Thursday, December 12, 2013

Ethiopia: Human Rights Day 2013

December 11, 2013Ethiopiawinnet: Council for the Defense of Citizen Rights
December 10, 2013 is Human Rights Day (HRD). Proclaimed in 1950 by the United Nations as a marker for the UniversalGreen, Yellow and Red, Ethiopian flag Declaration of Human Rights and in 1993 as the establishment of the UN High Commissioner for Human Rights, HRD is a solemn day to remind us of the dire human rights situation in Ethiopia. Thousands of courageous political prisoners languish in the country’s notorious jails without due process as do many prisoners of conscience (such as journalists and religious leaders).

ሰበር ዜና በኢትዬጲያ ሙስሊሞች ላይ መንግስት የጥፋተኘነት ውሳኔ አስተላለፈ፡፡

በኢትዬጲያ ሙስሊሞች ላይ መንግስት የጥፋተኘነት ውሳኔ አስተላለፈ፡፡
በኢትዬጲያ ሙስሊሞች ላይ መንግስት የጥፋተኘነት ውሳኔ አስተላለፈ፡፡
መንግስት በኢትዬጲያ ሙስሊሞች ላይ የጥፋተኘነት ውሳኔ ማስተላለፉን ምንጮች አስታወቁ፡፡ ለታህሳስ 3 በተቀጠረው የብይን ቀነ ቀጠሮ መሰረት 10 ተከሳሾችን ነፃ ናቸው ሲል ፍርድ ቤቱ ያሰናበተ ሲሆን የተቀሩት ላይ ግን በሽብር ድርጊት ፈፃሚነት ወንጀል ጥፋተኛ ናችሁ ሲል ብይን አስተላልፏል፡፡

በዚህም መሰረት ሁሉም በዕድሜ የገፉት አባቶች ዶ/ር ከማል ገለቱ፣ሼህ አብዱረህማን፣ሼህ ሃጂ ኢብራሂም፣ ሼህ ጣሂር፣.ሼህ ሱልጣን አማን፣ ኡስታዝ ጀማል ያሲን ፣ኡስታዝ ሰኡድ አሊ ፣ወንድም አሊ መኪ ፣ ወንድም ሀሰን አቢ እና ወ/ሮ ሃቢባ መሃመድ በነፃ ፍርድ ቤቱ እንዲሰናበቱ መወሰኑ ተዘግቧል፡፤
በተቀሩት ላይ ደግሞ የጥፋተኘነት ክስ በማስተላለፍ ለጥር 22 የመከላከያ ምስክራቸውን እንዲያቀርቡ ውሳኔ በማስተላለፍ ችሎቱ ተጠናቋል፡፡

መንግስት በኢትዬጲያ ሙስሊሞች ላይ የጥፋተኘነት ውሳኔ ማስተላለፉን ምንጮች አስታወቁ፡፡
ለታህሳስ 3 በተቀጠረው የብይን ቀነ ቀጠሮ መሰረት 10 ተከሳሾችን ነፃ ናቸው ሲል ፍርድ ቤቱ ያሰናበተ ሲሆን የተቀሩት ላይ ግን በሽብር ድርጊት ፈፃሚነት ወንጀል ጥፋተኛ ናችሁ ሲል ብይን አስተላልፏል፡፡

በዚህም መሰረት ሁሉም በዕድሜ የገፉት አባቶች ዶ/ር ከማል ገለቱ፣ሼህ አብዱረህማን፣ሼህ ሃጂ ኢብራሂም፣ ሼህ ጣሂር፣.ሼህ ሱልጣን አማን፣ ኡስታዝ ጀማል ያሲን ፣ኡስታዝ ሰኡድ አሊ ፣ወንድም አሊ መኪ ፣ ወንድም ሀሰን አቢ እና ወ/ሮ ሃቢባ መሃመድ በነፃ ፍርድ ቤቱ እንዲሰናበቱ መወሰኑ ተዘግቧል፡፤

በተቀሩት ላይ ደግሞ የጥፋተኘነት ክስ በማስተላለፍ ለጥር 22 የመከላከያ ምስክራቸውን እንዲያቀርቡ ውሳኔ በማስተላለፍ ችሎቱ ተጠናቋል፡፡

Wednesday, December 11, 2013

በጅዳ ቆንስል በር ውላ የምታድረው እህት ክራሞት…

December 11, 2013ነቢዩ ሲራክ
  • Ethiopian woman in Saudi Arabia, Jiddah Ethiopian embassy ይህችን እህት በጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት በር ተቀምጣ ካየኋት ሳምንት አልፏል። አልፎ አልፎ ላነጋግራት ብሞክርም መልስ አትሰጥም። መጀመሪያ ያየኋት ቀን አካባቢ ከስራ ለተፈናቀሉ እህቶች አነሰም በዛ መጠለያ እያለ ፣ ለምን በር ላይ ትሆናለች? ብየ የጠየቅኳቸው የቆንስሉ ጸጥታ አስከባሪ “አንተየ የዚህች እህት ጉዳይ አስቸጋሪ ነው ። ከመጠለያው ብዙ ቆይታለች ፣ አሁን በር ላይ የሆነችው ሃገር ቤት ለመሄድ ወረቀቷ አልቆ እያለ “ሃገር ቤት አልሄድም!” በማለቷ እነረደሆነ ተነግሮኛል ። “በመጠለያው የነበሩት ሰነዳቸው ባሳር በመከራ አልቆ ሲሸኙ ወደ ሃገር ቤት አልሸኝም ብላ ረብሻ ከማንሳት አልፎ ከተዘጋጀው መኪና ወርዳ ይህን የምታየው ሚኒባስ መስታውት ሰብራዋለች! ከዚያን ቀን ወዲህ አትበላም አትጠጣም ፣ እኛንም የገረመን ይሄ ነው! ምን ታደርጋለህ! ” ነበር ያሉኝ …

በብሔር ፖለቲካ ሥር “የተቀበረው ፈንጂ”!


(ከዋለልኝ እስከ ህወሃት/ኢህአዴግ)

article 39
የብሔር ጥያቄ በኢትዮጵያ ምላሽ እንዳገኘ የሚያስተጋባው ኢህአዴግ “የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች” በዓልን ማክበር ከጀመረ ስምንት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በአንፃሩ “ተመልሷል” የተባለው ጥያቄ እንደተቀበረ ፈንጂ በየጊዜው በየቦታው እየፈነዳ በህይወት፣ በንብረትና በኢትዮጵያዊነት ላይ አደጋ ማድረሱን ዳዊት ሰለሞን ሁነቶችን በመጥቀስ ይሞግታል፡፡
ከአስርት አመታት በፊት
የኢትዮጵያ ተማሪዎች በለውጥ አብዮት ናፍቆት እየተናጡ ነው፡፡ እዚህም እዚያም በተፈጠሩ ቡድኖች የማርክሲስት-ሌኒንስት ፍልስፍናን የሚሰብኩ የርዕዮተ ዓለም ጽሁፎች ይነበባሉ፡፡ ተማሪው ይከራከራል፣ የሌኒኒዝም ፍልስፍና ቀለም ቀለም መሽተት ለጀመረው የ1960ዎቹ ትውልድ ልብ የቀረበ ሆኗል፡፡ ፍልስፍናውን በአገራቸው የፖለቲካ ግለት ለመተርጐም የቋመጡት ወጣቶች በሁለት ጠርዝ ተሰልፈው በኢትዮጵያ ያለው “የመደብ ወይስ የብሔር ጭቆና ነው” በሚል በጠረጴዛ ዙሪያ ይፋለማሉ፡፡

አንዱዓለም አራጌ ከእስር ቤት “እኔ እስሩ አልከበደኝም፤ በጣም ያሳዘነኝ ግን በኔ መታሰር ልትጠቀሙበት አልቻላችሁም” አለ


(ዘ-ሐበሻ) የ2005 ዓ.ም የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ምርጥ ተብሎ የተሰየመውና በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት የሚገኘው ወጣቱ ታጋይ አንዱዓለም አራጌ እስር ቤት ሊጠይቁት ለሄዱት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች መልዕክት አስተላለፈ። በጣም ማዘኑንም ገለጸ። ዕድሜ ልክ እስራቱን ተቀብሎ እስር ቤት የሚገኘው አንዷለም አራጌ “ይቅርታ አልጠይቅም” በሚል እስካሁን በእስር ቤት እየማቀቀ ሲሆን “በእኔ መታሰር ብዙ ልትጠቀሙበት ስትችሉ አለመጠቀማችሁ ያሳዝነኛል:: እኔ አሁን በእስር ባለሁበት ሰዓት የኢትዮጵያን ሕዝብ የነፃነት ትግሉን ወደ ፊት ለመግፋት አጋጣሚ ሊሆንላችሁ ቢችልም አልተጠቀማችሁበትም ” ሲል የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን መውቀሱን የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች ገልጸዋል።
“እኔ መታሰሩና፤ በእስር ቤት እየደረሰብኝ ያለው ስቃይ አልከበደኝም። የከበደኝ ግን በኔ መታሰር ልትጠቀሙበት አለመቻላችሁ ነው። በኔ መታሰር መንግስት ብዙ ጫና ውስጥ እንዳለ ይታወቃል። በኔ መታሰር ብዙ ሥራ ልትሰሩበት፤ ትግሉን ወደፊት ልታስኬዱበት ስትሉ ይህን አላደረጋችሁም” ያለው አንዷለም አራጌ አሁንም የመንፈስ ጥንካሬው አብሮት እንዳለ በ እስር ቤት ካነጋገሩት ወገኖች መካከል ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል።
 
አንዷለም አራጌ የፌደራሉ ማረሚያ ቤት የሚጠይቁህን ሰዎች ስም ዝርዝር አስመዝግብ ተብሎ ተጠይቆ የነበረ ሲሆን እርሱ ግን ማንም ሰው መጥቶ ሊጠይቀኝ መብቱ ነውና ስም ዝርዝር አውጥቼ አልሰጥም ሲል ፈቃደኛ አለመሆኑን ዘ-ሐበሻ ከዚህ ቀደም መዘገቧ አይዘነጋም።

እዩኝ እዩኝ ደብቁኝ ደብቁኝን ያመጣል :: አቶ ሀብታሙ አያሌው = ከኢህአዴግ ወደ መድረክ የተላከ ሰርጎ - ገብ

December 11/2013
ምኒልክ ሳልሳዊ

እዩኝ እዩኝ ደብቁኝ ደብቁኝን ያመጣልጋሻው መርሻእንዳለመታደል ሆኖ የሀገራችን ፖለቲካ የሚተረማመሰው በአማተሮችና ሆድ - . አደር አሽከሮች ነው ይህ በመሆኑ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከገዥው ፓርቲ ጋር ከሚደርጉት ትግል የበለጠ የሚያደክማቸው አግድም / ሆርዞንታል / እርስ በርስ የሚያካሂዱት መቦጫጫቅ ነው ለዚህ ደግሞ ምቹ ሁኔታዎችን በማመቻቸት በኩል የራሳቸው አስተዋጽኦ ሚያደርጉ ሰርጎ - . ገቦች በየዘመኑ ይነሳሉ ምንም እንኳን ይህ አላስፈላጊ መሸነቋቆጥና ስድብ / መተቻቸት አላልኩም / የማልወደው ቢሆንም የአውራው ፓርቲ የውስጥ አርበኞች የትግሉን ስሜት ለማቀዝቀዝ የሚያደርጉት እሰጥ አገባና , አጀንዳ መዘዛ , እውነተኛ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና ሀገር ወዳድ ዜጎች ባላወቁት ወጥመድ እየገቡ መሆኑን ስመለከት የሚያውቁትን መረጃ አለማጋለጥ የሚረጩትን መርዝ ሰርጎ እንዲገባ እገዛ ማድረግ መስሎ ስለተሰማኝ ይህንን እውነት ለመከተብ ተነሳሁ .

‎በዋልድባ ላይ ለሚሰራው የሥኳር ፕሮጀክት ነዋሪዎች መነሳት ጀመሩ


#‎በዋልድባ ላይ ለሚሰራው የሥኳር ፕሮጀክት ነዋሪዎች መነሳት ጀመሩ #‎የቆራሪት_ከተማ በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል በዋልድባ ገዳም ላይ ለሚገነባው የስኳር ልማት ፕሮጀክት በመጀመሪያ ዙር 1800 አባወራዎች ከቦታቸው መነሳታቸው ታወቀ። ለተነሱ አር... አደሮቹ 127.5 ሚሊዮን ብር የካሳ ክፍያ ተሰጥቷል። ለእነዚህ ተነሺዎች ከወራት በፊት የገጠር ከተማ መልክ በመያዝ በተገነባችው የቆራሪት ከተማ ላይ የማስፈር ስራ ተከናውኗል። ለዚች ከተማ ምስረታ ምክንያት ደግሞ በዋልድባ ገዳም ላይ የሚሰራው የስኳር ልማት ፕሮጀክት መሆኑ ታውቋል። በአሁኑ ሰዓት ከቦታው የተነሱት 1800 ነዋሪዎች ከወልቃይት ወረዳ ከቃሌማ እና ፅምሪ ቀበሌ ይኖሩ የነበሩ አርሶ አደሮች ናቸው። መንግሥት እንደሚለው ለእነዚህ የልማት ተነሺዎች ለተነሱበት ቦታ በምትኩ የእርሻ የመኖሪያ ቤት ሙሉ የቤት እና የሰብል ካሳ ክፍያ ፈጽሜያለሁ ብሏል። ለአርሶ አደሮቹ ነዋሪዎች መንግሥት 127.5 ሚሊየን ብር ካሳ መስጠቱ ታውቋል በሁለተኛ ዙር የሰፈራ ፕሮግራሙ ላይ 4ሺህ ሰዎች ከቦታው ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሰፈራው የሚቀጥል ሲሆን ለሚነሱት 13 ለማያንሱ አብያተ ክርስቲያናት ምትክ አዳዲስ ቤተክርስቲያን በቆራሪት ከተማ መሰራት መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሏል። የዚህ ፕሮጀክት እሳቤ መነሻው 1991 . ቢሆንም አሁን ላይ ግን ወደ እውነታው እየተቃረበ ያለ ይመስላል ከዓመት በፊት ብዙ ሲያነጋግር የነበረው ይህ የሥኳር ፕሮጀክት አሁን ላይ የቁርጥ ቀኑ የቀረበ መስሏል መንግሥት ገዳሙን አልነካሁም በማለት አይኔን ግንባር ያድርገው እያለ ቢምልም መሀላው እውነታው ሊደብቀው አልቻለም። ገዳማውያኑም የሚደርስባቸው መከራ ከቀን ቀን እየጨመረ መምጣቱ ከቦታው የሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ ጥቂት የማይባሉት መከራውን በመቋቋም የሚመጣውን ነገር ሁሉ በጸጋ ለመቀበል በአቋማቸው ፀንተው አሁንም ድረስ ያሉ ሲሆን ጥቂት መነኮሳት ግን የመንግሥትን የአምስት አመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ከግብ ለማድረስ ቀን ከሌት ከመንግሥት ሹማምንት ጋር ዳገት ሲወጡ ቁልቁለት ሲወርዱ ተስተውሏል። 2005 . በጀት ዓመት የሥኳር ኮርፖሬሽን ዓመታዊ አፈጻጸም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀረበበት ጊዜ መንግሥት በበጀት እጥረት የሰፈራ ፕሮግራሙን በአግባቡ ለማስኬድ እንቅፋት እንደሆነበት ሚኒስትሩ ለምክር ቤቱ ማቅረባቸው ይታወሳል ከዚህ በተጨማሪም ቦታው ድረስ በመሄድ ስራውን የሚያከናውን የተማረ የሰው ኃይል እጥረት እና ቦታው ላይ ረዥም ጊዜ አለመቆየት መቻልን ለፕሮጀክቱ መጓተት እንደ ሁለተኛ ምክንያት አቅርበው ነበር። አንድ አድርገን ከውስጥ ሰዎች ባገኝችው መረጃ መሰረት በአሁኑ ሰዓት ዋልድባ ላይ እየተሰራ ላለው የሥኳር ፕሮጀክት የወራት ዝምታ መንስኤው ባለሙያዎች ቦታው ላይ ይህን ሥራ ለመስራት ፍቃደኛ አለመሆናቸው መሆኑን ለማወቅ ችላለች። በተለያዩ ጊዜም ለሥራ ወደ ቦታው ያቀኑ ባለሙያዎች በራሳቸው ፍቃድ ስራውን ያለደመወዝ እየለቀቁ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ እኛስ የኃያሉን የአምላክን እጅ እጠብቃለን ።