Saturday, October 12, 2013

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ጎፋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በመገኝት ጸሎት አደረጉ


ff (አንድ አድርገኝ ጥቅምት 2 2006 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ነገ ጥቅምት 3 2006 ዓ.ም ከናይጄሪያ ብሐየራዊ ቡድን ጋር ላለባቸው ወሳኝ ጨዋታ ትላንትና አርብ አመሻሹ ላይ ጎፋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በመሄድ አምላክ ድሉን እንዲያጎናጽፋቸው ጸሎት አድርገው ወደ ማረፊያቸው ኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል ተመልሰዋል ፡፡ ከሳምንት በፊት ዴቪድ ማርክ የተባሉ የናይጄሪያ ሴናተር መላው ናይጄርያዊ ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረገውን ጨዋታ ለማሸነፍ እንዲያበረታታ በካቶሊክ አማኞች ለ9 ቀናት የሚዘልቅ የፀሎት ስነስርዓት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበው ነበር፡፡ በአሁኑ ሰዓት በርካቶች በአዲስ አበባ እና በበርካታ ክልል ከተማዎች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን ማሊያ ፤ ስካርፍ እና እጅ ላይ የሚደረጉ ማጌጫዎችን በመግዛት ቡድኑን ለመደገፍ ከፍተኛ ዝግጅቶችን እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ባሳለፍነው የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሐየራዊ ቡድን አንዲት ጎልን ብቻ አግብቶ ወደ ሀገሩ ሲመለስ የጎሏ መገኛ የቅዱስ ገብርኤል ወዳጅ 19 ቁጥር በመልበስ የሚጫወተው አዳነ ግርማ መሆኑ አይረሳም፡፡
የኢትዮጵያ አምላክ ይርዳችሁ

ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ሲኤንኤን በየአመቱ የሚያዘጋጀው የአፍሪካ ጋዜጠኞች ሽልማት ተበረከተለት፡፡



wtt</a
ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ አሸናፊ የሆነበትና ሲኤንኤን በየአመቱ በሚያዘጋጀው መልቲቾይስ የአፍሪካ ጋዜጠኞች ሽልማት ስነስርዓት እየተካሄደ ነው፡፡
ባለቤቱ መምህርት ብርሀን ተስፋዬ እና ልጁ ፍትህ ውብሸት በደቡብ አፍሪካ ኬፕ ታውን ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር ተገኝተው ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ሽልማቱን ተቀብለዋል፡፡ የሽልማት ስነስርዓቱ በ45 የአፍሪካ ሀገራት በቀጥታ እየተላለፈ ይገኛል፡፡

“አዲሱ ፕሬዚዳንት ከኢህአዴግ ማዕቀፍ ወጥተው የራሳቸውን አሻራ ማኖር አለባቸው”

Posted: October 12, 2013 in Uncategorized

0

“አዲሱ ፕሬዚዳንት ከኢህአዴግ ማዕቀፍ ወጥተው የራሳቸውን አሻራ ማኖር አለባቸው”እኛ ስራ እንሰራለን እንጂ ከኢህአዴግ ጋር አተካራ ውስጥ አንገባም – የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ
ባለፈው ሰኞ ላለፉት 12 ዓመታት የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት በመሆን ያገለገሉት አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስ ተሰናብተው አዲስ በተመረጡት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ተተክተዋል፡፡

በፓርላማ የአዲሱን ፕሬዚዳንት በእጩነት መቅረብ ተከትሎ በምክር ቤቱ ብቸኛው የተቃዋሚ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ በሰጡት አስተያየት “አገራዊ መግባባትን ያመጣሉ ብለን ተስፋ በማድረግ ሙሉ ድጋፍ ሰጥተናል” ሲሉ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ናፍቆት ዮሴፍ፤ በአዲሱ ፕሬዚዳንት አመራረጥና በስልጣን ዘመናቸው በሚጫወቱት ሚና እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ከአቶ ግርማ ሰይፉ ጋር ቃለምልልስ አድርጋለች፡፡

መብቱን ለማስከበር ታስሮም እንደማያጎበድድ በእስር ላይ የሚገኘው አንዷለም አራጌ አረጋገጠ


580fa-andualem-arage
October 12, 2013
ፋሽስት ወያኔ ባቀነባበረው የውሸት ክስ በሽብርተኝነት ተከሶና በወያኔ አሻንጉሊት ዳኞች እድሜ ልክ ተፈርዶበት ቃሊቲ ወህኒ ቤት የሚገኘው የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አንዳለም አራጌ ዛሬም በእስር ቤት ለመብቱ እየታገለ እንደሆነ ተገለጸ። በውጭ ያሉት የተቃውሞ ሃይሎች መሰባሰብና እየተጠናከሩ መምጣት ሰላም የነሳው ፋሽስት ወያኔ በሀገር ውስጥ በቁጥጥሩ ስር ባለው የፓርቲዎች ሰላማዊ ሰልፍ እንቅስቃሴ ላይ ዛቻ እንዲያሰማ እንዳደረገው ይታወሳል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ነው እንግዲህ ፋሽስት ወያኔ ለአቶ አንዷለም አራጌ ሰላም በማሰብ በሚል በእስር ቤት የሚጠይቁትን ሰዎች ቁጥር ለመወሰን የፈለገው።
ፋሽስት ወያኔ ከሌሎች የቆዩ እስረኛ ጓደኞቹ ጋር እንዳይገናኝ በማሰብ እስካሁን ድረስ አቶ አንዷለም አራጌን በጊዜያዊ ማቆያ ውስጥ ማሰሩ ሳያንስ ይህን የነጻነት ታጋይ የሚጎበኙ ሰዎች ቁጥር ለመገደብ በመወሰን እነማን እንዲጎበኙት እንደሚፈልግ ስም ዝርዝር እንዲያቀርብ ጥያቄ ማቅረቡ አንዷለምን አበሳጭቷል ተብሏል። በማንኛውም ጊዜና ቦታ ለመብቱ እንደቆመ አስረግጦ በማሳየት ላይ ያለው አንዷለም ግን “መጎብኘት ሕገመንግስታዊ መብቴ ነው ። የስም ዝርዝርም አልሰጥም” በማለቱ የተነሳ ከመስከረም 29 2006 ዓ/ም ጀምሮ ማንም ሰው እንዳይጎበኘው ክልከላ መጣሉን ፓርቲው አንድነት አሳውቋል።

ፖለቲከኛና ሚስማር ሲመታ ይጠብቃል የሚሉ ወገኖች የነጻነት ታጋዩ የሞራል ፅናትና ጥንካሬ ከመቼውም በላይ መድረሱን አድንቀው፤ ፋሽስት ወያኔ የደረሰበት የወረደና የዘቀጠ የፍርሃት ደረጃ ግን በእስር ቤት አጉሮ እያሰቃያቸው ያሉትን የነፃነት ታጋዮች እስካለማመን አድርሶታል ያላሉ። እውነት አስፈሪ ናት የሚሉት እነዚሁ ወገኖች ሕገመንግስታችን የሚሉትን ተረት ተረት እንኳ ሳይቀር ከፋሽስት ወያኔ በተሻለ ሁኔታ የነጻነት ታጋዩ አንዷለም አራጌ አሳምሮ እንደሚያውቀውና እያከበረው መሆኑን የሚያውቀው ሕሊናቸው ጫፍ ከሌለው ፍርሃት ውስጥ እንደከተታቸውም ጨምረው ጠቁመዋል።

የአቶ ዳውድ ኢብሳ ባለቤት አረፉ



የአቶ ዳውድ ኢብሳ ባለቤት ወ/ሮ ሴና ትናንት ምሽት ኖርዌይ በሚገኝ የስደተኛ መጠለያ ውስጥ ማረፋቸው ተሰማ። ወ/ሮ ሴና ላለፉት 20 አመታት ኤርትራ ውስጥ የነበሩ ሲሆን እዚያ በደምግፊት ህመም ይሰቃዩ እንደነበርም ኖርዌይ የሚገኝ ምንጫችን ገልጾልናል።

ምንጫችን እንደገለጸልን ከሆነ ወይዘሮዋ ኖርዌይ ከመግባታቸው በፊት እውነተኛ ስማቸውን በመቀየር በስዊድን የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቀው ነበር። ስማቸውን ለመቀየር የተገደዱበትም ምክንያት የአቶ ዳውድ ኢብሳ ባለቤት መሆናቸው ቢታወቅ ትግሉን ሊጎዳ ይችላል በሚል ሂሳብ መሆኑ ነው።

የስዊድን  መንግስት የጥገኝነት ጥያቄያቸውን ውድቅ በማድረጉ ወይዘሮዋ ወደ ኖርዌይ በመግባት እዚያው እንደገና የፖለቲካ ጥገኝነት ይጠይቃሉ።  ይሁንና የአሻራ ምርመራቸው ሲጣራ ስዊድን ጥገኝነት ጠይቀው እንደነበር በማሳየቱ፡ የኖርዌይ መንግስትም ጥያቄያቸውን ውድቅ አደረገ።  በዚህ መሃል የወይዘሮዋ  የደምግፊት ህመም ጠንቶ፡ ከዚህ አለምበሞት መለየታቸው ታውቋል። ነብስ ይማር። ለቤተሰቦቻቸውም ጽናቱን ይስጣቸው።

የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በትራንስፖርት እጦት ተጉላሉ



የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በትራንስፖርት እጦት ተጉላሉ Written by  አለማየሁ አንበሴ
            የዩኒቨርስቲ የምዝገባ ቀን እንዳያመልጣቸው የሰጉ ተማሪዎች ሰሞኑን ከሌሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ የአውቶቡስ ትኬት ለመቁረጥ እየጣሩ መሆናቸውን ገልፀው፤ የትራንስፖርት ታሪፍ በግማሽ ተጨምሮበትም ትኬት ሊያገኙ አልቻሉም፡፡
ወደ ጅማ ለመሄድ የ177 ብሩ ትኬት ሃምሳ በመቶ ተጨምሮበት ከ260 ብር በላይ ሆኖበት የተቸገረ ተማሪ፤ ያም ሆኖ ትኬት አልቋል በሚል እንደተንገላታ ገልጿል፡፡
ቀድሞ መኪና ሲያመልጥ ወይም ሲበላሽ ቲኬቱን መልሶ ገንዘብ መቀበል እንደሚቻል የሚገልፁት ተጠቃሚዎች፤ አሁን ግን መደበኛው ታሪፍ እንጂ 50 በመቶ (የፐርሠንት) ጭማሪው እንደማይመለስ ገልፀዋል፡፡
ከተለያዩ ክልሎች በአዲስ አበባ በኩል ወደየተመደቡበት ዩኒቨርስቲ የሚጓዙ ተማሪዎች ይበልጥ ተቸግረዋል፡፡ አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ተመድቦ እሁድ ማምሻውን ወደ አዲስ አበባ የመጣ የደብረ ብርሃን ተማሪ፤ ሠኞ እለት ወደ አርባ ምንጭ እሄዳለሁ የሚል ተስፋ የነበረው ቢሆንም፤ በማግስቱም ትኬት ስላላገኘ የምዝገባ ቀን እንዳያልፍበት መስጋቱን ተናግሯል፡፡
ብዙ መንገደኞች እየተጉላሉ መሆናቸውን ያመኑት የመነሃሪያው የህዝብ ትራንስፖርት ተቆጣጣሪ አቶ ሃይሌ ገብሬ፤ የመነሃሪያው አስተዳደር ሃላፊዎችና ሠራተኞች በተቻላቸው አቅም ችግሩን ለመቅረፍ እየሠራን ነው ብለዋል፡፡ የትራንስፖርት እጥረት የተፈጠረው ዩኒቨርስቲዎች በተመሣሣይ ጊዜ ተማሪዎቻቸውን በመጥራታቸው ነው የሚሉት አቶ ሃይሌ፤ በቲኬት አቆራረጥ ላይ ለሚነሱ ቅሬታዎች ተጨባጭ ማስረጃ እንዳልቀረበላቸው ገልፀዋል፡፡ ከሌሊቱ 10፡30 ጀምሮ መነሃሪያው እንደሚከፈትና የቲኬት ቢሮዎችም (ፉካዎች) ደንበኞቻቸውን እንደሚያስተናግዱ የገለፁት አቶ ሃይሌ፤ ቲኬት ቆራጮች የትራንስፖርት ቢሮው ሠራተኞች ሣይሆኑ በመነሃሪያው ውስጥ ያሉት ከ20 በላይ የትራንስፖርት አገልገሎት ሠጪ ማህበራት ሠራተኞች ናቸው ብለዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲ ምዝገባ ሲቃረብና በበአል ወቅቶች የተጓዦች ቁጥር ስለሚጨምር የቲኬት መቁረጫ ቢሮዎቹ እየተጣበቡ ከቢሮ ውጭ ቲኬት ለመቁረጥ ይገደዳሉ የሚሉት አቶ ሃይሌ፤ “በዚህ መሃል አልፎ አልፎ ህገወጥ ተግባራት ሊፈፀሙ ይችላሉ” ብለዋል፡፡ የመነሃሪያው አስተዳደር በውስን የቁጥጥር ሠራተኞች በተቻለው አቅም ቁጥጥር ያካሂዳል፤ ከመነሃሪያው ውጪ ትኬት ይቆረጣል የሚባለው ቅሬታ ግን፣ በአካል ሳናይ ወይም ተጨባጭ ማስረጃ ሳይቀርብልን የትራንስፖርት ማህበራት ሠራተኞችን ጥፋተኛ ማድረግ አንችልም” ብለዋል፡፡
የ“ፐርሠንት ጭማሪ” የሚባለው ክፍያ ምን እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ሃይሌ፤ በአንድ መስመር የሚመደቡት አውቶብሶች በቂ በማይሆኑበት ጊዜ ተጨማሪ አውቶቡሶች በጊዜያዊነት እንዲመደቡ የሚደረግበት አሠራር እንደሆነ ጠቁመው፣ በጊዜያዊነት የተመደቡ አውቶቡሶች ተሣፋሪውን አድርሠው ባዶአቸውን ስለሚመለሱ ቢያንስ የነዳጅ ወጪ ለመሸፈን በመደበኛው ታሪፍ ላይ ማካካሻ ክፍያ ይጨመርበታል ብለዋል፡፡ ከአዲስ አበባ ከ400 ኪ.ሜ በላይ ለሚርቁ ቦታዎች 35 በመቶ፣ ከዚያ ለሚያንሡት ደግሞ 50 በመቶ ጭማሪ ይደረጋል ሲሉም አስረድተዋል፡፡ ቲኬት የሚመልሱ ደንበኞች ከከፈሉበት መደበኛ እና ጭማሪ ታሪፍ ላይ 10 በመቶ ተቀናሽ ተደርጐ ገንዘባቸው እንደሚመለስላቸው አቶ ሃይሌ ጠቅሰው፤ 10 በመቶ የሚቀነሠውም መኪናው ነዳጅ አቃጥሎ በተቆረጠ ቲኬት ስለሚጓዝ ነው ብለዋል፡፡

የህግን የበላይነት ማረጋገጥ የተሳነው ስርኣት የወለዳቸው ስብርባሪ መንግስታት




ምንሊክ ሳልሳዊበሃገሪቱ የተፈጠሩ ስብርባሪ ህወሓት መራሽ መንግስታት የህዝቦችን የመኖር መብት ደፍጥጠዋል::በሃገራችን ውስጥ ላለፉት 22 አመታት ተንሰራፍቶ ያለው የአንድ ፓርቲ ህገወጥ አገዛዝ ለህዝቦች ነጻነት የሚከፈለውን መስእዋትነት እንደ መንግስት ሳይከፍል ህዝብን በማሸበር እና በማወናበድ የህግ የበላይነትን ደፍጥጦ ለስልጣኑ ብቻ እየተራወጠ ይገኛል::በሃገሪቱ የህግ የበላይነት የተከበረ ጊዜ ስልታንህ ያበቃል የተባለ ይመስል ከበላይ ባለስልጣናት ጀምሮ እስከ በታች ካድሬዎች ድረስ የህግን የበላይነት ክደዋል:: ማንም ማንንም ማዘዝ በማይችልበት እና የተሰባበሩ ትንንሽ በንግስታት በራሳቸው ሂደት የተፈጠሩባት ኢትዮጵያ ባለስልጣናቱ መናበብ አለመቻላቸው ህዝቡ በፍትህ ላይ ተስፋ ከቆረጠ ውሎ አደረ አድሮም ኖረ::
ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች ከዚህ ቀደም በቁንጯቸዉ በመለስ ዜናዊ በኩል እንኮረኩማለን፤ ምላስ እንቆርጣልን ወይም እጅ እናስራለን እያሉ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያስተላልፉ የነበረዉን የማስፈራሪያ ቃላት ጋጋታ ባለፈዉ ዐርብ መስከረም 26 ቀን ለዚሁ እኩይ ተግባራቸዉ በቀጠሩት ታማኝ ሎሌያቸዉ በኃ/ማሪያም ደሳለኝ በኩል ሲያስተላልፉ ተደምጠዋል። እንዳሰለጠኑት ጌኛ ፈረስ ወያኔ ባሳየዉ አቅጣጫ ሽምጥ የሚጋልበዉና ከጭንቅላቱ ወጥቶ የሚነገር ምንም ነገር የሌለዉ ኃ/ማሪያም ደሳለኝም የአሜሪካዉን ፕሬዚዳንት የባራክ ኦባማን አባባል እንዳለ በግርድፉ ወስዶ “ከቀይ መስመር በላይ መሄድ የሚፈልግ ይቆነጠጣል” ሲል በዚያ ባልተቆነጠጠ አፉ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ደንፍቷል። የወያኔዉ ተላላኪ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ አልገባዉም እንጂ ይህ ቀይ መስመር ታልፉና ወዮላችሁ የሚሉት ዛቻ አንኳን በአንድ ጀምበር ትርምስምሱ ሊወጣ በሚችል የጦር ኃይል ለሚተማመነዉ ወያኔን ለመሰለ ፀረ ህዝብ ኃይል ቀርቶ በህዝብ ሙሉ ፈቃድ የተመረጠዉና የአለማችንን አስፈሪና እጅግ ጠንካራ ጦር የሚመራዉ ባራክ ኦባም ከተናገረና ከዛተ በኋላ ዛቻዉ አላዋጣ ስላለዉ ሌሎች አማራጮችን ለመመልከት ተገድዷል። ባለፈዉ ዐርብ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ የተናገራቸዉን ተራ ንግግሮች ሁሉ እንመልከት ብንል እንደሱ ስራ ፈቶች አይደለንምና ግዜዉም ፍላጎቱም የለንም፤ ሆኖም አንዳንድ ንግግሮቹ የኢትዮጵያ ህዝብ ለመብቱና ለነጻነቱ የሚያደርገዉን ትግል በንቀት አይን የተመለከቱ ናቸዉና ግንቦት 7 የሚያካሄደዉ የነጻነት ትግል ኃ/ማሪያም ደሳለኝን ከወያኔ ባርነት ነጻ ማዉጣትንም ያጠቃልላልና ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ይህንን ምክር አዘል መልዕክታችንን እንዲያዳምጥ እንጋብዘዋለን። ደግሞም የግንቦት ሰባትን እንቅስቃሴ እከታተላለሁ ብሎ ሲናገር ከራሱ አንደበት ሰምተናልና ምክራችንን ይሰማል የሚል ሙሉ እምነት አለን።

Activists in DC to protest October 12 against World Bank, IMF


October 11, 2013 untitled
The World Bank in Washington, DC

WASHINGTON, DC — Activists who have been accusing the World Bank and IMF of financing tyranny in Ethiopia will protest here in front of the headquarters of the World Bank on Saturday.
Poor Ethiopian farmers as well as indigenous people are being uprooted from their ancestral lands so as to pave the way for corrupt tycoons and foreign corporations, the activists said in a press release sent to Ethiomedia.

In Gambella more than 3 million hectares of Annuak land was sold to foreigners to produce food for their own people. Saudi Arabia and other Gulf nations claim securing land to feed their people for future. More than 70,000 Annuaks have already been removed from their land and another 150,000 will be displaced in the coming few years.
“All this eviction and ethnic cleansing is financed by World Bank. The Ethiopian dictatorial minority

የአገሪቱ ብቸኛ የአስከሬን ምርመራ ክፍል ሥራውን አቋረጠ

Posted: October 12, 2013 in Uncategorized

1

ብቸኛዋ ኩባዊት ባለሙያ የስራ ውላቸውን ጨርሰዋል

ሆስፒታሉ አስከሬን አልቀበልም ብሎ ማስታወቂያ ለጥፏል
በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል ስር በሚገኘው የአገሪቱ ብቸኛ የአስክሬን ምርመራ ክፍል ሲሰሩ የቆዩ ኩባዊት የህክምና ባለሙያ የስራ ውላቸዉን አጠናቅቀው ስለተሰናበቱ የምርመራ አገልግሎቱ ተቋረጠ፡፡ ለስድስት አመት የስራ ውል እየተፈራረመ በሚያስመጣቸው ኩባዊ ባለሙያዎች አማካኝነት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው የአስክሬን ምርመራ ክፍል፣ እስካለፈው ሳምንት ድረስ ሲያገለግሉ ከቆዩት ኩባዊት ዶክተር ጋር የተፈራረመው ውል ለሁለት አመት ብቻ እንደሆነ ታውቋል፡፡ በወቅቱም፣ በአስከሬን ምርመራ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ሃኪሞች ባለመኖራቸው ከኩባ ተጨማሪ ባለሙያዎችን ለማስመጣት አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቅቄያለሁ በማለት አንድ የሆስፒታሉ የስራ ሃላፊ መናገራቸዉ ይታወሳል፡፡ የኩባዊቷ ሃኪም የወር ደሞዝ 6ሺ ብር እንደነበር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከሦስት ሳምንት በፊት መስከረም 6 ቀን 2006 ዓ.ም ባለሙያዋ በመታመማቸው ለሶስት ቀናት የአስከሬን ምርመራ ተቋርጦ



እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ በርካታ የሟች ቤተሰቦችና ሃዘንተኞች ለቀብር ስነ ስርዓት መንገላታቸውን እንደዘገብን ይታወቃል። ይሁን እንጂ፣ ኩባዊቷ ሃኪም የስራ ውላቸዉ ተጠናቅቆ ሰሞኑን ሲሰናበቱ ምትክ ባለሙያ ባለመዘጋጀቱ አገልግሎቱ የተቋረጠ ሲሆን፣ ሆስፒታሉ ለምርመራ የሚመጡ አስከሬኖችን እንደማይቀበል የሚገልፅ ማስታወቂያ ለጥፏል፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ምርመራ ሊካሄድባቸዉ የሚገቡ አስከሬኖችን ለማስቀመጥ የሚያስችል የማቆያ ስፍራ ስለሌለው በሆስፒታሉ ውሳኔ አልተስማማም፡፡ የፖሊስና የሆስፒታሉ ሃላፊዎች ተነጋግረውም ነው፣ ሆስፒታሉ ትናንት አስከሬኖችን መቀበል የጀመረው። ሆስፒታሉ መቼ የምርመራ ባለሙያ እንደሚያገኝና መቼ አገልግሎቱን እንደሚጀምር የታወቀ ነገር የለም፡፡

ሰላም ገረመው(addisadmass)

በውያኔ /ህዋህት የ22 አመት  የስልጣን ግዜት ብዙ የሚያሳዝኑ ህዝብያልተደሰተባቸው መሰራት ሲገባቸው ያልተሰሩ  ነገሮች እንዳሉ የሚታወቅ ሲሆን ዛሬ ደግሞ እጅግ በጣም ሰፊ በሆነችው በኢትዮጲያ  የአገሪቱ ብቸኛ የአስክሬን ምርመራ ክፍል  አስከሬን አልቀበልም ብሎ ማስታወቂያ ለጥፏል አስፋብለው ሲነግሩን ያልሃፍረት ነው በ22 አመት አንድ የሰለጠነ ባለሙያ እንኩዋን አለመኖሩ ምን እንደሚያሳየ ለአንባቢው እተዋለሁ::

Friday, October 11, 2013

ድል ለዋሊያ!

ሰዓሊ አአሌክስን እናመሰግናለን!
ሰዓሊ አአሌክስን እናመሰግናለን
አሌክስ ሲስል እኮ ይስላል አይገልጸውም… ይቀርፀዋል፡፡ አረ አይበቃውም… ያበጀዋል፡፡ ቆይ ሌላ ቃል… ይፈለግ… ይቀምረዋል፡፡ አረ በፍጹም አልተገለፀም…
እስቲ ቃል አዋጡ
እኔስ ቃልም የለኝ
እፁብ ነው ድንቅ ነው
ብለው አልበቃ አለኝ…

ቆይማ የሆነ ቀን አድባራችንን ተለማምጠን በተሟላ ግጥም እናሞካሸዋለን እንጂ ይሄን የመሰለ ስዕልማ ኮምኩመን ፀጥ አንልም!
ለማንኛውም…  በምስጋናዎቹ መሃል፣ በወቀሳዎቹም ጣልቃ፣ በሀዘናችን ውስጥ በጭቅጭቃችን ላይ በዝምታችን ሁሉ ሳቀር ድል ለዋሊያ ድል ለብሄራዊ  ቡድናችን እንላለን!!!

በሽብርተኝነት ተከስሶ ዕድሜ ልክ እስራት ተበይኖበት በቃሊቲ ቅጣት ቤት የሚገኘው የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ አቶ አንዷለም አራጌ በጎብኚዎች እንዳይታይ መደረጉ አንድነት ፓርቲን አሳስቧል

በሽብርተኝነት ተከስሶ ዕድሜ ልክ እስራት ተበይኖበት በቃሊቲ ቅጣት ቤት የሚገኘው የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ አቶ አንዷለም አራጌ በጎብኚዎች እንዳይታይ መደረጉ አንድነት ፓርቲን አሳስቧል፡ More..
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/8274
 
በሽብርተኝነት ተከስሶ ዕድሜ ልክ እስራት ተበይኖበት በቃሊቲ ቅጣት ቤት የሚገኘው የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ አቶ አንዷለም አራጌ በጎብኚዎች እንዳይታይ መደረጉ አንድነት ፓርቲን አሳስቧል፡፡አንዷለም ፍርድ ከተላለፈበት በኋላ በማረሚያ ቤቱ የፍርድ ቤት ጉዳያቸውን ከጨረሱ እስረኞች ጋር መቀላቀል ይገባው የነበረ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ሆን ተብሎ እርሱን ለመጉዳት ጊዜያዊ እስረኞች በሚገኙበት ‹‹ቅጣት ቤት ››ውስጥ እንዲታሰር መደረጉም ህገ ወጥ ድርጊ…
ZEHABESHA.COM

የቢቢኤኑ ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ በአሜሪካ የሚገኙትን አቶ ስብሃት ነጋን አፋጠጣቸው ድምፃችን ይሰማ በማለ

የቢቢኤኑ ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ በአሜሪካ የሚገኙትን አቶ ስብሃት ነጋን አፋጠጣቸው ድምፃችን ይሰማ በማለት ድምፁን አስምትዋል
Breaking News ! Ato Sebhat Neggaa begazetegna Sadiq Ahmed Washington DC lai begeff Qalitina Qillenttoo Seletaserut wendemochachen gudai bettyaqee afatetew.
For More see this video http://www.ethiotube.net/video/27898/Breaking-New-Ato-Sibhat-Nega-confronted-in-Washington-DC-by-activist-Sadiq-Ahmed–October-11-2013

የኢህአዲግ አፈና በሰማያዊ አመራሮች እና አባላት ላይ ተጠናክሮ ቀጥሏል!!!

ፍጥጫ በሞላበት የብአዴን አባላት ግምገማ ከ 1 መቶ 70 በላይ ሰዎች በአንድ ጊዜ መልቀቂያ አስገቡ


ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በ2005 ዓም የስራ ክንውንና በ2006 ዓም የስራ እቅድ በሚል ርእስ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የኢህአዴግ አባላት ግምገማዎች እየተካሄዱ ነው።

በኦሮሚያ ክልል በርካታ የኢህአዴግ አባላት የሆኑ የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች አክራሪነትንና ሽብረተኝነትን በተመለከተ ኢህአዴግ የሚከተለውን ፖሊሲ መተቸታቸውን ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል።
በአማራ ክልል በመካሄድ ላይ ባለው ግምገማ ደግሞ በርካታ የብአዴን አባላት በፓርቲውና በስርአቱ ላይ ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል።

ኪራይ ሰብሳቢነት በሚለው አጀንዳ አባላቱ ኪራይ ሰብሳቢነትን ለመዋጋት ከተፈለገ እኛን ሳይሆን ሚሊዮኖችን የሚዘርፈውን አካል በቅድሚያ መዋጋት ያስፈልጋል ብለዋል።

እኛን እስክርቢቶ ወስዳችሁዋል በማለት ከምትገመግሙን ከአገር የሚወጣውን በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በጊዜ ብትቆጣጠሩ ይሻላል ሲሉ በምሬት የገለጹዩ ነበሩ።


ለአባልነት በሚል በየወሩ 105 ብር በግዴታ እየወሰዳችሁብን የምንበላው ፣ የቤት ኪራይ የምንከፍለው አጥተናል ያሉት አባላቱ፣ በዚህም የተነሳ የድርጅቱ አባላት በየጊዜው የአባልነት መልቀቂያ እያስገቡ ነው ብለዋል።
በ2005 ዓም ብቻ 173 የብአዴን አባላት መልቀቂያ አስገብተዋል።


ለብአዴን አባላት መገምገሚያ ተብለው ከቀረቡት አዳዲስ መስፈረቶች መካከል አንዱ አክራሪነትንና ሽብርተኝነትን መዋጋት የሚለው ይገኝበታል። የድርጅቱ አባላት አክራሪነትን ከደገፉ፣ አክራሪዎችን እያዩ ዝም ብለው ካለፉ፣ ከተቃዋሚዎች ጋር ካበሩ፣ አክራሪነትን በሚደግፉ ሰልፎች ላይ ከተገኙ በአክራሪነት ይፈረጃሉ። አክራሪዎችን መደገፍ የሚለው የሁሉም የሲቪል ሰራተኞች መገምገሚያ መሰፈርት ሆኖ መቅረቡን መዘገባችን ይታወቃል።


በባህርዳር በተደረገው ግምገማ ኢሳት የሚያቀርበውን መረጃ በተመለከተም ተነስቶ ውይይት ተደርጎበታል።
የክልል ሀላፊዎች ከኢሳት የሚወጡትን መረጃዎች ተከታትለው ምላሽ በመስጠት፣ ቢቻል በመቅደም ካልተቻለ ደግሞ ዘግይቶም ቢሆን በቀረበው ዜና እና ፕሮግራም ላይ ከልማት አንጻር እየታየ መለስ እንዲሰጡ ታዘዋል።

ኢህአዴግ ኢሳት ለሚያሰራጨው ዜና ፣ የቻይናን የሚዲያ ፖሊሲ በመከተል ማምከን የሚል ስትራቴጂ ለመከተል እቅድ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ነው።


“ኢሳት ለምን እንደ ችግር ሆኖ ይቀርባል ፣ ችግር የሰለቸው ህዝቡ ነው በማለት ” አስተያየት የሰጡም ነበሩ።
ግምገማው ከክልል እስከ ወረዳ ባሉ እርከኖች እየተካሄደ ይገኛል።
የግምገማውን ተጨማሪ ዘገባ በነገው እለት ይዘን እንቀርባለን።

ግንቦት 7 ለአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ንግግር ምላሽ ሰጠ – “ኃ/ማሪያምንና ጌቶቹን እንዲህ ያቃዣቸዋል?”

አያ ጅቦ  ሳታመካኝ ብላኝ !!!

 
ኃይለማሪያም ደሳለኝ በአንድ ወቅት ዉሸትን የማያዉቅ ጠንካራ ክርሰቲያን ነዉ ተብሎ ሲነገርለት ሰምተን ነበር፤ ታድያ ይህ ሰዉ መለስን ሲተካ ብዙዎች በጥርስ የለሽ አንበሳነቱ ቢስማሙም ዉሸት እንደ ንጉስ በነገሰባት ኢትዮጵያ ዉስጥ ዉሸት የማያዉቅ መሪ መጣ መባሉ ብዙዎቻችንን ነጻነት የተገኘ ያክል አስደስቶን ነበር። ሆኖም ከወያኔ ጋር የዋለ ሰዉ እራሱን ሆኖ መክረም አይችልምና ኃይለማሪያምም ባስቀመጡት ቦታ የማይገኝ የሌላ መንደር ሰዉ ሆኖ ተገኘ። በዚህም የዜጎችን ተሰፋ አመከነ፤ ደስታቸውንም ወደ ኃዘንና ትካዜ ለወጠው።


በሐረማያ ዩንቨርስቲ የመንግስት ባለስልጣናትና የዩንቨርስቲዉ አመራር በጠሩት ስብሰባ ላይ ጽኑ ተቃዉሞ ገጠማቸዉ

መስከረም 30/2006) ቢቢኤን ዋሽንግተን ዲሲ፦ አክራሪነትና ጽንፈኝነትን አስመልክቶ ስልጠና ለመስጥት የፈዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከሐረማያ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ዛሬ ያደረገዉ ስብሰባ ያለዉጤት መበተኑ ታወቀ።
የስብሰባዉ ተሳታፊዎች በግልጽ መንግስት ስም እያመጣ አክራሪ አሸባሪ ብሎ መፈረጁ ግዜ ያለፈበት ነው የተማረዉ የዩንቨርስቲዉ ማህበረሰብ ቀርቶ ዛሬ አባቶቻችንም አይቀበሉትም የመረጃ ምንጫችን ኢቲቪ ብቻ ነው ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ ተሳስታችሗል በማለት ተማሪዎችና የዩንቨርስቲዉ መምህራን የመንግስት ባለስልጣናትን መሞገታቸዉ ለማወቅ ተችሏል።
ጽንፈኛ የሚለዉ ቃል በባርያ ፍንገላ ግዜ በባሪያ አሳዳሪዎች ላይ ያምጹ ለነበሩ ግለሰቦች የተሰጠ ስያሜ ነው በማለት የተናገሩት ክርስቲያን ታዳሚ መንግስት የእስልምና ሐማኖት ተከታዮች ጦርነት በክርስቲያኑ ላይ ሊያዉጁ ነው ብሎ ቢናገር ህዝበ ክርስቲያኑ እንደማያምን በመግለጽ ኢትዮጵያ ዉስጥ አክራሪ አለ ማለቱ አለማቀፋዊ እዉቅናን ያላገንኘ ተዓማኒት የለዉ መሆኑን ገልጸዋል።

ዩንቨርስቲዉ ሶላትና ሂጃብን አስመልክቶ እገዳ ለማድረግ እቅድ እንዳለዉ የገለጸ ቢሆንም ታዳሚዎቹ በሐይማኖት ሳይለያዩ ሐሳቡን ዉድቅ ማድረጋቸዉ ም ታዉቋል።ኢትዮጵያን ልክ እንደ አፍጋኒስታንንና ፓኪስታን ችግር ያለባት ማስመሰሉ ተገቢ አይደልም የኢትዮጵያ ህዝብ ተቻችሎ ያለ በመሆኑ ያንዱ ወገን ሐይማኖት መተግበር ለሌላዉ ስጋት አይደለም የሐማኖት አልባሳት ከበር መልስ የሚለዉ የዩንቨርስቲዉ እቅድ ተቀባይነት የለዉም ሰዎች ሐይማኖታዊ አለባበሳቸዉን ከቀየሩ አማለካከታቸዉን ይቀይራሉ ማለቱ ተቀባይነት የለለዉ ነዉ በማለት ሐሳባቸዉን የገለጹም ነበሩ። ሽብር በሌለበት አገር ስለ ሽብር ማዉራቱ ነራሱ ማሸበር ነው ያሉት ሌላ ተሳታፊ ሙስሊም እንደመሆናችን በቀን አምስት ግዜ መስገድ አለብን በዶርም (በማደሪያ) ዉስጥ መስገድ ከተከለከልን ግቢዉ ዉስጥም እንዳንሰግድ ከተደረግን አስቸጋሪ ነዉ የሚሆነዉ ግን ኢትዮጵያዊ ሙስሊም በመሆኔ በጣም እኮራለሁ ስለምን ካላቹህ ኢትዮጵያ የሰላም አገር ናትና! ምን አልባትም ሶማሊያዊ፣ናይጄሪያዊ ካልያም አፍጋኒስታናዊ ብሆን ኖሮ ይህንን ያገኘሁት ሰላማዊነት አለገኝም ነበር በማለት አስተያታቸዉን ሰጥተዋል።

ወደ ኢትዮጵያዉ መዝገበ ቃላት የሚገቡ አዳዲስ የፖለቲካ ቃላቶች እየተፈጠሩ ለስብሰባ እየተጠራን ለምን ግዜ ይባክናል? ለምን አገርን ለማስደግ ለልማት አንሰበሰብም አያዉቁም ብላቹህ አትናቁን እኛ ከናንተ የበለጠ እናዉቃለን በማለት የመንግስት ካድሬዎችን ያሳፈሩ እንደነበሩ ለማወቅም ተችሏል።

መንግስት ፍርሃትንና መፈራራትን በህዝብ ዘንድ ለማንገስ አክራሪነት፣አሸባሪት እና ጽንፈኝነት በማለት በተለያዩ የትምርት ተቋማት በስልጠናና በዉይይት ስም የሚጠራዉ ተከታታይ ስብሰባ መንግስት ኪሳራን የሚጎናጸፍበት ነዉ! ህዝቡ ከፍርሃት ተላቆ ለመብቱ እንዲታገል የሚጋብዝ መሆኑ በገሃድ እየታየ በማለት ሀሳባቸዉንም የሚገልጹ አሉ።

በዛሬዉ እለት በሐረማያ ዩንቨርስቲ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር አክራሪነትንና አሸባሪነትን አስመልክቶ ባዘጋጀዉ ስልጠና ላይ እስከ አስራ ሁለት ሺ የሚጠጉ ተማሪዎች የተሳተፉበት ሲሆን ተማሪዎች የመንግስት ባለስልጣናት የሚያቀርቡትን ሐሳብ በድምጽ እና ስብሰባዉን ረግጦ በመዉጣት ዉድቅ አድርገዉታል። አንደ ታዛቢዎች አገላለጽ ስልጠናዉ በተገላቢጦሽ ለመንግስት የአመራር አካላት ስልጠና የተሰጠበት ነበር።
ቢቢ ኤን በዛሬዉ ፕሮግራሙ ሰፋ ያለ ዘገባ ይኖረዋል።

“የስደተኛው ማስታወሻ” አዲስ መጽሀፍ ከተስፋዬ ገብረአብ

October 11, 2013 ጋዜጠኛና ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ “የስደተኛው ማስታወሻ” መጽሀፉን በነጻ እንዲነበብ ለቆታል። [ሙሉውን መጽሀፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]
እንደማስገንዘቢያ፣ ድረ-ገጻችን ይህንን የተስፋዬ ገብረአብ አዲስ መጽሀፍ “የስደተኛው ማስታወሻ” አስፈንጣሪ ይዞ የሚቆየው አንባቢያን መጽሀፉን አንብበው ከሚሰጡት አስተያየቶች በመነሳት ይሆናል።
yesedetegnaw mastawesha tesfaye gebereab

Thursday, October 10, 2013

ሼኽ አላሙዲ በዕዳ የተያዘውን ካሩቱሪን ለመጠቅለል አስበዋል

“ኢትዮጵያ ከሁለቱም ያተረፈችው እዳ ነው”alamudi-
በኢትዮጵያ ባሏቸው ኢንቨስትመንቶች መልከ ብዙ ችግሮች እንዳሉባቸው የሚነገርላቸው ሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ በዕዳ የተያዘውን የካሩቱሪን የእርሻ መሬት ለመግዛት ከድርድር ላይ ናቸው ተባለ። ድርድሩ በስምምነት ከተቋጨ የሳዑዲን የምግብ አቅርቦት ለመሸፈን የሚንቀሳቀሱት “ባለሃብት” በጋምቤላ ብቻ ከ230 ሺህ ሄክታር በላይ ድንግል መሬት ባለቤት ይሆናሉ። በድርድሩ መሰረት እስከዛሬ ከወሰዱት በተጨማሪ ብድርም ከንግድ ባንክ ያገኙበታል።

የሳዑዲን የምግብ ኮታ ለመሸፈን ታስቦ እንደተመሰረተ የሚነገርለት የሳዑዲ ስታር አግሮ ኢንዱስትሪ በ2001 ዓ ም 10ሺህ ሄክታር መሬት ተረክቦ በጋምቤላ ስራ ሲጀምር ተጨማሪ 500 ሺህ ሄክታር መሬት እንደሚሰጠው ቃል ተገብቶለት እንደነበር በወቅቱ የተለያዩ መገናኛዎች ዘግበው ነበር።

የሪፖርተር ማኔጂንግ ኤዲተር በደቡብ ክልል ፖሊስ ተወሰደ

የሪፖርተር ማኔጂንግ ኤዲተር በደቡብ ክልል ፖሊስ ተወሰደየሪፖርተር ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር መላኩ ደምሴ ዛሬ ሐሙስ መስከረም 30 ቀን 2006 ዓ.ም. እኩለ ቀን ላይ አዲስ አበባ ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ ከሚገኘው የሪፖርተር ቢሮው በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል የፖሊስ ኃይል አባላት ተይዞ ወደ ሐዋሳ ከተማ ተወሰደ፡፡

የፖሊስ አባላቱ የያዙት የፍርድ ቤት ማዘዣ እንደሚያመለክተው፣ ሪፖርተር ጋዜጣ ረቡዕ ነሐሴ 29 ቀን 2005 ዓ.ም. በጋዜጣው የፊት ገጽ ላይ ‹‹የደቡብ ክልል ሦስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች ከኃላፊነት ተነሱ›› በሚል ባተመው ዜና ምክንያት ጋዜጠኛ መላኩ ለጥያቄ መፈለጋቸውን ይገልጻል፡፡ አዘጋጁ በቅድሚያ አምቼ አካባቢ በሚገኘው በቦሌ ክፍለ ከተማ በፖሊስ ማዘዣ የተወሰደ ሲሆን፣ በኋላም ለክልሉ ፖሊስ አባላት ተላልፎ መሰጠቱ ታውቋል፡፡
የክልሉ ኃላፊዎቹ ተነስተዋል በሚል ሪፖርተር ጋዜጣ የዘገበው ዜና ስህተት መሆኑን በማመን በቀጣይ ዕትሙ እሑድ ጳጉሜን 3 ቀን 2005 ዓ.ም. ላይ ዜናው በወጣበት የጋዜጣው የፊት ገጽ ላይ ማስተካከያ ማውጣቱ የሚታወስ ሲሆን፣ በሐዋሳ የሚገኘው የሪፖርተር ባልደረባም ይህንን ዘገባ በማጠናቀርና በመዘገብ ለሠራው ስህተት ዝግጅት ክፍሉ አስተዳደራዊ ዕርምጃ መውሰዱ ይታወቃል፡፡

የአማራ ክልል የድንበር ከተሞች ለአጎራባች ክልሎች ሊሰጡ ነው፡፡

የአማራ ክልል የድንበር ከተሞች ለአጎራባች ክልሎች ሊሰጡ ነው፡፡
ኢሳት ከአማራ ክልል ባለስልጣናት ባገኘው መረጃ የጃን አሞራ፣ የማይጸብሪ አዋሳኝ፣ ራስዳሸንን ጨምሮ የአዲአርቃይን አካባቢዎች ወደ ትግራይ፣ በመተማ በኩል ደግሞ የተወሰነውን ክፍል ለቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለመስጠት ድርድር በመካሄድ ላይ ነው።

ባለስልጣናቱ ቀደም ብለው የህዝቡን የልብ ትርታ ለማዳመጥ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር የደረሰን መረጃ የሚያመለክት ሲሆን፣ አንዳንድ የወረዳ ባላስልጣናት ጉዳዩን ወደ መድረክ እንድናወጣላቸው ተማጽነዋል።

መንግስት ከአሁን በፊት በአማራ ክልል ስር የነበረውን የመተከል ዞን ለቢኒሻንጉል ጉምዝ ፤ራያና ቆቦ ፤ዳንሻ እና ሁመራ ፤በመተማ በኩል ለሱዳን ፤የመተማ ቀሪው ክፍል ለቤንሻንጉል ፣ በሰሜን ሺዋ በኩል ለኦሮምያ የልማት እገዛ በሚል መሰጠቱን በማውሳት ፣ አሁንም ተጨማሪ መሬት እየተቆረሰ ክልሎችን ለማስደሰት እየዋለ ነው በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

የአንቀጽ 39 ቱርፈቶች የሰጡን ገፀ በረከቶች ናቸው ሲሉ የአማረሩት የድንበር ከተማ ነዋሪዎች፣ ”ጨለምተኛ አባት መሬት እየሸጠ ልጆቹን ከእርስት ይነቅላል፡፡ ጨለምተኛ መንግስት አገርን በመሸጥ ዜጎችን ያስደፍራል፡፤ ምንነታቸውን ያሳጣል መንግስትም ማንነታችን እየነጠቀን ነው ሲሉ” ገልጸዋል።

ትንሽ ስለ ተስፋዬ ገብረአብ

October 10, 2013
Abraha Desta the facebook
አብረሃ ደስታ
‘የተስፋዬ ገብረአብ ማንነት አጋለጠ’ የተባለውን ፅሑፍ አነበብኩት። ገረመኝም። ረዥም ነው። የአንድ ሰው ማንነት ለማጋለጥ አርባ ምናምን ገፅ? ተስፋዬ ገብረአብን ‘ያጋለጠ’ ፅሑፍ ለኔ ምንም ዓይነት ተጨማሪ መረጃ አልሰጠኝም።
ስለ ተስፋዬ ገብረአብ ትንሽ ለመፃፍ የተገደድኩት ምክንያት አንዳንድ የህወሓት ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች ‘የተስፋዬን መጋለጥ’ ምክንያት በማድረግ እኔ አንድ ነገር እንድልላቸው ስለወተወቱኝ ነው። አንዳንዴ’ኮ ጎበዞች ናቸው። ተፎካካሪያቸውን ማኖ ማስነካት ይችላሉ። እኔ ደግሞ ማኖ መንካት እወዳለሁ፤ (ማኖ ካልነካንላቸው ከስድብ ዉጭ ሌላ የሚያውቁት ነገር የላቸው)።
ተስፋዬ ገብረአብ ጎበዝ የስነ ፅሑፍ ሰው ነው። ፅሑፉን ለመገምገም ማንነቱና ስራው አያገባንም። የፅሑፉ ይዘትና መልእክት መገምገም በቂ ነው። እንደ የስነፅሑፍ ሰው ጥሩም መጥፎም ስራዎች ይኖሩታል። ለምሳሌ ‘የቡርቃ ዝምታ’ ፅሑፉ መጥፎ ዓላማ ያለው መሆኑ የሚያሳይ ነው።

በኖርዎይ የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይልን ለመርዳት በ28 ሴፕቴምበር 2013 በተዘጋጀው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በደማቅና በአስገራሚ ሁኔታና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ

g7pf event2በኖርዎይ የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይልን ለመርዳት በ28 ሴፕቴምበር 2013 በተዘጋጀው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በደማቅና በአስገራሚ ሁኔታና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፥፥ ይህ ዝግጅት ከተለያዩ የኖርዎይ ክፍለ ሃገራት እንዲሁም ከሎንደን ድረስ ኢትዮጵያውያን ህዝባዊ ሃይሉን ለመርዳት የተሰባሰቡበትና አጋርነታቸውን የገለፁበት ነበር፥፥
ይህንን ከፍተኛ አላፊነት በመሸከም ፕሮግራሙ ለዚህ መሳካት ያበቃችሁ ያአብይ ኮሚቴና የተለያዩ የሰብ ኮሚቴዎች አባላት፣ በተለያየ ቡድን ለስራው መሳካት የተሰለፋችሁ ወገኖች፣ በመላ አለም እንዲሁም በኖርዌይ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን፣ ታላቅ ምስጋና ይድረሳችሁ፥፥

በማያያዝም በተደጋጋሚ እዚህ በኖርዌይ ምድር አከርካሪያቸው የተሰበረው የወያኔ ቡችሎች እና ሎሌዎች የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይልን የድጋፍ ፕሮግራም ለማስተጓጎል ያደረጉት ሙከራ በማህበረሰባችን ሙሉ የነቃ ተሳትፎና ክትትል ከንቱ ሊሆን ችሏል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ
ኖርዌይ፣ ኦስሎ ሰፕቴምበር 29፣ 2013

በኦስሎ በተካሄደው የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት የተሳካ እንደነበር ትህዴን ዘገበ

tpdm
በተለያዩ አገራት የሚገኙ የትህዴን ደጋፊዎች ግንቦት-7 እያካሄደው ባለ ስብሰባ መገኘታቸውን የትህዴን የህዝብ ግንኝነት ገለጸ፣ ትህዴን የትጥቅ ትግል በማካሄድ ላይ ከሚገኘው ግንቦት-7 ጋር

ተባብሮ ለመስራት መግባባት ላይ ከመድረሱም በላይ በተግባር በተለያየ መልኩ ሲተጋገዙ የቆዩ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተለያዩ ሃገራት የሚገኙ የትህዴን አባላት የግንቦት-7 አመራር ከአባላቱ ጋር

በተለያዩ ሃገራት እያካሄደው ባለ ስብሰባ በመገኘት አንድነታችንን አጠናክረን እጅ ለእጅ ተያይዘን እንሰራለን ሲሉ ለግንቦት-7 ያላቸውን ድጋፍ መግለጻቸውን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣፥

በስብሰባው የተገኙ የትህዴን ተወካዮች አያይዘው እኛ በዚሁ ስብሰባ ስንገኝ ለይምሰል ሳይሆን የህዝብን ድምጽ በአፈሙዝ ረግጦ ስልጣን የተቆናጠጠውን ከፋፋዩን የኢህአዴግ ስርዓትን በሚገባው ቋንቋ
በትጥቅ ትግል ከስሩ መንግሎ ለመጣል ገና ከመነሻው ትህዴን አምኖበት የተነሳለት በመሆኑ የድርጅቱን ዓላማ ዕግቡ ለማድረስ የሁለቱም ድርጅቶች አባላትና ደጋፊዎች የኢህአዴግ ስርዓት መለያ

ከሆነው በዘር የመከፋፈል አባዜ በመውጣት በሙሉ ልብ ድርጊቱን በማውገዝ ከሃገር ውስጥ ይሁን ከሃገር ውጭ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ከመቸውም ጊዜ በላይ ግንኝነታችንን አጠናክረን ተባብረን መስራት ይጠበቅብናል በማለት ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፣፥
የግንቦት-7 አመራርና አባላት በቡኩላቸው የትጥቅ ትግል በማድረግ ላይ ካሉት ተቃዋሚ ድርጅቶች በመሳሪያ ፤ በሰው ሃይልና በዓላማ ሲታይ ትህዴን ጠንካራ መሆኑን በመግለጽ እንዲህ ካለው አስተማማኝ
ድርጅት ጋር ተባብሮ ለመስራት ከመግባባት አልፈን አብረን እየሰራን ነው፣ ይህ መልካም ጅምር አጠናክረን እንቀጥልበታለን ሲሉ መግለጻቸውን የደረሰን ዘገባ ያስረዳል፣፥
ምንጭ፥ http://www.tpdmonline.com/news/NEWS_2013/OCTOBER_2013/ARTICLE_NEWS/abalat_demhit_ab_nay_gunbet-7_akheba_tesatifom.pdf

 
 

The Total Domination of the Ethiopian Army by Ethnic Tigrean Officers

Ginbot 7 Report
Originally Posted May 30th, 2009
Since day one of its active political life, Ginbot 7 has repeatedly informed the international community that the ethnocentric political and economic policies of the TPLF regime are the primary sources of violence and instability in Ethiopia and the Horn of Africa at large Despite the different masks that this crafty regime wears to dupe donor nations and other stakeholders, Ginbot 7 has delved deep into the inner workings of the TPLF regime and exposed the toxic ethnic policies that consumed the life of many Ethiopians, and forced many others to seek refuge in neighboring countries.

ይድረስ ለፕሬዚደንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ

October 10, 2013 ይሄይስ አእምሮ
ክቡር ፕሬዚደንት ግርማ ሆይ፣
ኢትዮጵያንና “ሕዝቦቿ”ን የሚወዱ ከሆነ ቀጥዬ የምነግርዎትን ከልብ እንዲሰሙኝ በሚያምኑት እለምነዎታለሁ፡፡
ሰሞኑን በጡረታ ሊሰናበቱ እንደሆነ ከተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ዜና ዘገባ ሰማሁ፡፡ በመጀመሪያ ሥራዎን ጨርሰው ለዚህ በመብቃትዎ እንኳን ደስ ያለዎ፡፡ ቀጥዬም በሥራ ዘመንዎ ምን እንደሠሩና እኛ በምናውቅልዎም ሆነ እርስዎ በሚያውቋቸው ምክንያቶች የተነሣ ምን ምን መሥራት ፈልገው ሊሠሩ እንዳልቻሉ “ፕሬዚደንታዊ የሥልጣን ዘመን”ዎን የኋሊዮሽ በማሰብ  ከራስዎ ጋር በምልሰት ለመነጋገር የሚያስችል የማሰላሰያ ጊዜ በማግኘትዎ አሁንም በድጋሚ እንኳን ደስ ያለዎ – መልካም ዕረፍት፡፡ ነገር ግን ከስንብትዎ ጋር በተያያዘ የሰማሁት፣ ክፉኛ ያስደነገጠኝና ማመንም ያቃተኝ አንድ ጉዳይ ስላለ ይህን ማስታወሻ ልጽፍልዎ ተገደድኩ፡፡ President Girma Wolde-Giorgis
ጡረታ ሲወጡ እንዲኖሩበት መንግሥት የተከራየልዎት ቤት በነዚሁ ሚዲያዎች እንደሰማሁት በርግጥም በወር ብር አራት መቶ ሺ ነው እንዴ???…(የመጀመሪያውና ባለ530 ሺው ቤት ምናልባትም “ስለተወደደ” ሊሆን ይችላል እንደተሰረዘ ሰምቻለሁ፡፡)
የሰማሁት ጉድ እውነት ከሆነ አሁኑኑ ተግባራዊ ሊያደርጉት የሚገባዎ አንድ ምክር ልለግሰዎ፡፡ ይህን የምለው በብዙ ምክንያቶች ነው፡፡ ዋናው ግን የራሴው ምክንያት ነው፡፡ ቤቴን ቢጎበኙ – እርግጠኛ ነኝ – “ይቅርብኝ በራሴው ቤት እኖራለሁ” ይላሉ፡፡
ውድ ፕሬዚደንት ግርማ፣

Ethiopian Government Choking Muslim Unrest

October 10, 2013Independent European Daily Express
ADDIS ABABA, Oct 10 (IPS) – The refusal by the Ethiopian government to redress grievances harboured by the Muslim community here, which comprises about 34 percent of the country’s 91 million people makes this Horn of African nation vulnerable to extremism.Ethiopian Muslims rocked Addis Ababa
“If legitimate grievances are not met there is a risk that extremist violent elements will exploit those grievances to further their own aim,” Mehari Taddele Maru, head of the African Conflict Prevention Programme at the Pretoria-based Institute for Security Studies, told IPS.
Ethiopia’s Muslim community has been taking part in major demonstrations over the last two years against the country’s ruling regime for alleged interference in its religious affairs. The majority of Ethiopians are Christian.

“አንድነት” ፓርቲ የአዲስ አበባ አስተዳደርና ፖሊስን እከሣለሁ አለ

 ባለፉት ሶስት ወራት “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል መሪ ቃል የመጀመሪያ ዙር ህዝባዊ ንቅናቄ ሲያደርግ የቆየው አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ፤ ባለፈው እሁድ የማጠቃለያ ሰልፉን ሲያደርግ ደርሶብኛል ላለው የሞራልና የንብረት ጉዳት የአዲስ አበባ አስተዳደርና ፖሊስን በህግ እንደሚጠይቅ አስታወቀ፡፡ አንድነትና 33ቱ ፓርቲዎች ከትላንት በስቲያ በአንድነት ፅ/ቤት በሠጡት መግለጫ፤ የህዝባዊ ንቅናቄ ማጠቃለያ ሰልፉን መስከረም 19 አዲስ አበባ ላይ ለማካሄድ እንደምንችል የሚያረጋግጥ የእውቅና ደብዳቤ የከተማ መስተዳደሩ የከንቲባ ፅ/ቤት ቢሰጣቸውም፣ በእጅ አዙር ሠልፉ በመስቀል አደባባይ እንዳይደረግ መከልከላቸውን፣ ከህግ ውጪ በፀጥታ ተቋማት አካባቢ ሰልፉ እንዲከናወን መገደዳቸውንና ቅስቀሣ እንዳይደረግ መታገዳቸውን አመልክተዋል፡፡
 

Sunday, October 6, 2013

ሊበሏት የፈለጓትን አሞራ ይሏታል ጅግራ

ሊበሏት የፈለጓትን አሞራ ይሏታል ጅግራ

26351fb59e29fb0a1375427042 October 6, 2013
ባለፈዉ ዐርብ መስከረም 25 ቀን 2006 ዓ.ም. የወያኔዉ ሎሌ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ አዲስ አበባ ዉስጥ ለአገር ዉስጥና ለዉጭ አገር ጋዜጠኞች በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በየእሁዱ ለሚጠሩት ሰልፍ ጥበቃ ማድረግና በየእሁዱ ተመሳሳይ ጥያቄ ማድመጥ መንግስትን ከሚገባዉ በላይ ያሰለቸዉ ስለሆነ እነዚህ አንድ አይነት ጥያቄ ያነገቡ ሰልፎች የሚቀጥሉ ከሆነ የተቃዉሞ ሰልፍ ማድረግ ይከለከላል በማለት ጌቶቹና ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች የመብትና የነጻነት ጥያቄ የሚያነሳ ማንንም ሰዉ ለማሰር፤ ለመደብደብና ለመግደል ያላቸዉን እቅድ በግልጽ ተናግሯል። የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ ባቀረቡ ቁጥር መሪዎቻቸዉ የሚታሰሩባቸዉ፤ አባላቶቻቸዉ የሚደበደቡባቸዉና ቢሯቸዉ ተሰብሮ ንብረታቸዉ የሚዘረፍባቸዉ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ድርጅቶች አንድም ቀን ሰለቸን ሳይሉ ደብዳቢዉ፤ አሳሪዉና የተቃዋሚ ድርጅቶችን ቢሮ እየሰበረ ንብረታቸዉን የሚዘርፈዉ ወያኔ ሰላማዊ ሰልፍ “ሰለቸኝ” ማለቱ ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረግ ምንም አይነት ትግል የሱን የስልጣን “ዘለአለማዊነት” የሚጻረር መስሎ ከታየዉ ምንም ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ የማይመለስ ፀረ ህዝብ ኃይል መሆኑን እንደገና አረጋግጧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ጋዜጣዊ መግለጫቸው (ከፋሲል ግርማ)

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ጋዜጣዊ መግለጫቸው (ከፋሲል ግርማ)

October 6, 2013
ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ከአካላዊ እንቅስቃሴያቸው እና ድምፀታቸው ጀምሮ እስከ ሚቀልዷቸው ቀልዶች እና የሚያስተላልፏቸው መልዕክቶች በሙሉ የቀድሞውን ሟች ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሚያስታውስ መልኩ ያካሄዱት ጋዜጣዊ መግለጫ ባብዛኛው ተቃርኖ የበዛበት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም በጋዜጣዊ መግለጫቸው ከጥያቄ እና መልሱ አስቀድመው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መንግስት ያለውን መረጃ የተናገሩ ሲሆን እንዲሁ በደፈናው አሃዝ ሳይጠቅሱ የሃገሪቱ ምጣኔሃብት እያደገ መሆኑን፤ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ዘርፉ ካለፈው አመት የተሻለ መሆኑን እና በሰላም እና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከጎረቤት ሃገራት ጋር ኢትዮጵያ ያላትን ግንኙነት ለማብራራት ሞክረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ከኤርትራ በስተቀር ከሌሎች ጎረቤት ሃገራት ጋር ያላት ግንኙነት ስትራቴጂካዊ መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለይ የኢትዮጵያ መንግስት ከሶማሊያ መንግስት ጋር ያለውን ግንኙነት ዘርዝረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ቡጂሌው ወያኔ እናት ሀገራችን ኢትዮጵያን ታሪኳን ማንነቷን እያጠፋ የገኛል ስለዚህ ሁሉም የፓለቲካ ድሪጅት አብሮ መስራት ይጠበቅበታል አንድነት ካለ ውጤት አለ አንድነት ካለ ማሸነፍ አለ  አንድነት ካለ ድል አለ አንድነት ካለ ወያኔ ይፈራል  አንድነት ካለ ወያኔ ሀይል  ይለውም አንድነት ካለ  አገራችን ከወያኔ ሥቃይ ትወጣለች ድል ለሀገራችን>

ወያኔን ለማስወገድ አስገዳጅ የትግል ስልት ወሳኝ ነው!!!



      ወያኔን ለማስወገድ አስገዳጅ የትግል ስልት ወሳኝ ነው!!!
ከለምለም አንዳርጌ(ኖርዌይ)
ላለፉት ሁለት አስርተ አመታት ኢትዮጲያና ሕዝቦ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ ይህ ነው የማይባል ግፍና ሰቆቃ ሲፈጽም የኖረው የዘረኛው የወያኔ ስርዓት የእድሜ ዘመኑ ማብቂያ ጠርዝ ላይ ለመሆኑ ኢትዮጲያን ያህል ሃገርና ህዝብ ከሚመራ ስርዓት የማይጠበቁ የማፍያ ተግባራቱ ስርዓቱ ያለበት የዝቅጠት ደረጃ ጠቋሚዎች ናችው፡፡ በእድሜ ዘመን መጀመሪያ በስም እንጂ በተግባር ዴሞክራሲን የማያቀው የአንድ ጎጥ ቡድን ለይስሙላ ባስቀመጠው ህገ-መንግስት የተካተቱትን የዜጎችን መብት በመሻር ሃገሪቱን የምድር ሲኦል አርገዋታል፡፡ በሃገሪቱ ህገ-መንግስት መሰረት መብታቸውን አውቀው የተቋቋሙ የሞያ ማህበራትም ሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶች በራሳቸውም ሆነ በስርዓቱ ተጽእኖ ይህ ነው የማይባል ተግባራት ሳይከውኑ በዘረኛው ስርዓት እየተኮረኮሙ ይፈርሳሉ አልይም በሞኖፖል በተያዘው የፍትህ ስርዓት ተወንጅለው በግፍ በእስር  ይማቅቃሉ፡፡


 

ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ አላደርግም አለች

 

ኢ.ኤም.ኤፍ – ከአፍሪካ ለአለም ዋንጫ ካለፉት አስር አገሮች መካከል፤ ኢትዮጵያ እና ግብጽ ይገኙበታል። እሁድ ኦክቶበር 13 ኢትዮጵያ እና ናይጄርያ – ኦክቶበር 19 ግብጽ ከጋና ጋር ይጫወታሉ። ኢትዮጵያ ከናይጄሪያ ጋር ለምታደርገው ግጥሚያ ከወዲሁ ዝግጅት ላይ መሆናቸው ባለፈ፤ ከሌላ አገር ጋር የወዳጅነት ጨዋታ አላደረጉም። ሱፐር ስፖርት ድረ ገጽ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽንን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ ግን፤ ግብጽ ለኢትዮጵያ ያቀረበችውን የወዳጅነት ጨዋታ ውድቅ አድርጋዋለች።
xz ፌዴሬሽኑ በዚህ ጉዳይ ምላሽ ሲሰጥ፤ “አዎ ከግብጽ በኩል የወዳጅነት ጥያቄ ቀርቦልናል። ሆኖም በግብጽ አገር መረጋጋት የለም። በ እንዲህ አይነቱ አለመረጋጋት በሌለበት አገር ጨዋታ ማድረግ አንችልም። ለነገሩ ከዚህ በፊት እኛ የወዳጅነት ጨዋታ እንዲያደርጉ ጠይቀናቸው ፈቃደኛ አልሆኑም። የአሁኑ የኛ ውሳኔ ለተጨዋቾቻችን ደህንነት ሲባል የተደረገ እንጂ፤ ግብጽን ካለማክበር የመጣ አይደለም።” ብለዋል። በ እርግጥም በግብጽ አገር ባለው አለመረጋጋት ምክንያት ኦክቶበር 19 ቀን ከጋና ጋር የሚደረገው ጨዋታ በዝግ ስቴዲየም ውስጥ እንዲሆን በፊፋ በኩል ተወስኗል። የት ሊሆን እንደሚችል ገና አልታወቀም። ቀኑ ሲደርስ ደግሞ ተመልካች በሌለበት ይጋጠማሉ ማለት ነው። ለጋና ተጫዋቾች ደህንነት ሲባል እስካሁን የትኛው ስቴዲየም እንደሚጫወቱ ይፋ አልተደረገም።
EMF

ጥያቄው ሃይመኖታዊ ነፃነት መብት ወይስ ፖለቲካዊ ……(አቶ ይድነቃቸው ከበደ)

October 5, 2013 ‹‹ መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፤ሃይማኖትም በመንግስት ጣልቃ አይገባም፡፡ ›› ሕገ መንግስት አንቀጽ 11 ንዕሱ አንቀፅ 3 ፡፡ ‹‹ መንኛው ሰው የመሰብ፤የሕሊና እና የሃይማኖት ነጻነት አለው ፡፡ ይህ መብት ማንኛውም ሰው የመረጠውን ሃይመኖት ወይም እምነት የመያዝ ወይም የመቀበል ሃይማኖቱንና እምነቱን ለብቻ ወይም ከሌሎች ጋር በመሆን በይፋ ወይም በግል የማምለክ፣ የመከተል፣የመተግበር ፣የማስተማር ወይም የመግለጽ መብትን ያካትታል፡፡››ሕገ መንግስት አንቀጽ 27 ንዕሱ አንቀፅ 1 ፡፡Yidenachew Kebede

‹‹ ማንኛውም ሰው የሚፈልገውን እምነት ለመያዝ ያለውን ነጻነት በኃይል ወይም በሌላ ሁኔታ ማስገደድ ወይም መከልከል አይቻልም፡፡ ›› ሕገ መንግስት አንቀጽ 27 ንዕሱ አንቀፅ 3 ፡፡
የሙስሊሞች ጥያቄ

1ኛ. በስልጣን ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች ያለምርጫ የመጡና ህዝቡን የማይወክሉ በመሆናቸው ህዝቡ በነፃ ፍላጎቱ፤ በገለልተኛ አስመራጮች እና በመስጂድ ደረጃ በሚመርጡ አመራሮች ይተኩልን፡፡
2ኛ. አህባሽ የተባለው እምነት እንደ ማንኛውም እምነት እራሱን ችሎ የመንቀሳቀስ መብት ይኖረዋል እንጂ በሙስሊሙ መስጂዶችና መዋቅር ውስጥ በግድ እንዲጫን ሊደረግ አይገባውም ፡፡
3ኛ. አወሊያ የህዝብ ንብረት እንደመሆኑ መጠን እራሱን በአግባቡ ማስተዳደር ለማይችለው መጅሊስ መሰጠት የሌለበት ሲሆን ህዝብ በሚመርጣቸው የቦርድ አባላት ይተዳደር ፡፡

እነዚህን ጥያቄዎች ለመንግስት ለማድረስና መፍትሄ ለማፈላለግ ደግሞ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በራሱ ፍቃድ 17 አባላት ያላቸውን ተወካዮች (ከሃገር ሽማግሌዎች፤ ከሃይማኖት ኣዋቂዎች፤ ከምሁራን እና ከሰባኪያን) ጥቆማውን በመቀበል እና ከመላ ሃገሪቱ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የተፈረሙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የድጋፍ ፊርማዎችን በማስረጃነት በመያዝ እነዚህን ሦስት ጥያቄዎች ብቻ በመያዝ ምላሽ ለማፈላለግ ከላይ ታች ሲሉ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሜቴዎች ስምንት ወራት አለፉ፡፡ በሂደቱ ከክፍለ ከተማ እስከ የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት፤ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እስከ ሁሉም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ድረስ እነዚህን ጥያቄዎች በመተንተን በተለያየ ግዜ አቅርበዋል ውጤቱ ግን አራተኛ ጥያቄ ወለደ እሱም፡-
4ኛ. ከላይ ለተዘረዘሩት ጥያቄዎች ለመንግስት ለማድረስና መፍትሄ ለማፈላለግ ሃይማኖታዊ ግዴታቸውን በመወጣታቸው ለእስር የተዳረጉ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሜቴዎች ይፈቱ ፤የሚል ነው፡፡

ሆኖም በምድር ላይ የሚከናወኑ ነገሮች ሁሉ ፖለቲካዊ እንድምታ አላቸው ከሚል የተቆነጠረ ሃሳብ በመነሳት ምክንያቲዊ እና ወቅታዊ ነገሮችን ግምት ውስጥ ሳያስገብ ተቃራኒን ሃሳብ ለማሸነፍ ወይም ድጋፍ ለማግኘት ተብሎ መሰረታዊ የህግ ስእተት እና ፖለቲካዊ ወለምታ ከመዳረግ በፊት በመግቢያነት የተጠቀሱት የህገ መንግስቱ ድንጋጌዎችና የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄ ጎን ለጎን በማስተያየት የተሻለ ሃሳብ እስኪገኝ ድረስ ለድምዳሜ የሚያገለግሉ ናቸው፡፡

በመሆኑም ከላይ የተገለጹት የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄ የመብት ጥያቄዎች ናቸው መብት ደግሞ ከህግ የሚመነጭ ሲሆን የህግ ጥያቄ መጠየቅ በራሱ ፖለቲካዊ ጥያቄ መሆን አይችልም፤የፖለቲካ ጥያቄ መሆን የሚችለው እስላማዊ መንግስት እናቋቁም ወይም ፖለቲካዊ ሥልጣን ይኑረን እና የመሳሰሉት ከሙስሊሙ ማህበረሰብ የተነሱ ሃሳቦች እና በዚህ ምክንያት የደረሰ ጉዳትና እስራት ቢኖር ሂደቱ ፖለቲካዊ ነው ብሎ በመደምድም በጉዳዩ ላይ ከአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት አቋም መያዝ ይቻላል ግን እውነታው የመብት እንጂ ፖለቲካዊ ጥያቄ አለመሆኑ ነው፡፡

በተጨማሪ እነዚህ ግልፅ የመብት ጥያቄዎች በሃይል በመጠምዘዝ ፖለቲካዊ ይዘት ለማላበስ በመንግስት የሚደረገው ጥረት ለማንም ግልፅ ቢሆንም የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄዎች ንፁህ የመብት ጥያቄ ነው፤የፖለቲካ ጥያቄ ነው ለማስባል ተራ አሉባልታ ለማጠናከር ተደጋጋሚ በእውነት ላይ ያልተመሰረተ ዘጋቢ ፊልም በኢቲቪ በማቅረብ ያልተሳካ ጥረት ተደርጓል፤ በቀጣይም ይበልጥ ተጠናክሮ የህዝብን አንድነትን ሊንዱ በሚችሉ መልኩ ተቀነባብሮ ሊቀርቡ እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡

ይሁን እንጂ ከሃይማኖታዊ መቻቻል ባለፍ ሃይማኖታዊ መከባበር ላይ የተመሠረተ ግንኝነትን ባዳበር ህዝብ መካከል አንዳችም አስፈሪ ነገር እንደማይኖር ይገመታል፤ለዚህም ጥሩ ማሳያ የሚሆነው የሙስሊሙ ማህበረስብ ጥያቄ ከእምነት ነፃነት መብት የመነጨ ጥያቄ መሆኑን በመረዳት የሌላ እምነት ተከታይ ለሙስሊም ማህበረሰብ ጥያቄ ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያለሆነ ድጋፍ በመስጠት ላይ ይገኛል ይህ ደግሞ የመንግስትን አፍራሽ ተልኮ ያጋለጠ ነው፡፡

በመሆኑም የሙስሊሞች ጥያቄ ከህገ መንግስቱ ጋራ ሲመሳከር ሙሉ በሙሉ የመብት ጥያቄ ነው ለዚህም ነው ከአንድ ዓመት ከ 6 ወር በላይ ‹‹ ፍትህ ፍትህ ፍትህ ፍትህ………. ›› ሲሉ የከረሙት መንግስት ደግሞ በተቃሪኒው ‹‹ የሃይማኖት አክራሪነት ለማስፋፋት እና ድብቅ ፖለቲካዊ አጀንዳቸውን ለማስፈጸም የሚጥሩ ›› በማለት እየወነጀላቸው ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ የሙስሊሞች ጥያቄ ሃይማኖታዊ ጥያቄ ነው፡፡ ስለሆነም የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄ እና የመንግስት ተሳትፎ በማስተያየት ጥያቄው ሃይማኖታዊ እንጂ ፖለቲካዊ ላለመሆኑ እነዚህን ማስረጃዎችን መመልከት ተገቢ ናቸው፡-

1ኛ. መንግስት በቀጥታ እጁን በማስገባ የመጅሊስ ምርጫ በቀበሌ እና በመንግስት ካድሪዎች እንዲካሄድ አድርጓል፡፡የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄ ደግሞ የመጅሊስ ምርጫ በተቻለ ፍጥነት እና በገለልተኛ አስመራጭ አማካኝነት ምርጫ መካሄድ የሚኖርበት ሲሆን ጉዳዩም ሃይማኖታዊ እንጂ ፖለቲካዊ ባለመሆኑ በመስጂድ ሊካሄድ ይገባዋል፡፡

2ኛ. አህባሽ የተባለው እምነት ሸኽ አብደላ አልሃረሪ በሚባሉ የሚመራ እምነት በመንግስት ልዩ ድጋፍ ተደርጎለት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትሩ በወኑት ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም አማካኝነት ሃምሌ 2003 ዓ.ም በጊዮን ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ‹‹ይህንን አመለካከት በሃገራችን ለማስፋፋት እንዴት ብንሰራ ይሻላል በሚል መንግስት ለረጅም ግዜ ሲመክር ቆይቷል›› በማለት በሰጡት ሰፊ ጋዜጣዊ መግለጫ የአህባሽ እምነት ከመንግስት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ከመኖሩ ባለፈም አስተምህሮቱን መንግስት ለማስፋፋት ፍላጎት እንዳለው የሚያሳይ ነው፡፡ የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄ ደግሞ መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፤ሃይማኖትም በመንግስት ጣልቃ አይገባም፡፡ የሚለውን ህገመንግስታዊ ድንጋጌ ተጥሷል በተጨማሪ አህባሽ የተባለው እምነት እንደ ማንኛውም እምነት እራሱን ችሎ የመንቀሳቀስ መብት ይኖረዋል እንጂ በሙስሊሙ መስጂዶችና መዋቅር ውስጥ በግድ እንዲጫን ሊደረግ አይገባውም ፡፡

3ኛ. አስተዳደራዊ የሆነ ጥያቄ ሲሆን እሱም አወሊያ ት/ት የህዝብ ንብረት እንደመሆኑ መጠን እራሱን በአግባቡ ማስተዳደር ለማይችለው መጅሊስ መሰጠት የለበትም ህዝብ በሚመርጣቸው የቦርድ አባላት ይተዳደር የሚለው የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄ ነው ፡፡ ይህን ጥያቄ በሁለት መንገድ ማየት ይቻላል አንድም መጅሊሱ የሙስሊሙ ማህበረስብ ውክልና እንደሌለው ሁለተኛ ደግሞ የአወሊያ ት/ት አስተዳደር ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለው እንዲሆን ካስፈለገ የተለያዩ መመዘኛዎችን መሰረት በማድረግ ህዝብ በሚመርጣቸው የቦርድ አባላት ይተዳደር የሚል ነው፡፡

4ኛ. ከላይ የተዘረዘሩት ችግሮችን ለመግለፅ እና ለችግሮቹሁ መፍትሔ ለማፈላለግ የተመረጡ የኮሜቴ አባላት ከመንግስት ተወካዬች ጋር በተደጋጋሚ በመገናኘት ጥያቄው ሃይማኖታዊ መሆኑ እና መፍትሔም ሊገኝለት የሚችለው ሃይማኖታዊ በሆነ መንገድ ብቻ መሆኑን ሲያስረዱ ሰንብተዋል፤ መንግስትም በጉዳዩ ላይ ከኮሜቴ አባላት ጋር ሲደራደር ቆይቷል፡፡ይሁን እንጂ መንግስት በስተመጨረሻ ካፈርኩ አይመልሰኝ በሚል ተልካሻ አስተሳሰብ በመነሳት የኮሜቴ አባላትን በሽብርተኝነት ስም ከሶ ለእስር ዳረጋቸው፡፡

ይሁን እንጂ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄ ሲመረመር በየትኛውም መመዘኛ የሃይመኖት ነፃነት መብት ጥያቄ ነው ፤ በመንግስት በኩል ደግሞ እየሆነ ያለው ፖለቲካዊ አካሄድ ነው ለዚህም ነው ጥያቄችን ሃይማኖታዊ እንጂ ፖለቲካዊ አይደለም በማለት ከመናገር እና ከመፃፍ ባለፈም ሰላማዊ በሆነ መንግድ በተለያ ቦታና ጊዜ ድምፃቸውን ሲያሰሙ የከረሙት፡፡ የነገሩ አካሄድ እንዲ በሆነበት ሁኔታ የሙስሊሞች ጥያቄ የፖለቲካ ጥያቄ ነው በማለት ከፖለቲካ ፓርቲ መገለጹ ከስእተትም በላይ ስእተት ነው፤ ነገ ደግሞ ከችግሩ ለመላቀቅ በአቻነት አብረን እንስራ ወደሚል ጥያቄ እንዳያመራ ያሰጋል ፡፡ ነግር ግን በህገ መንግስቱ የተቀመጡ መብቶች እንዲከበሩ አደርጋለው ለዚህም ድጋፋቹሁን ስጡኝ ብሎ የፖለቲካ አጀንዳ አድርጎ መታገል እና ጥያቄ ማቅረብ ከፖለቲካ ድርጅቶች የሚጠበቅ ተግባር ነው ፡፡
Yidenachew-Kebede

No Human Rights = No Development

September 26, 2013

Oakland Institute and the Housing and Land Rights Network Submit Human Rights

መሬት የማን ነው?

ክፍል አንድ – ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
land
October 6, 2013 10:53 
አገር ማለት በአባቶች፣ በአያቶችና በቅድማያቶች አጥንትና ደም ተገንብቶ የታጠረ መሬት ነው፤ የዶር. በድሉ ዋቅጅራን ዋይታ እየኮረኮረ የሚያወጣውና የሚያስተጋባው የፍቅር ስሜት ምንጭ ነው።
የተከሰከሰውና ተፈረካክሶ አፈር የሆነው አጥንትና የወረደው የአያቶችና የቅድማያቶች ደም እየፈሰሰ መሬቱ ላይ በሚገኙ ወንዞች ውስጥ ሁሉ ገብቶአል፤ እንዲያውም እነዚህ ወንዞች ወስደው በቀይ ባሕር፣ በሜዲቴራንያን ባሕርና በሕንድ ውቅያኖስ ጨምረውታል፤