Monday, June 10, 2013

ዜና በጨዋታ፤ የፍትህ ሳምንት በኢትዮጵያ ተቀበረ (ተከበረ ማለቴ)

ETHIOPIA AFRICAN UNION MEETING
ዜና በጨዋታ፤ የፍትህ ሳምንት በኢትዮጵያ ተቀበረ (ተከበረ ማለቴ)
በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ዳኞች፣ የፍርድ ቤት ሰራተኞች፣ የማረሚያ ቤት ፖሊሶች እና የፍትህ ሚኒስቴር ሰራተኞች በመሆን ከሜክሲኮ አደባባይ እስከ ልደታ ፍርድ ቤት በፖሊስ ማርሽ ታጅበው ስለ ፍትህ እየዘመሩ የፍትህ ሳምንት አከባበርን አንድ ብለው ጀመሩ፡፡




ይህ የፍትህ ሳምንት ከሰኔ ሶስት አስከ ሰኔ ዘጠኝ 2005 ዓ.ም ድረስ የሚከበር መሆኑን ከስፍራው ራቅ ብለው የቆሙ ሰዎች አይተው ነግረውኛል፡፡
በሀገራችን በርካቶች የፍትህ ያለ እያሉ አቤት ቢሉም ሰሚ ባጡበት በዚህ ወቅት “የፍትህ ሳምንት በኢትዮጵያ ተከበረ” የሚለው ዜና ሲሰራ፤ “የፍትህ ሳምንት በኢትዮጵ
ዜና በጨዋታው በዚህ አበቃ በዝርዝር ጨዋታዎች እስክንገናኝ እንኳን ለሰኞ አደረሳችሁ!

One Response to ዜና በጨዋታ፤ የፍትህ ሳምንት በኢትዮጵያ ተቀበረ (ተከበረ ማለቴ)

በለው ! ያ ተቀበረ” ብሎ መሳሳት እንደመሳሳት አይቆጠርም፡፡ (ሲሉ ዜናውን የተሳሳቱ አንዳንድ ግለሰቦች ገልፀዋል) ፍትህ ጠያቂን እያሠሩ
ፍትህ ጋዜጣን እያከሰሩ
የፍትህ ሚኒስትሩን እያበረሩ
የፍትህ ቀን ብለው ካከበሩ
ከሞተ ቆይቷል ተጠናቋል ቀብሩ
ሼም አደለም ወይ ነገሩ አደብ ግዙ እፈሩ
ሳምንት ተጨፍሮ ሊወጣ ይሆናል ተስካሩ። እውነትም ይቺ ሀገር አድጋለች
በአጋጣሚው ሁሉ ታስጨፍራለች
በነፍስ ወከፍ ገቢ ዕድገቷ በ፬ነጥብ የሞተች
፴፩ከመቶ በገበያ ዋጋ ንረት የገሸበች
፶፭ በመቶ ሥራ አጥና ገንዘብ ውድቀት ያመጣች
አቤት ሀገሬ በሙስና ተሽሞንሙና በፍትህ ተሽቆጥቁጣለች
በሀገር ያላችሁ ዳኞች፣ ፖሊስ፣ ዓቃቢ ህግጋን የፍርድ ቤት ሠራተኞች፣ የማረሚያ ቤት ፖሊሶቻችን
በፖሊስ ማርሽ ታጅባችሁ ፍትህ! ፍትህ! በሉልን
ሌላውን የሚሠማው የለም እናንተው ጩሁና እናንተው ሥሙልን
ነገሩ የተገላቢጦሽ የማጭበርበርም የማላገጥም ሆኖ ተሳቀን አሳቀን!!።
*************************
በለው!

No comments:

Post a Comment