን የሱን ሕይወት ለማትረፍ ሁለት ሺህ ፓውንድ ያጣውን ኢትዮጵያዊ ወታደር ሳያውቀው መሞቱ ነው።

የኢትዮጵያ አርበኞች ታሪካቸው ተቀብሮ የቀረው እንዲህ እየሆነ ነው፤ ታዴዎስ ታንቱ ሥራዬ ብሎ የተረሱ አርበኞችን ከመቃብር እያወጣ ያስተዋውቀናል፤ በሌሎች አገሮች እንደዚህ ለአገር ትልቅ ፋይዳ ያለው ሥራ በአንድ ሰው በበጎ ፈቃድ የሚሠራ ሳይሆን ዋና የመንግሥት ተግባር ነው።


ሻምበል ጉታ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ባይሆንም ራሱን ችሎ ለኔልሰን ማንዴላ መቃብር ደርሶአል፤ በአገር ደረጃ በሥልጣን ወንበሮቹ ላይ ለአገር የሚያስቡ ሰዎች አለመኖራቸውን ለማወቅ ግሩም ማስረጃ ነው፤ ለቀብር የሄደው ባለሥልጣን ሻምበል ጉታን ይዞ ቢሄድ ኖሮ ለራሱም ሆነ ለአገሩ ክብርና ጌጥ ይሆንለት ነበር፤ ለደቡብ አፍሪካ ሕዝብም ሆነ ለዓለም በመላ አንድ ኢትዮጵያዊ ወታደር አልሸጥም-አልለወጥም ብሎ የኔልሰን ማንዴላን ሕይወት ማትረፉን በማስታወቅ አገሪቱን ያስከብር ነበር፤ የታፈነው ታሪክ አፈትልኮ ሲወጣ ከስደተኞች ጋር ተያይዞ መሆኑ ኢትዮጵያ የደረሰችበትን የአደባባይ መክሸፍ የሚያሳይ ነው፤ ባለቤት ያቀለለውን አሞሌ ባለዕዳ ተቀበለው፤ መንግሥት ያፈነውን ክብር ስደተኞች አጌጡበት!


ለእኔ አሁን አንድ ጥያቄ ይቀራል፤ ሻምበል ጉታ የአገሩን ክብር ከራሱ ጥቅም በላይ በማድረጉ፣ የተቀበለውን አደራ በመጠበቁ ቢያንስ ሁለት ሺህ ፓውንድ አጥቷል፤ እንዳጣ ሊቀር ነው? ቢያንስ የከፈለውን ሁለት ሺህ ፓውንድ ወይስ ያንን አሥር እጥፍ አድርገን እንከፍለዋለን? ሻምበል ጉታን የምናመሰግነው በርጥቡ ነው በደረቁ? እኛ ያለጥርጥር ኮርተንበታል፤ ሁላችንም በኢትዮጵያዊነታችን የሱን ክብር በመጋራት ራሳችንን አክብረናል፤ ሻምበል ጉታም በእኛ እንዲኮራና በእኛ እንዲከበር ማድረግ ያለብን ይመስለኛል፤ ስለዚህ ምን እናድርግ? ለራሱ ክብር፣ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ክብር ሲል የከፈለውን እስቲ ከወሬ ያለፈ ነገር እናስብና ለዚህ ጀግና የምንችለውን አድርገንለት እግዚአብሔር ዕድሜ ይስጥህ እንበለው።

የቀደምቶቹን ወንጀል ለማጋለጥ መቃብር ሲምስ የኖረው ወያኔ በራሱ ጦር ካምፕ ውስጥ የተገኘውን አስከሬን መደበቅ ለምን አሰፈለገው?

January 11, 2014Ginbot 7 weekly editorialአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ፈረንሳይ ለጋሲዮን በሚገኘው የክብርዘበኛ ጦር ካምፕ ውስጥ ማንነታቸው ያልታወቁ የ6 ዜጎች አስከሬን ለመንገድ ሥራ በተሠማሩ ቆፋሪዎች አማካኝነት መገኘቱ የሰሞኑ አሳዛኝ ዜና ነው።
አንድ አይነት ቀለም ባላቸው ብርድ ልብሶች ተጠቅልለው ከተገኙ 6 አስከሬኖች የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሰለባዎች ታስረውበት የነበረው የእጅ ሰንሰለታቸው እንኳ እንዳልወለቀና ከተቀሩት የአንዱ እጆች ደግሞ የፍጥኝ ወደ ኋላ እንደታሰሩ መገኘታችው ግድያው በቅርብ እንደተፈፀም አንዱ አስረጂ ነው።

ዘመኑ በፈቀደው የአረብ ሃገር ስደትን በኮንትራት ስራ የሳውዲን ምድረ በዳ የባለ ጸጎች ሃገር የረገጠከው ራስክን ደግፈህ ፣ ወላጅ ቤተሰብ፣ ዘመድ አዝማድ ወገኖችህን ለመደገፍ ነበር ። በሳውዲ ቆይታህ በትዕግስት ስታልፍ ያስብከውን ሁሉ ባይሳካም ጋብቻ መስርተህ ሌላዋን የኮንትራት ሰራተኛ ስደተኛ እህትክን ባንድ አቅፈህ ፣ ራስክን በሙያ አንጸህ የተረጋጋ ኑሮን በመኖርህ ላይ እንዳለህ ሳታስበው በውስጠ ደዌ በሽታ ተወጋህ ! ክፉውን ሁሉ የስደት ህይወት በትዕግስት ገፍተህ ደስተኛ ሆነህ ኑሮን ትገፋ እንደነበር አህትህና ባለቤትህ ቅሪት ገላህን ወደ ሃገር ለመሸኘት ለስንብት ስንጓዝ አጫውተውኛል። ፎቶህን አይቸ በህይወት ዘመንህ በአንድ አጋጣሚ አውቅህ እንደነበር ሳውቅ ደነገጥኩ ፣ ድንጋጤየን ዋጥኩት ! ነፍስህን ይማረው ወንደም አለም
ስንብት …


ወደ አልሰሜ እናትና ዘመድ አዝማድ የሚላከውን በድን አካልክን ለመሰናበት በሔድንበት አጋጣሚ በዚያው የሬሳ ማቆያ ጽህፈት ቤት ሃላፊውን ስንት የኢትዮጵያውያን ሬሳ አለ ብየ ጠየቅኩት ። የደስደስ ያለው አረብ ሲመልስ ” አሁን እንኳን ብዙ አይደሉም ፣ ከዚህ በፊት ብዙ ነበር ። እዚህ ማቆያ ውስጥ ፈላጊ ያልመጣላቸው ከአስር የማያንሱ የኢትዮጵያውያን ሬሳ ይገኛል!” ሲል ዘርዘር አድርጎ መለሰልኝ ። ጠያቂ ስለሌላቸው ፣ ስማቸው ስላማይገኝ ሬሳዎች እጣ ፈንታ ብቻ ሳይሆን የሬሳው ማንነት ታውቆ የሚያስቀብር ጠያቂ ከጠፋ በማዘጋጃ ቤትና በፖሊስ እንደሚቀበሩ ያጫወተኝ … ሊሰሙት የሚከብድ እውነት !
Nebiyu Sirak
ከሬሳው ማስቀመጫ መስሪያ ቤት ሃላፊ ጋር ላፍታ ባደረግነው ቆይታ የሰማሁት አሳዛኝ ነባራዊ ሁኔታ ውስጤን አደማው ። ሬሳውን ወደ ምንቀበልበት የጓዳ በር ለየራሳችን ቆዛዝመን ደረስን: ( ታሞ ፣ እህት ሚስቱ አስታምመውት ፣ ማንነቱ ታውቆ እና ወደ ሃገር መላኪያ ገንዘብ ተገኝቶ ዛሬ ወደ ሃገር ለመሄድ ተዘጋጅቷል ፣ ከምሽቱ 9:45 … የብርቱ ወዳጀ አብሮ አደግ ከፈን ከተቀመጠበት ማቀዝቀዣ ወጣ … በተዘጋጀው የእንጨት ሳጥን ሆኖ ወደ አንቡላንስ ከመሸኘቱ በፊት በስትሬቸር እየተገፋ መጣና ለስንበት ፊቱ በአንድ የፊሊፒን የሬሳው ክፍል ሰራተኛ ተገለጠ … ያ ዘንካታ አይኑን ጨፍኖ ታጋድሟል …አንጀንታቸው የሚላወሰውን እህት ፣ ሚስት፣ ጓደኞች እና ጎረቤቶች ሃዘናቸውን እንደፈለጉ ጮኸው በማይገልጹበት ግቢ የወንድማቸውን በድን ተሰናበቱት … በሬሳው ክፍል ሃላፊ ባጫወተኝ አሳዛኝ ታሪክ ተጽናንቸ የነበርኩት እኔም እህት የወንድሟን ፣ ሚስት የባሏን ግንባር እየሳሙ በታመቀ የሃዘን ስሜት ድምጻቸውን አርቀው እያነቡ ሲሰናበቱት ሳይ ብርክ ያዘኝ !
ሽኝት …


በእርግጥም እኒህኞቹ ወገኖችም ሆኖ ታሞ አስታመውት የሞተው ወንደም እድለኛ ነው! ነገ የሃገሩን አፈር ፣ ታሞ እያለ እናቱን ናፍቆ ሁለቴ ለመሄድ ተነስቶ በተመለሰበት አውሮፕላን ዛሬ በድኑ በውድ ዋጋ ተጭኖ ይደርሳል ! እናት እና ልጅ ተነፋፍቀው አልተገናኙም: ( እናም አልሰሜ እናት አለም ነገ ሬሳ ለመቀበል በጠዋት መርዶ ይጠብቃታል !