Wednesday, June 12, 2013

ትንሽማሟሺያ ፤”ከብርሃን ልክፍት”

ትንሽማሟሺያ ፤”ከብርሃን ልክፍት”

268970_538199819551757_896179330_nትንሽማሟሺያ ፤”ከብርሃን ልክፍት”
ድሮ ከቁርስ በፊት የሚበላ ሟሟሽያ የሚባል ምግብ ነበር፡፡ ከዛ ዋናው ቁርስ ከዛ ምሳ ከዛ ደግሞ ከእራት በፊት መክሰስ ከዛ እራት፡፡ እንዲህ ሲኖር ሲኖር ሲኖር ታጋዮቹ መጡ እና የኢትዮጵያ ህዝብ በቀን ሶስቴ እንዲበላ እናደርጋለን አሉ፡፡ እውነትም እቅዱ በጣም ስለተሳካ ማሟሽያም ጠፋች መክሰስም ጠፋች እራትም የት እንደደረሰች እነጃላቷ ቁምሳ እና ምራት ተጀመሩ፡፡ ቁምሳ ቁርስ እና ምሳን በማዳቀል ወደ አምስት ሰዓት አካባቢ የሚበላ ሲሆን ቁምራ ደግሞ ምሳ እና እራትን አዳቅሎ ወደ አስራ አንድ ሰዓት አካባቢ ይበላል፡፡ ከዛ ሰላም አሳድረኝ ብሎ ለጥ ነው፡፡




የምኖርበት “ኮንዶሚኒየም” በሉት ከስር አንድ ናይጄሪያዊ ቤተሰብ ከፊት ለፊቴ ደግሞ ቻይናዊያን ባልና ሚስት ከልጃቸው ጋር ይኖራሉ፡፡ አንዳንድ ምሽቶችን ናይጄሪያዊቷ በጣም ድምጧን ከፍ አድርጋ ስትዘፍን ይሰማኛል፡፡ ትዝፈን በይ ካላት ምን ይደረጋል… ብዬ ጸጥ እላለሁ፡፡ አንዳንዱን ረፋድ ደግሞ ቻይናዊያኑ “ቹን ቻን ቹንግ…” እየተባባሉ ሲጯጯሁ እሰማለሁ፡፡ ደስ እንዳላቸው ይሁኑ በሉ ካላቸው እምቢኝ አይሉት ነገር፡፡ እኔስ ታድያ፤ ዛሬ ማለዳውን የጀመርኩት የዮሃንስ ሞላን ግጥሞች ከጣራ በላይ ጮክ ብዬ በማንበብ ነው፡፡ ጎረቤቶቼ ከሰሙ በል ብሎታል ይበለው እንደሚሉኝ እየገመትኩ ከግጥሞቹ አንዱን እነሆ በረከት፤

ወደ ሌሎች ጨዋታዎች ሳናሳልጥ በፊት እስቲ ወግ ይድረሰን እና ይቺን ማሟሽያ እንቃመሳት!
ግርማ ሞገሳሟ ቴ


“ጠጅም እንዳያምረኝ፤ ድሮ ጠጥቻለሁ፤
ሥጋም እንዳያምረኝ፤ ቋንጣ ሰቅያለሁ፤
ቢሻኝ ከወንድሜ፤ ከአቤቴ እበላለሁ፡፡
አንድ እግር በርበሬ መንቀል አቅቷችሁ፤
አንድዶ፣ ለብልቦ፣ አቃጥሎ ፈጃችሁ፡፡
ሺህ ፈረስከኋላው ሺህ ፈረስ ከፊቱ፣
ሺህ ብረት ከኋላው፣ ሺህ ብረት ከፊቱ፣
ይህን ሳታይ ሞተች ኮሶ ሣጭ እናቱ፡፡
ይህህ ሲሰማ ያጓራል ላመሉ፤
“ማናት” ም ቢላችሁ፤ ምንትዋብ ናት! በሉ፡፡

እያልሽ ስትወርፊው፣ በደጉ ዘመንሽ፣
በየደረሰበት፣ ስትዘልፊው በቃልሽ፤
በደሉን ቢረዳ፤

… አባት ወንድም ነስቶሽ፤ልብሽ እንዳዘነ፣
ካሳ ሰፈረ እንጂ፤ መች ባንቺ ጨከነ?
የታደልሽ እመቤት፣ ግንባርሽ ያማረ፣
ገድ የተቃናልሽ፣ ለቅሶሽ የከበረ፣
ያ ኩሩ መይሳ፣ ላንቺ ተመለሰ፤
ይሰፍርሻል ሲባል፤ እንባሽን አበሰ፡፡
ዛሬ እናን ባየሽን…

እንኳን ስሙን ጠርተን፣ ደርሰን ከሰፈሩ፤
ልኩን አስታጥቀነው፣ ገጥመን ከግንባሩ፣
እንዲሁም እንዲሁ ነን፣ ትርጁማን አናጣ፣
ያልነው ተተርጉሞ፣ ባላልነው ሚቀጣ፡፡  
ብናለቅስ… “አበዱ”፤ ጥለን… ብንሄድ “ፈሩ”  
ብንጠይቅ… “ጠገቡ”፤ ብናውቅ “አሸበሩ”፤
የሚለን ብዙ ነው፣ ሚከሰን ዘርዝሮ፣
እንኳንስ ሊሸኘን፤ ካሳ ድርጎ ሰፍሮ፡፡ 
ዮሀንስ ሆይ ግጥሞችህ ይባረኩ! አንተም ተባረክ!

No comments:

Post a Comment