"ቴዎድሮስ አድሃኖም ህገወጥ ኢትዮጵያውያን እንዲያዙ የተስማማበት ሰነድ አለን"የሳኡዲ ባለስልጣናት
በሪያድ የዛረው ሰልፍ የሚመጣውን አደጋ በመፍራት ተበትኗል::
"ቴዎድሮስ አድሃኖም ህገወጥ ኢትዮጵያውያን እንዲያዙ የተስማማበት ሰነድ አለን"የሳኡዲ ባለስልጣናት
አምስተኛ ቀኑን የያዘው የሳኡዲ ጸረ ኢትዮጵያውያን ዘመቻ እንደቀጠለ ሲሆን ሁኔታዎችን ለመፍታት የተደረጉ ጥረቶች ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግስት እና የቆንስላው ዲፕሎማቶች በሰርኡት ስህተት መስመር ሊይዝ አልፈለገም:: እንደ ሳኡዲ ባለስልጣናት አነጋገው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም ባደረጉት ጉብኝት ሃገራቸው ህገወጥ ኢትዮጵያውያንን እንዲያስወጣ እና በምትኩ 40,000 ህጋዊ ስደተኞችን እንደሚልኩ የፈረሙበትን ማስረጃ ይዘዋል:: በሪያድ መንፉሃ ወደ ሃገራችን ስደዱን በሚል መንፉሃ ባንክ አልራጅህ አካባቢ በርካታ ኢትዮጵያውያን መንግስት የወሰደውን እርምጃ ተቃውመው ሰልፍ መውጣታቸው ተሰማ። እንደ አረብ ኒውስ ዘገባ መሰረት በሰልፈኞች በተወረወሩ ድንጋዮች አንድ የሳውዲ ዜጋ መሞቱንም ዘግቧል።
እነዚሁ በነዋሪዎች ድብደባና በደል የደረሰባቸው ኢትዮጲያውያን ወደ ሪያድ ኢምባሲና ኮሚኒቱ መስሪያ ቤት በእግራቸው ያመሩ ሲሆን መንፉሃ አካባቢ የቀሩት ከፖሊስ ጋር ባደረጉት ግጭት አንድ የፖሊስ መኪና እንደተሰበረ የአይን እማኞች ገልጸውልኛል።
# Minilik Salsawi#
No comments:
Post a Comment