Saturday, October 26, 2013

‘ወደፊት እያሰብን ወደኋላ መሮጥ ተገቢ አይደለም። በመጣንበት መንገድ ብንመለስ፣ የተነሳንበት ቦታ ላይ ነው መልሰን የምንደርሰው። ‘ http://sebhatamare.files.wordpress.com/2013/10/entc3.jpg

የሽግግር ምክርቤት የራድዮ ርእሰ አንቀጽ – የሽግግር ምክርቤት የራድዮ ርእሰ አንቀጽ
— October 21, 2013
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሽግግር ም/ቤት ማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት በመረጠው የትግል ስልት
የመታገል መብቱን ያከብራል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሽግግር ም/ቤት አላማ ፤ በአገራችን እየተከሰተ
ያለው የፖለቲካ ሁኔታ አደጋ ሊያመጣ የሚችል በመሆኑ ቀድመን ለአደጋው እንዘጋጅ ከሚል መርህ
ውጪ ሌሎች እንዳይደራጁና ድምፃቸውም እንዳይሰማ ጥረት አያደርግም፤ ፍላጎቱም የለውም።
በአንዳንድ የአሜሪካና የአውሮፓ ከተሞች የሚታዩት ሁኔታዎች ግን የተገላቢጦሽ ሆነዋል። ሰላማዊ
ትግልን የሚኮንኑና ከነሱ ድርጅት ውጪ በሌሎች ድርጅቶች የሚደረጉ የትግል እንቅስቃሴዎችን ሁሉ
የሚያንኳስሱ ተግባራት በተለያዩ ዘዴዎች በመገለፅ ላይ ናቸው። የፈለገው የፖለቲካ ድርጅት
በመረጠው የትግል ስልት ይታገል እንጂ ፤ በአገር ቤት የሚደረግን ሰላማዊ ትግል አጋዥነት ወይም
ሌሎች ድርጅቶች የሚያደርጉትን ተጋድሎ አስተዋፅኦ የሚክድ አንድም ድርጅት ይኖራል ብለን
አንጠብቅም ። የሚከተሉት የትግል ስልት ያዋጣል አያዋጣም ሌላ ጥያቄ ነው ፤ ቢያንስ ያደክማል።
አለበለዚያ የነርሱ የትግል ጎዳና ብቻ ትክክል ለመሆኑ ከፈጣሪ ማህተም ያስመታ አንድም ድርጅት የለም ።
በአለማችን ዛሬ በአመጽ ብቻ የሚያምኑ ድርጅቶች እንኳ በህቡዕ የተደራጀ ህዝባዊና ሰላማዊ
እንቢተኝነት አንዱ የትግል ስልታቸው እንደሆነ እየተናገሩ ነው። ሁሉም ባመነበትና በመሰለው መንገድ
ለፍትህ፤ ዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር ትግል ጠጠር እስከወረወረ ድረስ አጋር የማይደረግበት ምንም ምክንያት የለምና “እናደንቃለን” ሲሉ እየተደመጡ ነው ። ታዲያ የሃገርቤቶቹን ሰላማዊ
ታጋዮችም ሆነ ሌሎችን ለማበረታታትና ለመደገፍ መለመጡ ከየት መጣ? ለመሆኑ በሊትዮጵያ ውስጥ
የሰብአዊ መብት መረገጥና የፖለቲካ አፈና መኖሩን በተጨባጭ አሳዩ ብንባል ምንድነው የምናደርገው?
Aministy International , Freedom House , CPJ , Pen International, HRW , Reporters Without Borders , እያልን አይደለም እንዴ የምንጠቅሰው?
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ርእዮት አለሙ፣ ውብሸት ታየ፣ ፖለቲከኛው አንዷለም አራጌ፣ በቀለ ገርባ
ሃይማኖተኛው አቡበከርን ወዘተ አይደለም እንዴ የምንጠቅሰው? እነዚህ እነማን ናቸው? አፈና
ውስጥም ቢሆን፤ እንታገላለን ሲሉ ሰለባ የሆኑ የሰላማዊ ትግል አርበኞች አይደሉምን? በትጥቅ ትግል
ወስጥ የታሰረ ወይም የተገደለ ወገን እኮ እንደማስረጃ ሊቀርብ አይችልም። ታዲያ በሃገር ወጥና በውጪ
ያሉ የዲሞክራሲ ሃይሎች መያያዝ ፣ መተባበርና መደጋገፍ ይገባቸዋል እንላለን።
በእኛ እምነት በሃገርቤት ውስጥ በፈለገው ደረጃ የሚካሄድ ትግል፣ አገዛዙን በመሳሪያ ለመፋለም
ለቆረጡ እንኳን ለድላቸው ተኪ የሌለው ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ነው። አንድ የፖለቲካ ንቅናቄ
ወይም ድርጅት ውስጥ መኖር ወይም አለመኖር ሁለተኛ ጉዳይ ነው። በግለ-ሰብ ደረጃ ወስኖ
ለሃገር ነፃነትና አንድነት ተግባራዊ አስተዋፅኦ መነሳት፣ ቁም ነገሩ እሱ ነው።
ወድ ወገኖች “ ያልተባበር የተቃዋሚ ትግል ግቡን አይመታምን”  እየዘመርን በየድርጅቶቻችን ካርቶን
ውስጥ ተወሽቆ መቅረትስ እስከመቼ? በአገር-ቤት ያሉ ድርጅቶች “ሚሊዎኖች ለነፃነት” በሚል መርህ
ባለፉት ሶስት ወራት ከአገዛዙ ጋር ሲተናነቁ ታይተዋል ። ከሰማኒያ ሽህ ያላነሰ ህዝብ በአዲስ አበባ፤
በብዙ ሺህዎች ደግሞ በየክልሉ ለሰልፍ አውጥተዋል። ለምን ቤተ-መንግስት አልገቡም ካልተባለ
በስተቀር፤ የባርነትን ድባብ መግፈፍ ጀምረዋል ። ይህ ተጠናክሮ ይቀጥል ዘንድ ደግሞ ለእነርሱ
መስዋእትነት የግድ የኛ ድጋፍ ያሻቸዋል። እያንዳንዱ የፖለቲካ ድርጅት ነፃ የሚያወጣት የራሱ ብቻ
የሆነች ኢትዮጵያ የለችውም። የኔም ናት የሚሉ ሌሎችም አሉ። በመሆኑም የሚያገባን ሁሉ
ተግባብተን ካልታገልን፤ ድል ይርቃል፤ ተጠቃሚውም የወያኔ አገዛዝ ብቻ ይሆናል። አገዛዙ ላለፉት
ሃያ ሁለት አመታት የፈረጠመው በኛ አለመተባበር ነው ካልን፤ ከሃያ ሁለት አመታት በኋላ፤ መፍትሄው ሊጠፋን አይገባም። ወደፊት እያሰብን ወደኋላ መሮጥ ተገቢ አይደለም። በመጣንበት
መንገድ ብንመለስ፣ የነነሳንበት ቦታ ላይ ነው መልሰን የምንደርሰው።

No comments:

Post a Comment