Tuesday, December 3, 2013

በአዲስ አበባ ከተማ ለ 2ተኛ ጊዜ ታላቅ ገድል ተሰርቶ አደረ፡፡

     Free our heroes በአዲስ አበባ ከተማ ለ 2ተኛ ጊዜ ታላቅ ገድል ተሰርቶ አደረ፡፡ FOH_News አዲስ አበባ ከተማ ሰኞ ማታ በድጋሚ ለ 2ተኛ ጊዜ በግራፊቲ ፅሁፎች አሸብርቃ አደረች፡፡ እሁድ ለሊት የተጀመረው በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ የሙስሊሙን የትግል መፈክሮች መፃፍ በትላንትናው እለትም ቀጥሎ ውሏል፤ትላንትና ሌሊት አለም ባንክ እና አካባቢዋ በግራፊቲ ጽሁፎች አሸብርቃ ማደሯን የ “FOH” ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በትላንትናው እለት በአለም ባንክ እና አካባቢዋ ላይ ተጽፈው ከነበሩት ጽሁፎች ውስጥ ድምፃችን ይሰማ፤ ኮሚቴው ይፈታ፤ህገ መንግስት ይከበር፤ትግሉ ይቀጥላል የሚሉት ዋነኞች እና ተጠቃሾቹ እንደነበሩ የ“FOH” ምንጮች ገልጸዋል፡፡፡ ከትላንት ወዲያ እሁድ እና በትላንትና እለት በርካታ ቦታዎች ላይ የተፃፉት የብዙሀኑን ትኩረት ከመሳባቸውም በላይ ህዝበ ሙስሊሙ ላቀረባቸው ስላማዊና ህገ -መንግስታዊ ጥያቄ ማንኛውንም መስዕዋትነት ለመክፈል ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየ ሆኖ አልፏል፡፡ መንግስት ጥያቄዎችን ከመመለስ ይልቅ በሀይል ለማፈን እየተሯሯጠ ባለበት በዚህ ሰዐት ህዝበ ሙስሊሙ የተለያዩ የሰላማዊ ትግል ስልቶችን በመጠቀም ትግሉን በሀይል ማፈን እንደማይቻል በመገኘት ላይ ሲሆን የመንገድ ላይ ፅሁፍ (Graffitis) የሰላማዊ ተቃውሞ መግለጫ መንገድ ሲሆን እሁድ ለሊትም በርካታ የመዲናችን አካባቢዎች ላይ ህዝበ ሙስሊሙን ለአዲሱ ሰለማዊ ትግል ራሱን እንዲያዘጋጅ የሚያስጠነቅቁ እና የሙስሊሙን ጥያቄዎች በሚያስተጋቡ ጽሁፎች አሸብርቃ ማዳሯ የሚታወስ ነው፡፡ ኮሚቴዎቻችን ተፈተው ጥያቄዎቻችንን ሳይሸራረፉ እስኪመለሱ ድረስ ትግላችን ይቀጥላል፡፡ ፍትህ ለኮሚቴው!! ፍትህ ለኢትዬጵያ ሙስሊም!! አላሁ አክበር!! ================================= የኢትዬጵያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ትግል 24 ሰአት የሚዘግበው ፔጅ ላይክ በማድረግ ይቀላቀሉ:: ==> https://m.facebook.com/freeourhero ==> https://www.facebook.com/freeourheroImage

No comments:

Post a Comment