
በነ እስክንድር ነጋ … የእስር ፍርድ ምክንያት በማድረግ ስለ ጉዳዩ አስተያየት እንድሰጥ የተለያዩ የፌስቡክ
ጓደኞቼ ሲወተውቱኝ ከርመዋል (የቅርብ ጓደኞቼ ግን ዝምታን መምረጥ እንዳለብኝ መክረውኛል)። አስተያየቴን እንድገልፅ
የገፋፉኝ ጓዶች በቁጥር ብዙ ቢሆኑም ምክንያታቸው ወይ ዓላማቸው ግን የተለያየ ነው።
ብዙ ግዜ አስተያየቴን እንድሰጥ ከወተወቱኝ ሰዎች አብዛኞቹ የኢህአዴግ ደጋፊዎች (በፌስቡክ በሚፅፉት መሰረት)
ናቸው። ለምን በነ እስክንድር ነጋ ዙርያ አስተያየት እንድሰጥ ገፋፉኝ? እኔን “ማኖ ለማስነካት” ታስቦ ነው። እኔን
“ማኖ ማስነካት” እንዴት ይቻላል? ከሰዎች ጋር በማጣላት ነው። እንዴት ማጣላት ይቻላል?