
Friday, June 7, 2013
The Anguish of Higher Education Students in Ethiopia
Academic activities such as studying, teaching, inventing, leading,
a
dministrating and other responsibilities in a university or college
require at a minimum academic freedom. Unfortunately, however, academic
freedom in higher education institutions of Ethiopia is drier than the
Sahara desert. Ethiopians who have been part of these institutions as a
student, teacher, or any other workers have been grilled by this desert.
Although, no one can tell better than we, the victims of this inferno;
national and international human rights organizations have documented
the absence of freedom of expression, association, and assembly in the
colleges and Universities of Ethiopia(1).

፨፨፨የዘራነውን እናጭዳለን!፨፨፨
፨፨፨የዘራነውን እናጭዳለን!፨፨፨
ሰሞኑን አብዛኛው ኢትዮጵያ ፌስቡከኛ ግብፅ ላይ ሲሸልልና ሲፎክር ነው የሰነበተው "አዝምቱን አታስጨርሱንም" ያሉም
አልጠፉም። የዛሬዋ "ግብፃችን" ደግሞ "ቤተልሄም አበራ" የተባለች ወጣት ናት "ኢትዮጵያን አዋረደች" ተብላ
ውግዘት እየደረሰባት ነው የአገሬ ፌስቡከኛ ሆየ "መብቷ ነው" እንዲሁም "ኢትዮጵያን አትወክልም ይች ሀገር አሰዳቢ"
እያለ ይነታረካል።የልጅቷን የብክነት ቪዲዮን እኔም እንዳየሁት ያማል ያበሳጫል ነገር ግን "ኢትዮጵያ መዋረድ" ዛሬ
የጀመረች ይመስል "የኢትዮጵያን ውርደት" በሙሉ ቤተልሄም ጫንቃ ላይ ማሳረፍ አግባብ አይመስለኝም ።እጅግ ቢመረንም
እንዋጠው "ቤተልሄም የዚህ ማህበረሰብ ውጤት ናት"። አይናችንን ጨፍነንና ጆሮችንን ደፍነን አላይም አልሰማም
ካላልን በስተቀር ኢትዮጵያችን "በወሲብ አብዮት" መናጥ ከጀመረች እኮ ቆየች!የግል ኤፍኤሞች ግራ የገባቸው ጋዜጠኞች
ከእኛ በተሰበሰበ ቀረጥ የሚተዳደሩት ሚዲያዎች ሳይቀር ሌት ተቀን የሚለፉት ትውልድን ቀራጭ በሆኑ ፕሮግራሞች እኮ
አይደለም ሁሌም የሚሰብኩት ስለልቅነት ነው በግልፅነት ሽፋን አፈንጋጭ የወሲብ በሀል ነው ሀገራችንን
የወረራት።አዲስአበባ እና ብዙ የክልል ከተሞች ሲናጡ የሚያድሩት በወሲብ ገበያ እንደሆነ እረሳነው!? እለት እለት
ሀገሪቷን እያጥለቀለቁ ባሉት ጫት ቤቶች፥ማሳጅ ቤቶችና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እራቁት ዳንስ ቤቶች ምን ሲሰራ
እንደሚዋልና እንደሚታደር ለማንም ግልፅ ነው።በገፅታ ግንባታ ስም ሀገራችን እንደ ታይላንድ የአፈንጋጭ "የወሲብ
ቱሪስቶች" መናሃሪያ ከሆነች ሰነበተች።ሌላውን እንተወውና ፌስቡክ እንኳን "ልቅ ወሲብ" ያሰከራቸው ስንት የመከኑ
ኢትዮጵያውያን እንዳሉ ለመታዘብ ቀላል ነው አስታውላችው ካያችው ብዙ የፌስቡክ ፍሬንድ ያሏቸው፣ገጻቸው በብዙ ሰው
ላይክ የተደረገና ብዙ አባላት ያሏቸው ግሩፖች ቁምነገር የሚያወሩ ስለፖለቲካዊ ለውጥ የሚያወሱት ሳይሆኑ ነፃነትን
ሳይሆን ልቅነትን የሚያስፋፉት "አፈንጋጭ የወሲብ አብዮተኛ" የሆኑት ኢትዮጵያውያን ናቸው ።በየውርደታችን ከመጯጯህ
ሰከን ብለን ለምን ተዋረድን ብለን እንጠይቅ።በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ለዜጎቹ የሚቆረቆር መንግስት ፤ ለትውልዱ
ስብዕና የሚታትር የሀይማኖት አባት፤ ለዜጎቹ ጠቃሚ መረጃ የሚሰጡ የሚዲያ ተቋም ወዘተ የሉንም አንድ ታዳጊ ወጣት
ቀና ብላ/ብሎ የምታየው/የሚያው አርእያ በሀገራችን ከጠፋ ሰነበተ።ቆም ብለን ልቦና ሰጥቶን የሀገራዊ ችግሮቻችን
ምንጭ ለይተን ካላወቅንና መፍትሄ ካልፈለግን ነገም እንደ ቤቲ ያሉ ኢትዮጵያውያን የዘራነውን ያሳጭዱናል እንደ
ሀገርም የያዝነው የቁልቁለት ጉዞ እናጠናክራለን።
Tuesday, June 4, 2013
ምከረው ምከረው እምቢ ካለ ሞክረው…
Subscribe to:
Posts (Atom)