Thursday, May 16, 2013

ልቅ የሆነ የሙስና ግንኙነት…

melaku_fenta
ልቅ የሆነ የሙስና ግንኙነት… (ትንሽ ወግ)
አቶ መላኩ ፈንታ መንግስት የሚያውቀው በሽታ አለብኝ እና በዋስ ልፈታ፤ አሉ አሉ፤…
እኔ ደግሞ እንዲህ አልኩ፤
ምን ነካዎ አቶ መላኩ፤ መንግስት በሚያውቀው በሽታዎ ነውኮ ዘብጥያ የወረዱት፤ እርግጥ ነው ይህንን በሽታ ከየትም አላመጡትም፤ ከመንግስትዎ ጋር ባደረጉት ጥንቃቄ የጎደለው እና ልቅ የሆነ የሙስና ግንኙነት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ እርግጥ ነው መንግስታችን ራሱም የዚህ በሽታ ተጠቂ መሆኑ እሙን ነው፡፡ እርግጥ ነው በማራዘሚያ ብዛት እንጂ ሁሉም ባለስልጣኖቸች የዚህ ህመም ሰለባ መሆናቸውም ግልጽ ነው፡፡

Wednesday, May 15, 2013

ዲያስፖራው አምርሯል!

ዲያስፖራው አምርሯል!

ዲያስፖራው አምርሯል!

መንግስታችን ለአመት በዓል መዋያ ነው መሰል ሰሞኑን በየሀገራቱ እርጥባን የሚጠይቁ ሰዎችን አሰማርቷል፡፡ አብዛኛዎቹ ቦታዎችም …እግዜርም የስራህን ይስጥህ እኛ ግን የምንሰጥህ የለንም… ብለው እያባረሩት ነው…! ትላንት በኖርዌይ ኦስሎ ለሁለተኛ ጊዜ እንዲሁም ዛሬ ደግሞ በሳንዲያጎ ደጅ ጥናት የሄዱ የኢህአዴግ ባለስልታናትን ክፍ ብለዋቸዋል፡፡ ዲያስፖራው አምርሯል! መንግስታችን ግን… ልመና ይቁም…  የሚለን ዘርፉን ብቻውን መቆጣጠር ፈልጎ ነው እንዴ…!?

ማመልከቻ፤ ኢህአዴግ እንድትታሰር ስለመጠየቅ

eprdf-logoእኔ አመልካች ስሜ ከበስተመጨረሻ ባይገለፅም ግድ የለም፤ የማመለክተው ፍሬ ሀሳብ ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ ኢህአዴግ የተባለች የአራት ጥምር ፓርቲዎች ግንባር እንዳለች ይታወቃል፡፡ ግንባሯ ስሟ ግንባር ሲሏት ትንሽ ትመስላለች እንጂ በተለይ ሀብት ንብረቷን እንቁጠረው ብንል ማለቂያም የለው እና ግንባር ብቻ ሳትሆን ፊት፤ ፊት ብቻም ሳትሆን ጀርባ፤ ጀርባ ብቻም ሳትሆን ዳሌ ናት እንጂ ግንባር የሚለው ብቻ አይበቃትም፡፡ (በቅንፍም ለወደፊትም “ኢህአዴግ” የሚለው ስሟ አይስተካከላትምና  ”ኢህአዴዳ” ብትባል የሚል ሀሳብም አለኝ)
ለማንኛውም ግንባሪቱ፤ የሞጃዎች ሞጃ፤ የባለጠጎች ባለጠጋ፤ የቱጃሮት ቱጃር ናት፡፡

የባህር ዳሩ ገዳይ ጉዳይ፤ ኮስተር ያለ ወሬ

የባህር ዳሩ ገዳይ ጉዳይ፤ ኮስተር ያለ ወሬ

935211_10151657933187065_2091855276_nየፌስ ቡክ ወዳጆቼን ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና የኢትዮጵያ መንግስት የባህር ዳር ግድያን አስመልክቶ ምን ብለው ይሆን… የሚለውን ጠይቄ ነበር፡፡ ብዙዎቹ ያመለጠኝን ሲነግሩኝ ሌሎቹም ደግሞ በቀጣይ ኢቲቪ በጉዳዩ ላይ ሊያወራ የያዘውን ቀጠሮ ነገሩኝ፤ እኔም አድብቼ ጠብቄ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን አየሁት፤

እንደተለመደው ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሆነ የማጭበርበር ነገር ይታይበታል፡፡ ለምሳሌ የገዳዩ አስከሬን ከአባይ ወንዝ ውስጥ ሰጥሞ በመከራ ነው ያገኘነው ሲሉ አሰማን፡፡ የገዳዩን ፎቶ እንዳየነው ግን ውሃ የነካውም አይመስልም፡፡ ታድያ ጋዜጠኛው… ማንም ሊጠይቅ የሚችለውን ጥያቄ መግለጫ የሚሰጡትን ሰውዬ  ለምን አልጠየቀም ብለን ብንጠይቅ፤  የሆነ ማጭበርበር እንዳለ እንረዳለን፡፡

Tuesday, May 14, 2013

የአንደኛ ዓመት ማስታወሻ፤ ሽቅቡም ቁልቁሉም!

ዞን ዘጠኝ እንዴት ተመሠረተ? ለምን ተመሠረተ? ለምን ዞን ዘጠኝ ተባለ?… እና ሌሎችም ተመሳሳይ ጥያቄዎች ባሳለፍነው ዓመት በዞን ዘጠኝ የፌስቡክ ገጽ በብዛት ያስተናገድናቸው ጥያቄዎች ናቸው፡፡ እነሆ ‹ዞን ዘጠኝ› የሚለውን ስም አውጥተን ጦማሩን (ብሎጉን) የፈጠርንበትን ቀን (ግንቦት 5/2004) አንደኛ ዓመት በማስመልከት ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት እንሞክራለን፡፡
በሊባኖስ ቤይሩት በአሠሪዎቿ ድብደባ የደረሰባት የዓለም ደቻሳ ሞት ብዙ የማኅበራዊ አውታር ኢትዮጵያውንን አስቆጣ፡፡ ይህ ምሬት ፌስቡክን እንደማህፀን ተጠቅሞ ‘ደጉ ኢትዮጵያዊ’ የተሰኘውን ቡድን ወለደ፡፡ በአጋጣሚ የተወሰኑ የዞን ዘጠኝ አባላት እነዚህ ስብስብ ውስጥ ተገኘን፤ እንዲሁ አጋጣሚ! አንዳንዱ ለሰላምታ፣ አንዳንዱ ሲያልፍ ሲያገድም አንዱ ደግሞ የዓለም ጉዳይ አስቆጭቶት፡፡

Monday, May 13, 2013

የህዝብ አስተያየት፣ የሙስና እስርን አስመልክቶ

ሰሞኑን በወያኔዎች ቤት ብዙ ነገር እየሰማን ነው ። በተለይ ከሙስና ጋር በተያያዘ ጉዳይ ። ነገር ግን በዚህ ሙስና በሚባለው ጉዳይ የሚሰራ አንድ ድርጅት አለ ” ጸረ ሙስና ” የሚባለው ማለት ነው ። ይህ መስሪያ ቤት ከወያኔ የፋሽስት ስርዐት ለማፈንገጥ የሚሞክሩን ወይም ከዚህ የማፊያ ቡድን የተለየ ሃሳብ አመጣለሁ ለሚሉትን ወደ ከርቸሌ መወርወሪያ መስመር ነው።


ነገሩ እንዲህ ነው የወያኔ ባለስልጣን ሆኖ በሙስና ያልተዘፈቀ የለም ። ይህም መረጃ በጸረ ሙስና ቢሮ እጅ ይገኛል ። ወያኔ ማሰር ሲፈልግ በስልጣን እያሉ የተጨማለቁበትን የሙስና ጉዳይ መዘዝ በማድረግ ግለሰቦቹን ለማሸማቀቅ ብሎም ሌሎች ሙሰኞችን አድርጉ የተባሉትን ህሊናቸውን ሺጠው ህዝብን ማሰቃየትን ሳያቅማሙ እንዲቀጥሉ ለማስጠንቀቅ የተመሰረት መስሪያ ቤት ነው ።

ሰበር ዜና፣ በባህር ዳር ከተማ ከ16 በላይ ሰዎች ተገደሉ

እሁድ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ገደማ የአባይን ድልድይ እንዲጠብቅ የተመደበ የፌደራል ፖሊስ አባል እያነጣጠረ ሰዎችን ሲገድል አምሽቷል። የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከ16-18 ንጹሀን ዜጎች ያለምንም ምክንያት ከፌደራል ፖሊሱ በተተኮሱ ጥይቶች ተገድለዋል።
የፌደራል ፖሊሱ እያነጣጠረ ንጹሀን ዜጎችን ሲገድል በአቅራቢያው የነበሩ የብአዴን ጽ/ቤት ጠባቂዎች እርምጃ ከመውሰድ ተቆጥበው እንደቆዩ በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች ገልጸዋል።
የብአዴን ጽ/ቤት ጠባቂዎች በግለሰቡ ላይ አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ የዜጎችን ህይወት ሊታደጉ ሲገባቸው ይልቁኑም ሰውየውን ለመያዝ በመፈለግ ላይ ትኩረታቸውን በማድረግ ግለሰቡ ያገኘውን ሰው እየተኮሰ ሲገድል እንደነበር በአቅራቢያው የነበሩ ሰዎች ተናግረዋል።
ሁኔታው በባህር-ዳር ከተማ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ መረበሽ መፍጠሩ ታውቋል። የከተማው ነዋሪዎች የሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ የተካሄደውን ኢሰብአዊ ድርጊት ለማውገዝ እንደሚፈልጉም ዜናውን ያቀበሉን የባህር-ዳር ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል።