Tuesday, October 15, 2013

ነፃነት በትግል እንጂ በችሮታ አይጠበቅም፤ ሰላማዊ መንገድን ለማይቀበሉ የትጥቅ ትግሉ አስገዳጅ ምርጫ ነዉ፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለነፃነቱ እና ሀገሩ ክብር ሲል የዉጭ ወራሪዎችን የአገር ዉስጥ አባገነኖችን በመቃወም የመረረ የነፃነት ትግል ሲያካሂድ የቆየ፤ የነፃነት ትግሉንም በብዙ ምንገድ ሲያካሂድ የኖረ በድል ያስመሠከረ ጀግና አገር ወዳድ ሕዝብ ነዉ፡፡


የኢትዮጵያ ሕዝብ ትልቅ ታሪክ ያልዉ ኩሩ ና ጨዋ፡ ባሕሉንና ወጉን የሚጠብቅ ሌላዉን ዜጋ አክባሪ፡ እንገዳ ተቀባይና አብሮ መኖርን የሚያዉቅ ተወዳጅ ሕዝብ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህን ማራኪና ያሸበረቀ ባህልና ወግ ያለዉ የጀግንነት ታሪክን በየጊዜዉ በቆራጥነት ያስመዘገበ፤ አገሩንና ክብሩን ከአሸባሪዎችና ወራሪዎች የጠበቀ፤ ባሕሉንና ወጉን ክብሩን ያላስደፈረ ኩሩ ሕዝብ ነዉ፡፡
ነገር ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ይህን ጠንቃቃና ባለ ታሪክ ሕዝብ የታላቅ ሀገሩን ክብርና ባሕል ሚያጎድፍና የሚያረክስ መልኩን የቀየረ የዘረኝንት፣ ጠባብ የብሄርተኝነትን አሰተሳሰብ ያሰፈነና የሕዝቦችን የመተሳሰብ፣የመገባባት፣ የእኩልነት እና የአንድነትን ስሜት የገደለ፣ ሕዝቦችን በዘር፣በጎሣ፣በሃይማኖት ከፋፍሎ፤የከፋፍለህ ግዛን የእድሜ ማራዘሚያ ስልት ተጠቅሞ የሀገርን እድገትና የህዝቦችን ነፃነት የገፈፈ፤ ድህነትን በህዝቦች ጫንቃ ላይ የጫነ፣ትቂት የራሱን ተከታዮችና ራሱን ያለልክ ያበለጸገ ገፋፊ፣ ነፃነትን የገፈፈና ብዙዎችን አፍኖ የገደለ፣ የሕዝብን ድምጽ ያፈነ አባገነን ገዥና የህዝብን መብት የነጠቀ፣ የሰዎችን ሞራልና ወኔ የሰለበ፣ በብዙ ርካሽ አስተሳሠቦችና ልምዶች የሰዎችን ትኩረትና ዝንባሌ አጣርሶ ከመብት፣ ከፍትህ እና ከነፃነት ጥያቄ አርቆ በማዉጣት፡ አቅምንና ችሎታን ያሣጣ አገዛዝ ያለበት ቢኖር የወያኔ የዉነብድና ሥራ ነዉ፡፡
ታሪኩንና ባሕሉን እንድረሳ፣ እነዳያስታዉሰዉና እነዳያስበዉም ጭራሽም እነደሌለዉ፤ ከኖረዉም የዘር ልዩነትና ጥላቻን አስረግዞ በመራራ ምረዝ አገርን ለመግደልና ጨርሶ ለማጥፋት፣ የመቶ ዓመት ቁራጭ፤ ሥር ምሠረት አልባ ለማድረግ የታጠቀ ሕዝብ ጨራሽ፣ ታሪክ አጥፊ  ሽፍታ ምንግስት የተገለጠበት አሁንና አሁን ነዉ፡፡


የአዲስ አስተሳሰብ ግኝት እንዳይባል እዉነታን ክዶና ታሪክን አጥፍቶ፤ከባህልና ከእምነት ነጥሎ፡ ምንጭ የሌላትና ዝክረ ታሪክ አልባና የማትታወቅ አገር አድርጎ ለማስቀረት የጣረ፣  በመጽሐፍ ቅዱስ ሳይቀር ስሟ ተጠቅሶ ትልቅ ተስፋና ረጅም ታሪክ ያላትን አገር ባዶ ለማስቀረት፤

ብዙ የሞከረ፡ እንድህ የደፈረ፤
ወያኔ ብቻ ነዉ ተንኮል የቆፈረ፤
ግና መች ሆነና እነደዚህ አይሆንም ይዘከርላታል፣
ይህ ትዉልድ-ለትዉልድ አጥብቆ ይሰራል፤
ተስፋና ራእይዋ ላይቀር ይፈፀማል፡ እንድህ ይነገራል፡
ታሪኳም ይወራል አሏት ጀግኖች ልጆች የሚታገሉላት፣
ለነፃነት ክብሯ አለሁኝ የሚሏት፤ 2x
ወያኔ በጫካ በዱር ተሠማርቶ
ድንገት ሣያስበዉ ቤተመንግስት ገብቶ
ዘረጋ መረቡን ተረትን አጥንቶ
በስድብ በተረት ታሪክን ተክቶ
ባሕልን ከባህል በዘር አለያይቶ፣
ማባላት-ማናከስ ማካሰስ ጀመረ
ባህልና ፍቅር የዘር ትስስሩ በመርዝ ተቀየረ
የሕዘቦች አንድነት ሕብረት ትስስሩ ድንገት ተሠበረ
የታሪክ አሻራዉ ባህልና ፍቅሩ እንደት ተሠወረ፣
ከእምነት ከባህል ከታሪክ ነጥሎ
አሰበ ያ ባንዳ ምንጭ የሌላት አገር ሊያደርግታ አታሎ፤
ታሪክ የማያዉቃት አድርጎ ለማስፈር ምነዉ ተደፈረ
ይህ የቅኝ አገዛዝ የዉጭ ተጽዕኖ  ለምን ተነገረ
ባገር ባንዳ መንግስት በዘር መፀነሱ
እድል ማገኘቱ ለዚህ መደረሱ
እንድህ መተግበሩ ጭራሽ ያለታሪክ ያለወግ መቅረቱ
በጭራሽ አይሆንም ይበቃዉ ለወያኔ ህልምና ቅዠቱ
አሁን በደጅ ነዉ ሊገለጥ ዉርደቱ፤
ይህ የቅሌት ሥራዉ ተጠራርጎ  ወድቆ
የሁሉም ብሔር ልጅ ለነፃነት ክብር በጀግንነት ታጥቆ
ባንድነት ተነሳ በሕብር ቀለማት ዉብ ሆኖ አሸብርቆ
አለሁኝ ይላታል ኢትዮጵያ ሀገሩን ራዕይ ሠንቆ፤
ጀግናማ ጀግና ነዉ ታሪኩን አይለቅም
ክብሩን ነፃነቱን ፈሩንም አይስትም
ስለዚህ ባነዳዎች መንገዱን ልቀቁ
ይሄ ህዝብ ጀግና ነዉ ከልብ እንድታዉቁ 2x
መነሻ የሌለዉ እንዳደረጋችሁ
ታሪክን ይሠራል አሁን እያያችሁ 2x

ታሪክን ባህልን እምንትን ለማጥፋት ምነዉ ወደዳችሁ
ከቶ ለማን ይሆን ይሄ ትምህርታችሁ
ታሪክን ባህልን ምንም ለማያዉቀዉ
ወይስ ለሆድ አደር ለከሃድ-ባንዳዉ
እወቁ እንጅ ሰዎች ብዙ ህዝብ እነዳለ ታሪክ የሚጠብቅ
ዉርደት የሚጠላ ታጥቆ የሚያስታጥቅ
ዉሸትን ቅጥፈትን ዉርደትን የሚንቅ፣
በባህል በእምነቱ በታሪክ በዉቀቱ የተስተካከለ
ለትዉልድ ለሀገር የተቆረቆረ ህዝቡን የወከለ
እድገትን ልማትን ለዉጥን የናፈቀ
አርቆ የሚያስብ የነፃነት ፋና ሁሉን የሰነቀ
ራእይ አንግቦ ባጭር የታጠቀ
የነፃነት ጮራ ይሄዉ ይታየኛል አሁን ፈነጠቀ፡፡
እንድህ ባለ ትዉልደ መሃል አመባገነኑ የወያኔ መንግስት ወጣቱንና ምንም የማያዉከዉን ትዉልድ በዘርና በሃይማኖት በመከፋፈል፣ የብዙ ሱሶችና የስነ ልቦና ተጎጅ የሚያደርጉ የአጉል ባህል ማራገፊያ እንድሆን በማድረግ አቅሙን፡ እዉቀቱንና ወኔዉን በመንጠቅ ደካማ አድርጎ በማስቀረት ራእይና ተስፋ የሌለዉ ህዝብ በማድረግ በማን አለብኝነት ህዝብን ያደኸየ፡ ያነገላታ ብዙዎችን የገደለ፡ ከሀገር ያፈናቀለ፡ በእሰር እና በእንግልት በወኅኒ ያሰቃየና የገደለ አባገነን በሆኑ ይታወቃል፡፡
ነገር ግን ከዚህ በኋላ እምቢ ለአገሬ ለነፃነቴ፣ ለክብርና ለታሪኬ የሚል፤ለነገ ያገር እድገትና ነፃነት የሚቆም፣ አገራዊ ስሜት ያለዉና በአዲስ ራዕይ ፍትህና ነፃነት የሠፈነባት፡የሕዝቦች የበላይነትየሚረጋገጥበት፡ እኩልነትና አነድነት የሚነፀባረቅባት በአዲስ አስተሳሰብ ድመክራሲያዊ ኢትዮጵያን በነፃና ፍትሃዊ መልካም አስትዳድር ለመተካት የሚያስችል መርሃ ግብር በመክፈት ወቅታዊና አማራጭ በሆነዉ ትግል፤ ሁሉም አገር ወዳድ ዜጋና የሀገር እድገትና ለዉጥ የግድ የሚለዉ ትዉልድ ለዚህ የትግል ሂደት የበኩሉን ድጋፍና እገዛ በማድረግ በዚህ ጎዳና ለተሰለፍ ከጀግኖች የኢትዮጵያ ልጆች ጎን መሰለፍን የግድ ይላል፡፡
በዚህም መሠረት በየትኛዉም የትግል መስመር ለተሠለፍ የነፃነት ታጋይ ህዝቦች አበረታችና አኩሪ አጋርነትን ያመላከተ ተግባር በ28 ሰፕቴምበር 2013 እ.ኤ.አ በኖርዌ ኦስሎ ለግንቦት 7 ህዝባዊ ኃይል የተደረገዉ የገንዘብ ማሰባሰብ ሥራ፡ በኖርዌ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን አገራዊ ወኔ በተላበሰና የትግል አቋምን ያሳየ፣ ምሳሌያዊ እርመጃና ተግባር ተመሳክሮ የታየበት፡ የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳረጋቸዉ ጽጌ እና የግንቦት 7 ህዝባዊ ኃይል አዛዥ ኮማንደር አሠፋ ማሩ በተገኙበት ድጋፉንና አክበሮቱን የገለፀበት የወደፊት አቋሙን ያረጋገጠበት እለት ነዉ፡፡
ይህ ተመሣሳይ የሆነ የትግል ተግባር በየትኛዉም የዓለም ክፍል የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን በተለመደዉና ቀጣይ በሆነዉ የትግል ሂደት በተጠናከረ ሁኔታ እንድቀጥል ጋባዥ የሆነ እንቀስቃሴ ሲሆን፤ በተጠናከረ  አንድነትና ትብብር አገርና ህዝብ ነፃ የሚወጣበት የትግል አሰገዳጅ ምርጫ ሲሆን፤ ወያኔ ተንኮታኩቶ የሚወድቅብት አሁንና አሁን ነዉ፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
ወንድወሰን አደም (ከኖርዌ)

No comments:

Post a Comment