Wednesday, June 12, 2013

ወያኔ በሁመራ ከአርበኞች ጋር መዋጋቱን አመነ

ወያኔ በሁመራ ከአርበኞች ጋር መዋጋቱን አመነEthiopian People Patriotic Front fighters

June 12, 2013 ECADF – ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር “ነበልባል” በመባል የሚታወቀው ባብዛኛው በወጣቶች የተገነባው ተዋጊ ሀይል በሁመራ አካባቢ 35ኛውን የወያኔ ክፍለጦርና ሚሊሻዎችን ገጥሞ አንጸባራቂ ድል እንደተቀናጀ አስታውቆ ነበር። ዜናውን ለመመልከት እዚህ ይጫኑ።
ቁስለኞቹን እና የተገደሉ ወታደሮቹን ሲያሸሽ የከረመው ወያኔ ከሶስት ሳምንታት በሗላ አርበኞችን ገደልኩ… ብሎ ዜና ሰርቶ ለቋል።
በሁመራ አካባቢ የተደረገውን የአርበኞቹን የውጊያ ውሎ የግንባሩ ሬድዮ በበኩሉ እንደሚከተለው ዘግቦታል፣
“35ኛው የወያኔ ክፍለጦር አባላት አዳዲስ ኦራል መኪና በመንዳትና አዳዲስ ዩኒፎርም በመልበስ አስፈሪ የጦር ሀይል ይመስሉ ነበር… ይሁንና ያን ሁሉ ኩራት እና መመጻደቅ ግንቦት 24 ቀን ነበልባሉ አርበኛ ውሀ ቸልሶበታል.. አዳዲሶቹ ኦራል መኪኖችም የወያኔዎቹን ቁስለኛና ሟች ወታደሮች ሲያጓጉዙ ሰንብተዋል።”
እንደ ሬድዮው ዘገባ የጎንደር ነዋሪዎች በአርበኞቹ የወጊያ ብቃትና ጀግንነት እጅግ ተደንቀዋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ሬድዮ ዘገባን ያዳምጡ።
2. EPPF ሬድዮ (ሰኔ 1 – 2005)
Stopped
Play Pause
Stop
Next»
«Prev
HIDE PLAYLIST

No comments:

Post a Comment