Thursday, December 5, 2013

የእሳት አደጋ በመቀሌ

በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ትላንት እና ዛሬ በደረሱ የእሳት አደጋዎች ከፍተኛ ንብረት መውደሙ ተሰማ። የኣይን እማኞች እንደሚሉት ትላንትና ለሊት በከተማይቱ ቀበሌ 06 የኢንዱስትሪ ዞን ተብሎ በሚታወቅ ስፍራ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ በትንሹ 70 ያህል የማምረቻ ተቐማት ሙሉ በሙሉ ወድሟል።
esat 2
ዛሬ ማለዳም እዚያው መቀሌ ውስጥ አዲቀይ በተባለ የገበያ ስፍራ በተመሳሳይ ሁኔታ በተነሳ የእሳት አደጋ በርካታ የንግድ ቤቶች መውደማቸውን የከተማይቱ ማ/ቤት ኣስታውቐል። የአደጋው መንስኤ ገና በውል ባይገለጽም የማዘጋጃ ቤቱ የእሳት አደጋ መቆጣጠሪያ ተሽከርካሪዎች ግን ቃጠሎውን ለመቆጣጠር ኣለመሰማራታቸው ታውቐል።
የመጀመሪያው አደጋ የደረሰው ከትላንት በስተያ ሰኞ ለሊት ለማክሰኞ ኣጥቢያ ነበር፣ በመቀሌ ከተማ 06 ቀበሌ የኢንዱስትሪ ዞን ተብሎ በሚታወቅ ልዩ ስፍራ። በአደጋውም የኣይን እማኞች እንደሚሉት 70 ያህል የተለያዩ የማምረቻ ተቐማት ሙሉ በሙሉ ወድሟል። የጉዳቱም መጠን ከ22 ሚሊየን ብር በላይ ተገምቷል። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን የመቀlሌ ከተማ ማ/ቤት የእሳት አደጋ መቆጣጠርያ ተሽከርካሪዎች ወደስፍራው ኣለመንቀሳቀሳቸው ታውቐል። ምክኒያቱ ደግሞ ሁለቱም የማዘጋጃ ቤቱ የእሳት ኣደጋ ተሽከርካሪዎች ተበላሽተው ጋራዥ ገብቷል የሚል ነበር። በእርግጥ የአየር መንገድ የእሳት ማጥፍያ መኪና በመጨረሻው ሳዓት መድረሱ ታውቐል። የሲሚንቶ ፋብሪካው ግን ዘግይቶም ቢሆን መምጣቱ ባይቀርም በቂ ውኃ ሳይዝ በመምጣቱ ባይመጣ ይሻል ነበር ነው የተባለው። የአደጋው መንስኤ በአካባቢው የነበረው አሮጌ የኤሌትሪክ ማከፋፈያ ትራንስፎርመር በመፈንዳቱ ነው የሚሉት የመቀሌ ኗሪ አቶ አብረኃ ደስታ ቃጠሎውን በፎተግራፍ ለማንንሳት የሞከሩ ሰዎች በፖሊስ መከልከላቸውን ነግረውናል።
esat የመቀሌ ከተማ ማ/ቤት ስራ ኣስኪያጅ የሆኑት አቶ አሰፋ ተገኝ ደግሞ የደረሱት የእሳት አደጋዎች 3 ሳይሆኑ ሁለት ናቸው ይላሉ።
ከአዲስ ኣበባ በስተሰሜን 780 ኪ ሜ ላይ የምትገኘው መቀሌ ከ300 000 በላይ ህዝብ ሲኖራት ካለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት ወዲህ በተለይ በሰሜን ኢትዮጵያ ዋና የኢንዱስትሪ ማዕከልም ናት። መስፍን ኢንጂነሪንግን ጨምሮ መሶብ ሲሚንቶ እና ሌሎች በርካታ ፋብሪካዎችም ይገኙባታል። ዘመናዊው የዓሉላ አባነጋ ኣውሮፕላን ማረፊያና ትልቁ የመቀሌ ዩኒቨርስቲም ከሚጠቀሱት መካከል ናቸው።
ጃፈር ዓሊ
ተክሌ የኃላ

ወያኔ የአፄ ምኒልክ 100ኛ አመት መታሰብያ በዓል እንዳይከበር ፍቃድ ከለከለ

December 4, 2013የሰማያዊ ፓርቲ የአፄ ምኒልክ 100ኛ አመትን በተለያዩ ዝግጅቶች አስቦ ለመዋል በጃንሜዳ የመሰብሰብ ፍቃድ እንዲሰጠው ጥያቄ አቅርቦ ነበር፣ ይሁንና መንግስት ጥያቄውን ተልካሻ ምክንያቶችን በመደርደር ውድቅ ማድረጉን የሚገልጽ ደብዳቤ ለሰማያዊ ፓርቲ ልኳል።
Semayawi party, Addis Ababa
የፊታችን ታህሳስ 3 የእምዬ ምኒልክን 100ኛ እረፍት በሰማያዊ ፓርቲ አዘጋጅነት እንደሚዘክር የታወቀ ነዉ፡፡ በፕሮግራሙ ላይም በርካታከሀገር ዉስጥና ከዉጪ ሀገር ምሁራን ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ይገኛሉ ተብሉ ይጠበቃል፡፡ የፕሮግራሙ አዘጋጅ ሰማያዊ ፓርቲ ለዝግጅቱ በሚያስፈልጉ ጉዳዩች ላይ ስራ እየሰራ ይገኛል! በስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ አዋጅ መሰረትም ስብሰባ እንደሚያደርግ ለስብሰባና ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ደብዳቤ በትናንትናዉ እለት ያስገባ ሲሆን ዘሬ በደብዳቤ የተመለሰዉ መልስ እጅጉን አስቂኝና አጠያያቂ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡
በደብዳቤዉ ላይ ለምታደርጉት ስብሰባ እዉቅና ልነሳጥችሁ አንችልም ምክንያቱም የፖሊስ ጥባቃ መመደብ አንችልም የሚል ነዉ፡፡ የሚገርመዉ ደግሞ የፅፈት ቤቱ ሀላፊ ተብዬዉ አቶ አሰግድ በንቀት ደግሞ ማናችሁና ምኒልክ ምናምን የምትሉት ደግሞ ምኒልክ ማነዉ በሚል በእብሪት የመለሰዉ መልስ ነበር፡፡
እንኳን ድንኳን ጥሎ ለመሰብሰብ ይቅርና ጎዳና ሙሉ ህዝብ በመላበት የሩጫ የሰልፍ መሰል የገዢዉ ፓርቲ መልካም ፈቃድ ያገኙ ፕሮግራሞች ከህዝቡ እኩል ፌደራል ፖሊስ ለጥበቃ እንደሚታዘዝላቸዉ እየታወቀ ፤ በሌላ መልኩም በድፍረት እንወጣለን ብለን በተለያየ ምክንያት በተጠሩ ሰልፎች ላይ ለድብደባ የሚላከው ቁጥር ስፍር የሌለዉ የፀጥታ ሀይል አሁን ምን ቢውጠው ነዉ የጥበቃ የሚሆን የሰዉ ሀይል ልናስተባብር አንችልም ስለዚህ ዝግጅታችሁን እዉቅና አንሰጠዉም መባሉ??? ይህ ከእብሪት በላይ ምን ሊሆን ይችላል!!!?
ያም ሆነ ይህ ዝግጅቱ በታቀደለት ምልኩ እንደሚፈፀም በተለመደ ቁርጠኝነት ላይ ነን! ሲፈልጉ ለጥበቃ የከለከሉትን ሀይል ለድብደባ ይላኩት!!! እኛ የምንዘክራቸዉ ፍርሃት ካልፈጠረባቸዉ ሞተዉም መንፈሳቸዉ ካልተለየን እምቢ ባይ አባቶቻችን ተወልደናል፡፡
ድል ለኢትየጵያ ህዝብ!!!

የሳውዲ አረቢያው ቀውስ መከሰት ለኢትዮጵያውያን/ት ዲያስፖራ ፍቅርና አንድነት ትምህርት ሰጥቶ ይሆን?

December 5, 2013በፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሀገሬ

Ethiopian Diaspora teachable moment
በአረብ አገር በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሠራተኞች ላይ የሚደረገው ህገወጥ የማሰቃየት እርምጃ በአስቸኳይ ይቁም! በአሁኑ ወቅት በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኞች ላይ በሪያድና በአዲስ አበባ ከተሞች ባሉ ገዥ አካሎች እየተፈጸመ ያለው የሰብአዊ መብት እረገጣ ከፍተኛ ቁጣን የቀሰቀሰ ከመሆኑም በላይ ኢትዮጵያውያን/ት የዲያስፖራ ማህበረሰብ ለጉዳዩ ልዩ የሆነ ትኩረት እንዲሰጡትና ለወገኖቻቸው የማያቋርጥ ድጋፍ እንዲያደርጉ ምቹ አጋጣሚን ፈጥሯል፡፡ ባለፉት በርካታ ሳምንታት በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ እየተፈጸመ ባለው አስደንጋጭ የሰብአዊ መብት እረገጣ የቪዲዮ ምስል መታየት መጀመሩን ተከትሎከአውስትራሊያ እስከ አሜሪካ ባሉ በአስር ሺዎች በሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን/ት ዲያስፖራ ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ ቁጣ እና የልብ ስብራት በማስከተሉ ምክንያት በየአካባቢያቸው ባሉ የሳውዲ አረቢያ ቆንስላዎችና የዲፕሎማሲ ማዕከላት በሮች ላይ ፊት ለፊት በመሰለፍ በግንባር በመግጠም ባሳዩት ቆራጥ ኢትዮጵያዊ የተቃውሞ ወኔ የመብት ረጋጮችን የሳውዲ አረቢያ ገዥ ባለስልጣኖች በማሸማቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከ6  – 7 ሺ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን/ት ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ከሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት የሳውዲ አረቢያ ገዥ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ እየፈጸመ ያለውን ህገወጥ እርምጃና የሰብአዊ መብት እረገጣ በአስቸኳይ እንዲያቆም በመጠየቅ በሳውዲ አረቢያ ከሚገኙ ወገኖቻቸው ጋር የማያቋርጥ ትብብርና ወገናዊ ድጋፍ እንደሚያደርጉ በአደባባይ በግልጽ አሳይተዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን/ት የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ከአትላንታ እስከ ሲያትል ከተሞች በመሰለፍ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡ ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ በአውሮፓ የተለያዩ ከተሞች በመውጣት ሰላማዊ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡ የሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎች በየደረሱባቸው ቦታዎች ሁሉ ባነሮችን በመያዝ ድምጻቸውን ከፍ በማድረግ “ሳውዲ አረቢያ ሃፍረተኛ! ሃፍረተኛ! ሃፍረተኛ! “ሳውዲ አረቢያ ሃፍረተኛ!” በማለት ተቃዎሟቸውን አሰምተዋል፡፡

ዝምታችን በቃ!! የምናውቀው ብቻችን እጣ ፈንታችን ሰንጎነጫት ነው፡፡ በጣም እጅግ በጣም ከመሸ! ዝም ስንል እናልቃለን! ……

December 4/2013
‹‹መጀመሪያ በ‹‹አማራው›› ላይ መጡ ምንም አልተናገርኩም ምክንያቱም ‹‹አማራ›› አልነበርኩም፡፡ ቀጥለው ‹‹በኦሮሞ›› ላይ መጡ ምንም አላልኩም ምክንያቱም ‹‹ኦሮሞ›› አልነበርኩም፡፡ በመቀጠል ‹‹በሶማሊው፣ በጋምቤላው፣በትግሬው….ላይ መጡበት ምንም አልተናገርኩም ምክንያቱም ከአንዳቸውም አልነበርኩም ከዚህ በመቀጠል በሙስሊሙ ላይ መጡ አሁንም ምንም አላልኩም ምክንያቱም ሙስሊም አልነበርኩም በመቀጠል በክርስቲያኖቹ ላይ መጡ ምንም አልተናገርኩም ምክንያቱም ክርስቲያን አልነበርኩም በስተመጨረሻ በእኔ ላይ መጡብኝ አሁን ለእኔ የሚቆምልኝ ማንም አልቀረም፡፡ ብቻዬን ነኝ!››
 
ይህ በናዚዎች ስር የነበረው ህዝብ ታሪክ ነው፡፡ በአምባገነኖች ስር ያለና የነበረ ህዝብ ታሪክ ነው፡፡ የእኛው የኢትዮጵያውያን የወቅቱ ችግር ነው፡፡ኒይሞለር በአንደኛው የዓለም ጦርነት የተሳተፈና የናዚ ቀንደኛ ደጋፊ የነበር የፕሮቴስታንት ፓስተር ነበር፡፡ ጨፍጫፊው ናዚ ለጀርመናውያን እቆማለሁ ቢልም በሀሳብ የተለዩትን ጀርመናዊያን ላይ ግን ጠንካራ ብትሩን አሳርፎባቸዋል፡፡ እናም ኮሚኒስት፣ ሶሻሊስት፣ ቤተ እስራኤላዊያን፣ የሰራተኛ ማህበራት….ሌላም ሌላም ከናዚ አስተሳሰብ የሚቃረኑት በሙሉ በየተራ እርምጃ ተወሰደባቸው፡፡ በዛ ዘመን አንዱ ላይ እርምጃ ሲወሰድ ሌላው ዝም በማለቱ ናዚዎች የሚፈልጉትን ሁሉ በግፍ ጨፍጭፈዋል፣ አስረዋል፣ አሰቃይተዋል፡፡

መድረክ የጠራው ሰልፍ ተከለከለ


የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ህዳር 29 ቀን 2006 ዓ.ም ለማድረግ ያሳወቀው ሰልፍ ተከለከለ፡፡ መድረክ ሰልፉን ለመጥራት በሀገራችን መሰረታዊና ወቅታዊ የሆኑ ችግሮችን እንዲሁም በሰውዲና በአለም ዙሪያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው ሰቆቃ መሰረቱ የስደት መንስኤው ላይ በመሆኑ መንግስትን በሰላማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ እንደነበር ለማወቅ ችለናል፡፡

ሰልፉን ለማድረግ የታቀደው ስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ አምስተኛ በር ፊት ለፊት ከሚገኘው የመድረክ ቢሮ በመነሳት በአምስት ኪሎና ስድስት ኪሎ አድርጎ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ድረስ ለመጓዝ ነበር፡፡ ነገር ግን የአድስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንትባ ፅ/ቤት “ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እውቅና የጠየቃችሁበት ስፍራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስብሰባና የሰላማዊ ሰልፍ አሰራር ስነ-ስርዓት አንቀፅ አምስት ሀ እና መ የሰላማዊ ሰልፍ የማይካሄድባቸው ቦታዎች ተብለው የተጠቀሱ በመሆናቸው የተጠየቀው የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና መስጠት የማንችል መሆናችንን እንገልፃለን” ሲል መልስ ሰጥቷል፡፡
በጉዳዩ ላይ አስተያት እንዲሰጡ የጠየቅናቸው የመድረክ ስራ አስፈፃሚና የአንድነት ፓርቲ ዋና ፀሀፊ አቶ አስራት ጣሴ “መልሱ የመድብለ ፓርቲ ቅልበሳ ከመሆን አይዘልም” ይላሉ፡፡ አስተዳደሩ ጠቅሶ እውቅና ለመንፈግ የተጠቀመበት ደንብ ማንም የሚያውቀው መሆኑን የተናገሩት አቶ አስራት በማያውቁት ህግ እንደማይደኙ ገልፀውልናል፡፡ በተጨማሪ በዚህ ጉዳይ ላይ የወጣው አዋጅ መወቅ ቢችሉ እንኳ በተባለው ደንብ እንደማሻር አክለዋል፡፡

በ1983 ዓ.ም የወጣው የሰላማዊ ሰልፍና ህዝባዊ ስብሰባ አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 3 1983) የተከለከሉ ብሎ የሚጠቅሳቸው ቦታዎች እንደሌሉና ከኤምባሲዎች፣ ት/ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣ የሀይማኖት አምልኮ ስፍራዎች፣ በገበያ ቀን (ከገበያ ስፍራ) መቶ ሜትር መራቅ እንዳለበት ማዘዙን አቶ አስራት ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ከጦር ካምፕና የደህንነት ተቋማት 500 ሜትር መራቅ እንዳለበት አዋጁ ማስገደዱን ያስረዱት አቶ አስራት ከዚህ ቀደም አንድነት መስከረም 19 ቀን 2006 ዓ.ም በጠራው ሰልፍ ይህንን አዋጅ በመሻር በጦር ካምፕና በደህንነት መስሪያቤቶብ በተከበበው ጀንሜዳ እንድንወጣ ነግረውናል ብለዋል በተሰጠው መልስ ላይ አቋም ለመያዝ የመድረክ አመራር እንደሚሰበሰብ ከአቶ አስራት ጣሴ ለማወቅ ችለናል፡፡
መድረክ ህዳር 5 ቀን 2006 ዓ.ም መድረክ ለጠራው ሰልፍ አስተዳደሩ ከተደራራብ የስብሰባ ጫና የተነሳ የፖሊስ ሀይል ስለሌለኝ ጥበቃ ለማድርግ አልችልም በሚል እውቅና መንፈጉ ይታወቃል፡

Tuesday, December 3, 2013

A Call for Action by All Ethiopian Groups around the World

December 3, 2013For Immediate Release
The Global Alliance for the Rights of Ethiopians in Saudi Arabia (GAFRESA)
The Global Alliance for the Rights of Ethiopians in Saudi Arabia (GAFRESA) has been formed recently in response to the killings, gang rape, torture and other forms of crimes being committed against Ethiopian migrants in Saudi Arabia.

በአዲስ አበባ ከተማ ለ 2ተኛ ጊዜ ታላቅ ገድል ተሰርቶ አደረ፡፡

     Free our heroes በአዲስ አበባ ከተማ ለ 2ተኛ ጊዜ ታላቅ ገድል ተሰርቶ አደረ፡፡ FOH_News አዲስ አበባ ከተማ ሰኞ ማታ በድጋሚ ለ 2ተኛ ጊዜ በግራፊቲ ፅሁፎች አሸብርቃ አደረች፡፡ እሁድ ለሊት የተጀመረው በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ የሙስሊሙን የትግል መፈክሮች መፃፍ በትላንትናው እለትም ቀጥሎ ውሏል፤ትላንትና ሌሊት አለም ባንክ እና አካባቢዋ በግራፊቲ ጽሁፎች አሸብርቃ ማደሯን የ “FOH” ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በትላንትናው እለት በአለም ባንክ እና አካባቢዋ ላይ ተጽፈው ከነበሩት ጽሁፎች ውስጥ ድምፃችን ይሰማ፤ ኮሚቴው ይፈታ፤ህገ መንግስት ይከበር፤ትግሉ ይቀጥላል የሚሉት ዋነኞች እና ተጠቃሾቹ እንደነበሩ የ“FOH” ምንጮች ገልጸዋል፡፡፡ ከትላንት ወዲያ እሁድ እና በትላንትና እለት በርካታ ቦታዎች ላይ የተፃፉት የብዙሀኑን ትኩረት ከመሳባቸውም በላይ ህዝበ ሙስሊሙ ላቀረባቸው ስላማዊና ህገ -መንግስታዊ ጥያቄ ማንኛውንም መስዕዋትነት ለመክፈል ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየ ሆኖ አልፏል፡፡ መንግስት ጥያቄዎችን ከመመለስ ይልቅ በሀይል ለማፈን እየተሯሯጠ ባለበት በዚህ ሰዐት ህዝበ ሙስሊሙ የተለያዩ የሰላማዊ ትግል ስልቶችን በመጠቀም ትግሉን በሀይል ማፈን እንደማይቻል በመገኘት ላይ ሲሆን የመንገድ ላይ ፅሁፍ (Graffitis) የሰላማዊ ተቃውሞ መግለጫ መንገድ ሲሆን እሁድ ለሊትም በርካታ የመዲናችን አካባቢዎች ላይ ህዝበ ሙስሊሙን ለአዲሱ ሰለማዊ ትግል ራሱን እንዲያዘጋጅ የሚያስጠነቅቁ እና የሙስሊሙን ጥያቄዎች በሚያስተጋቡ ጽሁፎች አሸብርቃ ማዳሯ የሚታወስ ነው፡፡ ኮሚቴዎቻችን ተፈተው ጥያቄዎቻችንን ሳይሸራረፉ እስኪመለሱ ድረስ ትግላችን ይቀጥላል፡፡ ፍትህ ለኮሚቴው!! ፍትህ ለኢትዬጵያ ሙስሊም!! አላሁ አክበር!! ================================= የኢትዬጵያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ትግል 24 ሰአት የሚዘግበው ፔጅ ላይክ በማድረግ ይቀላቀሉ:: ==> https://m.facebook.com/freeourhero ==> https://www.facebook.com/freeourheroImage

Teachable Moments for the Ethiopian Diaspora?

December 1, 2013by Alemayehu G. Mariam
Stop the violence against Ethiopian migrant workers in Saudi Arabia now!
The ongoing human rights abuses of Ethiopian migrant workers in Saudi Arabia have triggered massive expressions of outrage against the regimes in Riyadh and Addis Ababa and unprecedented outpouring of concern and support in Diaspora Ethiopian communities. Over the past several weeks, enraged and brokenhearted by the shocking video clips of dehumanization of Ethiopians in Saudi Arabia, tens of thousands of Diaspora Ethiopians from Australia to the United States faced off cowering Saudi embassy and consular officials.  An estimated 6-7 thousand Ethiopians peacefully marched on the Saudi Embassy in Washington, D.C. to demand an immediate stop to the violence and abuse and to show their support and solidarity with their compatriots in Saudi Arabia. Tens of thousands rallied from Atlanta to Seattle. Thousands more marched throughout Europe.  Everywhere they carried banners and shouted, “Shame, shame, shame on you, Saudi Arabia!”The reactions of Diaspora Ethiopians and the regime in Ethiopia
The evidence of abuse and mistreatment of Ethiopian migrant workers in Saudi Arabia is incontrovertible. In its December 1, 2013 report, Human Rights Watch stated, “Ethiopian migrant workers have been the victims of physical assaults, some of them fatal, in Saudi Arabia following a government crackdown on foreign workers. Many workers seeking to return home are being held in makeshift detention centers without adequate food or shelter.”


የግለሰብ መብት ካልተከበረ የማንም መብት ሊከበር አይችልም::

  Post by Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
የግለሰብ መብት ካልተከበረ የማንም መብት ሊከበር አይችልም
የአንድን አገር ህዝብ የማይለወጠው የጋራ ማንነቱ ዜግነቱ ነው፡፡
     ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የግለሰቦች ጥርቅም እስከሆኑ ድረስ ኦነግ፣ ኦብነግ፣ ግንቦት ሰባት፣ ጽንፈኛ፣ አሸባሪ፣ ኪራይ ሰብሳቢ፣ ተላላኪ፣ ኒዮ ሌንራል፣…….የሚባሉት መለጠፊያዎች እየተሰጧቸው አሳራቸውን የሚበሉት ‹‹ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች›› ናቸው፡፡ ምንም ያህል ልዩነት ቢኖረው የአንድን አገር ህዝብ የማይለወጠው የጋራ ማንነቱ ዜግነቱ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ከሌሎች ህዝቦች ይልቅ የሚያመሳስሉን፣ የምንጋራቸው በርካታ እሴቶች አሉን፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ ኢትዮጵያውይነታችን (ዜግነታች) የጋራችን ነው፡፡ ብሄር፣ ብሄረሰብ፣ ህዝብ ተብሎ በጅምላ ዜግነት ሊሰጠው አይችልም፡፡ አንድ ሰው ኢትዮጵያዊ ለመሆን መደራጀት አይጠበቅበትም፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ግለሰብ ኦሮምኛ ተናጋሪዎችን ‹‹ኦሮሞ››፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩትን ግለሰብ አማርኛ ተናጋሪዎች ‹‹አማራ››፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ግለሰብ ሶማልኛ ተናጋሪዎን ‹‹ሶማሊ››…….እያሉ ነው

ኢትዮጵያውያንን ‹‹ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች›› በሚል አዲስ ማምነት የሚደረድሩን፡፡ ብሄር፣ ብሄረሰብ፣ ህዝብ የሚባለው ከግለሰቦች እንጅ ከምንም የመጣ አይደለም፡፡ የብሄር ብሄረሰቦች መብት መከበር ካለበት መጀመሪያ መቅደም የሚገባው የስሪታቸው የግለሰቡ መብት ነው፡፡ ‹‹ኦሮሞ፣ አማራ፣ትግሬ….› እየተባሉ የተቦደኑት ህዝቦች አንድ አይነት አይደሉም፡፡ እንዲያውም ኦሮምኛ ተናጋሪው ‹‹ኦሮሞ›› ከሚባለው ውጭ ከአማርኛ ተናጋሪው ጋር የሚጋራው በርካታ ማንነቶች ይኖሩታል፡፡ አማርኛ ተናጋሪው ‹‹አማራ›› ከተባለው ይልቅ ከኦሮምኛ ተናጋሪው ጋር የሚያመሳስሉት በርካታ ማንነቶች ይኖሩታል፡፡ ለአብነት ያህል ትግርኛ፣ አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ሶማሊኛ፣ ….ተናጋሪው ህዝብ ከቋንቋውም በላይ አንዱ የሌላውን ድንበር ተሸግሮ ከሌላኛው ቋንቋ ተናጋሪ ጋር

በእምነት፣ በፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ሌሎች ገመዶች ይገናኛል፡፡ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የአንድ ብሄር ሰዎች አይደሉም፡፡

የሙስሊሙ እንቅስቃሴ እንዲህ እስካሁን በጥንካሬ የዘለቀው በድንበር ተሸጋሪው ማንነቱ እንጅ በጠባብ ‹‹የብሄር›› ማንነት ታጥሮ አይደለም፡፡ ኦርቶዶክሶቹ፣ ፕሮቴስታንቶቹ፣ ካቶሊኮቹ በ‹‹ብሄር›› የታጠሩ አይደሉም፡፡ የአንድ ‹‹ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ…›› የእምነት፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ…መብቱ በግለሰብ ደረጃ ካልተጠበቀለት በስተቀር የ‹‹ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ…›› መብት ሊጠበቅ አይችልም፡፡ ችግሩ የ‹‹ብሄርና›› ሌሎች ማንነቶችን የሚጠቀሙ የፖለቲካ ቡድኖች ከግለሰብ ማንነት ይልቅ ጥቅል ማንነትን የሚያስቀድሙት ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ መሆኑ ነው፡፡ በ‹‹ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ፣ሶማሊ…….›› ስም በጅምላ ከመነገድ

ያለፈ ስለ እያንዳንዱ ህዝብ አያስጨንቀቃቸውም፡፡ 30 ወይንም 40 ሚሊዮን የአንድ ‹‹ብሄር›› ህዝብ በአንድ ጉዳይ ሊከፋ አይችልም፡፡ ቢያንስ ከገዥዎች ጋር ሆኖ የሚጠቀም አይጠፋም፡፡ ከፊሉን በእምነቱ፣ ከፊሉን በኢኮኖሚው፣ ከፊሉን እናከብርልሃለን በሚሉት ቋንቋው፣ ከፊሉን በነጻነቱ…. እያሉ ግን ሁሉንም ይጨቁኑታል፡፡ ሁሉንም ይጎዱታል፡፡ መስፈርቱ በብሄር ሳይሆን በግለሰብ ቢሆን ግን የሚድበሰበስ ነገር አይኖርም፡፡ ሁሉም የግለሰብ መብቶች እስከተከበሩ ድረስ የአገሪቱ ህዝብ መብት ይከበራል፡፡ የግለሰብ መብት ካልተከበረ ግን የማንም መብት ሊከበር አይችልም፡፡ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የግለሰቦች ጥርቅም እስከሆኑ ድረስ ኦነግ፣ ኦብነግ፣ ግንቦት ሰባት፣ ጽንፈኛ፣ አሸባሪ፣ ኪራይ ሰብሳቢ፣ ተላላኪ፣ ኒዮ ሌንራል፣…….የሚባሉት መለጠፊያዎች እየተሰጧቸው አሳራቸውን የሚበሉት ‹‹ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች›› ናቸው፡፡ with assisted by Getachew Shiferaw

መሪዎቻችን ዛሬ ፍርድ ቤት አለመቅረባቸው ታወቀ! (ድምፃችን ይስማ)

December 3, 2013ሰኞ ሕዳር 23/2006
በግፍ የታሰሩትን መሪዎቻችንን አስመልክቶ ፍርድ ቤት ለህዳር 23 ሰጥቶት የነበረው ቀጠሮ ለታህሳስ 3 መዛወሩ ይፋና መደበኛ ባልሆነ መንገድ መሰማቱ የመረጃ ክፍተት ፈጥሮ የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ከኮሚቴዎቻችን ጠበቆች አንዱ አቶ ተማም አባቡልጉ በሚዲያዎች ቀርበው ቀኑ ስለመተላለፉ የደረሳቸው ህጋዊ ይዘቱንና ፎርማሊቲውን ያሟላ መረጃ እንደሌለ መግለጻቸውም የቅርብ ቀናት ትውስታ ነው፡፡Ethiopian Musilms
የመረጃ ክፍተቱን ተከትሎ መንግስት ረጅሙ ቀጠሮ ሊደርስ ጥቂት ቀናት ሲቀሩት ይህን የመሰለ የቀጠሮ ለውጥ እንደሚኖር መደበኛ ባልሆነ መንገድ መግለጹ ጥቂት በማይባሉ አካላት ዘንድ ጥርጣሬ ፈጥሮ ነበር፡፡ ‹‹ይህን መሰል ድርጊት ህዝቡን ለማዘናጋት ያለመ ሊሆን ይችላል›› የሚል አስተያየትም ከበርካቶች ተሰንዝሯል፡፡

ዛሬ ህዳር 23 መሪዎቻችን ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ሊደረግ እንደሚችል አንዳንዶች አስተያየታቸውን ሰንዝረው የነበረ ቢሆንም በዛሬው እለት ግን ኮሚቴዎቻችን ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ እስካሁን ድረስ ግን አንዳችም ቀጠሮው መቀየሩንም ሆነ ወደታህሳስ 3 መዛወሩን የሚገልጽ ህጋዊ ፎርማሊቲ ያሟላ መረጃ ያልደረሳቸው መሆኑ መታወቁ የአገሪቱን የፍትህ ስርአት ይበልጥ ለትዝብት የሚዳርግ ነው፡፡ አንድ ታሳሪ ስለፍርድ ሂደቱ የተሟላና ህጋዊ ፎርማሊቲውን የጠበቀ መረጃ የማግኘት መብቱ በህገ መንግስቱ የተረጋገጠ ሆኖ ሳለ በተጨባጭ ግን እውነታው ሌላ መሆኑ የመሪዎቻችን የፍርድ ሂደት በፖለቲካዊ ውሳኔ የሚነዳ መሆኑን የሚያሳብቅ ሆኗል!

መንግስት የህዝብ ወኪሎችን ግልጽነት በጎደለውና ህገወጥ በሆነ የፍርድ ቤት ድራማ ማንገላታቱን ያቁም!!!
የህሊና እስረኛ መሪዎቻችን ማንገላታት ህዝበ ሙስሊሙን ማንገላታት ነው!!!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

Monday, December 2, 2013

ሰልፍ ብቻ በቂ ነው ወይ? አንድ መላ እንበል….ተርበዋል፣ ተጠምተዋል..እንድረስላቸው በግሩም ተ/ሀይማኖት

saudi-2-225x300
በሳዑዲ ለተከሰተው ሁኔታ..ለወገን ድምጽ ለማሰማት ይህ ሁሉ ኢትዮጵያዊ በየሀገሩ የሚያደርገውን ሰላማዊ ሰልፍ ሳይ ልቤ ቅቤ ጥጥት ያደርግና ሳይበቃው አንድ ሀሳብ ውስጤ ስውጥ ብሎ ይጦልማል፡፡ እንደገና ብልጭ ይልና ምላሽ ፍለጋ ያንከራትተኛል፡፡ ‹‹..እያደረግን ያለነው በቂ ነው ወይ? ድብደባውም ይቁም የሞቱትም ይታወሱ…በህይወት ያሉትስ ምን ሁኔታ ላይ ነው ያሉት? በተለያየ ቦታ ታጉረው ምግብ እጦት፣ ውሀ ጥም..ሌላም ሌላም ችግር አለባቸው፡፡ ሀገር ሲገቡም ማረፊያ ቦታ የሌላቸው ሞልተዋል…ይህን ሳስብ ምን ብናደርግ ይሻለናል?›› የሚለው ጥያቄ በጉልህ ውስጤ ተጽፎ ምላሽ ይናፍቃል፡፡ አምጬ አምጬ..ውስጤ ሲላወስ ቆይቶ መፍትሄ ፍለጋ ከማውቃቸው ጋር ሁሉ ስወያይ ቆይቼ አንድ ስለሺ የተባለ ወዳጄ ከወደ ሀገረ እንግሊዝ ሀሎ ብሎ አማካረኝ፡፡ ውስጤ ያሰበውን ስለነገረኝ ወይም ምን ማድርግ እንዳለብኝ እያሰብኩ የነበረውን አወጋሁት፡፡
 
የምናደርገው እንቅስቃሴ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ በእርግጥ በታሪካችን ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ህብረት አሳይተናል፡፡ ለነገሩ ኢትዮጵያዊያን ስንነካ እንደ ንብ ግር ብለን ህብረታችንን እናሳያለን፡፡ ግን ይህ ብቻ በቂ ነው ወይ? የገቢ ማሰባሰቢያ ማድረግ እና በማጎሪያ ቦታ ያሉትን ምግብ የምናቃምስበት ሁኔታ ቢፈጠር ጥሩ ነው፡፡ ሀገር የገቡትስ ቢሆን ነገ ጎዳና አናያቸውም ብሎ ማሰብ ሞኝነት ይመስለኛል፡፡ ከሳዑዲ ከመጡት ውስጥ የተወሰኑትን ለማናገር ሞክሬ ነበር፡፡ 12 

እና 13 አመት ሳዑዲ ሲኖር እናት አባቱ ሞተው ቤቱን ቀበሌ የተረከበበት ሁኔታ ያጋጠመው ልጅ እንዳለ..መግቢያ የሌለው በፊትም ቤተሰብ አጥቶ በባህር የወጣ አለ፡፡ ዛሬ የት ነው የሚገባው አግብቶ ወልዶ ያለም አለ ዛሬ የት ነው የሚመለሰው ቤተሰብ ላይ…ሁሉም ምላሽ የሌላቸው አሳሳቢ ነገሮች ናቸው፡፡ ገቢ አሰባስበን አንድ ነገር ማደድረግ እንዳለብን ይሰማኛል፡፡ እናንተ ምን ትላላችሁ? በውጭ ያሉ አርቲስቶችም ቢሆን የገቢ ማሰባሰብ ዝግጅት ቢያደርጉ በጣም በደስታ ብዙዎች እንደሚሳተፉ አምናለህ ወገን ለወገኑ የቻለውን ለማድረግ ወደ ኋላ አይልም የሚያሰባስበው ማጣት ይመስለኛል፡፡ እባካችሁ አንድ መላ እንበል….ተርበዋል፣ ተጠምተዋል..እንድረስላቸው

ሰበር ዜና፣ ግንቦት 7 ወያኔ ላቀረበው “እንደራደር” ጥያቄ መልስ ሰጠ

December 2, 2013

የወያኔ አገዛዝ በመልዕክተኞቹ በኩል ላቀረበው የ“እንደራደር” ጥያቄ ከግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ ምላሽ

ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ የገነባዉ ሥርዓት በከፍተኛ ችግሮች የተወጠረ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የመሪው ሞት በወያኔ መሀል ያስከተለው ቀውስ፤ የሕዝብ ሁለገብ ትግል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበት መሄድ የፈጠረበት ስጋት እና ምርጫ በደረሰ ቁጥር የሚደርስበት ጭንቀት መጨመር ተደማምረው ውጥረቱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ እያደረሱት መሆኑን የሚያሳዩ በቂ ምልክቶች አሉ። የእስካሁኑ ተሞክሮዓችን እንደሚያሳየው ወያኔ ውጥረት ሲበዛበትና መዉጪያና መግቢያዉ ሲጠፋዉ ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶችን “እንወያይ፣ እንደራደር” በማለት ለውጥረት ማስተንፈሻ ጊዜ የሚገዛ መሆኑን ነው። ሰሞኑን በወያኔ አገዛዝ መልዕክተኞች በኩል የደረሰንን “የእንደራደር” ጥያቄ ንቅናቄያችን በዋናነት ያየው ወያኔ እንደለመደው ድርድርን ለውጥረት ማስተንፈሻነት ለመጠቀም እየሞከረ መሆኑን ነው

Sunday, December 1, 2013

Saudi Arabia’s foreign labour crackdown drives out 2m migrants /The guardian/

ethjezanded

Ethiopian workers face hostility amid ‘Saudisation’ campaign to control foreign labour and get more Saudi citizens into work

Under the watchful eyes of Saudi policemen slouched in their squad cars along a rundown street, little knots of Ethiopian men sit chatting on doorsteps and sprawl on threadbare grass at one of Riyadh’s busiest junctions. These are tense, wary times in Manfouha, a few minutes’ drive from the capital’s glittering towers and swanky shopping malls.

አገር ማጣትንና ጥቃትን በኢሳት እንመክት !! እንግዳሸት ከኖርዎይ

215876_225725810894631_584578885_nምን ተሠራ ባዮች
እንዴት ተደፈርን እነ’ ትት ሰዎች
እንዴት ከረማችሁ – ዉላችሁ አደራችሁ ?
ትዕዛዝ የምትሰጡ – እናንት ግን የላችሁ
ምን ተሠራ ባዮች – ህዝብ የከሰሳችሁ
ክፍያ ሳትከፍሉ – ሰው የቀጠራችሁ
እጃችሁ ኪሳችሁ – የማይገባላችሁ
እትትን…እትትን ! ቀድማችሁ ያጮሃችሁ ፡፡
እንዴት ከረማችሁ ?

ኢሳት ባይኖር  በየአረቡ አገር በወገናችን ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ ማን ያሰማለት ነበር ?
ኢሳት ያንን ጣዕር ባያሰማ ኖሮ የወገንን ብሶት ለማስተጋባት ስር ነቅሎ የወጣው ህዝብ ከየት ይሰማ ነበር ?
ኢሳት ባይኖር ኖሮ የወያኔዎችን ዘረፋና ፣ አገርን ሸንሽኖ ለአረብና ፣ ለህንድ፣ መሸጥ ማን ለህዝባችን ያጋልጥ ነበር ?
ኢሳት ባይኖር ኖሮ በመረጃ እጦት ምክንያት ፣ የሚንገላታውን ህዝባችንን ማን ይደርስለት ነበር ?



Arab News: Saudi Investors Growing Food in Ethiopia to Provide Food Security for the KingdomImage

Saudis invest heavily in Ethiopian farm sector

ImageArab News | 29 May 2010

By K.S. RAMKUMAR

ዲፕሎማቱ በወገኖቻችን ስም ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ዶላር እና ሪያል ማግበስበሳቸውን ቀጥለዋል!

ዲፕሎማቱ በወገኖቻችን ስም ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ዶላር እና ሪያል ማግበስበሳቸውን ቀጥለዋል!
ትላንት ህይወቱን ከባእዳን ጥቃት ለመታደግ ሰንደቃላማው ወደ ተሰቀለበት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ የኮንቴነር መጠለያ በገቡ እህቶቻችን ላይ ግፍ እና በደል ሲፈጽሙ የኖሩት በሪያድ የኢትዮጵያ መንግስት ዲፕሎማቶች በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ወገኖቻችንን መርጃ በሚል ሽፋን ዶላርና ሪያል መሰብሰባቸውን አጠናክረው መቀጠላቸውን ማረጋገጥ ተችሎሏል። በሪያድ እና አካባቢው ማህበረሰብ የሚወገዙ እነዚህ የኢትዮጵያ መንግስት ዲፕሎማቶች ዛሬ መፉሃ ውስጥ ለተከሰተው እና ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ላለው ግፍ እና ስቃይ በቀጥታ መጠየቅ የሚገባቸው እና ከወገኖቻችን ስቃይ ይልቅ በወገኖቻችን ህይወት ለከበሩ የሰራተኛ እና ሰሪ አገናኝ ኤጀንሲ ባለቤት ለሆኑ የአረብ ደላላዎች ጥብቅና የቆሙ ወንጀለኞች መሆናቸውን የሚገልጹ ምንጮች ቀደም ሲል ወደ ኮሚኒትው መጠለያ ገብተው ከነብሩ እህቶቻችን መሃከል ለ3ቱ ሞት ተጠያቂ መሆናቸውን በማስረጃ አስደግፈው

ምሬታቸውን ይገልጻሉ ። በሳዲ አረቢያ የኢትዮጵያው ሰም አንባሳደር መሃመድ ሃሰን እና ዲፕሎማቱ ለእህቶቻችን ስቃይ እና መከራ ዴንታ የሌላቸው ከመሆናቸውም በላይ በተለያዩ ወቅቶች በአሰሪዎቻችን ተበድለናል ድረሱልን አጋር ሁኑንን ብለው ብሶውታቸውን ሊያሰሙ ወደ ኤንባሲ የመጡ እቶቻችን ሰበአዊ ክብር በሚንኩ ቃላቶች ሲሳድቡ ሲያዋርዱ የነብሩ መሆናቸውን በማስታወስ እንዚህ ዲፕሎማቶች ዛሬ ለህዝብ አዛኝ እና ተቅርቋሪ መስለው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ት/ቤት በሚገኙ ተላላኪዎቻቸው አማካኝነት ባዋቀሩት ኮሚቴ ከእስት ወደ ረመጥ። በተዘፈቁ ወገኖቻችንን ስም ህዝብን ለመመዝበር እያደረጉ ያለው እሩጫ በምንም ማመዛኛ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ይናገራሉ።

በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እንደተቋቋመ የሚነገርለት ይህ የእርዳታ አሰባሳቢ ኮሚቴ ቀደም ሲል በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ውስጥ የሚገኙ የነበሩ 12 ነስፈስ ጡሮችን ጨምሮ ከ 200 የሚበልጡ ወገኖቻችን ከስቃይ እና መከራ በማዳን በሚል ሽፋን « የአይሮፕላን » ትኬት መግዣ ቀደም ብሎ 1 መቶሺህ ሪያል አሊያም ግማሽ ሚልዮን ብር መሰብሰቡን በማውሳት የገበያ ግርግር ለምን ያመቻል እንዲሉ የመንፉሃውን ሁከት ተከትሎ ዲፕሎማቱ እህቶቻችን ከኮሚኒተ ግቢ በአውቶብስ አስጭነው እስካሁን በውል ወዳልታወቀ የሳውዲ መግስት ወዳ ዘጋጀው ጊዘያዊ መጠለያ ጣቢያ ወስደወ በመጣል የተጠቀሰውን ግንዘብ ዲፕሎማቱ የት እንዳደርሱት እንደማይታወቅ የሚናገሩ ምንጮች በወገኖቻችን ስም የሚደረግውን የማጭበርበር ተግባር ህዝቡ ከወዲሁ መቃወም ማክሸፍ እንድሚገባው አብክረው ገልጸዋል።
Ethiopian Hagere ሳውዲ አረቢያ ጅዳ በዋዲ

Saudi Arabia: Labor Crackdown Violence (Human Rights Watch)

Human Rights Watch spoke to five Ethiopian migrant workers in Saudi Arabia.

November 30, 2013
Ethiopian Workers Allege Attacks, Poor Detention Conditions
(Beirut) –  Ethiopian migrant workers have been the victims of physical assaults, some of them fatal, inSaudi Arabia following a government crackdown on foreign workers. Many workers seeking to return home are being held in makeshift detention centers without adequate food or shelter.
Human Rights Watch spoke to five Ethiopian migrant workers in Saudi Arabia. Four Ethiopians in Riyadh told Human Rights Watch that the attacks began after November 4, 2013, when authorities resumed a campaign to arrest foreign workers who they claim are violating labor laws.