Saturday, November 2, 2013

የኢትዩ ምህዳር ጋዜጠኞች ከቢሮ ታፍሰው ተወሰዱ

 በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ ክስ ቀርቦባቸው የፍርድ ሂደቱን ለመከታተል ሐዋሳ ከተማ ገብተው የተቀነባበረ የተባለለትን አደጋ ያስተናገዱት ምህዳሮች ጋዜጠኛ ኤፍሬም በየነን ኮሪያ ሆስፒታል በማስገባት የእለተ ማክሰኞዋ ጋዜጣ ለህትመት እንድትበቃ አደጋው ከፈጠረባቸው የስነ ልቦና ጫና እና የህመም ስሜት ጋር እታገሉ ዛሬ ማለዳ ቢሯቸው ገብተው ነበር፡፡ በድንገት ዘው ብለው የገቡት ከለገጣፉ መጣን ያሉ ደህንነቶች ጋዜጠኛ ሚልዩን ደግነው(ሚልዩን በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ ክስ የቀረበበትና ደረቱ ላይ አደጋ ያስተናገደ ጋዜጠኛ ነው) እና ጸሐፊ ቢሮ ውስጥ የነበሩ ሌሎች ጋዜጠኞችን በመኪና በመጫን ወስደዋቸዋል፡፡ጋዜጠኛ ጌታቸው በአጋጣሚ ከቢሮ ወጣ ብሎ ስለነበር ደህንነቶቹ ባያገኙትም ወደ ተንቀሳቃሽ ስልኩ በመደወል እንደሚፈልጉት ነግረውታል፡፡ በለገጣፎ ተፈጸመ የተባለን ከፍተኛ የመሬት ምዝበራና የመልካም አስተዳደር እጦት ምህዳር ጋዜጣ በተከታታይ መዘገቧ አይዘነጋም፡፡ #the upcoming Africa media leaders forum in my mind

No comments:

Post a Comment