
እንግዳችን የሺወርቅ ምህርቴ ትባላለች። የአልጋ ቁራኛ ከሆነች አንድ አመት አለፋት። የሺወርቅን ቅስም የሰበረው አደጋ ከመድረሱ በፊት ተወልዳ ካደገችበት ጎንደር ከተማ ወደ አዲስ አበባ ሄዳ ስራ እየሰራች ቤተሰቧን መርዳትም ችላ ነበር። ይሁንና የ 27 ዓመቷ የሺወርቅ የአንድ ቀን ገጠመኟ የህይወት ጉዞዋን ወዳልገመተችው አቅጣጫ ቀየረው። ለበርካታ ወራት ሆስፒታል ተኝታለች። ህክምናዋን መከታተል እንድትችል ስትልም በአዲስ አበባ በተከራየችው ቤት ትኖራለች። እናቷ ከጎንደር ሊያስታምሟት ሄደው አብረዋት ቀርተዋል። አልተሻላትም፤ አይኗን ስትከድን ትዝ የሚላት አደጋው ነው።
ከፍተኛ ስነ ልቦናዊ ጉዳትም ደርሶባታል።
ህይወቷን ስለቀየረው አደጋ አጫውታናለች። ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።
ልደት አበበ
audio http://www.dw.de/popups/mediaplayer/contentId_17260407_mediaId_17260303
source.dw.de
No comments:
Post a Comment