Tuesday, October 1, 2013

የአንድነት ፓርቲ ሰልፍ ተጠናቀቀ (ቀጥታ ሽፋን) clickhabesh | 29 בSeptember 2013 | 0 Comments

1:05  PM   (ኢትዮጵያ ሰዓት)
addis_udj2«ፖሊሶች ከአቅማቸው በላይ ነዉ። ሕገ መንግስትና በሕግ ሳይሆን በመመሪያ ነዉ የሚተዳደሩት። ሕዝቡ ሰላማዊ ሆኖም ከመርካቶ፣ ከሳሪስ፣ ከሜክሲሶ ሕዝቡ እንዳያልፍ ማድረጋቸው የፍርሃታቸው ጥግ የት እንደደረሰ የሚያሳይ ነዉ። የሰዉን ሁኔታ የተረዱ ይመስለኛል» አቶ ግርማ ሰይፉ

«ለአይንህ መጨረሻዉን የማታየው ሕዝብን ማየት ያሰደስታል። ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ በራሱ  ግብ አይደለም። ላለፉት 3 ወራት በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል ስናደርግ የነበረው የመጀመሪያ ፌዝ አጠናቀናል። የመጀመሪያዉን ፌዝ አጠናቀቅን ስንል ፣ የትግሉ ሂደት ተጠናቀቀ ማለት አይደለም። ከመጣነዉ ይልቅ የሚቀረን እንደሚረዝም ነዉ የምናስበዉ» አቶ ሃብታሙ አያሌው። አቶ ሃብታሙ በቅርቡ በጸረ-ሽብር ሕጉ ዙሪያ በኢቲቪ በተደረገው ክርክር አንድነት ወክለዉ ቀርቦ የነበረ ወጣት የአንድነት አመራር አባል ነዉ።


AFP, Bloomberg News, AL JAzria … [Al Jazeera] የመሳሰሉ በርካታ የዉጭ ጋዜጠኞች ተገኝተዉ ነበር። ፖሊሶች መንገዱን መዝጋታቸውን ታዝበዋል።  «ሰልፉ አልተፈቀደም እንዴ ? ከተፈቀደ ለምንድን ነው መንገድ የሚዘጉትም ?  ህዝቡ እንዳይቀላቀል ለምን ያደርጋሉ ? » የሚሉ ጥያቄዎችን አንስተዋል።

12:50  PM   (ኢትዮጵያ ሰዓት)
የሰላማዊ ሰልፉ መርሃ ግብር ተጠናቋል። ምንም እንኳን አገዛዙ አይን ባወጣ መልኩ የሕዝብን መብት ቢረግጥ የአዲስ አበባ ሕዝብ ምን ያህል የሰለጠነ እንደሆነም አሳይቷል። አንድ ሰው ሳይጎዳ፣ አንዲት ጠጠር ሳይወረወር ሰልፍ በሚያስደንቅ ሁኔታ ተጠናቋል።

ከመርካቶ፣ ከሳሪስ ልደታ የሚመጡ መንገድ ተዘግቶ መምጣት አልቻሉም። በመቶ ሺህ የሚቆጠረዉ በቀበና አደባባይ የተሰበሰበው ሕዝብ በአጭሩ ከአንድ አካባቢ የተሰበሰበዉ ህዝብ ነዉ። ፖሊሶች መንገድ ባይዘጉና፣  ከሁሉም የአዲስ አበባ ክፍሎች ሕዝቡ እንዲያልፍ ቢደረግ ኖሮ ሚሊዮኖች ሊገኙ የሚችሉበት ሁኔታ ነበር።
ሰልፉን ለመዝጋት ዶር ነጋሶ ንግግር አድርገዋል። ከሁለት ሳምንታት በፊት 70 አመታቸውን እንዳከበሩ የገለጹት  ዶር ነጋሶ የተሰማቸዉን ከፍተኛ ደስታ ገልሰዋል።
«እዚህ ያላችሁ አብዛኞቻችሁ የልጄቼ ልጆች ልትሆኑ ትችላላችሁ። ተስፋ የማድረግባችሁ ናችሁ» ብለዋል ዶር ነጋሶ
በመጨረሻ የሰልፉ አዘጋጆች መንገዱን ለዘጉባቸው ፖሊስ ሰራዊቶች ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።



12:30  PM   (ኢትዮጵያ ሰዓት)

 «ፖሊሶች በሚኒሊክ ሆስፒታል አድርጎ ወደ ጃን ሜዳ የሚሄደዉን መንገድ ብቻ ነበር የከፈቱት። ነገር ግን  ሕዝቡ እየገፋ ወደ ቀበና አደባባይ ደርሷል። በቀበና አደባባይ፣  ከመቶ ሺህ በላይ ሕዝብ ይገኛል። በዚያ የአንድነት አመራር አባላት ንግግር እያደረጉ ነዉ። ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል ከሚወስደው መንገድ ዉጭ ያሉ ሌሎች መንገዶች በሙሉ በታጠቁ ኃይላትና አመጽ በታኞች በመዘጋቱ፣ ሰልፉ በዚያዉ በቀበና አደባባይ ሳይጠናቀቅ አይቀርም።
አቶ ትእግስቱ አወሎ የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ጸሃፊ ንግግር አድርገዋል። በህዝቡ ያላቸውን ኩራት ገልጸዋል። «ነጻነት እስኪሰፍን ትግሉ ይቀጥላል» ብለዋል።
የአንዷለም አራጌ መልእክት ተነቧል።
«ብዙ ፈተናዎችንና አፈናዎችን አልፋችሁ በምታደርጉት በዚህ ታላቅ ሰላምዊ ሰልፍ በካል ባለገኝም በመንፈስ ከጎናችሁ ነኝ። በዚህም ታላቅ ደስታ ይሰመኛል። ፍርሃትን  ያላሸነፈ በአዋጅ ነጻ ሊሆን አይቻልም። ፍርሃት ያላሸነፈ ለልጆቹ ነጻ አገር ሊያወርስ አይችልም። ፍርሃትን አሸንፋችሁ ድምጻችሁን ማሰማታችሁ ትልቅ ድል ነዉ። እኔ እዚህ ያቆመኝ (እሥር) የነጻነት ናፍቆት ነዉ»  አንዱዋለም አራጌ
ኢንጅነር ኃይሉ ሻዉል የክብር እንግዳ ተደርገዉ ተጋብዘው ነበር። ግን በሕመም ምክንያት በአካል አልተገኙም። ነገር ግን በሰልፉ የሰማቸዉን ደሳት ገልጸዋል።

ከነበቀለ ገርባም የተላለፈ መልእክት ተነቧል።
የሕዝብ ማእበል – ፖሊስ ሕዝቡ ሰልፍ እንዳይቀላቀል ሲያከላክል (video)
11:55  AM   (ኢትዮጵያ ሰዓት)

«አስተዳደሩ አዞናል። እባካችሁ ችግር ዉስጥ አትክተቱን» በሚል ፖሊሶች ልመና አድርገዋል።  የአገዛዙ ፓርቲዎች ተደብቀዉ ህዝቡን እና ፖሊሲን ለማጋጨት እየሞከሩ ነዉ። ግን የአንድነት አመራሮች በአገዛዙ ወጥመድ ዉስጥ ላለመግባት በማስተዋልና በእርጋታ ሕዝቡን እየመሩት ነዉ።

«ሃሩር የሆነ  ጸሃይ ነዉ። ሕዝቡ ሂድ ስንለው ይሄዳል። ተቀመጥ ስንለው ይቀመጣል። በጣም ጨዋና ሰላማዊ ህዝብ ነዉ» አቶ ሃብታሙ አያሌዉ::
መፈክሮች!
ሕዝብ አሸማቆ መግዛት አሸባሪነት ነዉ !
ኢሕአዴግነት ከኢትዮጵያዊነት አይበልጥም!
አንድ ናት አገራችን !
ሙስና የስርዓቱ መገለጫ ነዉ !
መብታችንን ከኢሕአዴግ አንጠብቀም !
ይሄ ስርዓት እስኪለወጥ ትግላችን ይቀጥላል።

11:50  AM   (ኢትዮጵያ ሰዓት)
ዶር ነጋሶ «ከቀበና ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል አድርገን ወደ ጃን ሜዳ እንድንቀሳቀስ ነዉ የሚፈልጉት። ይሄ ደግሞ አይሆንም። አደባባዩን ለመዞር እየሞከርን ነዉ። ከዚያ ወደ አራት ኪሎ እንዞራለን።  ከፖሊስ ጋር ለመደባደብ አንፈልግም። እኛ ሰላማዊ ነን»  ዶር ነጋሶ የአንድነት ሊቀመንበር::
«ይሄን ሰልፍ ፖሊሶች እየዘጉት ያለዉ በአስተዳደሩ ቀጥተኛ ትእዛዝ ነዉ። ተጠያቂዉ አስተዳደሩ ነዉ» አቶ ዳንኤል ተፈራ።


11:30  AM   (ኢትዮጵያ ሰዓት)
የሰው ግድግዳ ላይ ያለ አግባብ ፖስተር ለጥፈሃል በሚል የታሰረው የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዳንኤል የሚከተለዉን አስተያየት ሰጠዋል፡

«ትላንት የነበረኝ ስጋት መታሰሩ ሳይሆን፣ ለብዙ ጊዜ የሰራንበት ሰልፍ ላይ ላልገኝ ይሆን የሚል ነበር ስጋቴ። ከምሽቱ ሁለት ሰዓት በዋስ ፈተዉኛል። በዚህ ታላቅ ሰልፍ  መገኘቴ በጣም አስደስቶናል። በኢትዮጵያ ሕዝብ በጣም ኮርቻለሁ። ከመቶ ሺሆች በላይ ሕዝብ ነዉ አሁን የሚገኘው። በመስቀል አደባባይ ቢኬድ ደግሞ አስቡት ምን ያህል ሊሆን እንደሚችል። አገዛዙ ለህዝብ የማይገዛ መሆኑን፣ ህግን የማያከበር መሆናቸውን  አሳይተዋል። ወደ ዘጠኝ አደባባዮች አማራጭ ብንሰጣቸውም አንዱን እንኳ መፍቃደ የመቻል አቅም የሌላቸው ናቸው። »
11:20  AM   (ኢትዮጵያ ሰዓት)
ብዙ ሕዝብ በሰልፉ ተገኝቷል። በየቦታዉ መንገዶች በፖሊሲ በመዘጋታቸው እጅግ በጣም ብዙ ሕዝብ ገና ሰልፉን አልተቀላቀለም። በመስቀል አደባባይ አካባቢም ብዙ ህዝብ ይገኛል። ሰልፈኞቹ ወደ ቀበና አደባባይ አካባቢ ናቸው። አገዛዙ መንገዶችን ከለቀቀና ዜጎችን ሰልፉን እንዲቀላቀሉ ካደረገ ሰልፈኛው ከቁጥጥር ዉጭ ይሆንብናል የሚል ፍራቻ ያላቸው ይመስላል። ሰላማዊ የሆነ የራሱን ሕዝብ እንደዚህ የሚያፍን መንግስት፣ በዚህ ዘመን መኖሩ ያሳዝናል።
udj_addis4
11:05   AM   (ኢትዮጵያ ሰዓት)
ሕግን ማስከበር፣ ሕዝብን ማገልገል የሚገባቸው ፌዴራሎች የሕዝብን ድምጽ ለማፈን ፣ ሕዝቡ እንዳያልፍ ለማድረግ፣  እጅ ለእጅ ተያይዘው መንገድ ሲዘጉ !!ሕዝቡ ግን እንደ እነርሱ እንዳልሆነ ለማሳየት «ፖሊስ የኛ» እያለ ነዉ። ፖሊሶች ይሄን እያዩ ከሕሊናቸው ጋር እንደሚነጋገሩ ነዉ።

«መንግስት በአስቸኳይ ብሄራዊ እርቅ ይጠራ !  ነጻነታችንን ከኢሕአዴግ አንጠበቅም !!!!» ከተሰሙት መፈክሮች መካከል !!!  ሰልፈኞቹ ቀናባ መንገዱ ላይ ተቀምጠዋል። ሰልፉ ደምቋል። ህዝቡ በብዛት እየተቀላቀለ ነዉ።

11:00   AM   (ኢትዮጵያ ሰዓት)
የርዮት አለሙ እህት «

የርዮት መታሰር ቢያሳዝነኝም። በሺሆች የሚቆጠሩ ርዮቶችን እንዳፈራች ነዉ የሚያሳየዉ። የሕዝቡ ስሜት በጣም የሚያ
ዶ/ር ነጋሶን ጨምሮ ሁሉም የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የ33ቱ ፓርቲዎች አመራሮች ሰልፉን ለማደናቀፍ ከተኮሎኮሉት የፖሊስና የደህንነት ሀይሎች ጋር ፊትለፊት ተጋፍጠዋል፡፡ ዶ/ር ነጋሶ ሰልፉን ሲቀላቀሉ ህዝቡ “ነጋሶ ማንዴላ!! ነጋሶ ማንዴላ!!” በማለት ተቀብሏቸዋል፡፡
ወጣት ሳሙኤል “ ነጻነትን ስለተጠማሁ ነዉ እዚህ የመጣሁት

10:55   AM   (ኢትዮጵያ ሰዓት)
ታላቅ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ነዉ። ሰልፉ በጣም ደምቋል። ፖሊሲ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደዉን መንገድ ዘግቷል። ሕዝቡ እየተንቀላቀለ ነዉ። ወደ መስቀል አደባባይ እንዳይኬድ ፖሊስ ስለዘጋ የፓርቲዉ አመራሮች ለጊዜዉ ወደ ቀበና አደባባይ ቀስ በቀስ ለመሄድ እየገፋ ነዉ። ከዚያም ወደ አራት ኪሎ ለመሄድ ሙከራ ይደረጋል።

ወደ ጃንሜዳ የሚወስደው መንገድ ክፍት ነዉ። አገዛዙ ጃንሜዳ ሄዳችሁ ሰልፍ አደርጉ እያለ ነዉ። ፓርቲዉ ግን ሰልፍ በጃንሜዳ ማድረግ ሕግን መጣስ እንደሆነ በመጥቀስ  ፣ «ሕግ እንዲከበር እናደርጋለን እንጂ ለሕግ ጥሰት አንተባበርም» በሚል የጃን ሜዳዉን ዉድቅ አድርገዉታል። የወታደራዊ ካምፕና ትምህርት ቤቶች በቅርበት ባሉበት ቦታ ሰልፍ መደረግ እንደማይቻል የሚጠቅሰዉን ሕግ በማጣቃስና በጃንሜዳ ትምህርት ቤቶችና ወታደራዊ ካምፖች በመኖራቸው ፣ በዚያ ስልፍ ማድረግ እንደማይታሰብ አሳዉቀዋል።

10:30   AM   (ኢትዮጵያ ሰዓት)
“ፖሊስ የሕዝብ ነዉ” እያሉ ሰልፈኞች እየጮሁ ናቸው። በጣም ብዙ ሕዝብ እየመጣ ነዉ። ወደ መስቀል አደባባይ ብዙ ሕዝብ እየሄደ ነዉ።

ፖሊሶችን ለማግባባትን ለማሳመን ሙከራ ቢደረግም ፌዴራሎች በጭራሽ ፍንክች አንልም ብለዋል። በሺሆዎች የሚቆጠሩ ወደ ሰልፉ እየመጡ ነዉ። ፖሊስ ወደ አደባባዩ እንዳይመጣ እያገደ ነዉ። አገዛዙ ረብሻ እንዲፈጠር የሚፈልግ ይመስላል። የአንድነት አመራሮችና ህዝቡ ግን በተቻለ መጠን ከፖሊስ ጋር ግጭት ላለማድረግ እየሞከረ ነዉ።ፖሊሶች  በየቦታዉ ወደ ሰልፉ የሚመጡትን እየበተኑ ነዉ።

ስደስት ነዉ። መስቀልአደባባይ ለሰልፍ አይመችም ነበር ያሉት። ግን ደመራ ሲብስራበት አይተናል። ይሄ የሕዝብን ድምጽ 
አቶ ትእግስቱ አወሉ፣ የብሄራዊ ምክር ቤት ዋና ጸሃፊ፣ የፓርቲዉ አመራር አባላት ስብሰባ አድርገዉ የፖለቲካ ዉሳኔ እንደሚወስዱ ገልጸዋል።

10:04   AM   (ኢትዮጵያ ሰዓት)
“የኢትዮጵያ ሕዝብ በኃይል አይንበረከክም! ሙስና የስርዓቱ መገለጫ ነዉ! የታሰሩ የሕሊና እስረኞች ይፈቱ! የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላማዊ ነዉ!” እያለ ሰልፈኞች ሰላማዊነታቸዉን  እና ጨዋነታቸውን እያሰሙ ነዉ።

ፖሊስ ሰልፉን ለማደናቀፍ ዘብ ቆሟል። ትራፊክ ፖሊሶችም ትራንስፖርት እንዳይኖር መኪኖችን እያስቆሙ ነው፡፡ ይህንን ሁሉ መሰናክል አልፈው ጀግኖቻችን በቦታው እየደረሱ ነው፡፡

ሰልፈኛዉ እንዲቀመጥ ጥሪ ቀርቧል። ፖሊሶች ወደ መስቀል አደባባይ አላሳልፍ ብለዋል። የሚያስገርም ነዉ።
ሰልፈኛዉ እንዲቀመጥ ጥሪ ቀርቧል። ፖሊሶች ወደ መስቀል አደባባይ አላሳልፍ ብለዋል። የሚያስገርም ነዉ።
 addis_udj2
9:50   AM   (ኢትዮጵያ ሰዓት)
ከኢትዮጵያ ጋር መስመር ማግኘት በጣም እያስቸገረ ነዉ። እስከአሁን ግን በደረሰዉ ዘገባ፣ ሕዝቡ ወደ ቀበና እየመጣ ነዉ። ከፓርቲዉ ጽ/ቤት አልፎ አስፋልት ላይ ደርሷል። ነገር ግን ወደ ቀበና የሚያመጣ ትራንስፖርት ሁሉ አገዛዙ አቋርጧል።  ሕዝቡ በእግር ነዉ የሚመጣዉ።  ፖሊስ አላሳልፍም እያለ ነዉ ያለዉ።  ወደ መስቀል አደባባይ አትሄዱም እያሉ ነዉ ፖሊሶቹ !!!! የአመራር አባላት ለማነጋገር እየሞከሩ ነዉ።
አንዲትም ጠጠር አትወረወርም! በሰላም ነዉ ሁሉንም የምናደርገዉ እያሉ ነዉ። ፖሊሶች እጅ ለእጅ ተያይዘው መንግዱን ዘግተዋል። ከአራት ኪሎ የመጡ ወደ ሰልፉ ለመቀላቀል የሚሞክሩትን፣  ፖሊሶች መንገዱን ዘግተዉ አላሳልፍ እያሉ ነዉ።

udj_addis1
9:50   AM   (ኢትዮጵያ ሰዓት)
ከኢትዮጵያ ጋር መስመር ማግኘት በጣም እያስቸገረ ነዉ። እስከአሁን ግን በደረሰዉ ዘገባ፣ ሕዝቡ ወደ ቀበና እየመጣ ነዉ። ከፓርቲዉ ጽ/ቤት አልፎ አስፋልት ላይ ደርሷል። ነገር ግን ወደ ቀበና የሚያመጣ ትራንስፖርት ሁሉ አገዛዙ አቋርጧል።  ሕዝቡ በእግር ነዉ የሚመጣዉ።  ፖሊስ አላሳልፍም እያለ ነዉ ያለዉ።  ወደ መስቀል አደባባይ አትሄዱም እያሉ ነዉ ፖሊሶቹ !!!! የአመራር አባላት ለማነጋገር እየሞከሩ ነዉ።
አንዲትም ጠጠር አትወረወርም! በሰላም ነዉ ሁሉንም የምናደርገዉ እያሉ ነዉ። ፖሊሶች እጅ ለእጅ ተያይዘው መንግዱን ዘግተዋል። ከአራት ኪሎ የመጡ ወደ ሰልፉ ለመቀላቀል የሚሞክሩትን፣  ፖሊሶች መንገዱን ዘግተዉ አላሳልፍ እያሉ ነዉ።

udj_addis19:40   AM   (ኢትዮጵያ )
9:50   AM   (ኢትዮጵያ ሰዓት)
ከኢትዮጵያ ጋር መስመር ማግኘት በጣም እያስቸገረ ነዉ። እስከአሁን ግን በደረሰዉ ዘገባ፣ ሕዝቡ ወደ ቀበና እየመጣ ነዉ። ከፓርቲዉ ጽ/ቤት አልፎ አስፋልት ላይ ደርሷል። ነገር ግን ወደ ቀበና የሚያመጣ ትራንስፖርት ሁሉ አገዛዙ አቋርጧል።  ሕዝቡ በእግር ነዉ የሚመጣዉ።  ፖሊስ አላሳልፍም እያለ ነዉ ያለዉ።  ወደ መስቀል አደባባይ አትሄዱም እያሉ ነዉ ፖሊሶቹ !!!! የአመራር አባላት ለማነጋገር እየሞከሩ ነዉ።
አንዲትም ጠጠር አትወረወርም! በሰላም ነዉ ሁሉንም የምናደርገዉ እያሉ ነዉ። ፖሊሶች እጅ ለእጅ ተያይዘው መንግዱን ዘግተዋል። ከአራት ኪሎ የመጡ ወደ ሰልፉ ለመቀላቀል የሚሞክሩትን፣  ፖሊሶች መንገዱን ዘግተዉ አላሳልፍ እያሉ ነዉ።

udj_addis19:40   AM   (ኢትዮጵያ ሰዓት)

No comments:

Post a Comment