እሁድ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ገደማ የአባይን ድልድይ እንዲጠብቅ የተመደበ የፌደራል ፖሊስ አባል እያነጣጠረ
ሰዎችን ሲገድል አምሽቷል። የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከ16-18 ንጹሀን ዜጎች ያለምንም ምክንያት ከፌደራል
ፖሊሱ በተተኮሱ ጥይቶች ተገድለዋል።
የፌደራል ፖሊሱ እያነጣጠረ ንጹሀን ዜጎችን ሲገድል በአቅራቢያው የነበሩ የብአዴን ጽ/ቤት ጠባቂዎች እርምጃ ከመውሰድ ተቆጥበው እንደቆዩ በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች ገልጸዋል።
የብአዴን
ጽ/ቤት ጠባቂዎች በግለሰቡ ላይ አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ የዜጎችን ህይወት ሊታደጉ ሲገባቸው ይልቁኑም ሰውየውን
ለመያዝ በመፈለግ ላይ ትኩረታቸውን በማድረግ ግለሰቡ ያገኘውን ሰው እየተኮሰ ሲገድል እንደነበር በአቅራቢያው የነበሩ
ሰዎች ተናግረዋል።
ሁኔታው በባህር-ዳር ከተማ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ መረበሽ መፍጠሩ ታውቋል። የከተማው
ነዋሪዎች የሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ የተካሄደውን ኢሰብአዊ ድርጊት ለማውገዝ እንደሚፈልጉም ዜናውን ያቀበሉን
የባህር-ዳር ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
No comments:
Post a Comment