Thursday, October 17, 2013
ባለፈዉ የኢትዮጽያና የናይጄርያ ጨዋታለት አንድ መለስ ዜናዊን ና ሰላዲን ሰኢድን ለይቶ የማያዉቅ ፌደራል ፖሊስ አጋጥሞኝ ነበረ::

የጀግናዉን ጉርድ ፎቶ
አንድ አንድ ብር
አንድ አንድ ብር
እንዲ ሲል የሰማዉ የፌደራል ፖሊስም ልጁን ና አተ? አለዉ
ልጁም*--- መጣ እስቲ ፎቶዉን? አለዉ ልጁም*--- ሰጠዉ
ከዛ ፎቶዉን አየት አረገና ለምንድ ነዉ ጀግና አይሞትም ተብሎ ያለተፃፈበት ?
ልጁ*--- በመገረም ለምን እንደዛ ተብሎ ይፃፍበታል ኢሄ እኮ መለስ ዜናዊ አይደለም::
ታድያ ኢሄ ማነዉየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋናዉና ምርጡ ተጫዋች ሰላዲን ሰኢድ ነዉ::
ፌደራሉም*--- እና ኢሔ ምኑ ጀግና ነዉ ጀግና አታዉቅም እንዴ ሂድ ከዚ ተንቀሳቀስ በቃ ብሎ ልጁን ገፍተር አደረገዉ::
ልጁም*--- በመልሱ በመበሳጨት እንዴት ነዉ አስተሳሰብህ? እንዴት ሰላዲንን ጀግና አይደለም ትለኛለህ? ሲለዉ ::
ፌደራሉ እኔን ነዉ እንዴት ነዉ አስተሳሰብህ ያልከኝ አለና አስተሳሰቡን ለማሳየት ነዉ መሠለኝ በያዘዉ ዱላ ማጅራቱን
ልጁም ወደቀ በወደቀበት ሊደግመዉ ሲል ባቅራብያዉ የነበሩ ልጆች መሀል ገብተዉ እባክህ ተወዉ ተሳስቶ ነዉ እንደዛ ያለህ ይቅርታ አርግለት ብለዉ ባያረጋጉት ኖሮ ያ ፋራ ፌደራል ፖሊስ በዛ ከ አመት ባል በላይ በነበረ ቀን ጉድ አድርጎት ነበር ::
"ከእንደዚ አይነት ፌደራል ፖሊስ ያርቃቹ"
//ፍቄ ቡርሼ// source:-//ፍቄ ቡርሼ//
No comments:
Post a Comment