Sunday, November 3, 2013

ህልም አለኝ

እህእህ አለች እማማ

እህ እህ አለች ሃገሪ
ተተብትቦ በያዛት በነካሳት አውሪ
ሴት እናት እህት ናት
ሴት ያ ገር እመቤት
የፍጡራን ሚስጥር እምብርት
ካስማ ማገር አንድነት
ገና ዛሬ ውልሽ ተፍቶ
ክብርሽ ዝናሽ ተቀምቶ
አሳር ግፍ ሲውርድብሽ
ቤት ማጀቱ ሴጎድልብሽ
ተጥለሻል በያገሩ
ገረድ ለትሆኝ ለቱጃሩ
ክብርሽ ና እምነትሽን
በዘረኞች ተከምተሽ
ከንቱ ሆነሽ ያለ ቅሪት
በሰው ሃገር ትኖራለሽ
ስድት ሆነ ያንቺ እጣ
ሆንሽ ቀረሽ ክብሩን ያጣ
ገና ህልም አለኝ የእውነት
ሴት እናት ልትሆን ቃሏየሚሰምርበት
ሲነሳ ምንሽር ሲወለወል አልቢን
ሃዝባዊ ሃይል ሆ ሲል
ሲቀርብ የድል ቀን
እ ውነትም ህልም አለኝ
እ ውነትም ራዕይ አልኝ
እናትም እህትም ሃገርም ነኝና
በቅርብ ይታየኛል የነጻነት ፋና
ህዝባዊ ሃይል ነው የድል መሰረቱ
ከፋፋይ ጉጅሌን የማስደፋ አንገቱን
ህልም አልኝ ሃገሬ ቅርብ ነው ይነጋል
በG7 ሃይል ጠላትሽ ይወድቃል


ለ ምለም

No comments:

Post a Comment