ቡርኪናም ቀረ..ምክንያት አልታወቀም!

ባለፈዉ አርብ አመሻሽ አዲሱ ፕሬዝዳንት ጁነዲን ባሻ አንድ ሰነድ ላይ ፈርመዉ ከቢሮ ወጡ፤የፌዴሬሽኑ መረጃ አቀባይም ለጋዜጠኞች በሙሉ የሰነዱን ይፋዊ ይዘት ያቀፈ መግለጫ ላከች፤ከካሜሮን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ሁሉም ነገር አልቅዋል፤ቀኑንም ይጠቅሳል መግለጫዉ..እንደዉም ጨዋታዉ እንዲገኝ ያደረገዉን ግለሰብ ያመሰግናል፤ከ2ት ቀናት በሁዋላ ደግሞ የካሜሮን ጨዋታ መሰረዝ እናም ደግሞ ቡርኪና ፋሶ ጋር ስለመጫወት ዉስጥ ዉስጡን ይወራ ነበር፤ ትላንት ልምምድ ቦታ ላይ ዋልያዎ በመጪዉ እሁድ ወደ ኡጋዱጉ አምርቶ ከቡርኪና አቻዉ ጋር ተጫዉቶ እንደሚመለስ ተነግርዋል፤ተጫዋቾችም ለመሄድ ዉስጣዊ ዝግጀት ላይ ነበሩ፤ዛሬ ምሽት ደግሞ የቡርኪናን ጨዋታ የሀገሪቱ መንግስት መከልከሉን ሱፐር ስፖርት ይፋ አድርግዋል፤ትክክለኛ ምክንያቱን የሚያቀዉ ጨዋታዉ እንዳይደረግ የዠዘዘዉ መንግስት ብቻ ነዉ፤አሁን ዋልያዉ ከማንም ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ሳያደርግ ወደ ካለባር ሊያቀና ቀናት ብቻ ቀርተዉታል፤ በዛሬዉ ልምምድ አሰልጣኙ 11 ለ11 ሙሉ ሜዳ ጨዋታ አጫዉተዋል፤ለ60 ደቂቃ ያህል ነበር ጨዋታዉ..እናም ቀጣይ የዋልያዉ እጣ ፈንታ የዛሬዉ አይነት የልምምድ ጨዋታ ይሆናል ማለት ነዉ፤ልክ ከአዲስ አበባዉ ጨዋታ በፊት ቤንቾቹን እነዚህ ናይጄሪያ ናቸዉ እናንተ ደግሞ ኢትዮጲያ..እስኪ እንደዛ አስባቸሁ ተጫወቱ እንደተባለዉ መሆኑ ነዉ፤ በደረጃ አነስ ያሉ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን የመግጠም አማራጭን ዋና አሰልጣኙ እንደማይመጥኑዋዉ በመግለጽ ዉድቅ ማድረጋቸዉ የሚታወስ ነዉ!!የነገ ተስፈኛ የወዳጅነት ጨዋታ ተጋጣሚ ደግሞ ማን ይሆን???
No comments:
Post a Comment