Saturday, October 12, 2013

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ጎፋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በመገኝት ጸሎት አደረጉ


ff (አንድ አድርገኝ ጥቅምት 2 2006 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ነገ ጥቅምት 3 2006 ዓ.ም ከናይጄሪያ ብሐየራዊ ቡድን ጋር ላለባቸው ወሳኝ ጨዋታ ትላንትና አርብ አመሻሹ ላይ ጎፋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በመሄድ አምላክ ድሉን እንዲያጎናጽፋቸው ጸሎት አድርገው ወደ ማረፊያቸው ኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል ተመልሰዋል ፡፡ ከሳምንት በፊት ዴቪድ ማርክ የተባሉ የናይጄሪያ ሴናተር መላው ናይጄርያዊ ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረገውን ጨዋታ ለማሸነፍ እንዲያበረታታ በካቶሊክ አማኞች ለ9 ቀናት የሚዘልቅ የፀሎት ስነስርዓት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበው ነበር፡፡ በአሁኑ ሰዓት በርካቶች በአዲስ አበባ እና በበርካታ ክልል ከተማዎች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን ማሊያ ፤ ስካርፍ እና እጅ ላይ የሚደረጉ ማጌጫዎችን በመግዛት ቡድኑን ለመደገፍ ከፍተኛ ዝግጅቶችን እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ባሳለፍነው የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሐየራዊ ቡድን አንዲት ጎልን ብቻ አግብቶ ወደ ሀገሩ ሲመለስ የጎሏ መገኛ የቅዱስ ገብርኤል ወዳጅ 19 ቁጥር በመልበስ የሚጫወተው አዳነ ግርማ መሆኑ አይረሳም፡፡
የኢትዮጵያ አምላክ ይርዳችሁ

No comments:

Post a Comment