እስቲ እንግጠም፤ …እኛ እና ግብጥ

እኛ…
ሃያ ሁለት አመት አንዱን ብቻ ለብሰንከላያችን አድፎ እንኳን መቀየሩ፤ ማፅዳት ሲቸግረን
የግብጥ ጎረምሶች እጅጉን ዘነጡ
በሁለት አመት ውስጥ ሁለቱን ለወጡ
ከዘነጡም ይልቅ፤
እጅግ ተቀናጡ
አረ ከዛም በላይ፤እጅጉን ቀበጡ
እንዲህ ያረጋቸው ምን ይሆን መጠጡ…
ጡ…
ጡ…
ጡ…(ግብጦ ጠጥተው ነው ያልከኝ ልጅ ግብጦ እኮ የኛ መጠጥ ነው… ሞቅ እንኳ አላደርግ አለን እንጂ… ልሳቅ ወይስ ልተወው… አለ ጥርሴ! (ማን ነበርክ አቤ አንተ እና ግጥም አልተገጣጠማችሁም ያልከኝ… ሰውን ሰው ያደረገው አስተያየት ነው ብዬ ሂስህን ተቀብዬዋለሁ፡፡ መግጠሜን ግን አቀጥላለሁ… መጋጠም ቢያቅተን መግጠም ምናባቱ!))