Friday, November 15, 2013

በሳዑዲ አረብያ የመከራ ማጥ ውስጥ ላሉት ወገኖቻችን ሲባል ፈጥነን እንነሳ!

November 11, 2013
ዳኛቸው ቢያድግልኝ
እንደ ሰው አንድ የሚያደርገን ባሕርይ፣ እንደ ኢትዮጵያዊነትም ሁላችንንም የሚመለከተንና የፖለቲካም ሆነ የሃይማኖት ልዩነት የማይነጣጥለው በደል በሳዑዲ አረብያ ግዛት እየተፈጸመ ነው። የጥቃት ዒላማዎቹ ኢትዮጵያውያን ናቸው። የጥቃቱ ልክ የለሽነትና አሰቃቂነት ደግሞ ይበልጥ የጎላው በሴት እህቶቻችን ላይ ነው። ይህ ዛሬ በሳዑዲ አረብያ የሚደረገው ጥቃትን ማስቆምና ቁጣችን መቆምያ እንደማይኖረው ማሳየት ለነርሱ ብቻ ሳይሆን ለራሳችን ደህንነትም ጭምር የምናደርገው ነው። ምክንያቱም ነገ ተመሳሳይ ጥቃትና በደል በመላው አለም ይስፋፋል። በአፍሪካ ሀገሮች የተበተኑ ኢትዮጵያን ከሶማሌና ኤርትራ ከሚሰደዱት በተለየ ይዘረፋሉ፣ ይደፈራሉ ይዋረዳሉ። እንደ አገር ልጅ አብረው እንዳይቆሙ በዘር በሀይማኖትና በፖለቲካ አቋም ምክንየት የተበተኑ ናቸው። ለሰላሳና አርባ አመት አምባገነኖች ያደረጉት ጭፈጨፋና በደል ፍርሃትን ሰማይ ጥግ አውጥቶታል። እናም ኢትዮጵያዊ በየተበተነበት ሁሉ ተኛ ሲሉት የሚተኛ አውልቅ ሲሉት እርቃኑን የሚቆም ፈሪ እንዲሆን ተደርጓል። ሲቸግረው የሚጮኸውን ያህል ሲመቸው ለወገን የሚደርሰው ጥቂቱ ነው። ይህ ሊቀጥል አይገባም!Protest at Saudi Arabia Mission to United Nations!
ቀደም ባለው ጊዜ አንድ ኢትዮጵያዊ ጥቃት ቢደርስበት ባገኘው መሳርያ ዘነጣጥሎም ቢሆን ይገድል ስለነበር ማንም አይደፍረውም ነበር። በዘመነ ኮሎኒያሊዝም ኢትዮጵያውያን በሄዱበት ሁሉ አንገት የማይደፉና ክብራቸውን የማያስነኩ ነበሩ። ዛሬ ጠቁመው የሚያስይዙ፣ ወገናቸውን የሚያሻሽጡና የሚሰልሉት ሁሉ ኢትዮጵያውያን ናቸው። የዚህ ጽሁፍ መነሻም ሆነ መድረሻው የድሮውን አሁን እየሆነ ካለው ጋር ማወዳደር አይደለም። ለዚህ የሚሆን የቅንጦት ጊዜም የለንም። ዓላማው አሁን እየደረሰብን ያለውን በደል በቁርጠኛነት አንታገለው ነው። ይህ ኢትዮጵያውያንን በሙሉ ከዳር እስከዳር ማስነሳት ካልቻለና ቁጣቸውንም ለመላው አለም ማሳየት ካልቻለ እውነትም አገራችን እያበቃላት ነው ማለት ይቻላል።

Ethiopian Police Crackdown on Anti-Saudi Protest


Ethiopian police have used force to disperse hundreds of people protesting against targeted attacks on Ethiopians in Saudi Arabia.
Police units Friday blocked roads to prevent the protest at Saudi Arabia Embassy from growing. Some two dozen people were detained.
TPLF-federal-police-beat-up-their-own-people-620
The police forced some journalists to delete photos. The government’s spokesman, Shimelis Kemal, wasn’t immediately available for comment.
One protester, Asfaw Michael, who was beaten, said he didn’t understand why Ethiopia wanted to shield Saudi Arabia from the protest.
Many foreign workers in Saudi Arabia are fleeing or are under arrest amid a crackdown on the kingdom’s 9 million migrant laborers. Close to 500 Ethiopians have been repatriated.
Last weekend, Saudi residents fought with Ethiopians. Video emerged of a crowd dragging an Ethiopian from his house and beating him.

Thursday, November 14, 2013

በግብጽ ኢትዮጵያውያን እየተሸጡ ነው!

የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ማህበር በግብጽ ባወጣው መግለጫ በሱዳን እና በግብጽ የድንበር ከተሞች በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ እየደረሰ ያለውን አሰቃቂ ድርጊት ዘርዝሮ አቅርቧል።

ዳግማዊ ሆሎኮስት በኢትዮጵያውያን ላይ? ከዲያቆን ዓባይነህ ካሤ

ኢትዮጵያውያን ደማቸው የዐረብን አስፋልት አቀለመው፡፡ ባንዲራውን በራሱ ላይ ሸብ ያደረገው የእማማዬ ልጅ የእኔ ጀግና ማንነቱን እየተናገረ በአናቱ ላይ የወረደውን የድንጋዩን ናዳ በሀገሩ ፍቅር ተቋቁሞ በክብር አሸለበ፡፡ ለእርሱ ከዚህ በላይ ሌላ ድል አልነበረምና፡፡ ድንጋዩስ እርሱን አሳርፎታል፡፡ ነፍሱን ይማርልን እንጂ! ባንዲራችን ግን እንደተመታች እንደታመመች ናት፡፡ እውን ይኽ የሆነው በእኛ ላይ ነው?
 ይህቺ ባንዲራ እኮ ጨርቅ አይደለችም፡፡ ያ በሳኡዲ መሬት ተወግሮ የሞተው ወንድሜ የኮራባት በሞቱ ጊዜ የለበሳት የክብሩ፣ የማንነቱ መገለጫ እንጂ፡፡ ማንም ባይደርስለት ባንዲራው ነበረችለት፡፡ በእርሷ ተጽናና፡፡ ሞተ አልለውም መሰከረ እንጂ፡፡ ባንዲራ ለብሶ መከራን መጋፈጥ የሰማእታት ወግ ነው፡፡

Tuesday, November 12, 2013

በሳዑዲ አረብያ የመከራ ማጥ ውስጥ ላሉት ወገኖቻችን ሲባል ፈጥነን እንነሳ!

በሳዑዲ አረብያ የመከራ ማጥ ውስጥ ላሉት ወገኖቻችን ሲባል ፈጥነን እንነሳ!

ዳኛቸው ቢያድግልኝ
እንደ ሰው አንድ የሚያደርገን ባሕርይ፣ እንደ ኢትዮጵያዊነትም ሁላችንንም የሚመለከተንና የፖለቲካም ሆነ የሃይማኖት ልዩነት የማይነጣጥለው በደል በሳዑዲ አረብያ ግዛት እየተፈጸመ ነው። የጥቃት ዒላማዎቹ ኢትዮጵያውያን ናቸው። የጥቃቱ ልክ የለሽነትና አሰቃቂነት ደግሞ ይበልጥ የጎላው በሴት እህቶቻችን ላይ ነው። ይህ ዛሬ በሳዑዲ አረብያ የሚደረገው ጥቃትን ማስቆምና ቁጣችን መቆምያ እንደማይኖረው ማሳየት ለነርሱ ብቻ ሳይሆን ለራሳችን ደህንነትም ጭምር የምናደርገው ነው። ምክንያቱም ነገ ተመሳሳይ ጥቃትና በደል በመላው አለም ይስፋፋል። በአፍሪካ ሀገሮች የተበተኑ ኢትዮጵያን ከሶማሌና ኤርትራ ከሚሰደዱት በተለየ ይዘረፋሉ፣ ይደፈራሉ ይዋረዳሉ። እንደ አገር ልጅ አብረው እንዳይቆሙ በዘር በሀይማኖትና በፖለቲካ አቋም ምክንየት የተበተኑ ናቸው። ለሰላሳና አርባ አመት አምባገነኖች ያደረጉት ጭፈጨፋና በደል ፍርሃትን ሰማይ ጥግ አውጥቶታል። እናም ኢትዮጵያዊ በየተበተነበት ሁሉ ተኛ ሲሉት የሚተኛ አውልቅ ሲሉት እርቃኑን የሚቆም ፈሪ እንዲሆን ተደርጓል። ሲቸግረው የሚጮኸውን ያህል ሲመቸው ለወገን የሚደርሰው ጥቂቱ ነው። ይህ ሊቀጥል አይገባም!
ቀደም ባለው ጊዜ አንድ ኢትዮጵያዊ ጥቃት ቢደርስበት ባገኘው መሳርያ ዘነጣጥሎም ቢሆን ይገድል ስለነበር ማንም አይደፍረውም ነበር። በዘመነ ኮሎኒያሊዝም ኢትዮጵያውያን በሄዱበት ሁሉ አንገት የማይደፉና ክብራቸውን የማያስነኩ ነበሩ። ዛሬ ጠቁመው የሚያስይዙ፣ ወገናቸውን የሚያሻሽጡና የሚሰልሉት ሁሉ ኢትዮጵያውያን ናቸው። የዚህ ጽሁፍ

ዜጎቹ በአረብ አገር እንደውሻ ሲታደኑ ወያኔ የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ ብሏል ፡፡

ከሳምንት በፊት እዚህ ኖርዌይ አንድ የደቡብ ሱዳን ተወላጅ ነው የሚባል ሰው ፣ የስደተኝነት ጥያቄው አሉታዊ መልስ እንዳሰጠው አውቆ ከከራረመ በኋላ ፣ እንደ ነገ ከመጣበት አግር ወደ እስፔን ሊመለስ በፖሊሶች ዝግጅቱ አልቆ ሳለ መረጃውን ከየት እንዳወቀ ባልታወቀ ምክንያት ፣ ክተጠለለበት ካምፕ ወጥቶ አውቶብስ ይዞ እንደወጣ ፣ ሰይጣን ጆሮው ላይ ምን ሹክ እንዳለው ሳይታወቅ ፣ ከካምፑ ይዞት በወጣው ቢለዋ ፣ አውቶቡሱን አግዶ በአውቶቡስ ውስጥ ያሉትን ሶስት ሰዎች ይገድላል ፡፡

Sunday, November 10, 2013

የኢትዮጵያው ጓንታናሞ ቤይ ‹‹ ማዕከላዊ ››አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሂዩማን ራይትስ ዎች እንዳለፉት አመታት ሁሉ የኢትዮጵያን መንግስት የሚያስቆጣ ባለ 70 ገጽ ሪፖርት ከሁለት ሳምንታት በፊት ይፋ አድርጓል፡፡ የተቋሙን ሪፖርት ከሌላው ጊዜ የተለየ የሚያደርገው በአንድ ርዕሰ ጉዳይ በአንድ ተቋም በማጠንጠኑ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የወንጀል ምርመራ ማዕከሎች መካከል በአዲስ አበባ ዕምብርት በሚገኘው ማዕከላዊ ተጠርጣሪዎች ግርፋት፣ማሰቃየትና ድብደባ እንደሚፈፀምባቸው ሪፖርቱ አትቷል፡፡

አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሂዩማን ራይትስ ዎች እንዳለፉት አመታት ሁሉ የኢትዮጵያን መንግስት የሚያስቆጣ ባለ 70 ገጽ ሪፖርት ከሁለት ሳምንታት በፊት ይፋ አድርጓል፡፡ የተቋሙን ሪፖርት ከሌላው ጊዜ የተለየ የሚያደርገው በአንድ ርዕሰ ጉዳይ በአንድ ተቋም  በማጠንጠኑ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የወንጀል ምርመራ ማዕከሎች መካከል በአዲስ አበባ ዕምብርት በሚገኘው ማዕከላዊ ተጠርጣሪዎች ግርፋት፣ማሰቃየትና ድብደባ እንደሚፈፀምባቸው ሪፖርቱ አትቷል፡፡
 
ዜጋህ እንደ ወንጀለኛ በየመንገዱ እየታፈሰ ሲታሰር፣ ምክንያቱ በግልጽ ባልታወቀ ሁኔታ ደግሞ አንዱ የአገርህ ልጅ በአረብ ፖሊስ ጥይት ተመትቶ ዋዕዩ በሚነድደው አስፓልት ላይ ደሙ ረግቶ ስትመለከት ምን ይሰማኻል? ይህ ሁሉ በሳዑዲ ምድር ላይ በየቀኑ እተፈጸመ መሆኑን ስትረዳ ውስጥህ ምን ይልኻል? ኢትዮጵያዊ ዜግነት ከሌላ ዜግነት በቅጡ አንሶ ይሆን?

ሀገራዊ ውርደት እንዲያበቃ ወያኔን ከሥልጣን ማስወገድ!!!

የወያኔ ገዢ ጉጅሌ በባህርዩ ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት አጋጥሟት የማያውቅ ፍጹም ኢሰብዓዊና ነውረኛ ስብስብ እንደሆነ ለመረዳት ኢትዮጵያዊያንን ለማዋረድ የሚጠቀሟቸውን ተግባራትና ቃላትን ማጤን ይበቃል።

Saudi police in Riyadh clash with migrant workers.BBC

Posted by Amha Alemu  //  Uncategorized  //  No Comments
Foreign workers wait for a taxi as they leave the Manfuhah neighbourhood of Riyadh. 10 Nov 2013Hundreds of foreign workers were leaving the Manfuhah district on SundayTwo people have been killed and scores wounded as Saudi police clashed with protesting foreign workers in a district of the capital, Riyadh.

"ቴዎድሮስ አድሃኖም ህገወጥ ኢትዮጵያውያን እንዲያዙ የተስማማበት ሰነድ አለን"የሳኡዲ ባለስልጣናት


በሪያድ የዛረው ሰልፍ የሚመጣውን አደጋ በመፍራት ተበትኗል::
"ቴዎድሮስ አድሃኖም ህገወጥ ኢትዮጵያውያን እንዲያዙ የተስማማበት ሰነድ አለን"የሳኡዲ ባለስልጣናት


አምስተኛ ቀኑን የያዘው የሳኡዲ ጸረ ኢትዮጵያውያን ዘመቻ እንደቀጠለ ሲሆን ሁኔታዎችን ለመፍታት የተደረጉ ጥረቶች ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግስት እና የቆንስላው ዲፕሎማቶች በሰርኡት ስህተት መስመር ሊይዝ አልፈለገም:: እንደ ሳኡዲ ባለስልጣናት አነጋገው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም ባደረጉት ጉብኝት ሃገራቸው ህገወጥ ኢትዮጵያውያንን እንዲያስወጣ እና በምትኩ 40,000 ህጋዊ ስደተኞችን እንደሚልኩ የፈረሙበትን ማስረጃ ይዘዋል:: በሪያድ መንፉሃ ወደ ሃገራችን ስደዱን በሚል መንፉሃ ባንክ አልራጅህ አካባቢ በርካታ ኢትዮጵያውያን መንግስት የወሰደውን እርምጃ ተቃውመው ሰልፍ መውጣታቸው ተሰማ። እንደ አረብ ኒውስ ዘገባ መሰረት በሰልፈኞች በተወረወሩ ድንጋዮች አንድ የሳውዲ ዜጋ መሞቱንም ዘግቧል።

እነዚሁ በነዋሪዎች ድብደባና በደል የደረሰባቸው ኢትዮጲያውያን ወደ ሪያድ ኢምባሲና ኮሚኒቱ መስሪያ ቤት በእግራቸው ያመሩ ሲሆን መንፉሃ አካባቢ የቀሩት ከፖሊስ ጋር ባደረጉት ግጭት አንድ የፖሊስ መኪና እንደተሰበረ የአይን እማኞች ገልጸውልኛል።

Minilik Salsawi#

በወያኔ የደህንነት መስሪያ ቤት የታቀደው የግንቦት 7 አመራሮች ላይና በሌሎች በኤርትራ በሚገኙት ተቃዋሚዎች ላይ ያልተሳካው የመግደል ሙከራ

  እውነተኛ መረጃዎችን  ለኢትዮጵያኑች በማቅረብ የታወቀው የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያ(ESAT )ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ባስተላለፈው ሰባር ዜና   የግንቦት 7 ንቅናቄ ዋና ጸሐፊ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን  እንዲሁም የግንቦት 7 ሕዝባዊ  ሐይል  ባለ ስልጣናትን ለመግደል በታቀደው የወያኔ ኦ ሚሊኒየም ዘመቻ መክሸፉን ማቅረቡ ይታወሳል ዛሬ ከሞላ ጎደል ጋዜጠኛ ሴሳይ አጌና እና መሳይ መኮንን በእፍታ ዝግጅታቸው ለኛ በሚገባ ሁኔታ አቅርበውታል እንከታተለው።
                                 http://ethsat.com/video/esat-efeta-special-11-november-2013