ሰሞኑን በወያኔዎች ቤት ብዙ ነገር እየሰማን ነው ። በተለይ ከሙስና ጋር በተያያዘ ጉዳይ ። ነገር ግን
በዚህ ሙስና በሚባለው ጉዳይ የሚሰራ አንድ ድርጅት አለ ” ጸረ ሙስና ” የሚባለው ማለት ነው ። ይህ መስሪያ ቤት
ከወያኔ የፋሽስት ስርዐት ለማፈንገጥ የሚሞክሩን ወይም ከዚህ የማፊያ ቡድን የተለየ ሃሳብ አመጣለሁ ለሚሉትን ወደ
ከርቸሌ መወርወሪያ መስመር ነው።
ነገሩ እንዲህ ነው የወያኔ ባለስልጣን ሆኖ በሙስና ያልተዘፈቀ የለም ። ይህም መረጃ በጸረ ሙስና ቢሮ እጅ ይገኛል ። ወያኔ ማሰር ሲፈልግ በስልጣን እያሉ የተጨማለቁበትን የሙስና ጉዳይ መዘዝ በማድረግ ግለሰቦቹን ለማሸማቀቅ ብሎም ሌሎች ሙሰኞችን አድርጉ የተባሉትን ህሊናቸውን ሺጠው ህዝብን ማሰቃየትን ሳያቅማሙ እንዲቀጥሉ ለማስጠንቀቅ የተመሰረት መስሪያ ቤት ነው ።
ይህ “ጸረ ሙስና “የሚባለው መስሪያ ቤት እንደ ስሙ ቢሆን አፈ ጉባኤው አባዱላ ገመዳ ታራሚ መሆን ሲጠበቅበት ለሙስና ክስ ምስክር ይሆን ነበር??? ሌላው የሙስና እናት አዜብ መስፍን እያለች ባጃጅ ሙሰኞች ቀድመው ይያዙ ነበር??? ለነገሩ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሁሉም የዘራውን ያጭዳል ! ለሁሉም ጊዜ አለው!
የባለስልጣናት ሚስቶችን፣ ዘመዶችና ወዳጆችን በተቋሞቻቸው ውስጥ በማይመጥኑት ሃላፊነት በመመደብ፣ ከተለያዩ የማማለያ ሽልማቶች ጋር ከፍተኛ ደሞዝ በመክፈል፣ አንዳንዴም ውጪ አገር ድረስ የህክምና ወጪ በመሸፈን ሰበብ የአገሪቱን የአመራር በትር ጨብጠው አገሪቱን እያለቡ ያሉት ወገኖች በይፋ እንደሚታወቁ የሚገልጹ ክፍሎች “አሁን ተጀመረ የተባለውና ይፋ የተደረገው የሙስና ትግል እነዚህን ክፍሎች ብብቱ ስር ይዞ የሚቀጥል ከሆነ ከቀልድ አይዘልም” ሲሉ ጥርጣሬያቸውን ያስቀምጣሉ። ጎልጉል
ሙስናን በስንጥር! ከዚያስ?
ዋናዎቹ “ሌቦች” በሞቀው ሆቴላቸው አሉ!!
በቀረጥ፣ በሙስናና ባለስልጣናትን የንግድ ሸሪክ በማድረግ ኢትዮጵያን እየጋለቡዋት ያሉ “ባለሃብቶችና
አሽከሮቻቸው” እስካልተነኩ ድረስ ኢህአዴግ በሙስና ላይ የጀመረውን ትግል ሙሉ ሊያደርገው እንደማይችል ተገለጸ።
ጅማሮው የችግሩ ቁልፍና እምብርት በሆነው ተቋም ላይ መሆኑ የሚደነቅ እንደሆነ የሚገልጹ ክፍሎች ደግሞ ድሩ
ያልተበተበው የለምና የመጨረሻው አካሄድ ወዴት እንደሚያመራ ለመገመት ቢቻልም ጅምሩ ይገፋል የሚል ጥርጣሬ እንዳላቸው
አስታውቀዋል።የባለስልጣናት ሚስቶችን፣ ዘመዶችና ወዳጆችን በተቋሞቻቸው ውስጥ በማይመጥኑት ሃላፊነት በመመደብ፣ ከተለያዩ የማማለያ ሽልማቶች ጋር ከፍተኛ ደሞዝ በመክፈል፣ አንዳንዴም ውጪ አገር ድረስ የህክምና ወጪ በመሸፈን ሰበብ የአገሪቱን የአመራር በትር ጨብጠው አገሪቱን እያለቡ ያሉት ወገኖች በይፋ እንደሚታወቁ የሚገልጹ ክፍሎች “አሁን ተጀመረ የተባለውና ይፋ የተደረገው የሙስና ትግል እነዚህን ክፍሎች ብብቱ ስር ይዞ የሚቀጥል ከሆነ ከቀልድ አይዘልም” ሲሉ ጥርጣሬያቸውን ያስቀምጣሉ።
አትራፊ የሆኑ የህዝብና የአገር ተቋማትን ወደ ግላቸው ያለ ክፍያ፣ ያለ ተመጣጣኝ ዋጋ፣ በተጭበረበረ ጨረታና አሰራር ወደ ግላቸው በማዞር አቶ መለስ “ተራው ህዝብ” በማለት በሚጠሩት ህዝብ ትከሻ ላይ እንዳሻቸው የሚዘሉትን “የሙስና አባቶችን” መታገል የማይችል የጸረ ሙስና ቀረርቶ ከተራ የፖለቲካ ልዩነት የዘለለ መነሻና መድረሻ ሊኖረው እንደማይችል እነዚሁ ወገኖች ይናገራሉ።
ሰሞኑን የመንግስት፣ የግል መሰል የድርጅት፣ የግል፣ የድረገጽ መገናኛዎች የተቀባበሉት ዜና የፌዴራሉ የጸረሙስናና የስነምግባር ኮሚሽን ይፋ ያደረገው የባለስልጣናት፣ የታዋቂ ነጋዴዎች እንዲሁም ተባባሪና የሙስናው ተዋናይ ናቸው የተባሉ አስራ ሶስት ሰዎች ስም የተጠቀሰበት እስር ነው። ይህንኑ ዜና በማድነቅ ጅምሩን የሚያበረታቱ ክፍሎች በበኩላቸው “ቢዘገይም፣ ችግሩና ንቅዘቱ እንዳለ ያደባባይ ሚስጥር ቢሆንም አሁንም አልረፈደምና ኢህአዴግ ለጀመረው የሙስና ትግል ድጋፍ መስጠት አግባብ ነው” ባይ ናቸው።
ኢህአዴግ “ገምተናል” በማለት ቃል ሳይመርጥ ራሱን ከፈረጀበት የሙስና አዘቅት አንድ ሁለት እያለ ዘመቻ መጀመሩ ሊበረታታ እንደሚገባ የሚጠቁሙ ክፍሎች “በአንድ ጀንበር ተዓምር መጠበቅ ከተራ የማንቋሸሽና ሁሌም የመቃወም አዝማሚያ ላይ የመኖር ያህል ያስቆጥራል። በርካታ ችግሮች ቢኖሩም ጅማሬው ወዴት እንደሚያመራ አይታወቅምና በትዕግስት መከታተሉ የተሻለ ይሆናል” ሲሉ በቀጣይ ርምጃው እየሰፋ እንደሚሄድ ተስፋቸውን ይገልጻሉ። ዜናውን ያቀረበው ኢቲቪን ግን ይወቅሳሉ።
'
ኢቲቪ ዜናውን ሲያውጅ አቶ መለስን ካሉበት ሰፈር ቀስቅሶ በዋቢነት ማቅረቡ ከዜናው በላይ አስገራሚ እንደሆነ አስተያየት የተሰጠው አፍታም ሳይቆይ ነበር። አቶ መለስ “በተከበረው ፓርላማ” ፊት “ቁርጠኛ” በማለት የሾሟቸውን ባለስልጣናት “ሌቦች፣ ተስፈኞች” እያሉ ሲያበሻቅጡ በማሰማት የጸረ ሙስና ኮሚሽን “በከባድ የሙስና ወንጀል” ስላሰራቸው ባለስ
“… መንግሥት አንድ እጁን ታስሮ ነው የሚታገለው። እጁም እግሩም ያልታሰረው ተራው ህዝብ ነው። ስለዚህ ተራው ህዝብ በዚህ ትግል ውስጥ ሊሳተፍ ይገባል” በማለት ለተራው ምስኪን ኢትዮጵያዊ ሲያነቡለት የሚያሳይ ቅንጫቢ ወሬ በማሰማት የባለስልጣኖቹን መታሰር የመለስ ህልምና ትግል ውጤት ለማስመሰል የሞከረው ኢቲቪ፣ ጅማሬው ሊመሰገን የሚገባውን ተግባር እንዳደበዘዘው ነው አስተያየት ሰጪዎች ለጎልጉልየገለጹት። ዜናው አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ “… ዛሬውኑ ማስረጃ በመያዝ ለጸረሙስና ኮሚሽን አቅርቡ፣ እኔው እራሴ ተከታትዬ አስፈጽማለሁ” በማለት አቶ መለስን ተከትለው ቃል ሲገቡ አሰምቷል።
ከሳምንት በፊት የፌደራሉ ጠቅላይ ኦዲተር ያቀረበው አስገራሚ ሪፖርት ያንገበገባቸው ወገኖች “ምን እየተደረገ ነው? መንግስት አለ ወይ?” በማለት ጥያቄ አቅርበው እንደነበር የሚያስታውሱ “የጠቅላይ ኦዲተር ባለስልጣን በየዓመቱ የሚያቀርበው ሪፖርት አስገራሚና አሳዛኝ ቢሆንም የዘንድሮው ግን አስደንጋጭ ነው” የሚሉት አስተያየት ሰጪ፣ ሪፖርተርና ሰንደቅ ጋዜጣ ያቀረቡትን ዜና በዋቢነት ያቀርባሉ።
- 1.4ቢሊዮን ብር ያልተወራረደ ሒሳብ አለ
- 313.6 ሚሊዮን ብር ዕዳ ሳይመልሱ የተሸጡ ድርጅቶች አሉ
- 897.5 ሚሊዮን ብር ሕጋዊ ያልሆነ ክፍያና ወጪ ተደርጓል
- ያልተወራረደው 1.4 ቢሊዮን ብር በ57 የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የታየ ነው
- 15 ድርጅቶች ወይም መሥሪያ ቤቶች ከልዩ ልዩ ገቢ ማስገኛ ምንጮች ገቢ የሚሰበስቡ ቢሆኑም፣ የገቢ ሪፖርት የማያደርጉ በመሆኑ ኦዲት ማድረግ አልተቻለም
- በ13 ናሙና መሥሪያ ቤቶች የተሟላ ማስረጃ ሳይቀርብ 132.364 ሚሊዮን ብር በወጪ ተመዝግቧል
- 22 መሥሪያ ቤቶች 13.8 ሚሊዮን ብር ማስረጃ የሌለው ወጪ አድርገዋል
- 30 መሥሪያ ቤቶች ደንብና መመርያ በመጣስ 353.568 ብር የሚያወጣ ግዥ ፈጽመዋል
- በውሎ አበልና በትርፍ ሰዓት ተመን 11 መሥሪያ ቤቶች 1.4 ሚሊዮን ብር አባክነዋል
- በኤርፖርት ተርሚናል የተሰማራ አንድ የግል ድርጅት ገንዘብ በውጭ ምንዛሪ ለመቀበል ፈቃድ ሳይኖረው ከአሥር ዓመታት በላይ እየሠራ እንደሚገኝና ተቆጣጣሪ አካላት ያደረጉት ምንም ነገር የለም
- 134.7 ሚሊዮን ብር ብድር ያልመለሱ የመንግሥት ድርጅቶች መኖራቸውን
- የመንግሥት ትርፍ ድርሻ የሆነ 18.549 ሚሊዮን ብር ሳይከፍሉ የተሸጡ ድርጅቶች እንዳሉ
- 44.254 ሚሊዮን ብድር ያለባቸው ድርጅቶች ሲሸጡም የገዛው አካል ለመንግሥት መከፈል የነበረበትን እዳ ያልተከፈለ
- መሆኑን እና ተመሳሳይ የመንግስት ብክነትና ወንጀሎችን ጠቅላይ ኦዲተር ይፋ ያደረገው ለዚሁ “የተከበረ”
ለሚባለው ፓርላማ ነበር፡፡ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሆነው የፌደራል የጸረ ሙስናና የስነ ምግባር ኮሚሽን ከብሔራዊ የመረጃና ደህንነት
አገልግሎትና ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመሆን በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን ተጠርጣሪዎች ስም ይፋ አድርጓል። የኢህአዴግ
አንደበት የሆኑት ዋልታ ኢንፎርሜሽንና ፋና ብሮድካስቲንግ የሁለቱን ዋና ባለስልጣናት ምስል አስደግፈው ያቀረቡት
ዜና ግንቦት3 ቀን 2005 የፌዴራሉ የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን የገቢዎች ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና
ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታን እንዲሁም፣ ምክትል ዳይሬክተሩን አቶ ገብረዋህድ ወልደ ጊዮርጊስን ጨምሮ 12
ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉንና ኮሚሽኑ በግለሰቦቹ ላይ በቂ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች ማሰባሰቡን፣ ጉዳዩ
ለፍርድ ቤት እስኪቀርብ ድረስም ተጠርጣሪዎቹን በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲቆዩ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ በመግለጽ
ነበር።
በቁጥጥር ስር የዋሉ 13 ሰዎች ስም ዝርዝር
1.የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታን
2.ምክትል ዳይሬክተሩ አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ
3.እሸቱ ወልደሰማያት በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የአቃቤ ህግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
4.አስመላሽ ወልደማሪያም የቃሊቲ ጉምሩክ ኃላፊ
5.ጥሩነህ በርታ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የተወረሱ ንብረቶች አስተዳደር ቡድን መሪ
6.አምኘ ታገለ የናዝሬት ጉምሩክ ኃላፊ
7.ሙሉጌታ ጋሻው በኦሮሚያ ልዩ ዞን መሀንዲስ
8.ከተማ ከበደ የኬኬ ትሬዲንግ ባለቤት
1
9.ስማቸው ከበደ የኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ባለቤት
0.ምህረት አብ አብርሀ ባለሀብት
11.ነጋ ገብረእግዚአብሄር የነፃ ትሬዲግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ባለቤት
12.ዘሪሁን ዘውዴ ትራንዚተርና ደላላ
13.ማርሸት ተስፉ ትራንዚተርና ደላላ
የፌደራል የጸረ ሙስና ኮሚሽን በህግ አዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት “ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተለያዩ ባለ ጉዳዮችና ከንግዱ ማህበረሰብ እንዲሁም፣ ከልዩ ልዩ መንግስታዊና ህዝባዊ አካላት ጥቆማዎችን ሲቀበል ቆይቷል። ጥቆማዎቹ በአንዳንድ የገቢዎችና ጉምሩክ መስሪያ ቤት ኃላፊዎችና ሰራተኞች እንዲሁም፥ በግል ንግድ በተሰማሩ ህገ ወጥ አካሄድን በሚያዘወትሩ ግለሰቦች ላይ ያተኮሩ” ነበሩ።
ኮሚሽኑ ከህዝቡ የተቀበላቸውን እነዚህን ጥቆማዎች መነሻ በማድረግም “ከብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር ጥናት ሲያደርግ ቆይቷል። በጥናቱም በቂ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን ሰብስቧል” በማለት የኢህአዴግ ልሳኖች መረጃ ማሰባሰቡ በቅርብ የተጀመረ ጥናት መሆኑንን ይፋ ሲያደርጉ፤ ኢቲቪ በበኩሉ ውሳኔው አቶ መለስ በህይወት እንዳሉ አድርጎ ለማሳየት “ለረዥም ዓመት፣ ለሶስት ተከታታይ ዓመታት ክትትል ሲደረግበት ነበር” ብሏል።
ሙስና በስንጥር! ከዚያስ?
አቶ መለስ በህይወት እያሉ በግልጽ የሚያውቁትን “የመበስበስ በሽታ” በእንጭጩ ከመቅጨት ይልቅ በማስፈራሪያነት ለንግግራቸው ማድመቂያ፣ ለሃላፊነታቸው ማስቀጠያ፣ ለተቀናቃኞቻቸው አንገት ማስደፊያ አድርገውት ይጠቀሙበት እንደነበር የሚያሳይ ተግባር ተከናውኗል ብለው የሚያምኑ ወገኖች እንደሚሉት “አሁን የተወሰደው ርምጃ በፖለቲካው አውራዎች መካከል ተፈጥሯል የተባለውን ልዩነት ተገን ያደረገና ተቀናቃቀኞችን የማጥራት ከቀድሞ ጀምሮ የኖረ አሰራር ቀጣይ ምዕራፍ ነው” ሲሉ ግልጽ አቋም ለመያዝ እንደሚቸገሩ ይናገራሉ።
እነዚህ ክፍሎች እንደሚሉት አቶ ገብረዋህድ ሃቀኛ ለመምሰል ሙሽሮች ተውበው በሊሞዚን ሲሄዱ “ሊሞዚኑ በህገወጥ የስም ዝውውር ለሶስተኛ ወገን የተላለፈ ነው” በማለት ሙሽራ አስወርደው መኪናውን ያሰሩ፣ ዘይት በተወደደ ጊዜ ከንግድ ሚኒስትሩ ጋር በመሆን ለጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ “ነጋዴዎች ሸቀጥ እየደበቁ የሚፈጥሩት ችግር ምስኪኑን ህዝብ እየጎዳው ነው። ለዚህ ምስኪን ህዝብ ልንደርስለት ይገባል። ጉዳዩ በዚህ ከቀጠለ አላስፈላጊ ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል” ብለው መናገራቸውን ያስታውሱና አንድ ትልቅ ነጥብ ያነሳሉ። የገቢዎች ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትርነት ወይም ዳይሬክተርነት ቦታ ኮታው የኦህዴድ ሆኖ ሳለ
አቶ ገብረዋህድ ከጉምሩክ የነበራቸውን ሃላፊነት በመያዝ በሚኒስትር ማዕረግ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክትር ሆነው ሲሾሙ፤ የወቅቱ የጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት የኦህዴድ ሰው እንዲነሱ ተደርጎ ነበር። ስለወቅቱ ድራማ የሚያውቁት አስተያየት ሰጪዎች፣ በወቅቱ ኦህዴድ ቅሬታውን አቶ መለስ ዘንድ ይዞ ቀርቦ ነበር። አቶ መለስ የኦህዴድን ቅሬታ ወደ ጎን በማለት አቶ ገብረዋህድ ቦታውን በመያዝ እንዲቀጥሉ መወሰናቸውን ተከትሎ ኦህዴድ ውስጥ ጉምጉምታ እንደነበር ከነዚሁ ክፍሎች ለመረዳት ተችሏል።
ቦታው አጓጊ የሆነው ኬላዎች ላይ ለመጠቃቀምና በመቀራረብ ምደባ በማካሄድ በትስስር ኮንትሮባንድ ንግድ ውስጥ ለመግባት አመቺ በመሆኑ እንደሆነ ያመለከቱት ክፍሎች “ከኬላ ጋር በተያያዘ ሁሉም ሃላፊነትና የምደባው እርከን አቶ ገብረዋህድን ስለሚመለከት፣ ምርመራው በጥብቅ ከተያዘ ወንጀሉ አቶ ሃይለማርያም እንዳሉት በሞቀ ሳሎናቸው የተቀመጡ በርካታ ሰዎችን ማዳረሱ አይቀርም”።
ይኸው ሙስናን በስንጠር የሚል ስያሜ የተሰጠው ርምጃ ተከትሎ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ባለስልጣኖች በላይ የኬኬ ሃላፊነቱ የተወሰነ የንግድ ማህበር ባለቤት አቶ ከተማ ከበደና የነጻ ትሬዲንግ ባለቤት አቶ ነጋ ገ/እግዚአብሄር ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኗል። የሁለቱ ቱጃሮች መታሰር በርካታ ነጋዴዎችን አስበርግጓል።
የኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ባለቤት ለሆቴላቸው ማስገንቢያ ከመንግሥት በብድር የወሰዱት ገንዘብ ለግንባታ ከሚፈጀው በእጥፍ የተጋነነ ግምት በመሆኑ የተበደሩትን ገንዘብ በሙሉ ለግንባታ ሥራ አላዋሉትም በሚል ከፍተኛ ቅሬታና ጥቆማ ቀርቦባቸው ነበር፡፡ በወቅቱ ስለሆቴሎች ብድር በቀረበ ጥናታዊ ጽሁፍ አብዛኛዎቹ ተበዳሪዎች ለአበዳሪ ባንኮች ኮሚሽን በመስጠት ከፕሮጀክት በላይ ብድር እንደሚወስዱ ተረጋግጦ ነበር፡፡ በዚሁ ስሌት መሠረት ከፕሮጀክት በላይ የሚወስዱትን የብድር ገንዘብ ወደ ዶላር በመቀየር በውጭ አገር ባንኮች እንደሚያቀምጡ የጸረ ሙስና ኮሚሽን ከበቂ በላይ መረጃ እንዳለው የጎልጉል ምንጮች አስታውሰዋል፡፡
የጎልጉል መረጃ አቀባዮች አንዳንድ መረጃዎችን ያሰባሰቡ ቢሆንም ከጉዳዩ ጥሬነት አንጻር ዝርዝሩን አሁን ከማቅረብ ታቅበናል።
በመጨረሻ በተገኘ ዜና የኮሎኔል ማዕረግ ያላቸው የአቶ ገብረዋህድ ባለቤትም ከፍተሻ የተረፉ ሰነዶችን ለመደበቅ ሲሞክሩ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰምቷል። የጎልጉል ምንጮች እንዳሉት ከዚሁ የሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ባለሃብቶችና ተጨማሪ ሰዎች ታስረዋል። ካገር እንዳይወጡ እየጠበቁ ያሉም አሉ። (ፎቶ: Addis Abeba Online)
http://www.goolgule.com/
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደጋጋሚ ስለመንግሥት ሌቦች እየተናገረ ነው፤ ሌቦቹን ግን እሱም አያውቃቸው፤ እነሱም እየሰሙት አይደለም፤ የመንግስት ሌቦች የተባሉት የሚግጡባቸው ዋናዎቹ መስኮች ታክስ፣ መሬትና የንግድ ውድድር መሆናቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጾአል፤ ከዚህም በላይ የተባሉትን የሌብነት መስኮች ከለምነት ወደበረሃነት ለመለወጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ኃላፊነት አለበት ያለ መሰለኝ፤ ሥልጣን ሳይኖር ኃላፊነት ከየት ይመጣል? እንግዲህ የፌዴራል ፖሊሱንና ሌላውን አልፎ፣ የደኅንነቱን ሰራዊት አልፎ፣ የጸረ-ሙስና ኮሚሽንን አልፎ፣ ዓቃቤ ሕግን አልፎ ሕዝብ እነዚያን ለምለም መስኮች ማድረቅ እንዴት ይችላል? ሌቦቹ ያሉት በመንግስት ጎራ ብቻ ሳይሆን በህዝብም ጎራ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቆም አድርጎአል፤ እንዲህ ከሆነ ‹‹አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ›› የሚባለው ሁኔታ ሰፍኖአል ማለት ይመስላል፤ ይህ እውነት ከሆነ ሌብነት ሥርዓት ሆኖአል ማለት ነው። (ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም)
የመንግሥት ሌቦች አደራ-ቢስነትና ሕዝብ ኃላፊነት (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም)
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያምጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደጋጋሚ ስለመንግሥት ሌቦች እየተናገረ ነው፤ ሌቦቹን ግን እሱም አያውቃቸው፤ እነሱም እየሰሙት አይደለም፤ የመንግስት ሌቦች የተባሉት የሚግጡባቸው ዋናዎቹ መስኮች ታክስ፣ መሬትና የንግድ ውድድር መሆናቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጾአል፤ ከዚህም በላይ የተባሉትን የሌብነት መስኮች ከለምነት ወደበረሃነት ለመለወጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ኃላፊነት አለበት ያለ መሰለኝ፤ ሥልጣን ሳይኖር ኃላፊነት ከየት ይመጣል? እንግዲህ የፌዴራል ፖሊሱንና ሌላውን አልፎ፣ የደኅንነቱን ሰራዊት አልፎ፣ የጸረ-ሙስና ኮሚሽንን አልፎ፣ ዓቃቤ ሕግን አልፎ ሕዝብ እነዚያን ለምለም መስኮች ማድረቅ እንዴት ይችላል? ሌቦቹ ያሉት በመንግስት ጎራ ብቻ ሳይሆን በህዝብም ጎራ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቆም አድርጎአል፤ እንዲህ ከሆነ ‹‹አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ›› የሚባለው ሁኔታ ሰፍኖአል ማለት ይመስላል፤ ይህ እውነት ከሆነ ሌብነት ሥርዓት ሆኖአል ማለት ነው።
ሌብነትን ሥርዓት የሚያደርገው ምንድን ነው? የባለስልጣን ጉልበተኛነትና የስልጣን ተጠቃሚ ደካማነት፣ የጨቋኝ የተጨቋኝ ግንኙነት የተስፋፋ ሲሆንና በእነዚህ ግንኙነቶች ውስጥ ወይም በእነሱ መሀከል የሚዳኝ ሕግ ሲጠፋ ወይም ሲደበዝዝ ነው፤ የዚህ ሁኔታ አንዱና ዋናው መገለጫው ፍርሃትና የማድበስበስ ባህል ነው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳስረዳው በሙስና ወይም በንቅዘት ጉዳይ የሌብነት ወንጀልን የሚፈጽሙት ጉልበተኛው ባለስልጣንም ደካማው በስልጣን ተጠቃሚውም ናቸው፤ ሁለቱም ሕግን ረግጠው ጥቅማቸውን ብቻ የሚያደልቡ ናቸው፤ በዚህ ሚዛን ሁለቱም ሌቦች እኩል ናቸው።
በተጨማሪ ደግሞ ጉልበተኛው ባለስልጣን አደራ አለበት ይባላል፤ ነገር ግን አደራውን የተቀበለው ከማንና በምን መንገድ መሆኑ በግልጽ ካልታወቀ ያባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ የሚለው መመሪያ በሥራ ላይ በዋለበት ሁኔታ ጉልበተኛው ባለሥልጣንና ምስኪኑ የምኞት ባሪያ አሁንም ወንጀላቸው እኩል ይመስለኛል፤ የባለሥልጣኑን ወንጀል ከምስኪኑ የምኞት ባሪያ ወንጀል የሚለየው የባለሥልጣኑ አደራ በላነት ሊባል ይችል ይሆናል፤ ነገር ግን በአደራ በላነት ሊያስከስሰው የሚችለው ሁኔታ የሚፈጠረው መንግሥተ-ሕዝብ ወይም ዴሞክራሲ በሚባለው ሥርዓት ነው።
በመንግሥተ-ሕዝብ ሥርዓት ሕዝብ ተቆጣጣሪም ዳኛም ሆኖ ለባለሥልጣኖቹ መሾምና መሻር ምክንያት ሊሆን ይችላል፤ ዳኞችንና ዓቃቤ ሕጎችን ለማሻር ምክንያት ሊሆን ይችላል፤ እንዲያውም ገዢውን ቡድን ሕዝቡ ሊለውጠው ይችላል፤ በዚህም ምክንያት ባለሥልጣኑ የሕዝብ ባለአደራነት ግዴታ አለበት ለማለት ይቻላል፤ በዚህም ምክንያት ባለሥልጣኑ የሕዝብ አገልጋይ እንጂ የአለቃው አሽከር አለመሆኑን በሚያረጋግጥ መልኩ በአሰራሩ ለህዝብ ግልጽነትና ተጠሪነትን ማሳየት ግዴታው ይሆናል፤ በዚህም ምክንያት ተገልጋዩ ሕዝብ በባለስልጣኖቹ ላይ ያለውን ሥልጣንና መብት አውቆና ተረድቶ በሙሉ ልብና በነጻነት በባለሥልጣኖቹ ላይ የሚያየውን ጉድለት ሳይፈራና ሳይሰጋ በአደባባይ መናገር ይችላል፤ በእንደዚህ ያለ ሥርዓት ውስጥ ሕዝቡ ባለሥልጣኖቹን የመቆጣጠር ኃላፊነት አለበት ለማለት ይቻላል።
ሕዝቡ ለጉልበተኞች ሌቦች በተጋለጠበት ሥርዓት ውስጥ ሕዝቡ ባለሥልጣን ሌቦቹን የማጋለጥ ኃላፊነት አለበት ማለት እንዴት ትክክል ይሆናል? ሕዝቡ ማድረግ የሚችለው ማሳበቅ ብቻ ነው፤ ይህም ቢሆን በያለበት ከሚርመሰመሱት ከመንግሥት አሳባቂዎች ጋር ያጣላል፤ ሌብነትን ለማቆም አስፈላጊ የሆኑት መዋቅሮች ሁሉ አሉ፤ ምንም የጎደለ አይመስለኝም፤ የጎደለው ኃላፊነት የሚሰማው ሰው ነው፤ ተደጋግሞ የሚሰማው ገጠመኝ አቤቱታ ያቀረቡበት ባለሥልጣን በጥቂት ጊዜ ውስጥ ሥልጣን ጨምሮ አቤቱታ የቀረበበት ወንበር ላይ ጉብ ብሎ ይገኛል የሚል ነው፤ እንግዲህ የተከሰሰው ሰው ዳኛ ሆኖ ሲገኝ ዳኝነት ከየት ሊገኝ ነው! ሌላ ቀርቶ በጠኔ የሚወድቁ ተማሪዎችን ምሳ ለማብላት ለሚጥሩ በጎ አድራጊዎች ግልገል ጉልበተኛ ባለስልጣኖች እንቅፋት እንደሚሆኑ ተደጋግሞ ይሰማል፤ እነሱ ድርሻቸውን ሳያገኙ በጠኔ የሚወድቀው ደሃ ተማሪ እርዳታ አያገኝም ነው? ወይስ ማናቸውም እርዳታ በእኛ በኩል ማለፍ አለበት ነው? ወይስ እኛን አስኮንናችሁ እናንተ አትጸድቁም ነው? በህክምናም በኩል ተመሳሳይ ችግር እንዳለ በሐሜት ደረጃ ይወራል፤ ነገር ግን ስለዚህ ተጠቃሚው ሕዝብ ኃላፊነቱን ተቀብሎ ከሐሜትና ከወሬ ይልቅ እውነቱን አደባባይ ለማውጣት ፈቃደኛ አይደለም፤ ለዚህ አልበቃም፤ የባሰ ይመጣል ብሎ ይፈራል፤ ጉልበተኛውን ባለስልጣን ይፈራል፤ ጉልበተኛውን ባለሥልጣን ለማሳጣት የሞከረ የምኞት ምስኪን ሌላ ትልቅ ወንጀል ተለጥፎበት እከብራለሁ ሲል ይደኸያል፤ ስለዚህ ጎመን በጤና ይልና ከጉልበተኛው ጋር ጮማውን አብሮ ይቆርጣል፤ ብሉ ሌበል ዊስኪውን አብሮ ይጠጣል፤ ሕዝብም ውሃውን ፈልጎ ይጠጣ!
ጠቅላይ ሚኒስትሩን ያሸነፉ ሌቦች ማንን ሊፈሩ ነው!
ዱሮ፣ ዱሮ በደጉ ዘመን በዱሮው ማዘጋጃ ቤት ፍርድ ቤት ነበረ፤ እዚያ የሰማሁትን ደማም ነገር አስታውሳለሁ፤ አንድ ኢጣልያዊ የከባድ መኪና ሹፌር በሁለት ጉዳይ ተከስሶ ቀርቦአል፤ አንደኛ የትራፊክ ሕግ በመጣስ፣ ሁለተኛ በመንግሥት መኪና የንግድ ዕቃ በመጫን ተብሎ ተነገረ፤ ዳኛው መነጽራቸውን አፍንጫቸው ጫፍ ላይ አድርገው እየጻፉ እንዳቀረቀሩ ‹‹ጥፋተኛ ነህ አይደለህም?›› ብለው ሲጠይቁት፣ ‹‹ኢኔ ሹፌር ኖ፤ መኪና የራስ…. (እንትና) ኖ፤›› ሲል ዳኛው የራስ እንትናን ስም ሲሰሙ ለመጀመሪያ ጊዜ ቀና አሉና የዓቃቤ ሕጉንም ስም አስታውሳለሁ፤ ‹‹ሞገስ! ብለህ ብለህ ከማን ጋር ልታላትመኝ ነው?›› ሲሉት ዘመናዩ ዓቃቤ ሕግ ‹‹ባለቤቱ ራስ እንትና ናቸው ካለ፣ እሳቸውን ያቅርብ፤›› አለ፤ ደማሙ እውነተኛ ዳኛ ቀበል አድርገው
በዓቃቤ ሕጉ እያሾፉ ‹‹እኮ ራስ እንትና እዚህ እንዲመጡ!›› አሉና ወደጣልያኑ ዞር ብለው ‹‹በል ሂድ ወዳጄ!›› ብለው አሰናበቱት።
ፈጣሪ ሰውን በአምሳሉ ከፈጠረ በኋላ ከዕጸ በለስ በቀር ሁሉንም ቅርጥፍ አርገህ ብላ ቢለው ዕጸ በለስንስ ለማን ትቼ አለና እሷንም ቅርጥፍ አድርጎ በላና ያስከተለውን ውጤት የማያውቅ አለ?
መላኩ ፈንታ በባህርዳሩ ስብሰባ ላይ ‹‹የህወሓት ስውር እጆች›› እንደሚደግፋቸው የሚነገርላቸውን ሁለት መቶ ነጋዴዎች በስም ጠቅሶ ‹‹አላሰራ አሉኝ፤ አስቸገሩኝ!›› ብሎ ሪፖርት ማቅረቡ ያስቆጣው አካል በእስሩ ላይ መኖር አለመኖሩን፤ አዜብ መስፍን በዛው ጉባኤ ላይ ‹‹መለስ ብቻ ነው በደሞዝ የኖረው›› የሚል ጥቆማ ከማቅረቧ ጋር ተያያዥነት አለው ወይስ የለውም? (ተመስገን
የእነ መላኩ ፈንታ ጉዳይ… (በተመስገን ደሳለኝ)
ከአንድ ወዳጄ ጋር ሃያ ሁለት አካባቢ ምሳ በልተን ስናበቃ እንደሌላው ቀን ሹፌሬ ስላልነበር በኮንትራት
ታክሲ ወደቤቴ (አሲምባ) አመራሁ፡፡ ታክሲው በውለታችን መሰረት የቀበናን አደባባይ ዞሮ ሲቆም፣ እኔም ሂሳቤን
አወራርጄ ወረድኩ፡፡ ሆኖም ጥቂት እርምጃ እንደተራመድኩ ያላስተዋልኳቸው ሁለት ሰዎች አጠገቤ ደርሰዋል፡፡ በዕድሜ
እኩዮቼ ይመስላሉ፡፡ አንዱ ቀጭንና ቀውላላ ነገር ነው፤ ሌላኛው ደግሞ ቁመቱ መካከለኛ ሆኖ፣ ደልደል ያለ ሰውነት
አለው፤ ሁለቱም ‹‹ጠይም›› የሚባሉ ናቸው፡፡ ቀውላላው፡-‹‹ሰላም ተመስገን!›› አለኝ፣
‹‹ሰላም!›› መለስኩኝ፡፡
‹‹ልናናግርህ ፈልግን ነበር?››
‹‹ይቅርታ አላወኳችሁም፡፡››
‹‹እሱን ተወው! የእኛ ማንነትንም እንድንነግርህ አትጠብቅ፣ ይገባሃል ብለን እናስባለን!›› አለ እስከአሁን ዝም ብሎ የነበረው ደልዳላው ሰው፡፡ ሆኖም ቀውላላው ጓደኛው አቋርጦት ቀጠለ፡-
‹‹ ምን መሰለህ? ሰሞኑን እነ መላኩ ፈንታ እንደታሰሩ ታውቃለህ፤ እናም የእነርሱ ጉዳይ የእኛ ብቻ ነው፤ አንተን አይመለከትህም፡፡››
‹‹አልገባኝም! ይህ ምን ማለት ነው?››
‹‹በቃ! በዚህ ጉዳይ ላይ ትንተና፣ ማብራሪያ እፅፋለሁ ምናምን እያልክ አትድከም ለማለት ነው!›› ቆጣ ባለ መልኩ መለሰልኝ-ደልዳላው ሰው፡፡
ከትከት ብሎ መሳቅ አማረኝ፤ በጣም መሳቅ! ሆኖም ለምን እንደሆነ አልውቅም-አልሳቅኩም፡፡ በግልባጩ ድንገተኛ ንዴት በመላ ሰውነቴ ሲሰርፅ ታወቀኝ፡፡ ከሰከንዶች በኋላም እስከአሁን ሲናገር ትህትና ያልተለየው ቀውላላው ሰው እንዲህ ሲል አግባባኝ፡-
‹‹እየውልህ፣ መንግስት ሰዎቹን ያሰረው በወንጀል ላይ በመሰማራታቸው ከመሆኑ በተጨማሪ ለህዝብና ለሀገር ጥቅም ነው፤ ስለዚህም ገና ፍርድቤት ስለሚቀርቡ፣ ምርመራውም ስላላለቀ አንተ በፅሁፍህ ተሳስተህ፣ ለሌሎችም የተሳሳተ መረጃ እንዳታስተላልፍ ለመምከር ነው፡፡››
‹‹ስለምክራችሁ በጣም አመሰግናለሁ! ነገር ግን እኔ የምሰራውን አውቃለሁና ለስራዬ መካሪ አያስፈልገኝም›› ስል ባለመካከለኛ ሰውነቱ አቋረጠኝና፤ ከቅድሙ በባሰ የቁጣ ቃል መናገሩን ቀጠለ፡-
‹‹ስማ! ልንመክርህ ወይም ልናባብልህ አይደለም የመጣናው፤ በቃ በማያገባህ ጉዳይ መግባት እንደሌለብህ ልንነግርህ ነው!››
ይህን ጊዜም አነጋገሩ በስሱ አስቆጣኝና፡-
‹‹እየወልህ! እናንተ ማንም ብትሆኑ ግድ አይሰጠኝም፤ ኋላ ኪሳችሁ ያለው መታወቂያም አያሳስበኝም፡፡ እስከዛሬ ድረስ የማደርጋትን እያንዳንዷ ነገር አስቤበትና አምኜበት ነው፤ ማስፈራሪያችሁ እኔ ጋ ቦታ የለውም፡፡ ምናልባት ‹ይህንን ጻፍ፤ ይህንን አትጻፍ› ስትሏቸው ትዕዛዛችሁን በመፈፀም ያስለመዷችሁ ጋዜጠኞች ካሉ ወደእነርሱ ልትሄዱ ትችላላችሁ›› ብዬ
መንገዴን ልቀጥል ስል፣ ትሁቱና ቀውላላው ሰው፡-
‹‹ተመስገን ብታስብበት መልካም ነው!›› አለ፣
‹‹ምንም የማስብበት ነገር የለም፤ ይልቅ አለቃችሁን ንገሩት፣ ሰሞኑን እንደናንተ አይነት ፀጉረ ልውጦች በቤቴ አካባቢ በዝተዋልና ሰብስብልኝ፣ ይሄ አንድም ስራ መፍታት ነው፤ ሁለትም የሀገር ሃብት ማባከን ነውና! ብሎሀል በሉት››
…ከዚህ በኋላ ቤቴ ገብቼ ስለገጠመኜ ማሰብ ስጀምር መልስ የሚያስፈልጋቸው ጥያቄዎች በአእምሮዬ ተመላለሱ፡- በዚህች ሀገር ላይ ምን እየተደረገ ነው? እነማን፣ በእነማን ላይ እያሴሩ ነው? መላኩ ፈንታ የታሰረው እውነት በሙስና ብቻ ነውን? ኢህአዴግስ ዕውን ሙስናን ለመከላከል ቆረጦ ተነስቷል?አሁን ማ ይሙት በሙስና መጠየቅ ከተጀመረ መላኩ ነው የመጀመሪያ የሚሆነው? ወይስ…
(የሆነ ሆኖ ይህችን የሞነጫጨርኩት ‹‹አይመለከትህም!›› ያሉኝ ሰዎች እንደሚመለከተኝ ይረዱ ዘንድ ነውና፣ በቅርቡ በስፋት የምመለስባቸውን የመነሻ ሃሳቦች አስቀምጬ ልሰናበት)
1. መላኩ ፈንታ በባህርዳሩ ስብሰባ ላይ ‹‹የህወሓት ስውር እጆች›› እንደሚደግፋቸው የሚነገርላቸውን ሁለት መቶ ነጋዴዎች በስም ጠቅሶ ‹‹አላሰራ አሉኝ፤ አስቸገሩኝ!›› ብሎ ሪፖርት ማቅረቡ ያስቆጣው አካል በእስሩ ላይ መኖር አለመኖሩን፤ አዜብ መ
(ስለሰውየው ብቃትና ከሙስና የፀዳ ስለመሆኑ በስፋት ይነገር እንደነበር አውቃለሁ፤ በአናቱም የኢህአዴግ አመራር ሆኖ ከሙስና የራቀ ይኖራል ብሎ ማሰብ በእጅጉ ይከብዳል፡፡ በእርግጥ ‹‹የመላኩ ችግር›› ተብሎ ሲነገር እስማ የነበረው ከመልከ መልካምነቱ ጋር ተያይዛ የምትነሳ ጉዳይ ነች-ቶሎ በፍቅር መሸነፍ፡፡ በነገራችን ላይ መላኩ ከሆኑ ጊዜያት በፊት ዱባይ ውስጥ የመኪና አደጋ ደርሶበት እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ለስራ ጉዳይ ሄዶ ግን አልመሰለኝም)
2. መቼም የማይካደው ሀቅ መላኩ ፈንታ ለፓርቲው ባለውለታ መሆኑ ነው፡፡ ይኸውም በተለይ ከምርጫ 97 በኋላ ኢህአዴግ ‹‹አይደግፉኝም›› ያላቸውን ነጋዴዎች የተለያየ ምክንያት እየለጠፈ እንደአኮሰመናቸው ይታወሳል፡፡ ይህንን የስራ ሂደት ካሳኩት ‹‹ዋነኞቹ አስፈፃሚዎች›› መካከል ደግሞ እርሱ ይመራው የነበረው መስሪያ ቤት ግንባር ቀደሙ ነው፡፡ እናም እዚህ ጋር የሚነሳው ጥያቄ ዛሬ መላኩ ፊቱን ከጠላት ወደወዳጅ (የስርዓቱ አውራ ጣት ወደሆኑ ነጋዴዎች) ማዞሩ የመዘዘው ጦስ በድርጅቱ ውስጥ ለተፈጠረው ልዩነት ‹‹መያዣ›› (የአብርሃም በግ) አድርጎት ይሆናል ብሎ መከራከር ይቻል ይሆን? መላኩስ ይህንን ጥያቄ ያቀረበው በራሱ ተነሳሽነት ነው? ወይስ ‹‹አይዞህ›› ብሎ አደፋፍሮት ሲያበቃ የከዳው ቡድን አለ?
3. በኢህአዴግ ውስጥ የእስክንድር ነጋ ጉዳይ ልዩነት ፈጥሯል፡፡ እነ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ እንዲፈታ ይፈልጋሉ፡፡ ብአዴንም ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ይህንን ሃሳብ ይደግፋል፡፡ እናም እነዚህ ልዩነቶች መስፋታቸው ይሆናል ሁለት የብአዴን አመራር አባል የሆኑ ሚንስትሮችን በአንድ ሳምንት ውስጥ ‹‹የነቀላ››ው ሰላባ አድርጓቸው ይሆን?
4. እንዲህ አይነቱ እስር እና ድንገት ከሃላፊነት መባረር በመላኩና በብርሃን ብቻ ይቆማል? ወይስ ይቀጥላል? ከቀጠለስ ወደ እነማን ያመራል?
ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ለማስከበር ማንኛውንም መስዋዕትነት መክፈል የሁላችንም ግዴታ ነው!
መንግስት እና የመንግስት ደጋፊዎችም ጉዳዩን እንደዋዛ ለማለፍ ሲሞክሩ እና አለፍ ሲል ደግሞ ጉዳዩ ኢህአዲግን አይመለከትም የሚል ፅሁፍ በማህበራዊ ድህረ ገፆች ለማስነበብ ሲዳፈሩ አስገርመውኛል። በመሰረቱ በስልጣን ላይ ያለ ፓርቲ ማለት በእያንድንዱ የስልጣን መዋቅር ውስጥ አለ ማለት ነው። ይህ ማለት ከገንዘብ ጀምሮ ማናቸውንም የሀገሪቱን ሀብት በመሰለው መልክ ውሳኔ እየሰጠ ነው ማለት ነው። ይህ ”የመንግስት ሀ ሁ” ነው። ይህንን ሃቅ ለመግፋት ያልተፈነቀለ ድንጋይ የለም። በመሆኑም ለደረሰው የገንዘብ ብክነት የገዢው ፓርቲ አባላት እና ባለስልጣናት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ተጠያቂ የሚሆኑባቸው ብዙ መንገዶች አሉ።
ባለፈው አመት ”ግሎባል ፋይናንሻል እንተግርቲ” የተሰኘ አለምአቀፍ ድርጅት ባወጣው ሪፖርት ከ 2000 እስከ 2009 ዓ.ም (እ.ኤ.አ.) ብቻ ከኢትዮጵያ ከ 11.7 (አስራአንድ ነጥብ ሰባት ቢልዮን ዶላር) በላይ በህገ-ወጥ መንገድ መውጣቱን ገልጧል። ይህ ማለት እንደ ኢትዮጵያ ላለች አንዲት ታዳጊ ሀገር የእድገቷ ብቻ ሳይሆን ሕልውናዋን የሚፈታተን ነው። ሚልዮኖች የሚበሉት አጥተው በሚንከላወሱባት ምድር ይህንን ያህል ገንዘብ በህገወጥ መንገድ ወጣ ሲባል እንዴት ዝም ይባላል? በሌሎች ሃገራት ቢሆን ከካብኔ እስከ ምክርቤት የመበተን እና መንግስት ስልጣን እስከመልቀቅ የሚደርስበት ጉዳይ ነበር። እኛ ሀገር ግን ስለ ጉዳዩ መንግስት ማብራርያ አልሰጠበትም። የሚጠይቀውም የለም። ለነገሩ አምባገነኖች ነፃ ሚድያውን ማፈን የሚጠቅማቸው ለእንደዚህ ያለ ጊዜ ነው። ፀጥ እረጭ ለማድረግ።
የ11.7 ቢልዮን ዶላር ጉዳይ ገርሞን (መቸም ሁሌ እንደገረመን ነው) ሳያበቃ የእራሱ የመንግስት መዋቅር የሆነው የዋናው ኦዲተር ሪፖርት ደግሞ አፍ የሚያስይዝ ሪፖርት ለምክርቤቱ አቅርቦ አፋችንን አስይዞናል።
በግንቦት 5/2013 እኤአ ሪፖርተር ባወጣው ርዕስ አንቀፅ ላይ እንዲህ ዘግቦታል። የሪፖርቱን ዋና ዋና ነጥብ፣
- 1.4 ቢሊዮን ብር ያልተወራረደ ሒሳብ አለ፡፡
– 313.6 ሚሊዮን ብር ዕዳ ሳይመልሱ የተሸጡ ድርጅቶች አሉ፡፡
– 897.5 ሚሊዮን ብር ሕጋዊ ያልሆነ ክፍያና ወጪ ተደርጓል፡፡ – ያልተወራረደው 1.4 ቢሊዮን ብር በ57 የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የታየ ነው፡፡
– 15 ድርጅቶች ወይም መሥሪያ ቤቶች ከልዩ ልዩ ገቢ ማስገኛ ምንጮች ገቢ የሚሰበስቡ ቢሆኑም፣ የገቢ ሪፖርት የማያደርጉ በመሆኑ ኦዲት ማድረግ አለተቻለም፡፡
– በ13 ናሙና መሥሪያ ቤቶች የተሟላ ማስረጃ ሳይቀርብ 132.364 ሚሊዮን ብር በወጪ ተመዝግቧል፡፡
– 22 መሥሪያ ቤቶች 13.8 ሚሊዮን ብር ማስረጃ የሌለው ወጪ አድርገዋል፡፡
– 30 መሥሪያ ቤቶች ደንብና መመርያ በመጣስ 353.568 ብር የሚያወጣ ግዥ ፈጽመዋል፡፡
– በውሎ አበልና በትርፍ ሰዓት ተመን 11 መሥሪያ ቤቶች 1.4 ሚሊዮን ብር አባክነዋል፡፡
– በኤርፖርት ተርሚናል የተሰማራ አንድ የግል ድርጅት ገንዘብ በውጭ ምንዛሪ ለመቀበል ፈቃድ ሳይኖረው ከአሥር ዓመታት በላይ እየሠራ እንደሚገኝና ተቆጣጣሪ አካላት ያደረጉት ምንም ነገር የለም፡፡
– 134.7 ሚሊዮን ብር ብድር ያልመለሱ የመንግሥት ድርጅቶች ሲኖሩ፣ የመንግሥት ትርፍ ድርሻ የሆነ 18.549 ሚሊዮን ብር ሳይከፍሉ የተሸጡ ድርጅቶች አሉ፡፡ 44.254 ሚሊዮን ብድር ያለባቸው ሲሸጡም የገዛው አካል ለመንግሥት መከፈል የነበረበትን ያልከፈለ መሆኑን፣ ወዘተ. ወዘተ. ወዘተ.
በትናንትናው ግንቦት 2/2005 ዓ ም የግምሩክ ባለስልጣን ምክትል እና ዋና ሥራ አስኪያጆች ከሙስና ጋር በተያያዘ መታሰራቸውን ኢቲቪ በምሽቱ የዜና እወጃው ላይ ገልፆ ቀሪ የታሰሩትን ስም ዝርዝር ግን ሳይጠቅስ አልፎታል።
የነፃ ሚድያውን የሚተካ ፀረ-ሙስና አካል አይገኝም
እነሆ አምባገነንነት የሰብአዊ መብት እረገጣን ይወልዳል፣ የሰብአዊ መብት እረገጣ ሙስናን ይወልዳል፣ሙስና ብዙ ልጆች ይወልዳል እነርሱም ድህነት፣ሥራ አጥነት፣የተማረውን ‘የኮብልስቶን’ ሥራ ነው ዕጣህ ማለትን፣ በሺ የሚቆጠሩ ሕፃናትን የጎዳና ተዳዳሪነትን፣በሺህ የሚቆጠሩ እህቶችን ለአረብ ሀገራት የባርነት ግዞትን፣ ሚልዮን ወጣቶች በሀገራቸው ተስፋ ቆርጠው መሰደድን ይወልዳል። ከእዚህ ሁሉ ጋር ግን አንድ የማንረሳውን ልጅ ደግሞ ሙስና ይወልዳል አርሱም የጥቂቶችን ቅምጥል ሕይወት፣የሚላስ የሚቀመስ የሚፈልጉ ሚልዮኖች ባሉባት ሀገር በ ሚልዮን ብር የሚቆጠር ”ሐመር”መኪናን በአዲስ አበባ እያሽከረከሩ መታየትን ሌላም ሌላም ልጆች ይወልዳል።
አምባገነኖች እራሳቸው በምዘውሩት የፀረ ሙስና ኮሚሽን እንዳኝ የሚሉት ጉዳቸውን ስለሚያውቁት ነው።አምባገነኖች የነፃ ሚድያን እንደ ጦር የሚፈሩት እውነተኛው የ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ነፃ ሚድያው ስለሆነ ነው።ነፃው ሚድያ እያንዳንዱ ባለስልጣን ከበላው እራት እስከ ቁርስ ድረስ ለሕዝቡ እንደሚዘግብ እና ማን የህዝብ አገልጋይ ማን ተገልጋይ መሆኑን ፍንትው አድርገው ስለሚያሳዩት አይፈልጉትም።ለእዚህ ነው እንደ እነ እስክንድር ያሉትን የነፃ ጋዜጠኛ ተምሳሌቶችን ”አሸባሪዎች” እያሉ እስከ እድሜ ልክ እስራት የሚፈርዱባቸው ከአስተዳደራዊ በደል ባለፈ የሙስናውን ጎራ እንዳይነካኩ ከመፍርዓትም ነው።
ሙስና በኢትዮጵያ ከግለሰብ ደረጃ አልፎ የመንግስት የአጠቅቀም ወይንም የአሰራር ስርዓት (system) ሆኗል
በኢትዮጵያ መንግስት ዘንድ ሙስና አሳፋሪ ጉዳይ እንዳልሆነ ብዙ ማስረጃ መጥቀስ ይቻላል። አዎን የፀረ ሙስና ኮሚሽን አለ።ሚድያው የሙስና መጥፎነትን ይነግረናል።አሁን አሁን ለምን እንደቀረ አይታወቅም እንጂ ቀድሞ የሚቀርቡት ማስታወቂያዎች እና ድራማዎች በደንብ የተጠኑ አስተማሪ መስለው ነበር።በፀረ-ሙስና ኮሚሽን ውስጥ በመርማሪነት የሚቀጠር ሰው ደሞዙ በወር እስከ አስራሁለት ሺህ የሚደርስ፣ የሚሄድበት እና የሚዝናናበት ቦታ ሁሉ የታወቀ መሆን እንዳለበት የቅጥር መስፈርቱ ያዛል።አመታት ሲቆጠሩ ግን ቀደም ብሎ የተወሰነ ስልጣን የነበረውን የፀረ ሙስና ኮሚሽን ጥርስ አልባ የማድረጉ ሂደት ከአቶ መለስ ተከታታይ ቁጣ ጀምሮ ኮሚሽኑ ውስጥ የተቀጠሩት የመጀመርያ ደረጃ መርማሪዎች ድንጉጥ እንዲሆኑ ማድረግ የተለመዱ ሆኑ።ሰራተኞቹ በውጭ የሚያዩት እና የሚሰራው አልጣጣም አላቸው።እናም ግማሾቹ በሙስናው ተነካኩ የተቀሩት ሀገር ትተው ሄዱ ሌሎቹ ሥራ ቀየሩ።
ከአንድ ሁለት ወር በፊት ይመስለኛል ሸገር ኤፍ ኤም የፀረ ሙስና ኮሚሽኑን ኃላፊ ” ከእናንተ ሰራተኞች መካከል በሙስና የሚታሙ አሉ ይባላል።እና የእዚህ አይነት ችግር ሲገጥማችሁ እንዴት ነው የምትፈቱት?” ተብለው ሲጠየቁ የመለሱት መልስ ”አዎን ይህ ያጋጥመናል በቅርቡም ተመሳሳይ ችግር አለ በቅርቡም ሁለት ሰራተኞች ላይ የተባለው ችግር ተገኝቷል።” ብለዋል። ይህ አንግዲህ ለሚድያ የተባለው እንጂ ወደ ዝርዝሩ ሲመጣ የባሰ ጉዳይ እንደሚኖር ይታመናል።
በእዚህ ሁሉ ነው እንግዲህ ሙስና ከግለሰብ አልፎ አሰራር ስርዓት(system) የሆነው።የአሰራር ስርዓት(system) የሆነ ሙስናን ለመዋጋት ግለሰቦችን ሳይሆን አሰራሩን(system) ማስወገድ ይሻል። አቶ መለስምሆኑአቶሃይለማርያምደጋግመው መንግስታቸው፣ባለስልጣኖቻቸው፣ነጋዴዎቻቸው ሁሉ ሙሰኛ እንደሆኑ በምክርቤት የተለያዩ ስብሰባዎች ነግረውናል።ይህ ማለት ችግሩ የግለሰቦች ሳይሆን የአሰራሩ ሙሉ መዋቅር -የመንግስት ችግር ነው ማለት ነው።የአሰራር እና የጠቅላላ የመዋቅር ችግር ደግሞ በጥገናዊ ለውጥ አይስተካከልም።ሙሉ በሙሉ የፖሊስ ለውጥ በማድረግ እና ስርዓቱን በመቀየር ብቻ ይፈታል። ይህ በእርግጥ ለመንግስት ከባድ ሊሆን ይችላል።ለሕዝቡ ግን ከባድ አይደለም። ምክንያቱም የሙስና ውጤት ልጆች በሀብት ከመምነሽነሽ በቀር ሌሎቹ አብረውት ስለሚኖሩ ያውቃቸዋል።እናም የሙስና ዋናውን ግንድ የመንግስትን መላውን መዋቅር ትተን ግለሰቦችን አንንቀስ።ግንዱን ትተን ቅርንጫፎችን አንቀነጣጥብ።በአደባባይ ሙስና እንደፈፀሙ የተናገሩ ግን በፈረንጁ አፍ ”ሶሪ” መሰል ንግግር አድርገው የሚኖሩባት ሀገር ውስጥ መኖራችንን አንዘንጋው።
በዘመነ ኢህአዲግ ፓርቲው ሙስና መኖሩ ትዝ የሚለው ሊያስወግዳቸው የሚፈልጋቸው ባለስልጣናት ሲኖሩ ወይንም እንደ ሰሞኑ አይኑን ያፈጠጠ ሪፖርት በተለያዩ ሚድያዎች ሲገለፅ ነው።የውስጥ ሹክቻ በሙስና ማንኪይ ትገላበጣለች። ትናንት የታሰሩት ባለስልጣናት ጉዳይ ላይ ”ለምን አሁን?” የሚል ጥያቄ የቀረበለት የቀድሞው አዲስ ነገር አምደኛ ዘሪሁን ትናንት ከኢሳት ጋዜጠኛ መሳይ ለቀረበለት ጥያቄ የመለሰው መልስ ግን አንጀት ጠብ የሚል ሆኖ አግኝቼዋለሁ እናም በእርሱ ሃሳብ ልደምድም። ”የትናንቱ እስር ከሙስናው ጉዳይ ይልቅ ፖለቲካው ድምፀቱ ነው የሚሰማኝ” ነበር ያለው።አበቃሁ
ጌታቸውኦስሎኦስሎኦስሎ
‹‹አንተ አታውቀንም! እኛ ነን የምናውቅህ››
‹‹የት ነው የምታውቁኝ? ማለቴ በምን መልኩ…››
ደሳለኝ)‹‹ሰላም!›› መለስኩኝ፡፡
‹‹ልናናግርህ ፈልግን ነበር?››
‹‹ይቅርታ አላወኳችሁም፡፡››
‹‹እሱን ተወው! የእኛ ማንነትንም እንድንነግርህ አትጠብቅ፣ ይገባሃል ብለን እናስባለን!›› አለ እስከአሁን ዝም ብሎ የነበረው ደልዳላው ሰው፡፡ ሆኖም ቀውላላው ጓደኛው አቋርጦት ቀጠለ፡-
‹‹ ምን መሰለህ? ሰሞኑን እነ መላኩ ፈንታ እንደታሰሩ ታውቃለህ፤ እናም የእነርሱ ጉዳይ የእኛ ብቻ ነው፤ አንተን አይመለከትህም፡፡››
‹‹አልገባኝም! ይህ ምን ማለት ነው?››
‹‹በቃ! በዚህ ጉዳይ ላይ ትንተና፣ ማብራሪያ እፅፋለሁ ምናምን እያልክ አትድከም ለማለት ነው!›› ቆጣ ባለ መልኩ መለሰልኝ-ደልዳላው ሰው፡፡
ከትከት ብሎ መሳቅ አማረኝ፤ በጣም መሳቅ! ሆኖም ለምን እንደሆነ አልውቅም-አልሳቅኩም፡፡ በግልባጩ ድንገተኛ ንዴት በመላ ሰውነቴ ሲሰርፅ ታወቀኝ፡፡ ከሰከንዶች በኋላም እስከአሁን ሲናገር ትህትና ያልተለየው ቀውላላው ሰው እንዲህ ሲል አግባባኝ፡-
‹‹እየውልህ፣ መንግስት ሰዎቹን ያሰረው በወንጀል ላይ በመሰማራታቸው ከመሆኑ በተጨማሪ ለህዝብና ለሀገር ጥቅም ነው፤ ስለዚህም ገና ፍርድቤት ስለሚቀርቡ፣ ምርመራውም ስላላለቀ አንተ በፅሁፍህ ተሳስተህ፣ ለሌሎችም የተሳሳተ መረጃ እንዳታስተላልፍ ለመምከር ነው፡፡››
‹‹ስለምክራችሁ በጣም አመሰግናለሁ! ነገር ግን እኔ የምሰራውን አውቃለሁና ለስራዬ መካሪ አያስፈልገኝም›› ስል ባለመካከለኛ ሰውነቱ አቋረጠኝና፤ ከቅድሙ በባሰ የቁጣ ቃል መናገሩን ቀጠለ፡-
‹‹ስማ! ልንመክርህ ወይም ልናባብልህ አይደለም የመጣናው፤ በቃ በማያገባህ ጉዳይ መግባት እንደሌለብህ ልንነግርህ ነው!››
ይህን ጊዜም አነጋገሩ በስሱ አስቆጣኝና፡-
‹‹እየወልህ! እናንተ ማንም ብትሆኑ ግድ አይሰጠኝም፤ ኋላ ኪሳችሁ ያለው መታወቂያም አያሳስበኝም፡፡ እስከዛሬ ድረስ የማደርጋትን እያንዳንዷ ነገር አስቤበትና አምኜበት ነው፤ ማስፈራሪያችሁ እኔ ጋ ቦታ የለውም፡፡ ምናልባት ‹ይህንን ጻፍ፤ ይህንን አትጻፍ› ስትሏቸው ትዕዛዛችሁን በመፈፀም ያስለመዷችሁ ጋዜጠኞች ካሉ ወደእነርሱ ልትሄዱ ትችላላችሁ›› ብዬ
መንገዴን ልቀጥል ስል፣ ትሁቱና ቀውላላው ሰው፡-
‹‹ተመስገን ብታስብበት መልካም ነው!›› አለ፣
‹‹ምንም የማስብበት ነገር የለም፤ ይልቅ አለቃችሁን ንገሩት፣ ሰሞኑን እንደናንተ አይነት ፀጉረ ልውጦች በቤቴ አካባቢ በዝተዋልና ሰብስብልኝ፣ ይሄ አንድም ስራ መፍታት ነው፤ ሁለትም የሀገር ሃብት ማባከን ነውና! ብሎሀል በሉት››
…ከዚህ በኋላ ቤቴ ገብቼ ስለገጠመኜ ማሰብ ስጀምር መልስ የሚያስፈልጋቸው ጥያቄዎች በአእምሮዬ ተመላለሱ፡- በዚህች ሀገር ላይ ምን እየተደረገ ነው? እነማን፣ በእነማን ላይ እያሴሩ ነው? መላኩ ፈንታ የታሰረው እውነት በሙስና ብቻ ነውን? ኢህአዴግስ ዕውን ሙስናን ለመከላከል ቆረጦ ተነስቷል?አሁን ማ ይሙት በሙስና መጠየቅ ከተጀመረ መላኩ ነው የመጀመሪያ የሚሆነው? ወይስ…
(የሆነ ሆኖ ይህችን የሞነጫጨርኩት ‹‹አይመለከትህም!›› ያሉኝ ሰዎች እንደሚመለከተኝ ይረዱ ዘንድ ነውና፣ በቅርቡ በስፋት የምመለስባቸውን የመነሻ ሃሳቦች አስቀምጬ ልሰናበት)
1. መላኩ ፈንታ በባህርዳሩ ስብሰባ ላይ ‹‹የህወሓት ስውር እጆች›› እንደሚደግፋቸው የሚነገርላቸውን ሁለት መቶ ነጋዴዎች በስም ጠቅሶ ‹‹አላሰራ አሉኝ፤ አስቸገሩኝ!›› ብሎ ሪፖርት ማቅረቡ ያስቆጣው አካል በእስሩ ላይ መኖር አለመኖሩን፤ አዜብ መ
(ስለሰውየው ብቃትና ከሙስና የፀዳ ስለመሆኑ በስፋት ይነገር እንደነበር አውቃለሁ፤ በአናቱም የኢህአዴግ አመራር ሆኖ ከሙስና የራቀ ይኖራል ብሎ ማሰብ በእጅጉ ይከብዳል፡፡ በእርግጥ ‹‹የመላኩ ችግር›› ተብሎ ሲነገር እስማ የነበረው ከመልከ መልካምነቱ ጋር ተያይዛ የምትነሳ ጉዳይ ነች-ቶሎ በፍቅር መሸነፍ፡፡ በነገራችን ላይ መላኩ ከሆኑ ጊዜያት በፊት ዱባይ ውስጥ የመኪና አደጋ ደርሶበት እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ለስራ ጉዳይ ሄዶ ግን አልመሰለኝም)
2. መቼም የማይካደው ሀቅ መላኩ ፈንታ ለፓርቲው ባለውለታ መሆኑ ነው፡፡ ይኸውም በተለይ ከምርጫ 97 በኋላ ኢህአዴግ ‹‹አይደግፉኝም›› ያላቸውን ነጋዴዎች የተለያየ ምክንያት እየለጠፈ እንደአኮሰመናቸው ይታወሳል፡፡ ይህንን የስራ ሂደት ካሳኩት ‹‹ዋነኞቹ አስፈፃሚዎች›› መካከል ደግሞ እርሱ ይመራው የነበረው መስሪያ ቤት ግንባር ቀደሙ ነው፡፡ እናም እዚህ ጋር የሚነሳው ጥያቄ ዛሬ መላኩ ፊቱን ከጠላት ወደወዳጅ (የስርዓቱ አውራ ጣት ወደሆኑ ነጋዴዎች) ማዞሩ የመዘዘው ጦስ በድርጅቱ ውስጥ ለተፈጠረው ልዩነት ‹‹መያዣ›› (የአብርሃም በግ) አድርጎት ይሆናል ብሎ መከራከር ይቻል ይሆን? መላኩስ ይህንን ጥያቄ ያቀረበው በራሱ ተነሳሽነት ነው? ወይስ ‹‹አይዞህ›› ብሎ አደፋፍሮት ሲያበቃ የከዳው ቡድን አለ?
3. በኢህአዴግ ውስጥ የእስክንድር ነጋ ጉዳይ ልዩነት ፈጥሯል፡፡ እነ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ እንዲፈታ ይፈልጋሉ፡፡ ብአዴንም ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ይህንን ሃሳብ ይደግፋል፡፡ እናም እነዚህ ልዩነቶች መስፋታቸው ይሆናል ሁለት የብአዴን አመራር አባል የሆኑ ሚንስትሮችን በአንድ ሳምንት ውስጥ ‹‹የነቀላ››ው ሰላባ አድርጓቸው ይሆን?
4. እንዲህ አይነቱ እስር እና ድንገት ከሃላፊነት መባረር በመላኩና በብርሃን ብቻ ይቆማል? ወይስ ይቀጥላል? ከቀጠለስ ወደ እነማን ያመራል?
ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ለማስከበር ማንኛውንም መስዋዕትነት መክፈል የሁላችንም ግዴታ ነው!
“የትናንቱ እስር ከሙስናው ጉዳይ ይልቅ ፖለቲካው ድምፀቱ ነው የሚሰማኝ”
ሰሞኑን ኢትዮጵያ ከነበረው ዜና ውስጥ ሕዝቡን እያነጋገረ የነበረው የዋናው ኦዲተር ሪፖርት ከፍተኛ የገንዘብ
ብክነት፣የአሰራር ዝርክርክነት እና ለምን እንደተከፈሉ የማይታወቁ ክፍያዎች በመንግስት መስርያቤቶች ላይ መኖራቸውን የ
2004 ዓም የሂሳብ ምርመራ ሲያደርግ እንደረሰበት ለምክርቤት ባቀረበው ሪፖርት መግለፁ ነበር። (ጌታቸው፣ ከኦስሎ)“የትናንቱ እስር ከሙስናው ጉዳይ ይልቅ ፖለቲካዊ ድምፀቱ ነው የሚሰማኝ”
ሰሞኑን ኢትዮጵያ ከነበረው ዜና ውስጥ ሕዝቡን እያነጋገረ የነበረው የዋናው ኦዲተር ሪፖርት ከፍተኛ የገንዘብ ብክነት፣ የአሰራር ዝርክርክነት እና ለምን እንደተከፈሉ የማይታወቁ ክፍያዎች በመንግስት መስርያቤቶች ላይ መኖራቸውን የ 2004 ዓም የሂሳብ ምርመራ ሲያደርግ እንደደረሰበት ለምክርቤት ባቀረበው ሪፖርት መግለፁ ነበር።መንግስት እና የመንግስት ደጋፊዎችም ጉዳዩን እንደዋዛ ለማለፍ ሲሞክሩ እና አለፍ ሲል ደግሞ ጉዳዩ ኢህአዲግን አይመለከትም የሚል ፅሁፍ በማህበራዊ ድህረ ገፆች ለማስነበብ ሲዳፈሩ አስገርመውኛል። በመሰረቱ በስልጣን ላይ ያለ ፓርቲ ማለት በእያንድንዱ የስልጣን መዋቅር ውስጥ አለ ማለት ነው። ይህ ማለት ከገንዘብ ጀምሮ ማናቸውንም የሀገሪቱን ሀብት በመሰለው መልክ ውሳኔ እየሰጠ ነው ማለት ነው። ይህ ”የመንግስት ሀ ሁ” ነው። ይህንን ሃቅ ለመግፋት ያልተፈነቀለ ድንጋይ የለም። በመሆኑም ለደረሰው የገንዘብ ብክነት የገዢው ፓርቲ አባላት እና ባለስልጣናት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ተጠያቂ የሚሆኑባቸው ብዙ መንገዶች አሉ።
ባለፈው አመት ”ግሎባል ፋይናንሻል እንተግርቲ” የተሰኘ አለምአቀፍ ድርጅት ባወጣው ሪፖርት ከ 2000 እስከ 2009 ዓ.ም (እ.ኤ.አ.) ብቻ ከኢትዮጵያ ከ 11.7 (አስራአንድ ነጥብ ሰባት ቢልዮን ዶላር) በላይ በህገ-ወጥ መንገድ መውጣቱን ገልጧል። ይህ ማለት እንደ ኢትዮጵያ ላለች አንዲት ታዳጊ ሀገር የእድገቷ ብቻ ሳይሆን ሕልውናዋን የሚፈታተን ነው። ሚልዮኖች የሚበሉት አጥተው በሚንከላወሱባት ምድር ይህንን ያህል ገንዘብ በህገወጥ መንገድ ወጣ ሲባል እንዴት ዝም ይባላል? በሌሎች ሃገራት ቢሆን ከካብኔ እስከ ምክርቤት የመበተን እና መንግስት ስልጣን እስከመልቀቅ የሚደርስበት ጉዳይ ነበር። እኛ ሀገር ግን ስለ ጉዳዩ መንግስት ማብራርያ አልሰጠበትም። የሚጠይቀውም የለም። ለነገሩ አምባገነኖች ነፃ ሚድያውን ማፈን የሚጠቅማቸው ለእንደዚህ ያለ ጊዜ ነው። ፀጥ እረጭ ለማድረግ።
የ11.7 ቢልዮን ዶላር ጉዳይ ገርሞን (መቸም ሁሌ እንደገረመን ነው) ሳያበቃ የእራሱ የመንግስት መዋቅር የሆነው የዋናው ኦዲተር ሪፖርት ደግሞ አፍ የሚያስይዝ ሪፖርት ለምክርቤቱ አቅርቦ አፋችንን አስይዞናል።
በግንቦት 5/2013 እኤአ ሪፖርተር ባወጣው ርዕስ አንቀፅ ላይ እንዲህ ዘግቦታል። የሪፖርቱን ዋና ዋና ነጥብ፣
- 1.4 ቢሊዮን ብር ያልተወራረደ ሒሳብ አለ፡፡
– 313.6 ሚሊዮን ብር ዕዳ ሳይመልሱ የተሸጡ ድርጅቶች አሉ፡፡
– 897.5 ሚሊዮን ብር ሕጋዊ ያልሆነ ክፍያና ወጪ ተደርጓል፡፡ – ያልተወራረደው 1.4 ቢሊዮን ብር በ57 የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የታየ ነው፡፡
– 15 ድርጅቶች ወይም መሥሪያ ቤቶች ከልዩ ልዩ ገቢ ማስገኛ ምንጮች ገቢ የሚሰበስቡ ቢሆኑም፣ የገቢ ሪፖርት የማያደርጉ በመሆኑ ኦዲት ማድረግ አለተቻለም፡፡
– በ13 ናሙና መሥሪያ ቤቶች የተሟላ ማስረጃ ሳይቀርብ 132.364 ሚሊዮን ብር በወጪ ተመዝግቧል፡፡
– 22 መሥሪያ ቤቶች 13.8 ሚሊዮን ብር ማስረጃ የሌለው ወጪ አድርገዋል፡፡
– 30 መሥሪያ ቤቶች ደንብና መመርያ በመጣስ 353.568 ብር የሚያወጣ ግዥ ፈጽመዋል፡፡
– በውሎ አበልና በትርፍ ሰዓት ተመን 11 መሥሪያ ቤቶች 1.4 ሚሊዮን ብር አባክነዋል፡፡
– በኤርፖርት ተርሚናል የተሰማራ አንድ የግል ድርጅት ገንዘብ በውጭ ምንዛሪ ለመቀበል ፈቃድ ሳይኖረው ከአሥር ዓመታት በላይ እየሠራ እንደሚገኝና ተቆጣጣሪ አካላት ያደረጉት ምንም ነገር የለም፡፡
– 134.7 ሚሊዮን ብር ብድር ያልመለሱ የመንግሥት ድርጅቶች ሲኖሩ፣ የመንግሥት ትርፍ ድርሻ የሆነ 18.549 ሚሊዮን ብር ሳይከፍሉ የተሸጡ ድርጅቶች አሉ፡፡ 44.254 ሚሊዮን ብድር ያለባቸው ሲሸጡም የገዛው አካል ለመንግሥት መከፈል የነበረበትን ያልከፈለ መሆኑን፣ ወዘተ. ወዘተ. ወዘተ.
በትናንትናው ግንቦት 2/2005 ዓ ም የግምሩክ ባለስልጣን ምክትል እና ዋና ሥራ አስኪያጆች ከሙስና ጋር በተያያዘ መታሰራቸውን ኢቲቪ በምሽቱ የዜና እወጃው ላይ ገልፆ ቀሪ የታሰሩትን ስም ዝርዝር ግን ሳይጠቅስ አልፎታል።
የነፃ ሚድያውን የሚተካ ፀረ-ሙስና አካል አይገኝም
እነሆ አምባገነንነት የሰብአዊ መብት እረገጣን ይወልዳል፣ የሰብአዊ መብት እረገጣ ሙስናን ይወልዳል፣ሙስና ብዙ ልጆች ይወልዳል እነርሱም ድህነት፣ሥራ አጥነት፣የተማረውን ‘የኮብልስቶን’ ሥራ ነው ዕጣህ ማለትን፣ በሺ የሚቆጠሩ ሕፃናትን የጎዳና ተዳዳሪነትን፣በሺህ የሚቆጠሩ እህቶችን ለአረብ ሀገራት የባርነት ግዞትን፣ ሚልዮን ወጣቶች በሀገራቸው ተስፋ ቆርጠው መሰደድን ይወልዳል። ከእዚህ ሁሉ ጋር ግን አንድ የማንረሳውን ልጅ ደግሞ ሙስና ይወልዳል አርሱም የጥቂቶችን ቅምጥል ሕይወት፣የሚላስ የሚቀመስ የሚፈልጉ ሚልዮኖች ባሉባት ሀገር በ ሚልዮን ብር የሚቆጠር ”ሐመር”መኪናን በአዲስ አበባ እያሽከረከሩ መታየትን ሌላም ሌላም ልጆች ይወልዳል።
አምባገነኖች እራሳቸው በምዘውሩት የፀረ ሙስና ኮሚሽን እንዳኝ የሚሉት ጉዳቸውን ስለሚያውቁት ነው።አምባገነኖች የነፃ ሚድያን እንደ ጦር የሚፈሩት እውነተኛው የ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ነፃ ሚድያው ስለሆነ ነው።ነፃው ሚድያ እያንዳንዱ ባለስልጣን ከበላው እራት እስከ ቁርስ ድረስ ለሕዝቡ እንደሚዘግብ እና ማን የህዝብ አገልጋይ ማን ተገልጋይ መሆኑን ፍንትው አድርገው ስለሚያሳዩት አይፈልጉትም።ለእዚህ ነው እንደ እነ እስክንድር ያሉትን የነፃ ጋዜጠኛ ተምሳሌቶችን ”አሸባሪዎች” እያሉ እስከ እድሜ ልክ እስራት የሚፈርዱባቸው ከአስተዳደራዊ በደል ባለፈ የሙስናውን ጎራ እንዳይነካኩ ከመፍርዓትም ነው።
ሙስና በኢትዮጵያ ከግለሰብ ደረጃ አልፎ የመንግስት የአጠቅቀም ወይንም የአሰራር ስርዓት (system) ሆኗል
በኢትዮጵያ መንግስት ዘንድ ሙስና አሳፋሪ ጉዳይ እንዳልሆነ ብዙ ማስረጃ መጥቀስ ይቻላል። አዎን የፀረ ሙስና ኮሚሽን አለ።ሚድያው የሙስና መጥፎነትን ይነግረናል።አሁን አሁን ለምን እንደቀረ አይታወቅም እንጂ ቀድሞ የሚቀርቡት ማስታወቂያዎች እና ድራማዎች በደንብ የተጠኑ አስተማሪ መስለው ነበር።በፀረ-ሙስና ኮሚሽን ውስጥ በመርማሪነት የሚቀጠር ሰው ደሞዙ በወር እስከ አስራሁለት ሺህ የሚደርስ፣ የሚሄድበት እና የሚዝናናበት ቦታ ሁሉ የታወቀ መሆን እንዳለበት የቅጥር መስፈርቱ ያዛል።አመታት ሲቆጠሩ ግን ቀደም ብሎ የተወሰነ ስልጣን የነበረውን የፀረ ሙስና ኮሚሽን ጥርስ አልባ የማድረጉ ሂደት ከአቶ መለስ ተከታታይ ቁጣ ጀምሮ ኮሚሽኑ ውስጥ የተቀጠሩት የመጀመርያ ደረጃ መርማሪዎች ድንጉጥ እንዲሆኑ ማድረግ የተለመዱ ሆኑ።ሰራተኞቹ በውጭ የሚያዩት እና የሚሰራው አልጣጣም አላቸው።እናም ግማሾቹ በሙስናው ተነካኩ የተቀሩት ሀገር ትተው ሄዱ ሌሎቹ ሥራ ቀየሩ።
ከአንድ ሁለት ወር በፊት ይመስለኛል ሸገር ኤፍ ኤም የፀረ ሙስና ኮሚሽኑን ኃላፊ ” ከእናንተ ሰራተኞች መካከል በሙስና የሚታሙ አሉ ይባላል።እና የእዚህ አይነት ችግር ሲገጥማችሁ እንዴት ነው የምትፈቱት?” ተብለው ሲጠየቁ የመለሱት መልስ ”አዎን ይህ ያጋጥመናል በቅርቡም ተመሳሳይ ችግር አለ በቅርቡም ሁለት ሰራተኞች ላይ የተባለው ችግር ተገኝቷል።” ብለዋል። ይህ አንግዲህ ለሚድያ የተባለው እንጂ ወደ ዝርዝሩ ሲመጣ የባሰ ጉዳይ እንደሚኖር ይታመናል።
በእዚህ ሁሉ ነው እንግዲህ ሙስና ከግለሰብ አልፎ አሰራር ስርዓት(system) የሆነው።የአሰራር ስርዓት(system) የሆነ ሙስናን ለመዋጋት ግለሰቦችን ሳይሆን አሰራሩን(system) ማስወገድ ይሻል። አቶ መለስምሆኑአቶሃይለማርያምደጋግመው መንግስታቸው፣ባለስልጣኖቻቸው፣ነጋዴዎቻቸው ሁሉ ሙሰኛ እንደሆኑ በምክርቤት የተለያዩ ስብሰባዎች ነግረውናል።ይህ ማለት ችግሩ የግለሰቦች ሳይሆን የአሰራሩ ሙሉ መዋቅር -የመንግስት ችግር ነው ማለት ነው።የአሰራር እና የጠቅላላ የመዋቅር ችግር ደግሞ በጥገናዊ ለውጥ አይስተካከልም።ሙሉ በሙሉ የፖሊስ ለውጥ በማድረግ እና ስርዓቱን በመቀየር ብቻ ይፈታል። ይህ በእርግጥ ለመንግስት ከባድ ሊሆን ይችላል።ለሕዝቡ ግን ከባድ አይደለም። ምክንያቱም የሙስና ውጤት ልጆች በሀብት ከመምነሽነሽ በቀር ሌሎቹ አብረውት ስለሚኖሩ ያውቃቸዋል።እናም የሙስና ዋናውን ግንድ የመንግስትን መላውን መዋቅር ትተን ግለሰቦችን አንንቀስ።ግንዱን ትተን ቅርንጫፎችን አንቀነጣጥብ።በአደባባይ ሙስና እንደፈፀሙ የተናገሩ ግን በፈረንጁ አፍ ”ሶሪ” መሰል ንግግር አድርገው የሚኖሩባት ሀገር ውስጥ መኖራችንን አንዘንጋው።
በዘመነ ኢህአዲግ ፓርቲው ሙስና መኖሩ ትዝ የሚለው ሊያስወግዳቸው የሚፈልጋቸው ባለስልጣናት ሲኖሩ ወይንም እንደ ሰሞኑ አይኑን ያፈጠጠ ሪፖርት በተለያዩ ሚድያዎች ሲገለፅ ነው።የውስጥ ሹክቻ በሙስና ማንኪይ ትገላበጣለች። ትናንት የታሰሩት ባለስልጣናት ጉዳይ ላይ ”ለምን አሁን?” የሚል ጥያቄ የቀረበለት የቀድሞው አዲስ ነገር አምደኛ ዘሪሁን ትናንት ከኢሳት ጋዜጠኛ መሳይ ለቀረበለት ጥያቄ የመለሰው መልስ ግን አንጀት ጠብ የሚል ሆኖ አግኝቼዋለሁ እናም በእርሱ ሃሳብ ልደምድም። ”የትናንቱ እስር ከሙስናው ጉዳይ ይልቅ ፖለቲካው ድምፀቱ ነው የሚሰማኝ” ነበር ያለው።አበቃሁ
ጌታቸውኦስሎኦስሎኦስሎ
‹‹አንተ አታውቀንም! እኛ ነን የምናውቅህ››
‹‹የት ነው የምታውቁኝ? ማለቴ በምን መልኩ…››
ጉምሩክና ገቢዎች ሚኒስትር ሲቀላቀሉ ኦህዴድ ቦታውን እንዲያጣ የተደረገው በቀጥታ በአቶ መለስ ትዕዛዝ እንደነበር ይጠቁማሉ።
No comments:
Post a Comment