Tuesday, October 15, 2013

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ገና በጠዋቱ በጩሀት ቀልጣለች::

ተማሪዎች ከግቢ ዉስጥና ዉጭ ሆነዉ ጩሀታቸዉን እያሰሙ ነዉ::የከተማዉ ህዝብም በርቀት ትዕይንቱን እየተመለከተ ነዉ::የፌደራልና የክልሉ ፖሊሶች በየሰፈሩ እየተራወጡ ነዉ::ደብረ ማርቆስ ዉስጥ ፖሊሶች ዛሬ ገና በጠዋቱ ስራ በዝቶባቸዋል!!! ፀቡ ከተጀመረ 3ኛ ቀኑ ቢሆንም ዛሬ ከጠዋቱ 12 ሰዓት የተጀመረዉ ረብሻ ግን ከሌሎች ቀኖች ጠንከር ያለ ነዉ::ተማሪዎች ፖሊስ ሲያባርራቸዉ ወደ ከተማ በመሮጥ በየሰፈሩ እየተሰገሰጉ ቢሆንም ፖሊሶችም እየተከተሉ እያባረሩዋቸዉ ይገኛሉ:

:የፌዴራል ፖሊስ በየሰፈሩ እየዞሩ ህዝቡ ወደ ቤቱ እንዲገባ ካልገባ ግን ርምጃ እንደሚወስድ በማይክሮ ፎን እያስጠነቀቀ ይገኛል::ተክለ ሀይማኖት አደባባይ በመባል የሚታወቀዉና የከተማዋ እምብርት የሆነዉ መዝናኛ(green area) ትንሽ ሰዉ ስለበዛበትበፖሊስ እየተጠበቀ ይገኛል::ዝርዝር መረጃ ባላገኝም የፀቡ መነሻ ተማሪዎች ነጠላ ለብሳችሁ ካፌ አትገቡም በመባላቸዉ እንደሆነ አረጋግጫለሁ::በጣም የገረመኝ ደግሞ አንድ የትራፊክ ፖሊስ አባል በዱላ እያባረረ ሲደባበብ ማየቴ ነዉ ያዉም በየሰፈሩ እየገባ !!ትራፊክ ደግሞ ምን አገባዉ??

No comments:

Post a Comment