Wednesday, October 2, 2013

ሰው እንደሚበላው ይሆናል፤ ክፍል ሁለት፡፡

Ethiopia Wake UP
ፍል አንድ ላይ ስለ ምግብና መጠጥ፣ ስፖርት፣ ጉርሻና አብሮ የመብላት ባህልን ባጭሩ አይተናል፡፡
አሁን እዚህ ሁለተኛውና የመጨረሻው ክፍል ላይ ደግሞ ዝርዝርና ተጨማሪ ምክሮችን እናያለን፡፡ የምግብ አይነት መቀያየሩን በተመለከተ ለምሳሌ ትላንት ስጋ፣ ዛሬ አሳ ነገ ደግሞ ፒዛ ብሎ ብዙ መጨነቅ በኔ አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡ ዋናው ነገር ግን ከተመረጠው ስጋ ወይም አሳ አይነት ጋር ምስርና ክክ፣ አትክልትና ፍራፍሬ በዛ አድርጎ ከተጨመረበት አንድ አይነት ምግብ በተከታታይ ለበርካታ ቀኖች ቢበላ ምንም አይደለም፡፡ መጠጥንም በተመለከተ ለምሳሌ ሁለት ሊተር ውኃ በሚይዝ ጠርሙስ አንድ ሎሚ ጨምቆ፣ አንድ መለስተኛ መጠን ያለውን ዝንጅብል በሰያፍ ቆራርጦና በውኃ ቀላቅሎ ቤት ውስጥ የተሰራ ለስላሳ ማዘጋጀት ይቻላል፡፡ ሰው የተለያየ ምርጫ ቢኖረውም ይህ አንድ ጥቆማ ነው፡፡ ሎሚና ዝንጅብል ደግሞ በሳይንስም ጤናማ ናቸው ይባላል፡፡ እውነቴን ነው ሎሚና ዝንጅብል በውኃ ከተቀላቀለ ከ15 ደቂቃ በኋላ ሲጠጡት በጣም ይጥማል፡፡ ጤናማም ነው፡፡ ያረካልም፡፡ ርካሽም ነው፡፡ ከሻይ ጋር ደግሞ ትንሽ ዝንጅብል በሰያፍ ቆራርጦ ከጨመሩ በሗላ ሻይ ጋር አዘውትሮ መጠጣት ይጥማል፡፡ ይጠቅማል፡፡ ጉንፋንም በቀላሉ አያጠቃም!!!!


ንደምታዩት በተቻለ መጠን ሰው ተፈጥሮአዊ የሆነ ነገር ቢጠቀም ጠቀሜታ አለው ለማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ውኃ፣ ዝንጅብል፣ ሎሚ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ወዘተ በፋብሪካ የተሰራ አይደሉምና፡፡ ሰወች ጊዜ ለመቆጠብም ይሁን በሌላ ምክንያት ማይግሮወይቭ ኦቭን እና የውኃ ማፍያ የመሳሰሉትን አዘውትረው የሚጠቀሙ አሉ፡፡ ይህ መጥፎ ወይም አደገኛ ነው ለማለት ሳይሆን ለምሳሌ በማይግሮወይቭ ኦቭን የተሰራ ወይም የሞቀ ምግብ ለዛውና ጣምናው በጣም ይቀንሳል፡፡ ለጥቂት ደቂቃ ቁጠባ ተብሎ በምግቡ እንዳንደሰት ያደርጋል፡፡ ለማንኛውም ሰው ልብ ካለ ነው ይህንን የሚያውቀው፡፡ የምግቡ ጣምናና ለዛ ከቀነሰ ደግሞ ሰው ድስት ወይም ብረት ምጣድ እንዲጠቀም እራሱን የቻለ ምልክት ነው፡፡ ውኋም ለማፍላት ጥሩ ማንቆርቆሪያ ወይም ጀበና ይሻላል፡፡ ውበትም አለው፡፡ ለኤሌትሪክም ሆነ ለቁሳቁስ እርካሽም ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜም ለምሳሌ ቤተሰቦች ለልጆች ወተት ለማሞቅ ወዘተ ማይግሮወይቭ ኦቭን ሲጠቀሙ ፍጥነት አለው፡፡ ያው ሰው እንደምርጫው ያደርጋል፡፡

ኛ በኢትዮጵያውያን ላይ ብቻ ሳይሆን በማንኛውም ዜጋ ላይ ጥራት ካለው ምግብ ከመብላት ይልቅ የቁሳቁስ ሃብት ላይ የሚያተኩሩ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ለምሳሌ ጥራት ያለው ምግብና መጠጥ ለመብላትና ለመጠጣት እድሉ ቢኖራቸውም እንደነገሩ የተገኘውን በልተውና ጠጥተው ከላይ ለሚታየው ለምሳሌ ለመኪና፣ ለልብስ፣ ልቤት ለመሳሰሉት ቅድሚያ የሚሰጡ ጥቂት አይደሉም፡፡ ሰው ቁሳቁስ ሲኖረው መጥፎ ነው ለማለት ሳይሆን መጀመሪያ ቅድሚያ መሰጠት ያለበት ወደ ሰውነት ውስጥ ለሚገባ እንጂ ከውጭ ለሚታየው ባይሆን ይመረጣል፤ ይጠቅማለም ለማለት ነው፡፡ በተለይ የሰው ልጅ ቢያንስ ሶስት ጊዜ መብላት ስላለበት ይህንን ትልቅና ሰፊ ፍላጎት ለመሸፈን የሚሸጠው ምግብ ባሰራሩ፣ በንጽህናውና በቆይታው ጤነኛ ይሁንም አይሁን የምግብ ነጋዴና አጭበርባሪው ጥቂት አይደለም፡፡ ንጽህናው፣ ይዘቱና አሰራሩ እቤት ውስጥ እንደሚሰራው አይደለም፡፡ በየቦታውና በየማዕዘኑ ንግዱ የጦፈ ነው፡፡ ስለዚህ ተጠቃሚው ጥንቃቄና መራጭ ከሆነ እራሱንም ይጠብቃል፡፡

ላው ደግሞ ቁርስ በደንብ መብላት ሰውነትንም ሆነ ሃሳብን ደግፎ ይውላል፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን ያው ሁሉም እንደአቅሙ ቢሆንም በተለይ ጥሩ የቁርስ ባህል አለን፡፡ ይዘቱና ጠቀሜታው የተለያየ ቢሆንም ለምሳሌ ቁርስ ላይ ፍርፍር፣ ዱለት የመሳሰሉት ስላሉ ጥሩና ከበድ ያለ የቁርስ ባህል አለን፡፡ ከተጠቀምንበት፡፡ ሃኪሞችም በቂ የሆነ ጥሩ ቁርስ መብላት ለልብ ትርታ መረጋጋት አስተዋጽኦ ያደርጋል ይላሉ፡፡ እኔ በበኩሌ ዱሮም ቢሆን ቁርሴን ግጥም አድርጌ ነው እምበላው፡፡ ሰው ቁርሱን ግጥም አድርጎ ከበላ ቢያንስ በኋላ ምሳ ለመብላት ብዙ አይቸኩልም፡፡ አንዳንድ ሰወች ቁርስ የማይዋጥላቸው እንዳሉ አውቃለሁ፡፡ ግን ቁርስ ለመብላት መለማመድና ጧትም ሰፋ ያለ ጊዜ መጠቀም ቁርስ ለመብላትም ሆነ እረፈደብኝ አልረፈደብኝም እያሉ ከመጨነቅ ያድናል፡፡

No comments:

Post a Comment