Friday, November 29, 2013

በሩሲያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አጠገብ የተገኘው ጥቅል ቦምብ መሆኑ ተረጋገጠ


በሩሲያ ሞስኮ ከተማ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አቅራቢያ በፖሊስና አነፍናፊ ውሻ አማካይነት የተገኘው ጥቅል፣ ቤት ሠራሽ ቦምብ መሆኑን የአገሪቱ የደኅንነት አገልግሎት ማረጋገጡን ዘገባዎች አመለከቱ፡፡
ዘ ቮይስ ኦፍ ራሺያ (የሩሲያ ድምፅ) የተሰኘው የአገሪቱ ሬዲዮ በድረ ገጹ እንዳለው፣ ባለፈው ሳምንት ዓርብ በፖሊስና በአጋዥ

አነፍናፊ ውሻ አማካይነት በኢትዮጵያ ኤምባሲ አቅራቢያ ተቀምጦ የተገኘው ጥቅል ዕቃ ወደ ላብራቶሪ ተወስዷል፡፡
በሞስኮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አካባቢ ከሚገኝ የቆሻሻ መጣያ አቅራቢያ ወድቆ ከተገኘውና በኋላም በቤት ውስጥ እንደተሠራ ከተረጋገጠው ቦምብ ጋር አብሮ የሞባይል ስልክ ተያይዞ መገኘቱን የአገሪቱ የደኅንነት አገልግሎትን የጠቀሰው ዘገባ ያመለክታል፡፡

በሩሲያ የአገር ውስጥ ደኅንነት አገልግሎት ላብራቶሪ የተመረመረው ጥቅል ዕቃ፣ በሦስት የፕላስቲክ ብልቃጦች ውስጥ በግምት 400 ግራም የሚሆን ፓይሮ ፓውደርና ሮው ቦልትስ የተሰኘ ተቀጣጣይና የፈንጂ ዱቄት ተሞልቶ ታሽጐ ነበር፡፡ የታመቀ ተቀጣጣይ ዱቄት ከተሞሉ ብልቃጦች ጋር ተያይዞ የተቀመጠው የሞባይል ስልክም ከርቀት ፍንዳታውን ለመቆጣጠር ያለመ መሆኑን ምርመራው አረጋግጧል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ ተጨማሪ ማብራሪያ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለማግኘት ያረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡
ethiopian reporter

የህዝባችን መከራ የወያኔ የፖለቲካ መጠቀሚያ አይሆንም!

በሳውዲ አረቢያ ውስጥ እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያን አሁንምመከራና ስቃይ ላይ ናቸው። የደረጃ ጉዳይ ነው እንጂ ችግሩ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የተንሰራፋ ነው። በመላው አለም ተበትኖ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ካለማቋረጥ ያደረገው ወገንና ሀገር አኩሪ ጩኸትና አቤቱታ ችግሩ በአለም ዙሪያ ትኩረት እንዲያገኝ ባያደረግ ኖሮ የወገኖቻችን መከራ ከዚህም በከፋ መልክ ይቀጥል እንደነበር ጥርጥር የለውም። አንድ ቀን እንኳን ለሚገዛው ህዝብ ሀላፊነትና ተጠያቂነት ተሰምቶት የማያውቀው የወያኔ ጉጅሌ መንግስት እግሩን እየጎተተ ቢሆንም ወደ ችግሩ አቅጣጫ እንዲመለከት የተገደደው በዚሁ የወገን ጩኸት መሆኑ ግልጽ ነው።

በደረሰባት የመኪና አደጋ ህይወቷ የተቀየረው እና የአልጋ ቁራኛ የሆነችው የሺወርቅ ምህረቴ
አንዳንዶች ጥሩ ገቢ አግኝተው ህይወታቸውን ለመቀየር ወደ ባህር ማዶ ተጉዘው ባዶ እጃቸውን ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ። ሌሎች በህመም ወይም በአደጋ ህልማቸውን ዕውን ከማድረግ ይሰናከላሉ። በዚህ ክስተት እነሱ ብቻ ሳይሆኑ የሚረዱት ቤተሰባቸውም ጭምር ችግር ይገጥመዋል። የዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት « አላማ በወጣትነት ሲቀጭ» ይሰኛል።
እንግዳችን የሺወርቅ ምህርቴ ትባላለች። የአልጋ ቁራኛ ከሆነች አንድ አመት አለፋት። የሺወርቅን ቅስም የሰበረው አደጋ ከመድረሱ በፊት ተወልዳ ካደገችበት ጎንደር ከተማ ወደ አዲስ አበባ ሄዳ ስራ እየሰራች ቤተሰቧን መርዳትም ችላ ነበር። ይሁንና የ 27 ዓመቷ የሺወርቅ የአንድ ቀን ገጠመኟ የህይወት ጉዞዋን ወዳልገመተችው አቅጣጫ ቀየረው። ለበርካታ ወራት ሆስፒታል ተኝታለች። ህክምናዋን መከታተል እንድትችል ስትልም በአዲስ አበባ በተከራየችው ቤት ትኖራለች። እናቷ ከጎንደር ሊያስታምሟት ሄደው አብረዋት ቀርተዋል። አልተሻላትም፤ አይኗን ስትከድን ትዝ የሚላት አደጋው ነው።
ከፍተኛ ስነ ልቦናዊ ጉዳትም ደርሶባታል።
ህይወቷን ስለቀየረው አደጋ አጫውታናለች። ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።
ልደት አበበ
audio http://www.dw.de/popups/mediaplayer/contentId_17260407_mediaId_17260303
source.dw.de

ADDIS STANDARD’S EXCLUSIVE INTERVIEW WITH ANA GOMES

 

Ana Gomez
Ana Gomes is coordinator and spokesperson of the foreign affairs committee for her political group, the Social-Democrat. With 200 members the Social-Democrat is the second largest group within the European Parliament. For Ethiopia and Ethiopians though Ana Gomes is best remembered for her role as the leader of the EU election observers’ team during the 2005 crisis-induced general election in Ethiopia. She has had a troubled relationship with Ethiopia’s late Prime Minister Meles Zenawi, who she still calls “a dictator,” after she published her report in which wrote the election was massively rigged. Eight years later, Ana Gomes came to Ethiopia to participate in the just concluded 26th ACP-EU parliamentary meeting. Her arrival in Addis Ababa caught many, who thought she would never be allowed to set foot in Ethiopia, by a surprise. Addis Standard’s deputy-editor-in-chief Tesfaye Ejigu met Ana Gomes during the meeting and held an exclusive interview. Excerpts:  

ኢትዮዽያኖች በሳውዲ መካ መዲና የመኪና መንገድ ዘግተው መዋላቸው ተሰማ

The Ethiopian immigrants demanded to be transported to Ethiopia. They blocked the road to Mekka as a form of protest. Currently tens of thousands of Ethiopians who were ordered to leave the country are stranded in Saudi Arabia after the Ethiopian regime has refused to evacuate them.
Image
ImageImage
source.ethiopian review

በቅርቡ ሪያድ አሚራ ኑራ ዩኒቨርሲቲ በተነሳው ሁከት በአውቶብስ ተጨፍልቃ የሞተችው ነፍሰጡር ኢትዮጵያዊት ምስል ይፋ ሆነ (18+)

NOV 28,2013
ኢትዮጵያን ሃገሬ ከጅዳ በዋዲ
22

በቅርቡ ሪያድ አሚራ ኑራ ዩኒቨርሲቲ በተነሳው ሁከት በአውቶብስ ተጨፍልቃ የሞተችው ነፍሰጡር ኢትዮጵያዊት ምስል ይፋ ሆነ (18+)

NOV 28,2013
ኢትዮጵያን ሃገሬ ከጅዳ በዋዲ
22
በሳውዲ አረቢያ ከእሳት ወደ ረመጥ ያመራው የወገኖቻችን ህይወት አሰቃቂ እና ዘግናኝ በሆኑ አደጋዎች ታጅቦ ግፍ እና መከራው ቀጥሏል::
በቅርቡ ሪያድ አሚራ ኑራ ዩነቨርስቲ በተነሳው ሁከት በአውቶብስ ተጨፍልቃ የሞተችው ነፍሰጡር ኢትዮጵያዊት ምስል ይፋ ሆነ። ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የሆኑ እንዲያዩት አይመከርም።
ኖቬብር 24 2013 ምሽት ሚን ዛህሚያ እይተባለ ከሚነገርለት ግዜያዊ መጠለያ «ወገን ማሰቃያ » ጣቢያ በ17 አውቶብስ ተጭነው ኤርፖርት እንወስዳችሃለን ተበልው ሪያድ ከተማ መለዝ እይተባለ ወደ ሚጠራ አሚራ ኑራ ዩንቨርስቲ እንዳቀኑ በሚገርላቸው እገኖቻችን እና በሳውዲ ፖሊሶች መሃከል በተነሳ ግጭት በአውቶብስ ተጨፍልቃ የሞተችው ነፍሰጡር እህታችን አሰቃቂ ሞት ይፋ ሆነ ።
11
በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እና በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወክለው ወደ ሳውዲ አረቢያ እንደግቡ የሚነገርላቸው የልዑካን ቡድን አባላቶች ይህን የወገኖቻችንን ዘግናኝ አሟሟት በዓይናቸው አይተውት እንደነብር የሚናገሩ ምንጮች ህይወቷ በአሰቃቂ ሁኔታ ላለፈቸው ነፍሰጡር ከማዘን ይልቅ ጉዳዩ ይፋ እንዳይወጣ አደጋው በተከሰተበት ወቅት ፎቶ ያነሱ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን የቅረጹትን ይህን ምስል ለማንም አሳልፈው እንዳይሰጡ ያስፈሯሯቸው ነደነበር ገልጸዋል።
በሳውድ አረኢያ ወገኖቻችን ላይ እይደረሰ ባለው አሰቃቂ ሁኔታ ኢትዮጵያውያን ከመቸውም ግዜ በላይ የከፋ ሁኔታ ውስጥ ስለሚገኙ ድምጻቸውንን ከፍ አድርገን መጮህ ይጠበቅብናል ።
http://www.zehabesha.com/
ለአውሮፓ፣ ኤዥያ፣ ካሪቢያን፣ፓስፊክና አፍሪካ ጉባኤ አዲስ አበባ የተገኙት የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች በቢሮአቸው ከተቃዋሚዎች ጋር ተወያዩ፡፡ ከስፔን፣ ፖርቱጋል፣ ማልታ፣ ፈረንሳይና እንግሊዝ የተወከሉ ልኡካን በኢትዮጵያ ስላላው አጠቃላይ ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ ከተቃዋሚዎች በኩል ከመድረክ ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ ከአንድነት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳና አቶ አስራት ጣሴ፣ ከመኢአድ አቶ አበባው መሀሪ፣ ከሰማያዊ ፓርቲ አቶ ይልቃል ጌትነት እንዲሁም ከኢዴፓ አቶ ልደቱ አያሌውና የፓርቲው ፀሀፊ ተገኝተዋል፡፡ ከተወካዮቹ በኩል የተነሱት ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው፡-
'India can partner Ethiopia in space technology'
By IANS
November 29, 2013


Addis Ababa, Nov 28 (IANS) With Ethiopia launching a new space programme last month, India can have a promising partnership with Africa in this frontier technology, India's outgoing ambassador here has said. "An Indian rocket may carry an Ethiopian satellite into space; that is possible," outoing envoy Bhagwant Singh Bishnoi told IANS at his farewell reception here organized by the Indian Business Forum (IBF) in Ethiopia.
"India's space launches are much cheaper (than in the West); hence launching micro satellites for Ethiopia is something that I think the two countries should work closely together for," he added.
After South Africa and Nigeria, Ethiopia is becoming a hub of Africa's aspirations in space with the East African nation's finalising the installation of two huge deep-space observatory telescopes to promote space research in the region, a prelude to its developing a space mission by launching its own satellites.

Indian technology has enabled the successful launching of satellites that now provide the country communication facilities and information on a range of subjects, including mineral deposits and weather trends.

"I will discuss this new partnership opportunity with my successor," Bisnoi said. On completing his four-year term, Bishnoi is moving to New York as deputy head of India's permanent mission at the UN. He will be succeeded by Sanjay Verma, currently India's consul general in Dubai.


He said Indian technological companies should invest in Ethiopia in the opportunities that are opening up. "The technologies that India brings are affordable, adoptable and suitable for household uses and others depending on the circumstances", the ambassador said.
"There is a lot of things that Indian industry has to offer."

During his tenure, the ambassador had encouraged Indian investment to Ethiopia and several Indian projects, especially in the manufacturing and agricultural sectors, have been set up.
"As a patron of IBF, he (Bishnoi) constantly guided us to achieve our main objectives of IBF," Mayur IBF president Suryakant Kothari told IANS.


According to Kothari, the other major contribution of the Indian ambassador was to create a platform for dialogue between Indian and Ethiopian government officials, which is also an objective of the IBF.
"Creating a dialogue between government officials is very important for investment and he enabled this platform where Indian investors frankly and candidly engage with Indian and Ethiopian government officials, and a lot of their challenges and problems were resolved," Kothari said.
One outcome of this dialogue is that India is the first country to sign a Memorandum of Understanding (MoU) with the Ethiopian Revenues and Customs Authority (ERCA) that has been successfully implemented by both sides.

The first visit of Indian leaders like Vice President Hamid Ansari and Prime Mnister Manmohan Singh, as well as of Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn to India when he was foreign minister happened during Bishnoi's tenure.


አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚንስትር የሚሆኑት መቸ ነው?!!!

du_pm_haile_mar_desነፍሳቸውን ይማረውና(ድንገት ነፍስ ካላቸው፣መንፈስ ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ ነው)የቀድሞውና ያሁኑ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ በሞት ካረፉና ካረፍናቸው ጀምሮ ታላቋ ኢትዮጵያ ያለ ሀገረ ገዥ የቀረች ይመስላል፡፡ሆደ ቡቡነታቸውን ለመለስ ዜናዊ ሲነፋረቁ ያረጋገጥንላቸው ሀ/ማሪያም ደሳለኝ ወንበሩ ላይ ቢቀመጡም እንደ ሁለት ወር ህጻን ከተጎለቱበት አላንቀሳቅስ ያላቸውን እርኩስ መንፈስ ሁለት ሰባት ቢታዘዝለት መልካም ነበር፣ነገር ግን ሰውየው በኢየሱሴ የዳኑ ናቸውና ጸበልን ከዚያው በጸበልህ የሚሉ መሆናቸው እኛ የእርሳቸውን ታማኞች መፍትሄ እንዳናዘጋጅ አድርጎናል፡፡ከሰሞኑ ደግሞ ይህ እርኩስ መንፈስ ምንም አላናግራቸው በማለቱ ጭንቀታችን የከፋ አድርጎታል፣መላ ያለህ ሁሉ ወዲ በል፡፡እርስዎስ ቢሆኑ በዚህ ቀውጢ ሰኣት ያልነገሱ መቸ ሊነግሱ ነው፡፡እኔ እንደው የእርስወ ነገር አያስችለኝምና ትንሽ ምክር ቢጤ ጣል ላድርግለዎት፣የ2007 ምርጫ ደርሶ ሱናሜው ሳይጠርግዎት ጠቅላይ ሚኒስትርነትን ቢሞክሯት መልካም ነው እላለው፡፡አይተ በረከት ስሞንስ እስከመቸ ነው የስሁል ሚካኤልን መንበር ተረክበው ሲሽሩና ሲሾሙ ምን አለበት አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝን ጠቅላይ ሚንስትር ቢያደርጓቸው፡፡(ስሁል ሚካኤል በጎንደር የነገስታት ዘመን ከትግራይ የመጡ መስፍን ሲሆኑ ከኋላ ሆነው ሲሾሙና ሲሽሩ የነበሩ ጉልበታም ናቸው)፡፡በመጨረሻም ለሃይለማሪያም ደሳለኝ የማስተላልፈው መልዕክት ቢኖረኝ እንደሚከተለው ይጠቃለላል፣ታሪክዎ ሲጻፍ ቤተ መንግስቱን ከሚጠብቁት ወታደሮች የተለየ አይሆንምና በጊዜ መላ ቢያበጁ፣ባይሆን ምን ማድረግ እንዳለብዎት ከጠፋብዎ አኔን ያማክሩኝ፡፡የሚሰማን የለምእንጅ ባለ ራዕይውንም መክረናቸው ነበር፡፡ምን ያደርጋል ምክራችን ይዘውት ሽል አሉ እንጅ፡፡Gashaw Mersha

ሰበር ዜና በሰሜናዊ ኢትዮጵያ በሁመራ ቃፍታ ወረዳ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የሰነዘረውን ጥቃት ከመንግስት አካል በኩል ተረጋገጠ


በሰሜናዊ ኢትዮጵያ በሁመራ ቃፍታ ወረዳ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የሰነዘረውን ጥቃት የወረዳው የፀጥታ ኃላፊ ገዛይ ዳኘው ለአካባቢው ራድዮ ማመናቸውን ቪኦኤ የአማርኛው አገልግሎት ዛሬ ህዳር 18/2006 ዓም አስታወቀ።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሽምቅ ውግያ ሂደቶች ከሰሜናዊ ኢትዮጵያ በኩል እየተሰማ ነው።''የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል'' እና ''የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር'' ያሰለጠኗቸውን ሰራዊቶች ማስመረቃቸውን በእዚሁ በያዝነው ህዳር ወር ላይ ስታወቃቸው ይታወቃል።
በእዚሁ ወር ኢሳት ለወራት በኢህአዲግ-ወያኔ ሲቀናበር የነበረ ኤርትራ በሚገኙ  በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል አመራሮች ላይ ግድያ ለመፈፀም የተሸረበ ሴራ መጋለጡ መዘገቡ ይታወቃል።የሴራው ሂደትም ኢህአዲግ-ወያኔ በቁጥር አንድ ያስጨነቀው ጉዳይ ወደ ትጥቅ ትግል የገቡ ኃይሎች መሆናቸውን ያመላከተ አይነተኛ ማስረጃ መሆኑን ብቻ ሳይሆን የአሁኑ ሂደት ከእዚህ በፊት ከነበሩት ሁኔታዎች የተለየ ነባራዊ ሁኔታ መኖሩን ብዙዎች ይስማማሉ።
ዛሬ ቪኦኤ የመንግስት መዋቅር የትግራይ ምዕራባዊ ዞን ቃፍታ ወረዳ የፀጥታ ኃላፊ ውግያውን ማመናቸውን ለአካባቢው ራድዮ መናገራቸውን ከመግለፁም በላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ ኑር ጀባን ቃለ መጠይቅ አድርጎላቸዋል።አርበኛ ኑር ጀባ ስለውግያው ሲናገር  በ24ኛ ክፍለ ጦር ላይ ጉዳት ማድረሱን እና በርካታ ቀላል እና ከባድ የጦር መሳርያዎችን መማርኩን ገልጧል።በነገራችን ላይ ኢሳት በትናንትናው እለት ቀደም ብሎ ዜናውን ማወጁ ይታወቃል።በውቅቱም ጦርነቱ የተደረገው ህዳር 13/2006 ዓም መሆኑ ተዘግቦ ነበር።
ከእዚሁ ጋር በተያያዘ ሰሞኑን ኢትዮጵያ ውስጥ በሌለበት ፍርድ ቤት ተከሶ የነበረው በአሁኑ ወቅት የግንቦት ሰባት ሕዝባዊ ኃይል አመራር ካሴ ዘመነ ''ከወያኔ ጋር ከአሁን በኃላ የምንገናኘው ቃሊቲ ወይም እስር ቤት ሳይሆን ጦር ሜዳ ነው እዝያው እንገኛኛለን'' ያለውም በእዚሁ በያዝነው ሳምንት ነው።

ጉዳያችን
ህዳር 19/2006 ዓም

Modern day slavery in the Arab world is not based on skin complexion, but rather on legal subordination.

Last updated: 28 Nov 2013 13:28
 
Opinion

The colour of slavery

Modern day slavery in the Arab world is not based on skin complexion, but rather on legal subordination.

Last updated: 28 Nov 2013 13:28
Khaled A Beydoun

Khaled A Beydoun is the Critical Race Studies Teaching Fellow at the UCLA School of Law.
Listen to this page using ReadSpeaker
Email Article
Print Article
Share article
Send Feedback
Opinion

The colour of slavery

Modern day slavery in the Arab world is not based on skin complexion, but rather on legal subordination.

Last updated: 28 Nov 2013 13:28
Khaled A Beydoun

Khaled A Beydoun is the Critical Race Studies Teaching Fellow at the UCLA School of Law.
Listen to this page using ReadSpeaker
Email Article
Print Article
Share article
Send Feedback
Manfuhah, a suburb of Riyadh, was the site of the worst anti-migrant violence [Reuters]The Islamic call to prayer emanated loudly from the nearby mosques. As Saudis filed toward the Manfuhah Mosque on November 4, government buses rolled in to carry 23,000 foreign workers to deportation centres, and then out of the kingdom.

ኢትዮጵያና ዩኤስ አሜሪካ በኬኔዲ ዘመን

ባለፈዉ ሳምንት ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ የተገደሉበትን 50ኛ ዓመት ዘክራ ዉላለች። እንደ ጎርጎረሳዉያኑ ህዳር 22 ፤ 1963 ዓ,ም ቀትር ላይ በደቡብ ቴክሳስ ዳላስ ከተማ፤ በጥይት የተገደሉት ፕሬዚደንት ኬኔዲ ሰለባ የሆኑት ስልጣን ላይ ከወጤ ሶስተኛ ዓመታቸ ን ሊይዙ ትንሽ ወራቶች እንደቀራቸዉ መሆኑን ዘገባዎች ያሳያሉ።
selam
ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ፤ በዚያ ወቅት ከኢትዮጵያዉ ንጉሰነገስት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንደነበራቸዉ ተመልክቶአል። በተለይ ጆን ኤፍ ኬኔዲ ከመገደላቸዉ ከአንድ ወር ቀደም ብሎ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አሜሪካንን መጎብኘታቸዉ ይነገራል። በለቱ ዝግጅታችን ጆን ኤፍ ኬኔዲ የተገደሉበትን 50ኛ ዓመት በማስመልከት፤ ኢትዮጵያ በጆን ኤፍ ኬኔዲ፤ ዘመነ ሥልጣን ከአሜሪካ ጋር የነበራትን ግንኙነት እንቃኛለን ።

የኔትዎርክ መቆራረጥ እንጂ የደንበኞች መቆራረጥ አልገጠመኝም” - ኢትዮ ቴሌኮም

Written by  ኤልያስ, AddisAdmassNews.com

ኢህአዴግም ያልተሰደደው ሥልጣን ላይ ስለሆነ ነው!የደከመው ባለስልጣን ማረፍ እንጂ አምባሳደር መሆን የለበትም! 

በአሁኑ ጊዜ የቱንም ያህል “ልማታዊ” ለመሆን ቢሞክሩ ፈፅሞ ያልተሳካላቸው የመንግስት ተቋማት ቢኖሩ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱት የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ኮርፖሬሽንና ኢትዮ ቴሌኮም ናቸው፡፡ (ልማታዊ ያልሆነ ሁሉ ኪራይ ሰብሳቢ ነው ማለት ግን አይደለም!) መብራት ሃይል መብራት እምቢ ሲለው፣ ቴሌኮምም ኔትዎርክ (በቴክኖሎጂ ግንኙነትን ማቀላጠፍ) አልሆንልህ ብሎታል (ምኑን ኖሩት ታዲያ?!) 
የኢትዮ ቴሌኮም ሃላፊዎች ሰሞኑን ለፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ በሰጡት ማብራሪያ፤ የኔትዎርክ መቆራረጥ የሚከሰተው በሃይል መቆራረጥና በኦፕቲክ ፋይበር መቆራረጥ እንደሆነ ገልፀዋል (በመቆራረጥ አለቁ እኮ!) ቴሌኮም እስካሁን የስራ አጋሩ በነበረው መብራት ኃይል ላይ የጣለው እምነት ተሸርሽሮ ማለቁን የሚጠቁም ፍንጭ እንደታየ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ በሰሞኑ ማብራሪያው በኤሌክትሪክ ሃይል መቆራረጥ የሚፈጠረውን የኔትዎርክ መቆራረጥ ችግር ለመቅረፍ ጄነሬተር እጠቀማለሁ ብሏል - ቴሌኮም፡፡ (እቺን ለማሰብ ግን ይሄን ሁሉ ጊዜ!) ይሄ ሁሉ የኔትዎርክ መቆራረጥና የኢንተርኔት አገልግሎት መንቀራፈፍ ቢኖርም ግን “የደንበኞቼን ቁጥር 26 ሚሊዮን አድርሻለሁ” ብሎናል - ቴሌኮም፡፡ (“የኔትዎርክ መቆራረጥ የደንበኞች መቆራረጥን አላስከተለብኝም” እያለ ነው!) እኔ ግን … ቴሌኮምን ብሆን አፌን ሞልቼ “ደንበኞቼ” አልልም ነበር፡፡ (አገልግሎት ሳይኖር ደንበኛ?) እናም … ደንበኞቼ ሳይሆን “የክብር ደንበኞቼ” ነበር የምላቸው፡፡ ለምን መሰላችሁ … እኒህ ሁሉ “ደንበኞች” እኮ በኔትዎርክ መቆራረጥ ሳቢያ በሞባይል ስልክ  እየተጠቀሙ አይደለም። 

ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ የመኪና አደጋ ደረሰ


ዛሬ ማለዳ ከጠዋቱ 11 ሰዓት ላይ ከሰሜት ሆቴል ወደ ጊዮርጊስ ቁልቁል ሲሄድ የነበረ አንድ ከባድ የጭነት ማመላለሻ(SINO TRUCK)  መኪና ባጋጠመው የፍሬን ችግር ምክንያት ሹፌሩ መኪናውን መቆጣጠር አቅቶት ቀጥታ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ቅጽርን ደርምሶ በመግባት ከፍተኛ አደጋ አድርሷል ፡፡  በወቅቱ በቦታው ላይ በእቅልፍ ላይ የነበሩ ሁለት ጎዳና ተዳዳሪዎች ወዲያውኑ ሕይወታቸው ሲያልፍ ተጨማሪ ሶስት ሰዎች ላይ ከባድ የሆነ አደጋ ደርሶባቸዋል ፤ ከፍተኛ አደጋ የደረሰባቸው ሶስቱ ሰዎች ወዲያውኑ በእሳት አደጋ ሰራተኞች እና አካባቢው ላይ ባሉ ሰዎች ጥረት ራስ ደስታ ሆስፒታል ተልከው ጊዜያዊ እርዳታ ከተደረገላቸው በኋላ ጉዳቱ ከፍተኛ በመሆኑ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተወስደዋል ፡፡ በአደጋው የቤተክርስቲያኑ መግቢያ በር እና ግንብ ከፍተኛ አደጋ የደረሰበት ሲሆን በተጨማሪ ሰው በፍርስራሽ ውስጥ ይኖራል ተብሎ በመገመቱ በአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ፍርስራሹን የማንሳት ስራ ሲያከናውኑ ተስተውሏል፡፡ የደረሰው አደጋ አሰቃቂ መሆኑን በቦታው የነበሩ ሰዎች ተናግረዋል፡፡
 
ከአደጋው በኋላ የመኪናው ሹፌር በሰጠው ቃል መሰረት የመኪናው ንፋስ እምቢ በማለቱ አደጋው የደረሰ መሆኑን ተናግሯል፤ በአሁኑ ሰዓት  ፖሊስ የመኪናው ሹፌር ላይ ተጨማሪ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
source.አንድ አድርገን

Thursday, November 28, 2013

በጅጅጋ የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን ለማድመቅ የተቀረጸው የመለስ ዜናዊ ሃውልት ፈረሰ

Thursday, 28 November 2013

በጅጅጋ የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን ለማድመቅ የተቀረጸው የመለስ ዜናዊ ሃውልት ፈረሰ

ሶማሌ ክልል 8ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ታከብራለች መባሉን ተከትሎ የክልሉን ዋና መቀመጫ ጅጅጋን  አርቲስቶች እና የመንግስት ባለስልጣናት በየጊዜው እየጎበኙዋት ነው።
ለበዓሉ ዝግጅት የተመደበለትን 31 ሚልዩን ብር ከዝግጅቱ በፊት ቀድሞ ያጠናቀቀው የሶማሌ ክልል መንግስትን ለበአሉ ማክበሪያ እና ማድመቂያ በማለት ተጨማሪ 14 ሚሊዮን ብር ጠይቋል።
ለበዓሉ ማስተናገጃ የሚሆን ስቴዲየም በመገንባት ላይ የተጠመደው ክልሉ ፤ በገጠመው የበጀት እጥረት የተነሳ በጅምር ባለ ስታዲየም በዓሉን ያከናውናል፡፡ የፌድሬሺን ምክር ቤት ባካሄደው ግምገማ ከ10 ሚልየን ብር በላይ ገንዘብ ያለ አግባብ የባከነ መሆኑን አረጋግጦዋል፡፡ በተመደበው በጀት ዘወትር ከስራ ስዓት ውጭ የከስዓት ጊዜን በመጠቀም የክልሉ ባለስልጣናት ገንዘቡን ጫት ቅመውበታል ሲል ምክር ቤቱ ትችት አቅርቧል።
የፌዴሬሺን ምክር ቤት በበኩሉ የተለያዩ ባለስልጣናትና አርቲስቶች የሶማሌ ክልልን ለማስጎብኝት በሁዱበት ወቅት ለመጓጓዝያ እና ለመስተንግዶ  200 ሚልየን ብር  ወጭ አውጥቻለሁ ብሏል፡፡
በዓሉን ለማድመቅ እና የመንግስት ባለስልጣናትን ለማስደሰት በማሰብ በ 243 ሺ ብር ወጭ በጅጅጋ ከተማ ለመለስ ዜናዊ ተብሎ የተቀረፀው ሃውልት እንዲፈርስ ተደርጓል፡፡ በፊደራል አመራሮች ቁጣን የቀሰቀሰው ይህ ምስል ፈጽሞ ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ምስል ጋር የማይመሳሰል እና ፈጽሞ  በመልክ እና በቁመና የማይገናኝ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ አስተያየት ሰጪዎች ሀውልቱ ከመለስ ይልቅ ግርማ ወልደ ጊዩርጊስን ይመስላል ሲሉ ተሳልቀዋል፡፡ የክልሉ ባለስልጣናት ሃውልቱ የተሸፋፈነበትን ሸራ እንደገለጡ ከፌደራል መንግስቱ ባለስልጣናት በደረሰባቸው ከፍተኛ ትችት ወዲያው በሸራ ሸፍነው አፍርሰውታል። ቀራፂው  በቁጥጥር ስር ውሎ ካለፉት ሶስት ሳምንታት ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛል፡፡
ለህዳር 29ኙ በአል ከተዘጋጁ ባነሮች መካከል ባቡር ፤ አባይ ግድብ ፤ ቤቶች እና ህገ መንግስት ይገኝበታል። ይህ ባነር ለህዝብ ተደብቆ ከቆየ በኃላ በህዳር 28 ይመረቃል፡፡

የወያኔ በዲሞክራሲ ቁማር እስከመቼ?

November 28, 2013በአሸናፊ ንጋቱ
በስልጣን ላይ ያለው የወያኔ መንግስት የዛሬ 22 ዓመት አንግቦት የነበረውን የዲሞክራሲ መፈክር በማየት ዲሞክራሲ የጠማው የኢትዮጵያ ህዝብ የደስታ ጮቤ በመርገጥ ነበር የተቀበለው፡፡ ነገር ግን ይህ መፈክር ድራማ መሆኑ እየዋል እያደረ ነበር እየተጋለጠ የመጣው። ጮቤ እየረገጠ፤ ትግሉን ተቀላቅሎ መስዋት የከፈለውን ህዝብ የቁልቁል ወደ ባሰ የመከራ ማጥ ከቶታል።

የህዝባችን መከራ የወያኔ የፖለቲካ መጠቀሚያ አይሆንም! (ግንቦት 7)

November 28, 2013
Ginbot 7 weekly editorialበሳውዲ አረቢያ ውስጥ እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያን አሁንም መከራና ስቃይ ላይ ናቸው። የደረጃ ጉዳይ ነው እንጂ ችግሩ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የተንሰራፋ ነው። በመላው አለም ተበትኖ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ካለማቋረጥ ያደረገው ወገንና ሀገር አኩሪ ጩኸትና አቤቱታ ችግሩ በአለም ዙሪያ ትኩረት እንዲያገኝ ባያደረግ ኖሮ የወገኖቻችን መከራ ከዚህም በከፋ መልክ ይቀጥል እንደነበር ጥርጥር የለውም። አንድ ቀን እንኳን ለሚገዛው ህዝብ ሀላፊነትና ተጠያቂነት ተሰምቶት የማያውቀው የወያኔ ጉጅሌ መንግስት እግሩን እየጎተተ ቢሆንም ወደ ችግሩ አቅጣጫ እንዲመለከት የተገደደው በዚሁ የወገን ጩኸት መሆኑ ግልጽ ነው።

Wednesday, November 27, 2013

MLDI launches international bid to quash the phony conviction of Ethiopian free press journalists

November 27, 2013The Horn Times Newsletter 27 November 2013 by Getahune Bekele-South Africa“It is virtually impossible within the Ethiopian justice system for a journalist who has been unlawfully imprisoned to get justice.” Nani Janson, MLDI senior legal counsel.
A UK based international charity organization is on fund raising mission to help secure the release of jailed Ethiopian journalists Eskender Nega and Reeyot Alemu.
Media Legal Defense Initiative
Peter Noorlander

Media Legal Defense Initiative, MLDI, well known for helping scores of independent journalists defend their rights, urgently needs 20,000 USD to file court cases against the ruling minority junta of Ethiopia.
The organization, which famously won standard-setting judgments on issues like the protection of journalist’s sources and criminal libel, said it has obtained the permission of Eskender Nega and Reeyot Alemu to bring their case to African commission on human and people’s rights that has a binding judgment and power to order the Ethiopian regime to free all unjustly convicted journalists.

EU Member of Parliament Ana Gomes in Addis Ababa


Serious talk! EU Member of Parliament Ana Gomes, known for publicly criticising Ethiopia following the

ኮንዶሚንየም ቤቶች የዝሙት መናሀሪያ ሆነዋል


መንግስት በተለምዶ ኮንደሚንየም ብሎ አንደነገሩ ገነባብቶ ቀብቶ ከሰራቸው እና ለህዝብ ካደላቸው በኣዲስ ኣበባ በየቦታው ባሉ የባለኣራት ፎቅ ኣፓርትመንት የጋራ የመኖሪያ ቤቶች ኣካባቢ የዝሙት፥ የመጠጥ እና የኣደንዛዥ እጽ መናሀሪያዎች ሆነዋል ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ::

Tuesday, November 26, 2013

ፖሊስ ኢትዮ-አሜሪካዊው በሜሪላንድ ሚስቱን እና ልጁን ገድሎ ራሱን አጥፍቷል አለ

ባለፈው ሳምንት ኢትዮ-አሜሪካዊው ቢኒያም አሰፋ፣ ባለቤቱ እና ልጁ በቤት ውስጥ ሞተው መገኘታቸውን ዘ-ሐበሻ የሜሪላንድ የዜና ማሰራጫዎችን መዘገቧ ይታወሳል። በወቅቱ ለ3 ሰዎች ሞት ተጠያቂው ማን እንደሆነ ያልተገልጸ የነበረ ቢሆንም፤ የባልቲሞር ፖሊስ በዚህ የሶስት ሰዎች ህይወት መጥፋት ዙሪያ ደረስኩበት ባለው የምርመራ ውጤት ላይ በሰጠው መግለጫ “አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ሶስት የቤተሰብ አባላት የተገደሉት በአቶ ቢኒያም አሰፋ ነው” ብሏል። ፖሊስ ኢትዮአሜሪካዊው ቢኒያም ሚስቱን እና ልጁን ከገደለ በኋላ ራሱን አጥፍቷል ብሏል። ለበለጠ መረጃ የኤስቢሲ ባልቲሞር ቲቪ ዘገባ የሚከተለው ነው። አቶ ቢኒያምን የምታውቁ በኮመንት ላይ አስተያየታችሁን ብትጽፉ ብዙ ወገኖች መረጃ ሊያገኙ ይችላሉ።
bbhttp://www.zehabesha.com/

ከአቶ ታምራት ላይኔ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ (ከአንድ ጉዳይ በቀር በርካታ ቁምነገሮች አለው)

(ዳዊት ከበደ ወየሳ) – ከአቶ ታምራት ላይኔ ጋር የተደረገው ቃለ ምልልስ አስገራሚ ነው። በአውስትራልያ የ-SBS አማርኛ ፕሮግራም ነው ይህንን ያስደመጠን – ምስጋና ይገባቸዋል። በቃለምልልሱ ውስጥ የምናውቃቸውና የማናውቃቸውን፤ በወሬ የሰማናቸውንም ሆነ በታሪክ ያየናቸውን ጉዳዮች ተካተዋል። ከራሳቸው የግል ህይወት አስተዳደግ እና አስተሳሰብ በመነሳት ስለ ትጥቅ ትግሉ ታሪክ ብዙ ብዙ ነገሮችን ብለዋል። ኢህዴን የተባለው ድርጅት ከጎንደር አካባቢ ተነስቶ ወደ ትግራይ ክልል ከመሄዱ በፊት፤ ከህወሃት ጋር የርስ በርስ ንግግር የተደረገ መሆኑን፤ ያንጊዜ ወደ ትግራይ እንዲገቡ ባይፈቅዱላቸው የርስ በርስ ግጭት ሊኖር ይችል እንደነበር ወይም ወደ ሱዳን ተመልሰው ሃይል አጠናክረው ትግራይ መግባታቸው የማይቀር መሆኑን ያብራራሉ። ከዚህም በተጨማሪ ኢህዴን በኤርትራ ላይ የነበረው አቋም ምን እንደነበረና በኋላም ከህወሃት ጋር ተቀላቅሎ “ኢህአዴግ” የተባለ ግንባር መመስረቱን፤ ከዚያም ይህ ድርጅት ከብሄራዊ ድርጅትነት ወደ ብሄር ድርጅትነት ወርዶ “ብአዴን” ስለመባሉ ይገልጻሉ። ነገር ግን ወደ ዝርዝር ማብራሪያ አልሰጡበትም። “ብዙ ነገር አለ” ብለው ያልፉታል። እነዚህ ከላይ የገለጽናቸውን ጉዳዮች በክፍል አንድ ላይ ሊያዳምጡት ይችላሉ።

Monday, November 25, 2013

ሰበር ዜና ሪያድ-በኢትዮጵያውያን እና በሳውዲ ፖሊሶች መሃከል በተነሳ ግጭት አንዲት ነፍሰጡር ኢትዮጵያዊት በአውቶብስ ተገጭታ ህይወቷ አለፈ።

ሪያድ አሚራ ኑራ ዩንቨርስቲ ውስጥ፡ግዜያዊ መጠለያ ሜዳል ላይ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና በሳውዲ ፖሊሶች መሃከል በተነሳ ግጭት አንዲት ነፍሰጡር ኢትዮጵያዊት በአውቶብስ ተገጭታ ህይወቷ አለፈ።

ተዋርደን አንቀርም!!!

SHARE:




  • 12
ሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ግፍና በደል በሰላማዊ ሰልፍ ለመቃወም ፓርቲያችን በወሰነው መሰረት ለሚመለከተው ክፍል አሳውቀን ነበር፡፡መቸም ህዝባችን በጭቆና ውስጥ ስለኖረ በመብቱና በግዴታው መሀል ያለውን ድንበር በውል ካለመረዳቱ የተነሳ ሰልፉ እንዲደረግ ስለመፈቀዱ በተደጋጋሚ ስንጠየቅ ነበር፡፡ህጉ የሚለው ግን ማስፈቀድ ሳይሆን ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡በተቃራኒው መንግስት በተለያዩ ጉዳዮች ሳቢያ በእለቱ ለሰላማዊ ሰልፉ የደህንነት ከለላ መስጠት የማይችልበት ሁኔታ ከገጠመው ሰልፉን ለጠራው አካል ችግሩን ገልጾ ቀኑ እንዲተላለፍለት ይጠይቃል፡፡በመሆኑም ይህን መሰል ጥያቄ ከሚመለከተው መስሪያ ቤት ለፓርቲያችን ባለመቅረቡ በሙሉ ልብ ቅድመ-ዝግጅት ማድረጉን ተያያዝን፡፡ ሁሌም ቢሆን መንግስት ሰበብ ፈልጎ ሊወነጅለንና ከመስመር ሊያስወጣን እንደሚፈልግ በሚገባ እናውቃለንና በጥቃቅን ጉዳዮች ላይ ሳይቀር ጥንቃቄ እናደርጋለን፡፡ለሚመለከተው መስሪያ ቤት ባሳወቅን በአስራ ሁለት ሰአታት ውስጥ ምላሽ ስላልመጣ ሙሉ በሙሉ ህጋዊነታችንን አረጋግጠናል ማለት ነው፣እነሱ ደግሞ ጠብ-መንጃ በእጃቸው አለና የፈለጉትን ሁሉ ማድረግ ይችላል፡፡

Sunday, November 24, 2013

በጎንደር ዩንቨርስቲ ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው .አንድ ተማሪ በታጣቂዎች ተገድሏል

ነገሩ የተፈፀመው የተማራቂ ተማሪዎች “ጌት ተጌዘር” አዘጋጅተው ያንን ፖሮግራም ጨርሰው ከምሽቱ ሁለት ሰአት ተኩል አካባቢ ወይም ከዛ ረፈድ ብሎ በቁጥር ወደ
ሀምሳ የሚሆኑ ተማሪዋች ወደ ዩኒቨርስቲው በር አካባቢ ሲደርሱ ሞች እና በወቅቱ ከሟች ጋር አብራ የነበረች ተማሪ ቀድመው
ወደ ጥበቃ በመድረሳቸው ጥበቃው እንዲቆሙ በሚያዛቸው ወቅት ሟች የለም ከግቢው በር ውጭ ልታስቆመን መብቱ
የለህም እንደውም መታወቂያህን አሳየኝ በማለት በመባባል ነገሩ እንደተጀመረ እና በወቅቱ ተማሪዎቹ መጠጥ መቀማመሳቸውን
፣ ሟችም በስካር መንፈስ ሆኖ ግብግብ መፈጠሩን ጥበቀውም ከሟች ጋር የነበረችውን ምንዋን እንደመቱዋት
ባልታወቀ ሁኔታ እራሱዋን መሳትዋን እና መውደቁዋ ፣ በዚህ መሀል ተማሪዋቹ ለማገላገል በሚጠበጉበት ወቅት ጥይት
በመተኰሱ በድንጋጤ (ሶሰት ግዜ መተኰስሱን ልብበሉ) መበታተናችወን እና ጠዋት ሟች በተባለው ቦታ ደም ፈሶት ሟቶ ስለመገኘቱ በጉንደር ዪኒቨርሰቲ የሳስተኛ አመት ማርኬቲንግ ተማሪ የሆነው እና በወቅቱ ቦታው ላይ የነበረው ወንድሜ
የነሀረኝን ሳልጨምር ሳልቀንስ!! በጣም የሚያመውና

የሚያቆስለው ሟች የተገደለው እርስ በርስ በጩቤ ተወጋግተው ነው በማለት አንድን ተጠርጣሪ ነፍሰ ገዳይ
ዘበኛ ለዛውም የህክምና እርዳታ ቢያገኝ ሊድን የሚችልን ልጅ እንደውሻ ጐትተው ወንዝ ዳር በመጣል የጭካኔ አገዳደል የገደለን ለማድበስበስ

መመኮራቸው ሳያንስ ይህን ለመቃወም ሰልፍ የወጡትን ተማሪዋች በፈደራል አስደብድበው የሰአት እላፊ አውጅው አስረዋቸዋል
ወጣት አንተነህ አስፋው ለገሰ  የማርኬቲንግ ማኔጅመንት የ፫ኛ ዓመት የድግሪ ተማሪ ነበር

“እኔ ራሴ ስድስት ያበዱ ሴቶችን ይዤ መጥቻለሁ..” ራውዳ ጀማል – ከሳዑዲ ተመላሽ ኢትዮጵያዊት (ቃለ ምልልስ)



“እኔ ራሴ ስድስት ያበዱ ሴቶችን ይዤ መጥቻለሁ..” ራውዳ ጀማል – ከሳዑዲ ተመላሽ ኢትዮጵያዊት (ቃለ ምልልስ)

Rawda Jemal
በሃገር ቤት እየታተመ የሚወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሃገራቸው ከተመለሱ ኢትዮጵያውያን ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል። ቃለ ምልልሱ ዘ-ሐበሻ ከዚህ ቀደም ትዘግባቸው የነበሩ የሳዑዲ ሕይወቶችን የሚያጠናክሩ በመሆናቸው ጋዜጠኛ አበባየሁ ገበያው ያደረገችውን ቃለምልልስ ለአንባቢዎቻችን እንደወረደ ይኸው፦
 

በሳዑዲ አረቢያ አልቃሲም ከተማ አፈሳ ተጀመረ

(ዘ-ሐበሻ) ከሳዑዲ አረቢያ 13 ግዛቶች ውስጥ በሰው ብዛት 7ኛ እንደሆነች በሚነገርላት አል ቃሲም ከተማ ስደተኞችን ማፈስ ተጀመረ። ከትናንት ጀምሮ ፖሊስ በየቤቱ እየሰበረ በመግባት ስደተኞችን እያፈሰ መሆኑን ከአካባቢው የዓይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ በላኩት መረጃ ዘገበዋል።
ከዚህ ቀደም በሪያድና በመካ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሞት፣ ለድብደባ፣ ለዝርፊያና ለአስገድዶ መደፈር ያበቃው ስደተኞችን የማባረሩ ተግባር ወደ አልቃሲም ከተማ ተሸጋግሮ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርካታ ኢትዮጵያውን ታስረዋል። ፖሊሶች ካለምንም ማስጠንቀቂያ ቤታቸውን ሰብረው በመግባት በተለይ በሴቶቻችን ላይ ጉዳት እያደረሱ እንደሚገኝ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በሳዑዲ አረቢያ ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን ለማስወጣት በሚል የተጀመረው ይኸው የአፈሳ ተግባር ከኢትዮጵያውያን ውጭ ሌሎችንም ሃገራት የሚመለከት ቢሆንም በኢትዮጵያኑ ላይ የሚደርሰው ጥቃት ግን ለየት ያለ ነው። ሰርተው ያፈሩትን ንብረት እየተዘረፉ የሚገኙት እነዚሁ ኢትዮጵያውያን እቃቸውን ሸጠው እንዳይጨርሱ በፖሊስ ስለማይጠበቁ ወደ እስር ቤት የሚጓዙት ካለምንም ንብረት ነው።


በአልቃሲም ከተማ በተጀመረው አፈሳ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እየተፈጸሙ ነው ያሉት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ይህ ስደተኞችን የማሳደድ ተግባር በ13ቱም የሳዑዲ ግዛቶች ይቀጥላል ተብሏል። እንደደረሰን መረጃ ከሆነ በአል ቃሲም ከተማ የመኖሪያ ወረቀት ለሌላቸው ወገኖች ቤት ያከራዩ ሰዎች ይቀጣሉ።
http://www.zehabesha.com/

“የኢትዮጵያ ህዝብ ለውጥ ፈልጓል፤ ግን ለውጡን የሚሸከምለት ፓርቲ ይፈልጋል”

“የኢትዮጵያ ህዝብ ለውጥ ፈልጓል፤  ግን ለውጡን የሚሸከምለት ፓርቲ ይፈልጋል”November 24/2013

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በቅርቡ ከአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ጋር ውህደት፣ ከሌሎች 10 ፓርቲዎች ጋር ቅንጅት ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ሲሆን ፓርቲው ከረጅም አመታት በኋላ የፕሬዚዳንት ለውጥም አድርጓል፡፡  ከአዲሱ ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሃሪ ጋር ፓርቲው ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር እየፈጠረ ስላለው ውህደት እና ቅንጅት እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ፤ በፓርቲው ጽ/ቤት