አሌክስ ሲስል እኮ ይስላል አይገልጸውም… ይቀርፀዋል፡፡ አረ አይበቃውም… ያበጀዋል፡፡ ቆይ ሌላ ቃል… ይፈለግ… ይቀምረዋል፡፡ አረ በፍጹም አልተገለፀም…
እስቲ ቃል አዋጡ
እኔስ ቃልም የለኝ
እፁብ ነው ድንቅ ነው
ብለው አልበቃ አለኝ…
ቆይማ የሆነ ቀን አድባራችንን ተለማምጠን በተሟላ ግጥም እናሞካሸዋለን እንጂ ይሄን የመሰለ ስዕልማ ኮምኩመን ፀጥ አንልም!
ለማንኛውም… በምስጋናዎቹ መሃል፣ በወቀሳዎቹም ጣልቃ፣ በሀዘናችን ውስጥ በጭቅጭቃችን ላይ በዝምታችን ሁሉ ሳቀር ድል ለዋሊያ ድል ለብሄራዊ ቡድናችን እንላለን!!!
No comments:
Post a Comment