Friday, June 28, 2013

ከዳር ቆሞ ለዉጥን መጠበቅ የህልም እንጀራ (ዶ/ር ፍስሀ እሸቱ)

ከዳር ቆሞ ለዉጥን መጠበቅ የህልም እንጀራ (ዶ/ር ፍስሀ እሸቱ)

ከዳር ቆሞ ለዉጥን መጠበቅ የህልም እንጀራ

dr feseha eshetu

ፍስሀ እሸቱ (ዶ/ር)

በሀገራችን ያለዉን ሁኔታ ስንመለከተዉ በጥቂት ቃላት ማጠቃለል የቻላል። ይህም ከድጡ ወደ ማጡ የሚለዉ በጥሩ ሁኔታ የሚገልጸዉ ይመስለኛል። አበዉ ጉልቻ ቢለዋወጥ እንደሚሉ አፈናዉ፤ ስለላዉ፤ እስሩ፤ ግድያዉ፤ ስደቱ፤ ዘረፋዉና፤ ማናለብኝነቱ ሳይቋረጥ ቀጥሏል። አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትርና አጋሮቻቸዉም ደግመዉ ደጋግመዉ አስረግጠዉ እንደተናገሩት ለዉጥ የሚባል ነገር እንደማይታሰብና የነበረዉ ሁኔታ ባለበት እንደሚቀጥል ነዉ። ከዚህ አንጻር የለዉጥ የተስፋ ጭላንጭል እንደሌለ በወሬ ብቻ ሳይሆን በተግባራቸዉም አሳይተዉናል። ምንም መራር ቢሆንም እዉነታዉ ግን ስርአቱ መሪዉን ቢያጣ እንኳን፤ በአላማ፤ በአቅም፤ በድርጅትና፤ በስነልቦና፤ ፍጹም የበላይነቱን

ሕገ መንግስቱና ምርጫ ቦርድ እያነቡ እስክስታ (ተቃዋሚ ፓርቲዎች)

ሕገ መንግስቱና ምርጫ ቦርድ እያነቡ እስክስታ (ተቃዋሚ ፓርቲዎች)

Ethiopian_Election_Board

በዚህ ዓመት ሊከናወን በእቅድ የተያዘው የአካባቢና የአዲስ አበባ ምርጫ በሚያዚያ ወር 2005 ዓ.ም እንደሚካሄድ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ አውጥቷል፡፡ ምርጫ ቦርድ እንደተለመደው ነጻ፣ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና ተአማኝነት ያለው ምርጫ እንዲሚካሄድ አረጋግጧል፡፡ ምርጫ ቦርድ ነጻ፣ ግልጽና ተአማኒነት ያለው ሲል ከየትኛው የምርጫ መመዘኛና መስፈርት ተነስቶ እንደሆነ ለመገመት አያዳግትም፡፡ ያው እንደተለመደው በውዝግብ ተጀምሮ በውዝግብ የሚጠናቀቀውን ዓይነቱን ምርጫ መሆኑ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም እንደታየው ሚዛናዊ የሆነ ውድድር ማድረግ ባለመቻሉ ምክንያት ውጥረት ውስጥ የወደቀው የመድብለ ፓርቲ ምርጫ ስርዓታችን በመቀጠል ፍጹም እንዳይዳፈንና በአንጻራዊነትም ቢሆን ሚዛናዊነቱን ሳይስት ከቅርጫ ወደ ምርጫነት እንዲሸጋገር በማሰብ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ባደረግነው ድርድር መሰረት በ2001 በተረቀቀውና በጸደቀው የተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ደንብ አንቀጽ 47 ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የገንዘብም ሆነ የቁሳቁስ ድጋፍ እንደሚያገኙ ቢደነገግም፣ በአሁኑ ምርጫ ይህ ሕጋዊ መሰረት ያለው ድጋፍ እንደማይኖር ምርጫ ቦርድ ገልጿል፡፡ ምርጫ ሰላማዊ ነጻና ገለልተኛ፣ በሁሉም አካለት ዘንድ የታመነና ተቀባይነት ያለው እንዲሆን ከተፈለገ አንዱና ወሳኙ ነጥብ የውድድር ሜዳውን ጨምሮ የቁሳቁስና የገንዘብ አቅርቦቱ ያለአድልዎ ለሁሉም በእኩልና በሚዛናዊነት መኖሩ ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡ ይህ ሚዛናዊ ስሌት ተጠብቆ ተግባር ላይ መዋሉን የማረጋገጥ ኃላፊነት የተጣለው ደግሞ በምርጫ ቦርድና በሌሌች መሰል የዴሞክራሲ ተቋማት ላይ ነው፡፡

 

የሚያስቅና የሚያሳቅቅ የፍርድ ቤት ውሎ

የሚያስቅና የሚያሳቅቅ የፍርድ ቤት ውሎ


Herut-Kefele going to court

አቤ ቶኪቻው

ዕለቱ “በእነ ኤልያስ ክፍሌ የፍርድ መዝገብ” ምስክርነት ይሰጣል የተባለበት ዕለት ነበር። በዚህ መዝገብ ውብሸት ታዬ፣ አቶ ዘሪሁን ገብረ እግዚአብሄር፣ ሂሩት ክፍሌ እና ርዮት አለሙ ክስ ተመስርቶባቸዋል።

እነ ውብሸት ታዬ መጀመሪያ ሲታሰሩ በቴሌቪዥን የሰማነው “የቴሌ እና የመብራት ሃይል ተቋማትን ማፈራረስ እና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ለመናድ መሞከር” የሚል ነበር። ከዛ እያደር እያደር አቃቤ ህግ በምን እንደከሰሳቸው ረሳው መሰለኝ፤ ለምስክርነት በሄድንበት ጊዜ የሰማነው አንድም ከመብራት ሃይልና ቴሌኮሚዩኒኬሽን ጋር የሚያያዝ ነገር አልነበረውም። አረ ልብ ብለን ካየነውማ ከህገ መንግስቱም ጋር የሚጋጭ ነገር አላየንበትም።

 

ሰብአዊ መብትና: መንግሥታዊ ግፊት በኢትዮጵያ (2012)

ሰብአዊ መብትና: መንግሥታዊ ግፊት በኢትዮጵያ (2012)

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

በዲሴምበር 2008 ላይ በኢትዮጵያ የ‹‹ለውጥ የሌሽ ዓመት›› በማለት እንጉርጉሮ መሰል መልእክት ጽፌ ነበር፡፡

2008 የ2007፤2006፤2005፤2004 ቅጂ ነበር… በየቀኑ ኢትዮጵያዊያን ሲነቁ ልክ እንደተሰበረ የሙዚቃ ሸክላ ባለፈው የሕይወት ስቃያቸው ድግግሞሽ መከራ ውስጥ በመዳከር ነበር የሚገኙት፡፡ እያንዳንዱ አዲስ ቀን ካለፈው የወረሰውን ይዞ ነበር የሚመጣው፡፡ ጫና፤ ማስፈራራት፤ ንቅዘት፤እስራት፤ ማጭበርበር… ጭካኔና የሰብአዊ መብት ገፈፋ… ከዚህ ክፉ ከሆነው የስቃይ፤ የጣረሞት ግርዶሽ፤ አዙሪት፤ የተስፋ እጦት፤ ውጣ ውረድ መከራ እንዴት እንደሚገላገሉ መንገዱን አያውቁትም፡፡ ስለዚህም ከዚህ መዓት ለመገላገል ያላቸው አንድ ተስፋ መጸለይ፤ መጸለይ፤ ደሞ መጸለይ ብቻ ነበር::

መንግስት የለም ወይ? መንግስት የለም ወይ? (ህዝብ)

መንግስት የለም ወይ? መንግስት የለም ወይ?  (ህዝብ)

ዘረኛው ህወሃት የኢትዮጵያ መንግስት እኔ  ነኝ ይላል። ህዝቡ ግን መንግስት የለም ወይ እያለ መጠየቁን አላቆመም። ህወሃት የመንግስት ቅርፅና መልክ የሌለው ቡድን ስለሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ መንግስት አለ ለማለት አይቻልም። ህወሃት መንግስት መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለማወቅ ብርቱ የሆነ የአቅም ችግር አለበት። ይሄን ደካማነቱን የተመለከተ ህዝብ ነው ድምጹን ከፍ አድርጎ መንግስት የለም ወይ ? መንግስት የለም ወይ? ብሎ የጠየቀው።ህወሃት የመንግስትነት ባህሪይ ቢኖረው ኑሮ ይሄን ድምጽ ማድመጥ በቻለ ነበር። እንዲህ ያለውን ድምጽ አሁን በዚህ ዘመን ያለ ይቅርና በዚያ በጨለማ ዘመን እግዚአብሄር ሾመን የሚሉ ነገስታት እንኳ ቢሆኑ ያደምጡት ነበር።ህወሃት ከጨለማው ዘመን ነግስታት እንኳ የማይሻል እጅግ ኋላ ቀር መሆኑን ከሚያሳዩን ድርጊቶቹ መካከል አንዱ ይሄው የህዝቡን ድምጽ መስማት አለመቻሉ ነው።

አዲሱ መጅሊስ ሲጋለጥ ያንብቡት!!!

አዲሱ መጅሊስ ሲጋለጥ ያንብቡት!!!

ethiopian muslim new mejliss

በአንድ የግል ጋዜጣ የዘንድውን አወዛጋቢ የመጅሊስ ምርጫ አስመልክቶ የተመረጡትን ሰዎች ፕሮፋይል እየተመለከትኩ ነበር፡፡ ከጎኔ የነበረ ሰው የሙስሊም ኮፍያዬን ቀና ብሎ ተመልክቶ ከበፊቱ መጅሊስ የተሻለ ዓለማዊም ሆነ ሃይማኖታዊ ዕውቀት እንዳላቸው ነገረኝ፡፡ በጋዜጣ መሸጫ ዙሪያ “ሲቪሎች” ስለሚበዙ እሱም መረጃ እየሰራ ይሆናል በሚል ግምት በአጭሩ ያለውን መስማማቴን በንቅናቄ ገልጬ ገጹን በመገልበጥ አባረርኩት (አባረረኝ)- ብቻ ያው ነው፡፡ ከዚህ ሰውዬ አስተያየት ጀምሮ እስከ ዛሬ ያማጥኩትን ለአንባቢያን ላበቃ ዘንድ እነሆ ብእሬን አነሳሁ፡ እኔ መሐመድ ካሊድ አዲሱ መጅሊስ  ባለስልጣናት /ፎቶ ምንሊክ ሳልሳዊ / ስለ ሰላማዊ ትግል በሚወራበትና ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ለ 1 ዓመት ሙሉ ሕገ ወጡ መጅሊስ ይወገድ ከማለት ጀምሮ እስከ መሪዎቼ ይፈቱ ከዚያም ምርጫው ውድቅ ይደረግ ጥያቄ በአወሊያ ተጀምሮ እስከ ታላቁ አንዋር መስጂድ በዘለቀው የሰላማዊ ተቃውሞ የአንድ ዓመት ክብረ በዓል እየተከበረ ባለበት ወርሐ ታኅሳስ የመጨረሻ ሳምንት ስለ በግዱ መጅሊስ ማውራት ባይመስጥም ቢያንስ ውስጣዊ አሰራሩን ታነቡት ዘንድ ከትቤዋለሁ፡፡



እንደ መከላከያ ሁሉ ኢትዮ ቴሌኮምም

እንደ መከላከያ ሁሉ ኢትዮ ቴሌኮምም

እንደ መከላከያ ሁሉ ኢትዮ ቴሌኮምም

Ethiopia telecomunication

ግንቦት 7 ርዕስ አንቀጽ


ለተከታታይ አስር ቀናት የሕሊና እስረኞች ላይ ምስክር መደመጥ ይጀምራል።

ለተከታታይ አስር ቀናት የሕሊና እስረኞች ላይ ምስክር መደመጥ ይጀምራል።

ለተከታታይ አስር ቀናት የሕሊና እስረኞች ላይ ምስክር መደመጥ ይጀምራል።

Ethiopian muslim Prisoners

በመሪዎቻችንና በሌሎችም የሕሊና እስረኞች ላይ ነገ ምስክር መደመጥ ይጀምራል
ምስክሮች ዛሬ የማጠቃለያ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል፤
ከነገ ጀምሮ ምስክሮቹ ለሚደመጡባቸው አስር ቀናት አገር አቀፍ ዱአ እንዲደረግ ታዟል፤
አላህ በመስካሪዎቹ ላይ ተአምሩን እንዲያሳየን ሁሉም በዱአ እንዲበረታ ታዟል፤

የወያኔን ሰላዮችን ከውጭ አለም ማጽዳት የወያኔን ሰላዮችን ከውጭ አለም ማጽዳት

የወያኔን ሰላዮችን ከውጭ አለም ማጽዳት

የወያኔን ሰላዮችን ከውጭ አለም ማጽዳት

ከእስከ ነጻነት

ኢትዮጵያ የነጻነት ቀንዲል ነች፡እንደ ስበሃት ነጋ ላሉ ባንዳ ወያኔዎች ግን ጣሊያንን አሸንፈን ለመላው የጥቁር ህዝብ የነጻነት ጎህ ቀዳጅ መሆናችን ኩራት ሳይሆን እፍረት ስለሚመስላቸው አገሪቷ ከነሰንደቅ አላማዋ ጥፍታ ማየት የዘወትር ጥረታቸው ነው፡ ሌት ተቅን የሚተጉትም ለዚህ ስለሆነ የኢትዮጵያዊነት ሰሜት ያላቸውን ሁሉ ማሰር፤ መግደል፤ ማጥፋት ዋና ትግባራቸው ነው፡ ይህም ተግባራቸው ከበረሃ እስከ አዲስ አበባ ከዛም ጎረቢት አገሮች ድረስ ዘልቆ አሁን ደግሞ ወደ ምእራብ ሐገራትም መጣሁ እያለ ነው።

 

Obama is Coming! Obama is Coming to Africa!!

Obama is Coming! Obama is Coming to Africa!!
By Alemayehu G Mariam
June 24, 2013



President Obama
(This week my regular Monday commentary is presented in the form of a “flash drama” on Obama (a sub-genre of theatrical play sometimes described as a “ten minute one-act play”).  

ፕሬዝዳንቱ በከባድ የማታለል ወንጀል በቁጥጥር ስር ዋሉ

ፕሬዝዳንቱ በከባድ የማታለል ወንጀል በቁጥጥር ስር ዋሉ

-የፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጎርጊስ ደብዳቤ ተቀባይነት አጥቷልdownload (1)
የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ሊቀትጉሀን አስታጥቄ አባተ ትላንት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታወቀ፡፡ ፕሬዝዳንቱ ዛሬ ከቀኑ8፡00ልደታ የሚገኘው ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 5ኛ የወንጀል ችሎት ይቀርባሉ፡፡


ፕሬዝዳንት ሊቀትጉሀን አስታጥቄ አባተ ሶስት የወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን ከክሱ ይዘት መካከል ቤት ለሌላቸው አርበኞች ከተሰጠው የኮንደሚኒየም ቤተች ውስጥ ቤት እያላቸው እንሌላቸው አድርገው በመውሰዳቸው 2ኛ እህታቸውን ጨምሮ አርበኛ ላልሆኑና ለማይመለከታቸው ግለሰቦች “አርበኛ ናቸው” ብለው በመስጠታቸው እንዲሁም ከማህበሩ ከፍተኛ መጠን ያለው የብር ጉድለት መታየቱ ይጠቀሳል፡፡

ፕሬዝዳንት ሊቀትጉሀን አስታጥቄ አባተ ላይ የተመሰረተው ክስ እንዲቋረጥ ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጎርጊስ ለፍትህ ሚኒስቴር የጻፉት ደብዳቤ ተቀባይነት አጥቷል፡፡

ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ በተለያየ ጊዜ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት በሆኑት በሊቀትጉሀን አስታጥቄ አባተ ተፈፅመዋል ስለተባሉ የተለያዩ የአስተዳደር በደልና የሙስና አቤቱታዎች መዘገቧ አይዘነጋም፡፡
finote netsanet

አሜሪካ ውስጥ ያለ ሕጋዊ ፍቃድና ሰነዶች የሚኖሩ ከአሥራ አንድ ሚሊየን በላይ ሰዎችን ወደ ዜግነት ሊወስድ እንደሚችል የታመነበት የኢሚግሬሽን ማሻሻያ ሕግ በሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ በከፍተኛ ድምፅ አለፈ፡፡

አሜሪካ ውስጥ ያለ ሕጋዊ ፍቃድና ሰነዶች የሚኖሩ ከአሥራ አንድ ሚሊየን በላይ ሰዎችን ወደ ዜግነት ሊወስድ እንደሚችል የታመነበት የኢሚግሬሽን ማሻሻያ ሕግ በሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ በከፍተኛ ድምፅ አለፈ፡፡

C76B7AE3-8C3B-441E-A763-5A2C1034660C_w640_s
ዓርብ, ጁን 28, 2013
አሜሪካ ውስጥ ያለ ሕጋዊ ፍቃድና ሰነዶች የሚኖሩ ከአሥራ አንድ ሚሊየን በላይ ሰዎችን ወደ ዜግነት ሊወስድ እንደሚችል የታመነበት የኢሚግሬሽን ማሻሻያ ሕግ በሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ በከፍተኛ ድምፅ አለፈ፡፡ አሜሪካ ውስጥ ያለ ሕጋዊ ፍቃድና ሰነዶች የሚኖሩ ከአሥራ አንድ ሚሊየን በላይ ሰዎችን ወደ ዜግነት ሊወስድ እንደሚችል የታመነበት የኢሚግሬሽን ማሻሻያ ሕግ በሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ በከፍተኛ ድምፅ አለፈ፡፡

በካይሮ የኢትዩጲያ ስደተኞች ማህበር የአደጋ ጊዜ መከላከያ ግብረ ሃይል የወጣ መግለጫና ማስጠንቀቅያ

በካይሮ የኢትዩጲያ ስደተኞች ማህበር የአደጋ ጊዜ መከላከያ ግብረ ሃይል የወጣ መግለጫና ማስጠንቀቅያ

በ 30-6-2013 በሀገሪቱ ላይ በሚደረገው ሰለፍ ተነሳ ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ ወጥተው በስደተኛው ላጭ ወጥተው በስደተኛው ላይ አደጋ ሊፈጥር እንደሚችል በቀጥታ የስደተኛው ጉዳይ የሚመለከተው የ UNHCR የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ ያወጣውን መግለጫ ማስነበባችን ይታወሳል። ይህ ባኢነዲህ እንዳለ ሌላኛው ከስደተኛው ጋር ግንኙነት ያለው የካሪታስ ቢሮ የችግሩን አደገኛነትና አሳሳቢነት በማመን የራሱነ መግለጫ ከማውጣቱም በላይ ቅድመሁኔታዎችን አስቀምጡአል በዚህም የተነሳ ማህበሩ ከስራ አስፈጳሚው ከሪጂናልና ከህብረተሰቡ ውሰጥ ተመረጡ አባላትን በማደራጀት ስደተኛውን ለመታደግ በዘመቻ መለክ የስራ እንቅስቃሴ ጀምርዋል።


ይድረስ ለኢትዮጵያው ሥውር መንግሥት

ይድረስ ለኢትዮጵያው ሥውር መንግሥት

June 28, 2013 ይነጋል በላቸው
ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ ኢትዮጵያን ማን እየገዛ እንደሆነ ከግምት ያለፈ ዕውቀት የለኝም፡፡ በመለስ ጊዜም ቢሆን ሀገሪቱ በዕውር ድንብርና በነሲብ ነበር የ…

የሚገርም አጋጣሚ ነው፡፡ በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንና በዚያ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያናችን ኃላፊዎች ጸሎት በቶሎ እንዲድኑ ሲጸልዩላቸው የሀገሪቱ የሃይማኖት ታዋቂ አባትና ተከታይ ምዕመኖቻቸው ግን በሰላም እንዲያርፉ ነው ጸሎት እየተደረገ ያለው – ለኔልሰን ማንዴላ፡፡ ይህ ነገር የሥልጣኔ ልዩነት ይሁን የባህል አልገባኝም፡፡ ይህን የዜና ሽፋን ከውጪ ወደ ሀገር ውስጥ በሚሰራጭ አንድ የተቃውሞው ጎራ ቴሌቪዥን አማካይነት እየተከታተልኩ ነኝ – ልክ አሁን፡፡ በመሠረቱ ከ94 ዓመታት ምድራዊ የሥጋ ለባሽ ሕይወት በኋላ አንድ ብዙ የሕይወት ውጣ ውረድ ያሳለፈና በእሥርም ብዙ የተሰቃዬ ሰው ዕድሜ እንዲረዝም መመኘት ከፍቅር ብዛት የሚመነጭ የዋህነት ይመስለኛል፡፡ በጀመርኩት ሃሳብ ትንሽ ልቆይና ወረድ ብዬ በዚህ ላይ እንደመጠቅለያነት እመለስበታለሁ፡፡


…በመለስ ጊዜም ቢሆን ሀገሪቱ በዕውር ድንበርና በነሲብ ነበር እስትንፋሷ ውሎ እሚያድረው፡፡ ሰውዬው የሚፈልገው ሁሉ እዛው ባለበት እየቀረበለትና እንደአንበሣ በብረት አጥር ውስጥ እየኖረ በስልክና በደብዳቤ ሲገዛንና ሲሸጠን ኖረ፤ ፈጣሪ በወደደው ሰዓት ያን የእፉኝት ልጅ ወሰደ፡፡ ጦስ ጥንቡሱ ግን አሁንም እንደገነነ አለ፤ መቃብር ውስጥ ሆኖ በመግዛት መለስ አንደኛ ሣይሆን አይቀርም፡፡ ይቺ ራዕይ የሚሏት ሀገርን የማጥፋት ተልእኮ በየወያኔው ጭንቅላት ውስጥ ሠርፃ ገብታ እነሱንም እኛንም ዕረፍት ነስታለች፡፡ አዳሜ እየተነሣ “ከመለስ ራዕይ ጋር ወደፊት!” ይላል፡፡ “ራዕያቸው ምን ነበር?”ተብሎ ሲጠየቅ በቅጡ የሚመልስ የለም፡፡ የፈረደበት የአባይ የሚሌኒየም ይሁን የሕዳሴ ግድብ አለ፡፡ እሱው መሰለኝ ትልቁ ራዕይ፡፡ በሌሎች ሀገሮች እዚህና እዚያ የተትረፈረፈ የወንዝና የኩሬ ግድብ እኛ ሀገር ሲደርስ ብርቅ ሆኖ ሰውን በመዋጮና በተስፋ ቁንጣን እየገደለ ነው፡፡ ራዕዩ ይሄው ነው፡፡ በተረፈ በሚሊዮኖች ላብና ደም ጥቂት ቅንጡ ሀብታሞችን የመፍጠር ራዕይ ካልሆነ በስተቀር፣ ለብዙ አሠርት ዓመታት ተከፍሎ በማያልቅ ብድር መንገድና ሕንጻ መሥራት ራዕይ ካልሆነ በስተቀር፣ ይበልጡን ለፖለቲካ ፍጆታ በሚመስል መልኩ የሀገርን ሀብት ለተወሰኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች በማዋል በአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞችና በኮብል ስቶን ሥራ አደራጅቶ ዜጎችን በጥቅም መከፋፈል ራዕይ ካልሆነ በስተቀር፣ ለዕይታ ሳይቀር የሚዘገንን የኔቢጤ (ለማኝ)፣ ወፈፌና ሰካራም፣ ብስጩና ግልፍተኛ፣ በረንዳ አዳሪና የዐዋቂና ሕጻናት ሴተኛ አዳሪዎችን በየዋና ዋና ከተሞች በብዛትና በስፋት ማምረት በልዩ ራዕይነት ካልተመዘገበ በስተቀር የመለስ ራዕይ ብሎ ነገር የሚጨበጥ ነገር አላየሁም – በዋና ራዕይነት እንዲመዘገብለት ከተፈለገ ዋናው የመለስ ራዕይ የተከፋፈለችና የደከመች፣ ለኤርትራ በምንም መንገድ የማታሰጋ ጥንጥዬ ኢትዮጵያን በሂደት መፍጠር ነው – ይሄ የሚታየው ብልጭልጭ ነገርና የዕድገት እመርታ የሚመስል የፎቅና የአስፋልት ወይም ሌላ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ሁሉ መለስ

ሳይወድ በግዱ በሥሩ ባሉ ጥቂት ሀገር ወዳድ ወያኔዎች አማካይነት የተከሠተ – ‹ከሬዲቱ› ለርሱ ብቻ የሚሄድ ሳይሆን ለማለት ነው- በመለስ የጥፋት ራዕይና በአፈጻጸሙ መካከል እንደሳይድ ኢፌክ ሊቆጠር የሚችል አጋጣሚ ነው፡፡ ምን ማለቴ ነው – መለስ ኢትዮጵያን በማጥፋት ሂደት ተጠምዶ ሳለ ያን ሂደት ተዓማኒነት እንዲኖረው ለማድረግ ኢትዮጵያዊ መስሎ መታየት ወይም ማታለል ስላለበት ለዚያም ሲባል አንዳንድ የሚታዩና የሚጨበጡ ነገሮችን ማድረግ ስለነበረበት በኢትዮጵያዊ ስብዕና ዓለም አቀፍ አመኔታን ለማግኘት ሲል ባልጠበቀው ሁኔታ ከእጁ ሾልከው ክፉ ገጽታውን በጥሩ ቅባት ያዋዙለት አጋጣሚዎች ነበሩ ወይም ናቸው(ለዚህም ይመስላል ብዙ ኢትዮጵያውያን በዚህ ሰው ‹ምትሃት› ተወናብደው የወያኔን ትክክለኛ ተፈጥሮ እንዳያውቁ የተደረገውና ዐይናቸው በወያኔ ጥፋት ላይ እንዳያማትር እንዲያውም በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጪም የርሱ ነገረ ፈጅ እስከመሆን እንዲደርሱ የተሞከረውና አሁን አሁን ደግሞ እየቆጫቸው መምጣቱን እየተገነዘብን ያለነው…) ፡- በሕክምና አነጋገር ለጉበት የወሰድከው መድሓኒት ኩላሊትህን ሊጎዳ ይችላል – ኔጌቲቭ ሳይድ ኢፌክት፡፡ ለራስ ምታት የወሰድከው መድሓኒት ከጨጓራ ህመምህ ሊፈውስህ ይችላል – ፖዚቲቭ ሳይድኢፌክት፡፡ የመለስም የአባይ ግድብና ሌላው ግርግር ሁሉ ከዚህ መሠረታዊ እውነት ያለፈ አይደለም፡፡ እውነተኛ የሕዝብ ፍቅርና የሀገር መውደድ ስሜት ቢኖረው ኖሮ… ታውቁት የለ – ምን ወደዚያ ውስጥ ከተተኝ … ፡፡ ይቅርታ – በዋናው የሃሳብ መስመሬ ላይ እንደአረብ ጣቢያ ጣልቃ እየገባ ኳርት የሚለዋውጥብኝና እንድዘባርቅ የሚያደርገኝ ዘርፈ ብዙው የሀገራችን ችግር በመሆኑ ታገሱኝ፡፡


ኢትዮጵያን በአሁኑ ወቅት እያስተዳደረ ያለው ማን ነው? የት ተቀምጦ? በስምና በአካል ይታወቃል ወይ? ብለን እንጠይቅ፡፡
እኔ በ


ግል እንደምታዘበው ኢትዮጵያን በአሁኑ ወቅት እያስተዳደራት የሚገኘው ሰው አይመስለኝም፤ መንፈስ ነው፡፡ ይህ መንፈስ ግማሹ ቅዱስ ነው፤ ግማሹ ደግሞ እርኩስ ነው – አሁንም በኔ ዕይታ፤ ዕይታየ ትክክል ነው ትክክል አይደለም የኔ ጉዳይና የናንተ የኅሊና ፍርድ ነው፡፡


ቅዱስ ያልኩት በተከመሩብን ሁለንተናዊ የፖለቲካና ማኅረሰብአዊ ችግሮች የተነሣ እርስ በርስ ተበላልተን እንዳናልቅ እየረዳን ያለ አንዳች ኃይል መኖሩን ከመገመት ባለፈ ስለማምን ነው፡፡ ይህ ኃይል ባይኖር ኖሮ በሀገሪቱ እንደሚታየው ጭቆናና የኑሮ ውድነት አንድም ሰው በአንጻራዊ ሰላም ከቤት ወጥቶ ወደቤት በሰላም ባልገባ ነበር – እውነቴን ነው የምለው ይህን ዓይነት ደግ መንፈስ ባይጠብቀን ኖሮ ተበላልተን ለማለቅ የሚፈጅብን ጊዜ ሰዓታትን ብቻ በወሰደ ነበር(ሦርያንና ሊቢያን… ያዬ ይፍረድ – ሊያውም ከኛ በእጅጉ ያነሰ ጭቆናና እንግልት ደርሶባቸው!) ፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠረው በረንዳ አዳሪ፣ ሥራ አጥና ቤት አልባውም በ”ሰላም” ካደረበት ከየቱቦውና ከየላስቲክ ቤቱ ወጥቶ በቀጣዩ ቀን በየአደባባዩ ባላየነው ነበር፡፡ ካለአንዳች አለሁህ ባይ የመንግሥት መዋቅር በራሱ ኃይልና እንዲሁ በኪነ ጥበቡ ርሀብና ችግሩን ችሎ የሚኖር ሕዝብ ማየት የሚገርምም የሚሰቀጥጥም በድንቃ ድንቅ መዝገብ ሊመዘገብ የሚገባውም የሚሌኒየሙ ተዓምር ነው፡፡ አንድም ሥራና አንድም ደመወዝ የሌለው በሚሊየን የሚገመት ዜጋ ቀኑን

አለበቂ ምክንያት እዚህና እዚያ ሲንከራተትና ሲንገላወድ ውሎ አሁንም ልድገመውና በየሥርቻውና በየሥርጓጉጡ በ”ሰላም” አድሮ የቀጣይዋን ዕለት ጀምበር ለማየት እባቡር መንገዱ ላይ ተሰጥቶ መታየቱ የትንግርትን እንጂ የመንግሥትን ኅልውና አያመላክትም፡፡ በዚህ ምክንያት የሀገራችንን በትረ ሥልጣን ከያዙ ሥውር ኃይሎች ውስጥ የተወሰነውን ‹የፓርላማ ወንበር› የተቆናጠጠው አንዳች የተቀደሰ ነገር መሆን አለበት ብዬ አምለሁ፡፡ እንዲያ ባይሆንማ ማን እየተዘባነነ ማንስ በችግር አለንጋ እየተገረፈ በርሀብና በጥም እየተሰቃዬ ይኖር ነበር? ሀሰት ነው?


በሌላ በኩል የሚታየውን መቋጫ የሌለው የግፍ አገዛዝና የዘረኝነት ቱማታ ስንቃኝ ከነዚህም ጋር የሚቆራኘውን አጠቃላይ የድቀት ሕይወት ስንታዘብ በተለይ በፖለቲካውና በሃይማኖቱ አመራር ረገድ የእርኩሱ መንፈስ ምን ያህል የበረታ እንደሆነ መረዳት አይቸግርም፡፡ ስለዚያም ምክንያት ይመስለኛል ይህ በመለስ የሙት መንፈስ የሚነዳ የአጋንንት መንጋ አንዳች ሥፍራ ተደብቆ ደህና ሰው ወደ አመራር ዝር እንዳይል እነአዜብንና በረከትን እየተመሰለ በላያችን ላይ የሚያንዣብብብን፡፡ እንደሚወራው አዜብ ወደ አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ምክትል ሆና አይደለም ጽዳትና ዘበኛም ሆና ብትመጣ እንኳን ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስቡት፡፡ በሌላ ቦታ እያለች የማዘጋጃ ቤት ሹሞችን በስልክ እያስፈራራችና በአካል እያስጠራች ስንትና ስንት ግፍና በደል መፈጸሟ እየታወቀ አንድያውን በዚያ ቢሮ ስትገኝማ ከተማዋን ብቻ ሣይሆን እኛን ነዋሪዎቹን በጅምላና በችርቻሮ ባወጣንበት ዋጋ ቸብችባ በጥቂት ወራት ውስጥ ትጨርሰናለች፡፡ አዜብ – ዮዲት ጉዲት – እንኳንስ ማዘጋጃ ቤት ገብታ በሩቅ እያለችም – ለብልግናየ ይቅርታና – ለውሽማዋም ይሁን ለምትፈልገው ማንኛውም ሰው ቦታ ለማሰጠት፣ መብራት ለማሰጠት፣ የንግድ ፈቃድ ለማሰጠት፣


እንዳስፈላጊነቱ ተመላሽ ሊደረግ ወይ ላይደረግ የሚችል) የባንክ ብድር ለማሰጠት፣ በመንግሥት ወጪ ረጃጅም የስልክና የውኃ መስመር ለማዘርጋት፣ የፈለገችውን ለማሾም ወይም ለማሻር፣ ንጹሕን ሰው ካለበደልና ጥፋቱ ዘብጥያ ለማስወረድ፣ በጥፋቱ የታሠረን በቅጽበታዊ ጣልቃ ገብነት ለማስለቀቅ፣ የዜጎችን ሀብትና ንብረት በሕግ ሽፋን ለማዘረፍና ለራሷ ካምፓኒዎች ወይም ለመሰላት ለማሰጠት፣ በነባርና አዳዲስ የአክሲዮን ካምፓኒዎች ራሷን በአባልነትና በቦርድ ሰብሳቢነት ለማስገባት፣ ወዘተ. ታደርገው የነበረውና አሁንም ከማድረግ የማትመለሰው አቅል ያጣ ሩጫ በሕዝብ ዘንድ የታወቀ ነው፡፡ ሴትዮዋ ለገንዘብና ለእንትን ሲሏት ገደል


እንደምትገባ የሚያውቋት ይመሰክራሉ – አጉል ተፈጥሮ፤ ከምን ዓይነት ሥጋና ደም ተፈጥራ ይሆን ወገኖቼ? በዚህ ዓይነቱ ለከት የሌለው የገንዘብና የሀብት ፍቅሯ ነው እንግዲህ ሰውዬውን ቤተ መንግሥት ውስጥ እንደውሻ አሥራ በርሱ ስምና በርሷ ድፍረት ባጠራቀመችው ንዋይ ከዓለም መሪዎች መለስን በሀብት የሚበልጠው እንዳይገኝ ከፍተኛ ጥረት ላይ የነበረችው – በየባንኩ ብዙ ገንዘብ ታቁር የነበረችው፣ በየዓለም ማዕዘናት ብዙ ቤቶችንና የንግድ ተቋማትን ትመሠርት የነበረችው፣ በፍቅረ ንዋይ መታወሯ እንዳንዳች እያደረጋት እንዲያ ዐይን ባወጣ መንገድ ትዝብት ላይ ወድቃ የነበረችው፡፡ ይህች በገንዘብና በእንትን ፍቅር ያበደች

የድብቁ ቢግ ብራዘር ተወዳዳሪ ሴት አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ብትገባ ምን ተዓምር ልትሠራ እንደምትችል ገምቱ – የምን መገመት ነው – ፍንትው ብሎ እየታዬ! የስንቱን ቤት እንደምታፈናቅልና ባወጣ እንደምትሸጥ፣ ስንቱን የኪስ ቦታ እንደምትቸበችብ፣ እንደ አንደኛው ባሏ ‹የዐይናችሁ ቀለም አስጠላኝ› እያለች ስንቱን ምሥኪን ሰው ከሥራና ከደመወዝ እንደምታግድ፣ እንደምታሳስርና ደብዛ እንደምታስጠፋ፣ ስንትና ስንት የሀገር ማፈሪያ ወንጀልና የቁጭ በሉ አሣፋሪ ድርጊቶችን እንደምትሠራ፣ ስንቱን ኮበሌ ካልተኛኸኝ እያለች ከትዳሩና ከጤናማ ኑሮው እንደምታፈናቅል (“አሮጊት ለምኔ! ገንዘብና ሥልጣን ባፍንጫየ ይውጣ!” ብሎ አሻፈረኝ የሚልን መቀመቅ እንደምታወርድ)፣ … በበኩሌ ቁልጭ ብሎ ይታየኛል – እባካችሁን ‹ህልም እልም› ብለን ሁላችን እናማትብበት፡፡ አዜብ ብሎ ከንቲባ? ወያኔ ይህን ካደረገ በርግጥም ራሱን ለማጥፋት ከምንጊዜውም በላይ ቁርጠኛ አቋም ላይ ደርሷል ማለት ነው፡፡ ይህችን የአጋንንት ውላጅ የባንዳ ልጅ ማሳረፍ ይገባል – በሰላም፡፡ በቃ – በመለስ ቀብር እንዳለችው ልጆቿን በማሳደግ ፈተና ላይ ብቻ ታተኩርና በዚያው ትታይ፡፡


አዜብ በሌብነቷ አይደለም ሹም አትሁን እያልኩ የምከራከረው፤ በሌብነቷ ከሆነ መብቷ ነው፡፡ ዓለማችን በሌቦችና አጭበርባሪዎች የተሞላች በመሆኗ የርሷ ሌባ መሆን እንግዳ ነገር አይደለም – በአመራርም ሆነ በተራ ዜጋነት ሌባና አጭበርባሪ ሀገር ምድሩን ሞልቶታል፡፡ አዜብ በተፈጥሯዊ ደመ ሞቃትነቷና ያንንም ተከትሎ በጉልህ ስለሚንጸባረቅባት የሴሰኝነት ጠባይዋ አይደለም ሹም እንዳትሆን የምመኘው፡፡ ያም መብቷ ነው – ካልሰለቻት እንኳንስ ነባር ታጋዮችን አዳዲሶቹንና እምቦቀቅላ ታጋዮችንም

ታነባብራቸው፡፡ አዜብም ሆነች ቤቲ በተፈጥሮ የተሰጣቸውን መብት እስከፑንት (ላንድ) ቢጠቀሙበት የነሱ ጉዳይ እንጂ የማንም ራስ ምታት ሊሆን አይገባም፡፡ እኔን ክፉኛ የሚያሳስበኝ ድንበር የማያውቀው ውሸቷ ነው፡፡ በተራ ቃል ‹ውሸታም› መባል በፍጹም አይመጥናትም፡፡


በባህር ዳሩ የወያኔ ስብሰባ የተናገረችው ውሸት ስለሷ ባሰብኩ ቁጥር ስለእውነት በጣም ያመኛል፡፡ በዚያ ስብሰባ ‹መለስ ከዓለም መሪዎች በደመወዙ ብቻ ቤተሰቡን እያሰቃየ የኖረ ብቸኛው መሪ ነው፤ ከስድስት ሺ ብር ደመወዝ ለኢሕአዲግ ተቆርጣ በምትደርሰው አራት ሺህ ምናምን ብር ወርን ከወር እየጣጣፍን በመከራ ሲያኖረን የነበረና አእምሮውን ብቻ ይዞ የተወለደ… ይህ ሊሠመርበት ይገባል ፤ ሰው የሚለው አይደለም – እርሱ በዚያች ትንሽ ደመወዝ ብቻ ኖሮ ያለፈ የተለዬ መሪ ነው…› እያለች


የቀላመደች ዕለት ስለርሷ ጨረስኩ፡፡ ስለርሷ ብቻም አይደለም፡- ስለወያኔ/ኢሕአዴግም ያኔውን ጨረስኩ፡፡ አንድ አንጋፋ ድርጅት ያን የመሰለ በሬ ወለደ ዓይነት ነጭ ውሸት ሰምቶ እርምጃ አለመውሰዱ ገርሞኛል – የዚያን ድርጅት የለዬለት ባዶነትም አረጋግጫለሁ፤ የሴትዮዋ ንግግር እውነትነት ቢኖረውም እንኳን የሀገርንና የድርጅትን ምስል በማጠየም ረገድ ቀልማዲት

ያደረገችው ነገር እጅግ ሰቅጣጭ በመሆኑ በሕይወት የመኖርን መብት ሳይጨምር ከብዙ ነገር ልትታገድ በተገባት ነበር፡፡ ሕዝብ በሆነ ምክንያት በይሁንታ አፉን ቢለጉም እውነት እንዳይመስላቸው፡፡ ሕዝቡ በዕውቀት ከነሱ ስለሚበልጥ በዚያን ሰሞን ይህን የአዜብን የድህነት ወሬ የቡና ማጣጣሚያ ነው ያደረገው – ሳይጠማን እየጠጣን ብዙ ቡና ፈጅተንበታል – ጊዜው ሲደርስ ይህንን ኪሣራችንንም ታወራርዳለች፡፡ የዚህች ቀልማዳ ሴት ንግግር በአሣፋሪነቱና አጸያፊነቱ በሺዎች ዓመታት አንዴ እንደሚያጋጥም እጅግ ነውረኛ አነጋገር ሊወሰድ ይችላል፡፡ የርሷ ስህተት እንደግለሰባዊ ስህተት ተቆጥሮ በዝምታ ሊታለፍ ይችላል፡፡ የወያኔው ድርጅት በፍርሀት ይሁን በሌለው ይሉኝታ እርሷን በዝምታ ማለፉ ግን ይቅር የማይባል ታሪካዊ ህፀፅ ነው፡፡ ለነገሩ አሁንም ብዙም አልረፈደምና የሴትዮዋን ተፈጥሮ የምታውቁ ወያኔዎች እባካችሁን አንድ ነገር አድርጉ – ለናንተው ስትሉ፡፡ እኛ ሁሉንም



ለምደነዋልና ስለኛ ብላችሁ እንደማትጨነቁ እናውቃለን፡፡ ሀፍረቱ ይበልጡን ለእናንተው ስለሆነ አዜብን ግዴላችሁም ተዋት፡፡
ቁጭ ብዬ በእርጋታ ሳስበው ሕዝብንና የታሪክ ፍርድን ንቆ ይህችን ሴት ባለሥልጣን ማድረግ የኋላ ኋላ ኢሕአዴግን ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍለው ይመስለኛል፡፡ እናም ኢሕአዴግ ለክብሩ ሲል – ክብር ካለው ነው ለዚያውም – አለበለዚያም ውርደቱን ቅጥየለሽ ላለማድረግ ሲል ይህችን ሴት ከማዘጋጃ ቤት ሹምነት የዕጩ መዝገብ ይፋቃት፡፡ እኔ ውርድ ከራስ ብያለሁ፡፡ ሰውን መናቅ ፈጣሪን መናቅ እንደሆነ ለሃይማኖት የለሹ ወያኔ መጠቆም እፈልጋለሁ፡፡ እርግጥ ነው – በአምባገነኖች ዘንድ ማይምንና እንደጤናማ ሰው ማሰብ የማይችልን አጋሰስ መሾም የተለመደ ነው፡፡ ሲበዛ ግን ያንገሸግሻል፡፡ ሕዝብ ስቆ ቢያልፈው የውሻን ደም መና የማያስቀረው ፈጣሪ፣ አይደለም ይህችን በሰው ቋንቋ ከመናገሯ ውጪ ከውሻ ብዙም የማትለየው ሴት ትቅርና ሂትለርንና ሙሶሊንን የመሰሉ ለሰማይ ለምድር የከበዱ አምባገነኖችን አይቀጡ ቅጣት አከናንቦ በጭቁኖች መሃል አዋርዷቸዋል፡፡


ይህች መናኛ ሴትም ከወያኔ ጋር የምትዋረድበት ዘመን እየመጣ ቢሆንም ማምሻም ዕድሜ ነውና ማሰብ ያልተሳናችሁ በጣት የምትቆጠሩ ወያኔዎች ካላችሁ የዛሬን ማሩን፤ ቀድሜ እንደገለጽኩት ውርደቱ የጋራችን ነው፡፡ ይበልጡን ግን – ልድገምላችሁ – የእናንተው ነው፡፡ ሴትዮዋን መሾማችሁ የግድ ከሆነ ብትፈልጉ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጓት፡፡ ያ ቦታ ከሕዝብ የራቀ በመሆኑ አንገናኝምና እንደፍጥርጥራችሁ፡፡ አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ግን ሺዎችን በየቀኑ የሚያስተናግድ የሕዝብ መናኸሪያ በመሆኑ ባለሥልጣናቱ የሕዝብን ቀልብ እንደነገሩም ቢሆን የሚስቡ መሆን አለባቸው፡፡ ይህች ሴት እኮ አርከበ ዕቁባይ ለሕዝብ ጥሩ ሠራ በመባሉና ሕዝብም በተወሰነ ደረጃና በግል አበርክቶው ስለወደደው በዚያ ቀንታበት ኤች አይ ቪ ሲመረመር የሚያሳየውን ቢልቦርድ በተሰቀለ በጥቂት ቀናት ውስጥ እንዲወገድና ከዕይታ እንዲሠወር አድርጋለች፡፡ የባል ተብዬው የመለስና የሚስት ተብዬዋ የአዜብ የክፋት ደረጃ እንግዲህ እስከዚህ የወረደና ከአንድ ተራ ዜጋ እንኳን የማይጠበቅ ነው – ለቅጣት መምጣታቸውን በበኩሌ አምናለሁ፡፡ ተራ ዜጋ ምቀኛና ቀናተኛ ቢሆን ምንም አይደለም፡፡ የአንድን ሀገር በትረ ሥልጣን የጨበጠ ቁንጮ ያገር መሪና ሚስቱ ግን እንዲህ ያለ በራሱ በመለስ ወራዳ የቋንቋ አጠቃቀም ለመግለጽ እንዲህ ያለ ወራዳና ልክስክስ ጠባይ ሲያሳዩ የሀገርን አጠቃላይ ውድቀት ነው በጉልህ የሚያስረዳን፡፡ ያልዘሩት መቼም አይበቅልም፡፡ የዘራነውን እያጨድን ነን፡፡


ለማንኛውም አዜብን በከንቲባነት መሾም – ምክትልም ሆነች ዋና ለውጥ የለውም – የሚያስከትለው አደጋና ውርደት ታስቦበት በጊዜ አንድ ነገር እንዲደረግ የዜግነት ጥሪየን ማስተላለፍ እፈልጋለሁ፡፡


በሌላም በኩል ይሄ ለይምሰል ያህል በብሔረሰብ ተዋጽዖ አንጻር የሚደረገው ሹመት ይቁም፡፡ ምክንያቱም አንደኛ ማንም አያምንም – ይህን ያረጀ ያፈጀ ሥልት አንቀልባ ውስጥ ያለ ጡት ያልጣለ ሕጻንም ያውቀዋልና፡፡ እኔ ለምሳሌ በደመቀ መኮንን መሾም ምክንያት አልተደሰትኩም፡፡ አንደኛውና ትልቁ ነገር እንደውሻ አጥንትና ደም አላነፈንፍም፡፡


በብቃትና በችሎታ ከሆነ ሁሉም የሚኒስትር ካቢኔ ከኮንሶና ከሙርሲ ቢሆን ሃሳቡ አይበላኝም፤ ወያኔንም የጠላሁት በመጥፎ ድርጊቱ እንጂ በተሹዋሚዎች የዘር ሐረግ አይደለም – በጭራሽ፡፡ ሁለተኛ የደመቀ መሾም ስሜትን በማይነካ የቃላት አጠቃቀም ለየዋሃን አማሮች ካልሆነ በስተቀር መሬት ላይ የፈጠጠውን ኢትዮጵያዊ እውነት ለሚረዳ ሰው ‹አማራ ተሾመልኝ!› በሚል የሚያስፈነጥዝ አይደለም፡፡ ራሱን ከጥቃት የማያድን አማራ፣ የራሱ ናቸው የተባሉ ወገኖችን ጥቃትና እንግልት ለማስቆም አንዳችም ተሰሚነት የሌለው በድንና ገልቱ ሰውዬ ተሾመልኝ ብዬ ጮቤ የምረግጥ ሞኝና ተላላ መስዬ ከታየኋቸው – አዝናለሁ – ሞኞቹ እነሱ እንጂ እኔ አይደለሁም፡፡ ደመቀን መሣይ ከረፈፍ ሆዳሞች በሥርዓቱ ውስጥ ወይነው ገብተው ሀገሪቱን ምን ያህል እየጎዱ እንደሆነ ማስታወስም ተገቢ ነው፡፡ በጣም የምወደው ኦባንግ ሜቶ ቅድም ሲናገር እንደሰማሁት ሁልጊዜም እኔ ራሴ እንደምለው ወያኔ ማለት በዘርና በቋንቋ ተወስኖ ወይም ተቀንብቦ የተቀመጠ አለመሆኑንም መረዳት ይገባል፡፡ መነሻውና አስኳል አመራሩ ከትግራይ ይሁን እንጂ ለዚህ የወያኔ ሥርዓት ማበብና ማፍራት ዋና ተባባሪዎቹ ትግሬ ያልሆኑ የተጋቦት ወያኔዎች መሆናቸውን እናውቃለን፡፡ ግን ግን “የምታሸንፈውን ምታ ቢሉት ወደ ሚስቱ ዞረ” እንዲሉ ሆኖብን አንዴ የፈረደበትን የትግራይ ሕዝብ ብዙዎቻችን


እንወርድበታለን፡፡ በበኩሌ አሁን እየሆነ ባለው ነገር ሁሉ የእያንዳንዳችን ልብ ሳይሰበር ነገ ይቅርታ እንደምንባባልና አብሮነታችን ካለሣንካ እንደሚቀጥል በሙሉ ልብ አምናለሁ፡፡ ንዴትና ብስጭት የማይፈጥረው አእምሮኣዊ ምስል ባለመኖሩ ደመናው ሲጠራና እውነት ስታሸንፍ አሁን ችግር የሚመስሉን ብዙ ነገሮች ከላያችን ላይ ተገፍፈው ይጠፋሉ፤ ያለ ነገር ነው – በዚህን መሰሉ ጊዜ የሚያጋጥም ብዙ ነገር አለ፡፡ መምሰልና መሆን ስለሚለያዩ የደፈረሰው ሲጠራና የሰላም አየር በሀገራችን ሰማይ ሲያረብብ የግጭትና የሁከት እርኩሳን መናፍስት ተጠራርገው ይወገዳሉና ስለነገው ከመጠን በላይ አንጨነቅ፡፡ የወቅት ንፋስ የሚፈጥራቸው ብዙ አላፊ ክስተቶች አሉ – በኛ ብቻ ሳይሆን በየሀገሩ፡፡ ሁሉም እንደሚያልፍ መረዳትና ለዚያ በርትቶ መታገል እንደሚገባ ተረድተን በወንድማማችነትና በእህትማማችነት ተባብረን ይህን የለያየንን ቆሻሻ ሥርዓት ለማስወገድ አብረን መታል ብቻ ነው የሚያዋታን፡፡


አለጥርጥር ሥርዓቱ ይወድቃል – ችግሩ በጣም ብዙ ምናልባትም ከእስካሁኑ የከፋ ቨስጠሊታ የታሪክ ጠባሳ ሳይተው የሚወድቀው እንዴት ነው? የሚለው ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የሁሉም ምክክር፣ ትብብርና ስምምነት ያስፈልጋል፡፡ እውነት ምን ጊዜም ከእውነት መንገድ ለማትወጣው ነገር በመለያየት አዲስ ግን በወያኔያዊ ትልምና ዐቅድ የተለወሰና በፀረ-ኢትዮጵያነት የተመረዘ ታሪክ ለማስመዝገብ የምንቻኮል ሰዎች ካለን ቆም ብለን እንድናስብ በእገረ መንገድ ጠቆም ባደርግ ደስ ይለኛል – ከወያኔ ብዙ ነገሮችን መማር እንችላለን፡፡ የሕዝቡ ችግረና ፍላጎት ይግባን፡፡ ‹ሕዝቡ ምን ይላል? ምንስ ይፈልጋል ?› ብለን እንራመድ እንጂ በየግል ፍላጎታችን የተጓዝን ተሳስተን አናሳስት፤ ታሪክም ይቅር አይለንም፡፡ መደማመጥ ለመልካም የጋራ ስኬት ጠቃሚ መሆኑን እየዘነጋን ለየህልማችን እውን መሆን በተናጠል ስንሮጥ የዓለም ፍጻሜ ተቃረበ፡፡


ማንዴላ እጅ ሆነዋል፡፡ ምናልባትም ይህች ጽሑፍ በአንዱ ድረ ገፅ ከመለጠፏ በፊት አንዳች ነገር ሊከሰት ይችላል፤ ወይም በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ ዜና ዕረፍታቸውን እንሰማ ይሆናል – ለነገሩ ‹እግረ ቀጭን እያለ እግረ ወፍራም ይሞታል› እንዲሉ ከማንዴላ በፊት ለምሳሌ እኔ ራሴ ልቀድም እችላለሁ፡፡ የወደፊቱን ያለማወቃችን ምሥጢር ነው ሕይወትን ትርጉም ያላት እንድትሆን ያደረጋት፡፡ ተስፋ ባትኖር ሁሉም በቁም እንደሞተ ያህል ነው – ጧት ከቤቱ በሰላም የወጣ ሰው ማታ ሬሣው ወደቤቱ ሊመለስ እንደሚችል ቢያውቅ ማንም የመኖር ጉጉት አያድርበትም – የእግዜሩም እንበለው የተፈጥሮ ጥበብ መገለጫም ይሄው ነው – ስለወደፊቱ አለማወቅ፡፡ በዚህም አለ በዚያ በማንዴላ ሁኔታ ዓለም በጭንቀት ላይ የምትገኝ ትመስላለች፡፡ ጭንቀቷ ግን ለማንዴላ ለራሱ እንዳይመስላችሁ፡፡ ምሥጢሩ ወዲህ ነው፡፡(በነገራችን ላይ ‹ድኅረ ገፅ› የምንል ሰዎች ‹ድረ ገፅ› ማለትን ብንለምድ ደስ ይለኛል፡፡ ‹ድኅረ› ማለት ‹በኋላ›(post) ማለት እንደሆነና ‹ድረ› የሚለው ቃል ግን ‹ድር› ከሚለው የአማርኛ ቃል ተወስዶና ከ‹ገፅ› ጋር ተጋምዶ ‹website› የሚለውን የእንግሊዝኛ ቃል እንዲተካ መደረጉን ምሁራን ይገልጻሉ፡፡ ዕውቀት አይናቅምና በተለይ ድረ-ገፆች እባካችሁን ይቺን ነጥብ አትናቋት፡፡ መናደድ ሲያምረኝ ከምናደድባቸው ነገሮች አንደኛዋ ይህች ነች፡፡ )


የዓለም ሕዝብ አንድ አባሉ ከ94 ዓመታት በላይ በመሬት ላይ እየኖረ እንዲሰቃይ የሚፈልግ አይደለም፡፡ ይህ ዓይነቱ ሰዎች እስከዘላለሙ እንዲኖሩ የሚፈለግበት ምኞት – ከልብ ስለመሆኑ ማወቅ ቢያስቸግርም – በብዛት የሚታየው በኛይቷ ሀገር በኢትዮጵያ ነው፡፡ የመቶ ሃያ ዓመት ሽማግሌ ሲሞት ፊት የሚነጨው በሌላ ሀገር አይደለም – በኢትዮጵያ ነው – ሊያውም ይበልጡን በአማራው አካባቢ፡፡ ባህላችን ከኛ ወቅታዊ ግንዛቤ በልጦ የሚገኝበትን ሁኔታዎች አንዳንዴ እንታዘባለን፤ ከአንዳንዴም በላይ እንዲያውም፡፡ ለዚህም ነው በዛሬዋ ውሎየ እንኳ ሁለት ተቃራኒ ጸሎቶችን የታዘብኩት – አንድ ከኢትዮጵያውያን፣ አንድ ከደቡብ አፍሪካውያን፡፡ መቼም እኛ ከነሱ በልጠን እግዜሩ ለማንዴላ የማቱሳላን ዕድሜ እንዲሰጥልን ልንጸልይ እንደማንችል ቢያንስ ኅሊናችን ያውቃል – እውነቱን እንነጋገር ከተባለ፡፡ ይህ ምን ያሳያል? ፊት ለፊት የሚታየው ባህላችን ለሰው መጥፎ የማይመኝ መሆኑንና በብዙ ነገር ከሌሎች የምንለይ ሕዝብ መሆናችንን ነው ለዓለም እያስመሰከርን የምንገኘው – ምነው እውነተኛና በምንም ዓይነት ማዕበል የማይናወጥ አቋም ባደረገልን!


ማንዴላ እንዳይሞት የምንፈልግበት ምክንያት ግልጥ ነው፡፡ ዓለማችን በሰው እጦት ምች ስለተመታች ጥሩ ሰው ስናገኝ እንደብርቅ እናየዋለን፤ ሞት እንዳይነጥቀንም እንሳሳለታለን፤ እስከወዲያውም አብሮን እንዲኖር እንመኛለን – ትውልድ ቢያልፍም ከቀጣዩ ትውልድ ጋር፡፡ ብዙ ደጋግ ሰዎች ቢኖሩን ኖሮ የዓለም ሕዝቦች ትኩረት በአሁኑ ሰዓት ያለቪዛና የትራንስፖርት ወጪ ደቡብ አፍሪካ ሄዶ ፕሪቶሪያ ሆስፒታል ዙሪያ ባልከተመ ነበር፡፡ ጥሩ ሰው ብርቅ በሆነበት ዘመን መፈጠር እንዴት መታደል ነው! መለስም እንዲያ የተንጫጫንለት እኮ የርሱን አእምሮ ይዞ የሚወለድ – እንደአዜብ አነጋገር በዓለም የአንጎል ገበያ ተመራጭ ጭንቅላት ይዞ በሺዎች ዓመታት አንዴ የሚወለድ ዐዋቂና ታዋቂ በመሆኑ ነው፡፡ እኔ ለመለስ የነጨሁት ፊት እስካሁን አላገገመም፤ የምለብሰውም ማቅ ከላየ ላይ አልወረደም፡፡ እርግጥ ነው – ይበልጡን ለክፋት ቢጠቀምበትም መለስን በዕውቀቱ መቀጣጠብ አይቻልም፤ ሰይጣን ለዘዴው ከመጽሐፍ ቅዱስ ይጠቅሳል እንደሚባል መለስም የነበረው ሁለገብ ዕውቀትና ብልጣብልጥ ተፈጥሮ ከብዙዎች መሪዎች ቢበልጥ እንጂ አያንስም፡፡ የኔነህ ሳይለኝ ቢሞትም የኔነው ማለት ወጪ የለውምና ሳልወድ በግዴ የኔነው ብዬ ብቀበለው ከሚኮሰኩሰው ኢትዮጵያዊነቱ አንጻር ብቻም ሳይሆን ከአጠቃላይ ስብዕናው የሚፈልቁ ብዙ የሚደነቁ ሰብኣዊ ተሰጥዖዎች እንደነበሩት አልክድም – አጭበርባሪው፣ አስመሳዩና መልቲው መለስ ዜናዊ፡፡ ግን ተሰጥዖዎቹን ለተንኮልና እንደሥራየ ቤት ነገርን በመጠምዘዝ ሕይወቱን ጨርሶ ዕውቀቱን ሳይጠቀምበት ሞተና ዐርፎ ዐሣረፈን፡፡ በሚስቱ ሲንገበገብ የነበረ አንድ ፈላስፋ መቃብሯ ላይ እንዲህ የሚል ጽሑፍ አስፍሯል አሉ፡- My wife lies here; let her rest in peace, so do I.
አትታዘቡኝ፡፡ በበኩሌ ማንዴላ እንዲያርፍ እጸልያለሁ – በሰላም ማረፍ ለኔ አይገባኝም – ሰው እየሞተ ምን ሰላም አለና፤ ማንዴላ በ‹ሰላም› እንዲያርፍም በ‹ሰላም› እንዲድንም ከጸሎት ጀምሮ ሁሉም ነገር ቢደረግም እስከዚች ሰዓት ድረስ አልዳነም ወይም አላረፈም፤ የዚህን ደብዳቤ የመጀመሪያ ረቂቅ ስጽፍ – አሁን ሰዓቱ ከሌሊቱ ስምንት ገደማ መሆኑን ልብ ይሏል – የማንዴላ የጤና ሁኔታ እንደሰሞኑ ሁሉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው የሚገኝ፤ ከአሳሳቢነቱም የተነሣ ፕሬዚደንት ጃኮብ ዙማ ሊያደርጉት የነበረውን የሀገር ውጪ ጉዞ እስከመሠረዝ ደርሰዋል፡፡ ዕንቁ ልጃችን – ብርቅዬ የአፍሪካ ብቻ ሣይሆን የዓለማችን ልጅ ማዲባ ሲያርፍ ደግሞ ነፍሱ በማኅተመ ጋንዲና በእማሆይ ተሬዛ፣ በአብርሃምና በያዕቆብ ነፍሳት አጠገብ እንድትቀመጥ የቸሩ እግዚአብሔር ፈቃድ ይሆን ዘንድ የሁላችንንም ጸሎት እኔም በበኩሌ እጸልያለሁ፡፡ ይቅርታችሁን – ቀደም ብዬ ማዲባን በአንቱታ የጠራሁት ብዙ ሰው ያለው እኔስ ለምን ይቅርብኝ ብዬ ከሰው ለመመሳሰል ነው፤ ስጨርስ በአንተ የጠራሁት የሕዝብ ሰው አንቱ እንደማይባል ስለምረዳ የአንጀቴን ነው – የሕዝብ ሰው ማለት ደግሞ የሚፈቀርና የሚወደድ ማለት ነው፡፡ አብንና ወልድን ማን አንቱ ይላል? ቅድስት ማርያምንስ? ኧረ መለስ ዜናዊንስ ማን በአንቱታ ጠርቶት ያውቃል? የሕዝብ ሰው ማለት እንዲህ ነው – ቺንዋ አቼቤ A man of the people የሚል ርዕስ ለአንድኛው መጽሐፉ የሰጠው እኮ ለነማንዴላ ዓይነቱ መላ ሕይወታቸውን ለራሳቸው ጥቅም መስዋዕት ላደረጉ ሣይሆን ለነመለስ ዜናዊ ዓይነቱ ለቤት ቀጋዎች ለውጭ አልጋዎች ነው፡፡ ዓለም ግን ምን ዓይነት የዕንቆቅልሽ ምድር ናት ጎበዝ?! ውድ ማንዴላ ሆይ! ሁልጊዜ ከኅሊናችን አትጠፋም – በአካል ብትለየን በመንፈስ ምንጊዜም አብረኸን አለህ – ከአሁኑም

ከወደፊቱም ትውልዶች ጋር፤ ፈጣሪ አንተን እንደወሰደ በምትክህ ለዓለም ሰላም የሚተጉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቅን አሳቢ ዜጎችን እንዲልክልን ስትሄድ አሳስብልን፡፡ አፈሩን ገለባ ያድርግልህ፡፡ የሁለት ወር ሀገርህን ኢትዮጵያንም በፈጣሪ ፊት አስባት፡፡ ስቃይና ጣር ሳይበዛብህ በቶሎ ሂድልን፡፡ በዚህች አንተን ሳይቀር ለ27 ዓመታት በእሥር ባንላታች የእርጉማን ምድር ከአሁን በኋላ ለሴከንድም መቆየቱ መከራና ስቃይ መጨመር እንጂ ጤናውም ጤና አይሆንህም፡፡ ሰዎች ስንባል ራስ ወዳዶች ነን፤ ‹ቆይልን› የምንልህ በአንተ ስቃይ የኛን ‹ኢጎ› ለማስደሰት እንጂ አንተ አልጋ ላይ ውለህ የመከራ ቀናትንና ሌሊቶችን በእዬዬ ማሳለፍህ፣ በድጋፍ ሰጪ የሕክምና ቴክኖሎጂ እየታገዝክ ካለ እንቅልፍ መቆየትህ አንዳችም ነገር አይፈይድልንም – ለአንተም ለእኛም፡፡ በሀገሬ ሰው ይሙት ተብሎ እንደማይጸለይ አውቃለሁ ማዲባየ – ግን ‹ይህን አለ› ተብዬ ኩነኔ መግባቱን እመርጣለሁ እንጂ ስትሰቃይ ለማየት ከእንግዲህ ቆይልን አልልህም፡፡ በቃ፡፡ በሰላም ሂድልን፡፡ ስትመጣ እንደምትሄድ ይታወቅ ነበር፡፡ እኛም በሕይወት አለን የምንል ወገኖችህም ወረፋችንን ጠብቀን እንከተልሃለን፡፡ ዱሮም መንገደኛ ፊትና ኋላ ነው መባሉም ለዚህ ነው፡፡ ይብላኝ ለኛ ግና፡፡


በጅቦችና በእሪያዎች መካከል እንደተጣልን ተለይተኸን ለምትሄደው ለኛ ይብላኝ እንጂ አንተማ ከፋም ለማም 95 የሚጠጉ ክረምቶችን ለሕዝብህ ስትል ከአፓርታይድና ከመጥፎ ግላዊ ገጠመኞችህ ጋር ስትፋለም ኖረህ አሁን በመጨረሻው ሥጋዊ ሽንፈትህ ደረጃ ላይ ደርሰሃል፡፡ በዚያች በደቡብ አፍሪካዊቷ አዜብ እንኳን ያየኸውን አበሳ ማን ይረሳዋል? ብቻ ሆድ ይፍጀው ማዲባየ፡፡


እዚያው እስክንገናኝ ደህና ሰንብትልኝ፡፡ ሰላም ለኢትዮጵያና ሕዝቧ፤ በዚህ ዓለም አቀፍ ሀዘን መጽናናት ለሚያስፈልገው ሁሉ ፈጣሪ እንዲያጽናናው እመኝለታለሁ፡፡

Wednesday, June 26, 2013

የሰንደቅ አላማ ክብር እና የብሔራዊ መዝሙራችን ጉዳይ

የሰንደቅ አላማ ክብር እና የብሔራዊ መዝሙራችን ጉዳይ


አንዲት ሀገር አንድነቷን፣ሉዓላዊነቷን እና የወደፊት ተስፋዋ ከሚግለፅበት መንገድ አንዱ ብሔራዊ
መዝሙሯ ነው። የብሔራዊ መዝሙርመከበር፣መወደድ እና ዋጋ መሰጠት ከሚገለፅባቸው መንገዶች
አንዱ ደግሞ ትምህርትቤቶች ናቸው። ከትምህርት መጀመር በፊት ተሰልፈውየሚያደርጉት
የ ሰንደቅ አላማ ማውጣት እና ማውረድ ትልቅ ዋጋ የሚሰጠው ጉዳይ ነው።


ቦይኮት (AESAONE)!

ቦይኮት (AESAONE)!

No-AESAONE-Amharic
June 25, 2013
አገራችንን እና ህዝባችንን አንቆ ከያዘው ከዘረኛው (TPLF) አምባገነን ስርዓት ጋር እጅ እና ጓንት ሆነው በተፈጥሮ ሃብቷ የሚበለጽጉ ሙሰኛ ባለጸጎች (crony tycoons) በህዝባችን ላይ አየደረሰ ላለው ፍትህ ማጣት፤መንገላታት፤መቸገር፤መታሰር፤መፈናቀል እና ማንኛዉም አይነት ግፍ ከስርዓቱ እኩል ተጠያቂዎች ናቸው።

ስደት ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን

ስደት ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን

suda-MMAP-md_61905628_sudan_meroe_pyramids_g June 25, 2013
ታክሎ ተሾመ
በየዓመቱ ከግንቦት 6 እስከ 20 2013 ዓ.ም ድረስ የስደተኞች ቀን ታስቦ እንደሚውል ይታወቃል። ስለሆነም የዚህች አጭር ጽሁፍ ዓላማ በሱዳን የስደተኞች ኑሮ ምን ይመስል እንደነበር አንዳንድ የኑሮ ትዝታዎችን ተመልሰን እንድናስታውስ ይረዳ ዘንድ ለመዳሰስ ነው፡፡

በረከት ስምኦን በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ እየዶለቱ ነው – (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

በረከት ስምኦን በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ እየዶለቱ ነው – (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

አቶ በረከት
በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ሊቀመንበርንት ከሚመራው ግንቦት ሰባት ጋር በተያያዘ በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ በረከት ስምኦን የሚመሩት የመንግስት አካል በምስጢር እየዶለተ መሆኑን ምንጮች ጠቆሙ። በቅርቡ በአንድ ድረገፅ ላይ የወጣውን የዶ/ር ብርሃኑን ንግግር በማስረጃነት ይዘው እየተንቀሳቀሱ ያሉት አቶ በረከትና ተከታዮቻቸው በአገር ውስጥ እየተንቀሳቅሰ የሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ « ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አለው፤ ከግንቦት ሰባት የገንዘብ ድጋፍ ይደረግለታል» በሚል እነበረከት ድምዳሜ ላይ መድረሳቸውን የጠቆሙት ምንጮቹ የፓርቲውን አመራሮች «ከሽብረተኛ ቡድን ጋር በመገናኘት» ብለው ለመክሰስ ሴራ እያበጃጁ መሆኑን

በዝዋይ እስር ቤት ለወራት የተሰቃየው ወጣት “ቤተሰቦቼን እንደሚፈጁ አስጠንቅቀውኛል” ይላል !

በዝዋይ እስር ቤት ለወራት የተሰቃየው ወጣት “ቤተሰቦቼን እንደሚፈጁ አስጠንቅቀውኛል” ይላል !

ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ በዝዋይ እስር ቤት ለወራት ስቃይ የተፈፀመበት
ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ይባላል፤ አርሲ አርባ ጉጉ ተወልዶ አዳማ/ናዝሬት አድጎ፣ በ1998 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሶሲዮሎጂ ተመርቋል፡፡ በ2000 ዓ.ም በባህልና ቱሪዝም ሚ/ር በሲኒየር ካልቸራል ኤክስፐርትነት የስራ መደብ እስከ ሚያዝያ 2003 ሰርቷል፡፡ ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በግልፅ ባልተረዳው ምክንያት የመንግስት ደህንነት ሀይሎች ተያዞ ለ23 ወር በዝዋይ እስር ቤት ከፍተኛ ስቃይ እየተፈፀመበት መቆየቱን ይናገራል፡፡ መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ.ም ከእስራት ሲለቀቅም አንድ ጊዜም እንኳን ፍርድ ቤት እንዳልቀረበ ለፍኖተ ነፃነት አስረድቷል፡፡ ከወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ጋር ያደረግነውን ቆይታ ተከታተሉን፡፡ፍኖተ ነፃነት፡- ማን ነበር ያሰረህ?


በቤተመንግስት ግቢ ዙሪያ አንድ ሰው ተገድሎ ተገኘ

በቤተመንግስት ግቢ ዙሪያ አንድ ሰው ተገድሎ ተገኘ

ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሀሙስ ከጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ጽህፈት ቤት ጀርባ  ሁለተኛው በር ከ150 እስከ 200 ሜትር  ባለ ርቀት ላይ አንድ ጎልማሳ አንገቱ ተቆርጦ  መገኘቱን የአይን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል።  -
 
እማኞች እንደሚሉት  ሟቹ እድሜው ከ45 እስከ 53 የሚጠጋ ጸጉር አልባ ጎልማሳ ነው። የሟቹ የራስ ቅል  ባእታ ክሊኒክ አቅራቢያ ባለ አንድ ቦታ ላይ ተጥሎ መገኘቱን የጠቆሙት ነዋሪዎች፣ ፖሊስ በአካባቢው ተገኝቶ አስከሬኑ እንዲነሳ ከአደረገ በሁዋላ ለአስከሬን ምርመራ ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል እንዲወሰድ አድርጓል።
 

ህወሃት ሊወድቅ ነው (ለነጻነታችን እንጨክን ፡ እንቆሽሽ!) – በያሬድ አይቼህ

ህወሃት ሊወድቅ ነው (ለነጻነታችን እንጨክን ፡ እንቆሽሽ!) – በያሬድ አይቼህ


ገዢው ፓርቲ ለጥገናዊ ለውጥ ምንም አይነት ቦታ የማይሰጥ መሆኑን በተደጋጋሚ ግልጽ አድርጓል።  ጠቅላይ ሚኒስትርም ይህንኑ ጉዳይ አስምረውበታል። ከዚህ የተነሳ ከገዢው ፓርቲ ጋር የነበረው የምርጫ ትግል በአጠቃለይ መክኗል። ዛሬ አገራችን ሙሉ በሙሉ ወደ ነጻነት ትግል ምዕራፍ ገብታለች።

ፓለቲካ አይነት ፡ አይነት አለው። የምርጫ ፓለቲካ እና የነጻነት ፓለቲካ አንድ አይደሉም። የምርጫ ፓለቲካ ንጹህ ነው ፡ ጭምት ነው። የነጻነት ፓለቲካ ግን ይጨክናል ፡ ይቆሽሻል።



ማነዉ ፈሪዉ ተቀዋሚ ወይስ ህወሃት/ ኢህአደግ..

ማነዉ ፈሪዉ ተቀዋሚ ወይስ ህወሃት/ ኢህአደግ..

ሰላም ፍቅሬ / ከጀርመን
ሰሞኑን በ20/06/2013 በአሜሪካ ኮንግረስ በኮንግረስ ማን የተከበሩ ሚስተር ስሚዝ ኢትዮጵያ ከመለሰ በኋላ ፦የወደፊት ዲሞ ክራሲና የሰበአዊ መ ብት በሚ ል ርዕስ በተደረገዉ  የም ስክርነት ቃል ላይ የተከበሩ አም ባሳደር ያማ ማ ቶ በተቃዋሚ ዎች ዙሪያ ሲናገሩ በራሳቸዉ  ስለማይተማ መኑና ስለሚፈሩ ነዉ ብለዉ መናገራቸዉን አድምጠናል።
በዚህ ጉዳይ ብዙ ማለት ይቻላል ፤ ይሁንና ለዛሬ በቅርብ የሆኑትንና በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ ላተኩር።
እዉነት አምባሳደር ያማማቶ እንዳሉት ፍርሃት ያለዉ በተቀዋሚ ጎራ ነዉ ፤ በህወሃት አካባቢ ነዉ ፤ ወይስ አሜሪካ የኢትዮጵያ ጉዳይ እያስፈራት መጣጉዳዩን ለፖለቲካ ጠበብቶች እተወዋለሁ ።

Tuesday, June 25, 2013

አዲስ መጽሀፍ፣ “ድርጅታዊ ምዝበራ” (በአክሎግ ቢራራ)

ዶክቶር አክሎግ ቢራራ በዚህ መጽሃፍ በማያሻማ ቋንቋ የኢትዮጵያን ሕዝብ የፖለቲካ፤ የኢኮኖሚ፤ የሶሻልና በአጠቃላይ የሕብረተሰቡን ከአስተዳደር ብልሹነት የመነጩ ውስብስብ ችግሮች፤ በጥናት፤ በምርምርና በማስረጃ የተደገፈ ትንተና አቅርበዋል።

 
 

አንዲት የኮንትራት ሰራተኛ በጅዳ ቆንስል በር ታንቃ ሞተች

አንዲት የኮንትራት ሰራተኛ በጅዳ ቆንስል በር ታንቃ ሞተች

(ነቢዩ ሲራክ)
ethio maids
በጅዳ መጠለያ አንዲት የኮንትራት ሰራተኛ በጅዳ ቆንስል በር ታንቃ ሞተች
በሪያድ “ኢትዮጵያዊቷ አሰሪዎቿን ለመበቀል የ6 አመት ህጻን ገደለች” የሳውዲ ጋዜጣ ዘገባ


Monday, June 24, 2013

አቶ ገብረመድህን አርአያ የዘማናችን አሉላ አባ ነጋ ተብለው በከፍተኛ ክብር ተሰየሙ

አቶ ገብረመድህን አርአያ የዘማናችን አሉላ አባ ነጋ ተብለው በከፍተኛ ክብር ተሰየሙGebremedhin Araya, awarded in Australia

June 24, 2013 በምእራብ አውስትራሊያ በፐርዝ ከተማና አካባቢዋ ኗሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ጁን 23 ቀን 2013 ባደረጉት ልዩ ዝግጅት ታዋቂውን የነፃነት ተፋላሚና የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጅ አቶ ገብረመድህን አርአያን የዘመናችን አሉላ አባ ነጋ በማለት በክብር ሰይመዋቸዋል። በዚህ ለእርሳቸው ታስቦ በተደረገው ልዩ የእራት ግብዣ ስነ ስርዓት ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን የተገኙ ሲሆን፣ እንግዶቹ ለአቶ ገብረመድህን አርአያ ያላቸውን ልዩ ክብርና አድናቆት በየተራ እየተነሱ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። በዚሁ መሰረትም አቶ ገብረመድህን ህወሓት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ይዞ የተነሳውን እኩይ አላማና ተግባር በማጋለጥ ያደረጉት ጉልህ አስተዋጽኦ፣ በተለያዩ የሚዲያ ዘርፎች በመረጃ የተደገፉ መግለጫዎችን እና ትምህርቶችን በመስጠት የከወኗቸው ሥራዎች፤ እንዲሁም ለእሩብ ምእተዓመታት ያህል በጽኑነት፤ በቆራጥነትና በሕዝብ ወገናዊነት መቆማቸው በምሳሌነት በጉልህ ተጠቅሰዋል።
ለአቶ ገብረመድህን ማህበረሰቡ በጋራ ባዘጋጀው በዚሁ ስነስርዓት ላይ በአረንጓዴ፤ ቢጫና ቀይ ቀለማት በደመቀ የኢትዮጵያ ሙሉ ካርታ ላይ የጀግናው ራስ አሉላ አባነጋ ምስል የተቀመጠበት የታሪክ ማስታወሻ ከታላቅ አክብሮት ጋር ተበርክቶላቸዋል። እንዲሁም ግለሰቦች በራሳቸው አነሳሽነት ያዘጋጁላቸው የተለያዩ ሽልማቶች ተበርክተውላቸዋል።

የትኛው አማራጭ ለአሜሪካ? “ኢህአዴግን ምን እናድርገው? ንገሩን!”

የትኛው አማራጭ ለአሜሪካ? “ኢህአዴግን ምን እናድርገው? ንገሩን!”

 
 
አሜሪካ ከመቼውም ጊዜ በላይ ደንግጣለች። ኦባንግ እንዳሉት ለህዝባቸው “ሬት” ለምዕራባውያንና “ማር” (የቤት ቀጋ፤ የውጭ አልጋ) የነበሩት አምባገነን በድንገት እንደ ተነቀለ ቡሽ ተስፈንጥረው ከሲስተም መውጣታቸው አሜሪካንን አስጨንቋታል። በተለይም እሳቸው አፍነው የያዙት የስርዓቱ “ክፉ ጠረን” አሁን እነርሱ (አሜሪካውያኑ) ደጅ የደረሰ ያህል መፍትሄ ለመፈለግ የወሰኑ ይመስላሉ። አውቀውና ፈቅደው ሲታለሉ የቆዩበትን ጊዜ አስልተው መንገዳቸውን የማስተካከል ስራ የጀመሩት ዛሬ አይደለም። አንዳንድ ምንጮች እንደሚሉት ከመለስ ሞት በኋላ አሜሪካ በምስራቅ አፍሪካ ላይ ሚዛኗን ሊያስታት የሚችል ውድቀት የሚደርስባት ኢትዮጵያ ላይ ያላትን አቋም ማስተካከል ሲያቅታት ብቻ እንደሆነ ይናገራሉ።

 

Sunday, June 23, 2013

ኮረዳይቱ ወደ ሀገሯ ልትመለስ ነው!

ኮረዳይቱ ወደ ሀገሯ ልትመለስ ነው!

ኮረዳይቱ ወደ ሀገሯ ልትመለስ ነው!
994174_561097347267400_570836208_n
 “አለን” የምን
ለው ካርቶኒስት አሌክስ እንዲህ ስሏል!
እኛም ለጊዜው እንዲህ ለጥፈነዋል፡፡ ጭማሪ ካለን ተመስጦ አድርገን እንመለሳለን!

ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. እና ኢትዮጵያ

ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. እና ኢትዮጵያ

tplf addis
ወደ ግንቦት 20ቀን, 1983 ዓ.ም. ከመግባታችን በፊት ትንሽ ወደ ኋላ መለስ በማለት የደርግ ስርዓትን በትንሹ እንቃኘው::
ደርግ
የካቲት ወር 1966 ዓ.ም. የዘውድ አገዛዙን ስርዓት በመቃወም በአርሶ አደሩ ፣ በተማሪው ፣ በአስተማሪው ፣ በመንግስት ሰራተኛው ፣ በወዛደሩ ፣ በነጋዴው እና በመለዮ ለባሹ ወዘተ ፣ ወዘተ የተቀጣጠለው ህዝባዊ አመጽ ጊዜ ሳይወስድበት በ6 ወራት ውስጥ የተነሳው ህዝባዊ አመጽ ግቡን መታ::

ህዝባዊ አመጹን የሚመራው የተደረጀ ፓርቲ ባለመኖሩ በር የተከፈተለት መለዮ ለባሽ አመቺ ሁኔታ በማግኘቱ በፍጥነት ተደራጅቶ ከተራ ወታደር ጀምሮ የተለያዩ ማእረግ ያላቸው አባላቱን አስመርጦ ወደ 120 የሚጠጉ ተወካዮቹን አዲስ አበባ በሚገኘው አራተኛ ክፍለጦር አሰባሰበ::


ከጦር ሃይሎች ፣ ከክቡር ዘበኛ እና ከፖሊስ የተውጣጡት እንኚሁ መለዮ ለባሾች በሰኔ ወር 1966 ዓ.ም. ተሰብስበው ብሄራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ መስርተው “ኢትዮጵያ ትቅደም ፣ አቆርቋዥ ይውደም” በሚል መርህ ስር ሰፊ ሊባል የሚችል የህዝብ ድጋፍም አግኝተው ነበር::

መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም. የተመሰረተው አስተባባሪ ኮሚቴ ንጉሱን ከስልጣን አውርዶ “ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ” የሚል ስም በመያዝ ኢትዮጵያን ማስተዳደር ጀመረ:: ቀስ በቀስም ደርግ የስልጣን ወንበሩን በማመቻቸት የሃገሪቷ መንግስት ለመሆን ቻለ::


በወቅቱ በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች ሃገራት ሶሻሊዝም ወይም ህብረተሰባዊነት በሚባል ርዕዮተ አለም እድገት እና ብልጽግና የማይገኝበት “ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን የማላይ” ስርዓት በቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት እና ቻይና ፕሮፖጋንዳ አለምን እንደማዕበል ሲወዘውዛት የነበረበው ሁኔታ ሆኖ በደርግ የተመሰረተው መንግስት ግራና ቀኙን ሳይመለከት ሶሻሊዝም በኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈጥረውን ቀውስ እና ችግር ሳያጤን እና ኢትዮጵያውያን ሊቃውንትን ሳያማክር በ1972 ዓ.ም. ኢሰፓአኮን(የኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲ አደራጅ ኮሚሽን) መሰረተ:: ይህንን ምስረታ ተከትሎም ደርግ አንድ እግሩን ገደል ከተተው::
በዚህ ጽሁፍ ሁለት ነገሮችን ለያይቼ በማሳየት ለማለፍ እሞክራለሁኝ፤

የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ከኃላፊነታቸው ተነሱ

የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ከኃላፊነታቸው ተነሱ

 የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ከኃላፊነታቸው ተነሱ

- ከምኒልክ ሆስፒታል ጥገና ጋር በተገናኘ መሆኑ ተጠቁሟል
በቅርቡ የተቋቋመው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙት አቶ ፈለቀ ኃይሌ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ታወቀ፡፡


በአቃቤ ሕግና በፍረድ ቤቱ መካከል አለመስማማት እየነገሰ መሆኑ ተሰማ!

በአቃቤ ሕግና በፍረድ ቤቱ መካከል አለመስማማት እየነገሰ መሆኑ ተሰማ!

ቅዳሜ ሰኔ 15/2005
‹‹ዳኞቹ እናንተ ናችሁ እኛ?›› ከዳኞቹ መካከል አንዱ ለአቃቤ ሕጎቹ ከተናገረው!
የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የክስ ሂደትን ታክኮ በአቃቤ ሕግና በዳኞች መካከል አለመስማማት መፈጠሩ ተነገረ፡፡ አለመስማማቱ የተፈጠረው አቃቤ ሕግ ለተደጋጋሚ ጊዜ በችሎት ውስጥ ከዳኞች ጭምር የበላይ መሆኑን ለማሳየት ጥረት በማድረጉ ነው ተብሏል፡፡ በዚሁ እያገባደድነው ባለው ሳምንት ተሰይሞ ምንም ሳያከናውን ተበትኖ በነበረው ችሎት ላይ አቃቤ ሕግ ቀድሞ ለፍርድ ቤት ሪጂስትራ ገቢ ማድረግ የነበረበትን ሲዲ እዚያው ለችሎቱ ገቢ ለማድረግ መሞከሩና ሲዲውን ገቢ ማድረግ የነበረበት ክሱ በተመሰረተበት ወቅት ማለትም (ከስድስት ወራት በፊት) ሆኖ ሳለ እስከአሁን ሳያስገባ መቆየቱ በዳኞቹና አቃቤ ሕጎቹ መካከል ፍጥጫ ጭምር እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል፡፡
 
 

ፕ/ት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የሌባ ተባባሪነት ለመደባቸው

ፕ/ት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የሌባ ተባባሪነት ለመደባቸው

Posted: June 23, 2013 in Amharic News
0
11
ከጥቂት ሳምንታት በፊት ዘ-ሐበሻ የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ሊቀትጉሃን አስታጥቄ አባተ አቅመ ደካማ ለሆኑ አባት አርበኞች የፈቀዱላቸውን 25 ኮንዶሚኒየም ቤቶች ለግል ጥቅም አውለዋል፣ ከሚያከራዩዋቸው ሕንፃዎች ከሚያገኙት ገቢ ላይ የአከራይ ተከራይ ግብር አለመክፈል፣ ያላግባብ ወጪ ማድረግና በመሳሰሉት ተጠርጥረው መከሰሳቸውን መዘገቧ ይታወሳል። ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ታትሞ የወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ “ፕሬዚዳንት ግርማ የአርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ክስ እንዲቋረጥ ጥሪ ማቅረባቸውን” ያትታል። ዜናውን ለተመለከተ ከዘራፊው የወያኔ ስርዓት ጋር በመተባበር “አበባ የመትከልና አበባ የመቁረጥ ስልጣን” ብቻ ተሰጥቷቸው ቁጭ ያሉት ፕሬዚዳንቱ እኚህን በርከት ያሉ አርበኞች አባቶችን ያስለቀሱትን ሊቀትጉሃንን ክሳቸው ተቋርጦ ይፈቱ ሲሉ በድፍረት መጠየቃቸው የሌባ ተባባሪነቱ ለመደባቸው፤ ወይም ከሌባ ጋር መተባበር ሱስ ሆነባቸው እንዴ? ያስብላል። የሪፖርተር ዜና እንደሚከተለው ነው። አንብቡትና ትዝብታችሁን ጣሉበት።