Monday, October 14, 2013

እኒህ አባት ሐሙስ በእለተ ዒድ ፖሊስ አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ ባደረሰባቸው ከፍተኛ ድብደባ ተዳክመው ይታያሉ፡፡ በእለቱ ከአፋቸው ደም ይፈስ እንደነበር የአይን ምስክሮች ገልጸዋል፡፡ ወደ ሆስፒታል በእለቱ የተወሰዱት እኒህ አባት አሁን ያሉበትን ሁኔታ ማወቅ አልተቻለም፡፡ እኒህን አባት ጨምሮ በርካቶች የዒድ የደስታ እለታቸውን በነፍስ ውጪ ግቢ እንዲያሳልፉ ተገደዋል፡፡ ዜጎች በጅምላ ጥቃት እንዲፈጸምባቸው ያዘዛችሁ ገዢዎቻችን ሆይ! በእኒህ አባት ላይ የተፈጸመው በኢትዮጵያውያን ሙስሊም አባቶች ላይ ሁሉ የፈጸማችሁት ነው፡፡ በእኒህ አባት ልጆች፣ በእኒህ አባት ቤተሰቦች፣ በእኒህ አባት ኢትዮጵያዊ ወገኖች ላይ ሁሉ የፈጠራችሁት የፍርሃት ስሜት አይደለም፤ የፈጠራችሁት ቁጭት ነው፡፡ ክስተቱ ኢ-ፍትሃዊነትን አምርረን አንድንጠላ ያደርገናል እንጂ ወደ ፈጽሞ ኃላ አያስብለንም፡፡ በእኒህ አባታችን ላይ የተፈጸመው በደል በሁላችንም ላይ ተፈጽሟል፡፡

No comments:

Post a Comment