የህወሓትን ፀረ ኢትዮጵያ አካሄድና ዓላማ በመቃወም የሕይወት መስዋእትነት የከፈሉ አመራር ነበሩ ወይ?
ከነበሩስ እነማን ናቸው?
ከዚህ ቀጥለን የምንመለከተው ትኩረት ያልተሰጠውን ተሸፍኖ የነበረውን እና የህወሓት መሪዎች፣ በሕይወት
ያሉትም የሞቱትም፣ ከወያኔ የተባረሩ አመራርም ጉዳዩ ወደ ውጭ እንዳይወጣ ተዳፍኖ እንዲቀር ከባድ ጥረት እያደረጉበት
ያለውን ነው።
በህወሓት የተፈጸመው እውንተኛ ታሪክና አሰቃቂ ወንጀሎች፣ የህወሓት አመራር በኢትዮጵያ ሃገራችን አሁንም እየፈፀሙት
የሚገኘው ግፍ በግልጽ ተጽፎ የወያኔ ጥቁር ታሪክ ለሕዝብ የሚቀርብበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። አሁንም እየቀረበ ነው።
ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተሓህት) ለትግል የተሰማራው በየካቲት 11 ቀን 1967 ደደቢት በረሃ እንደመሸገ
ማሀብር ገስገስቲ ብሄረ ትግራይ (ማገብት) የተዘጋጀው ፕሮግራም የተረከበው ተሓህት ወይም የዛሬው ስሙ ሀወሓት ነው።
ተሓህት ትግሉን በጀመረበት ወቅት ጥቂት ከነበሩት ታጋዮች ሊመሩን ይችላሉ ብሎ ከመረጣቸው መካከል፤ 1. አረጋዊ
በርሄ፣ ሊቀመንበር 2. ዘርኡ ገሰሰ 3. ግደይ ዘርአጽዮን 4. ገሰሰው አየለ 5. አባይ ፀሃየ 6. ሥዩም መስፍን
7. አለምሰገድ መንገሻ 8. አስፍሃ ሃጎስ ተመርጠው ተሓህትን መርተዋል።
በዚህ ጊዜ ነበር የማገብትን ውርስ ተሓህት ተረከበው ብሎ በጊዜው የነበረ ታጋይ ደስታውን የገለጸው። ውርስ ማለት
ፕሮግራሙ ነው። በጊዜው የነበረ ሁሉም ታጋይ ግን የፕሮግራሙን ይዘትና ምንነትቱን አያውቅም ነበር። ይህ ፕሮግራም
ነበር በ1968 ቀስ በቀስም ተሓህትን ለሁለት የመሰንጠቅ አደጋ የፈጠረበት።
የተሓህት-ህወሓት የመጀመሪያ መሰንጥቅ
ተሓህት ገና ከደደቢት በረሃ ሳይወጣ በፊት በሁለት ጎራ የተሰነጠቀበት ወቅት ነው። ይህን መከፋፈል የፈጠረው
የፕሮግራሙ ባለቤት ነን የሚሉ አመራር በድብቅና ከታማኝ ታጋዮች ጋር በመተባበር ወስጥ ለውስጥ ፕሮግራሙ ይዘጋጅ
ነበር። ይህን የማይደግፉና የሚቃወሙ አመራርም ነበሩ።
አክራሪና በአቋማቸው የጸኑ ግን ፕሮግራሙ በትክክል የተዘጋጀ ሃቀኛ የትግራይ ሕዝብ ምኞትና ፍላጎትን በጭብጥ
ያስቀመጠ፤ ትግራይን እና ሕዝቧን ከአማራው ቅኝ አገዛዝ ነፃ የሚያወጣ፣ የትጋላችን መርህ ፕሮግራም ነው አሉ። የዚህ
ተሳታፊውች፤ 1. አረጋዊ በርሄ 2፣ አባይ ፀሃየ 3. ሥዩም መስፍን 4. ግደይ ዘራጽዮን 5. ስብሃት ነጋ 6.
መለስ ዜናዊ 7. አስፍሃ ሃጎስ 8. አውአሎም ወልዱ 9. ስየ አብርሃ 10. ሃይሉ መንገሻ ናቸው። እነዚህ ሁሉ
አመራር የነበሩና ጥቂቶቹ ደግሞ ከአንድ ዓመት በኋላ ወደ አመራር የመጡ ናቸው።
በሁለተኛ ደረጃ በተቃውሞ የቆሙትና ፕሮግራሙ በጣም አደገኛ፣ ኢትዮጵያን የሚያፈርስ፣ ሕዝብ በታኝ፣ ጸረ-ሕዝብና
ጸረ-ኢትዮጵያ ሉአላዊነት ነው በማለት የተነሱት ደግሞ 1. ገሰሰው አየለ 2. አግአዚ ገሰሰ 3. አጽብሃ ዳኘው 4.
ዶ/ር አታክልት ቀጸላ ሲሆኑ፣ ከሻእቢያ መጥቶ ተሓህትን የተቀላቀለው መሃሪ (ሙሴ) ተክሌም 5ኛ ሆኖ ከነገሰሰው
አየለ ጋር ተቀላቀለ። እነዚህ ሁሉም የተሓህት አመራር የነበሩ ናቸው።
ማህበር ገስገስቲ ብሄረ ትግራይ (ማገብት) ገና ሲፈጠር ጎባጣ፣ ጸረ-ኢትዮጵያና ጸረ-ሕዝብ ሆኖ ነው የተመሰረተው።
ይህንን ውርስ ያስረከበው ለተሓህት በየካቲት ወር 1967 ነው። በደደቢት በረሃ ተጠናክሮ ፕሮግራም ሆነ። ከዚህ ጊዜ
ጀምሮ ፕሮግራሙን በመቃወም የተሰለፉት ያነሱት ነጥብ፤
- ተሓህት በጸረ ኢትዮጵያና በሕዝቧ ተቀናጅቶ መፈጠሩ ኢትዮጵያ የምትባለውን ሃገር መበታተን አለባት የሚለው በገጽ 8 የተዘጋጀው የባእዳን ሴራና ጸረ ሃገር ነው፣
- አማራ የትግራይ ሕዝብ ጨቋኝና ረጋጭ፤ ለድህነት፣ ለሽርሙጥና፣ ለስደት፣ ለመከራ የዳረጋት ጠላት ነው የሚለው ትንተና ሃቅነት የሌለው የፈጠራ ወሬ ነው። የተጻፈው አማራን ሆን ብሎ ለማጥቃት ነው። ይህም ከፕሮግራሙ መወገድ አለበት፣
- ኤርትራ የአማራው (ኢትዮጵያ) ቅኝ ግዛት ናት የሚለው ቅንጣት ታህል ሃቅነት የሌለው እናንተ አመረር የፈጠራችሁት የተገንጣይ ዓላማ ነው፣
- ትግራይ የአማራ ቅኝ ግዛት ናት ማለት የአእምሮ ድህነትና ጠባብ ዘረኝነት ነው፣ ስለሆነም መወገዝ አለበት።
- ተሓህት የኢትዮጵያ ጥንታዊና ታሪካዊ ግዛትዋን እና የባሕር በሯን የሚያስነጥቅ ፕሮግራም ነው። ስለሆነም ጸረ-ኢትዮጵያ ሉአላዊነት ነው። ፕሮግራሙ ይለወጥ ወዘተ. የሚሉ ሃሳቦች በማንቀሳቀስ ቀሪው ታጋይም የእነገሰሰው አየለን ሃሳብ መደገፉን በወቅቱ የነበሩ ታጋዮች በትክክል ተናግረውታል።
በተጨማሪም አጽብሃ ዳኘው፣ ዶ/ር አታክልት ቀጸላ የጨመሩበት ነጥብ ተሓህት በትግራይ ሕዝብ ተቀባይነት ወይም
የውክልና መሰረት የሌለው፣ ፕሮግራሙን በትግራይ ሕዝብ ስም መዘርጋት አግባብነት የሌለው፣ በሕዝብ ስም ማጭበርበር
ነው ብለው በማመን በወቅቱ የነበሩ አነስተኛ ታጋዮች በዚህ ሃሳብ ተስማሙ። በዚህ ጊዜ 1. በስብሃት ነጋ 2. መለስ
ዜናዊ 3. አውአሎም ወልዱ 4. ስየ አብርሃ ወዘተ. ተባብረው በአቶ ገሰሰው አየለ ላይ የስም
ማጥፋት ዘመቻ ጀመሩ። በስብሃት ነጋ እየተመሩ የገሰሰው አየለን ስምና ዝና በጥቁር ቀለም ቀቡት። ሻእቢያም ገሰሰው
ከተሓህት ተቀላቅሎ መታገሉን ከመጀመሪያው ያልተቀበለው ስጋት ወስጥ ስለጣለው ነው። ሻእቢያ ለተሓህት አመራር
ያስተላለፈው መልእክት፣ ገሰሰው አየለ በዚህ ከቀጠለ ተሓህትም ሆነ ሻእቢያ ትልቅ አደጋ ላይ እንደሚወድቁ ተናግሯል።
ገሰሰው አየለ ከምድረ ገጽ መጥፋት አለበት የሚለውን የተህሓት ጥቂት አመራር ሃሳቡን ተቀበሉት።
የእነ ስብሃት ነጋ ቡድን በገሰሰው አየለ ላይ ሲያስፋፉት የነበረውን የስም ማጥፋት ዘመቻ ጥቂቱን እንመልከት፤
- ድርጅታችን ተሓህት የገሰሰው አየለ ፊውዳል ድርጅት ነው እየተባለ ነው። ይህንን ግለሰብ ከድርጅቱ ማስወገድ ስላለብን እንተባበር (መለስ ዜናዊ)፣
- ገሰሰው አየለ ፊውዳል፣ ጸረ-ትግራይ ትግል በመሆኑ በተመቸው ጊዜ ጠብቆ ተሓህትን ከማጣፋት አይመለስም። የትግራይን ነፃ ሃገርነትና የትግራይን መንግሥት አይቀበልም። ጸረ-ኤርትራ ትግል ነው። የመትከል አገራችን ሻእቢያም ተማረውበታል። (ስብሃት ነጋ)፣
- ኤርትራና ትግራይ የአማራ ቅኝ ግዛት አይደሉም፣ አልነበሩም። ሁሉም የኢትዮጵያ ጥንታዊ ግዛትና አካል ናቸው፣ ስለዚህ የተሓህት ፕሮግራም ውድቅ ነው እያለ እንደ ምስጥ ውስጥ ለውስጥ እየተሽሎከሎከ ከሕዝብ እየነጠለን ነው (ስብሃት ነጋ)።
በዚህ ጊዜ የነበሩ ታጋዮች እንደሚናገሩት ከሆነ በገሰሰው አየለ ላይ በስብሃት ነጋና መለስ ዜናዊ የሚመራው ቡድን
የተሰማሩበት የስም ማጥፋት ዘመቻ በየቀኑ ይደርሰው ነበር። በመጨረሻ ተማሮ በህዳር 1968 ከማ/ኮሚቴ ሃላፊነቱ
ራሱን አግልሏል። ይህ በመሆኑ በሃዘን እና በቁጭት የሚናገሩ በወቅቱ የነበሩ ታጋዮች ነበሩ። አክራሪውን አመራር
ለመቆጣጠር አቅም ነበረን ግን ስህተት ፈጸምን ያሉም አልታጡም።
የዲማ ኮንፈረንስ
የዲማ ኮንፈረንስ የተካሄድው በመጋቢት መጀመሪያ በ1968 ነበር። በዚህ ጊዜ አቶ ገሰሰው አየለ በስብሰባው
አልታየም። በወቅቱ በዚህ ጉባኤ የተሳተፉት ታጋዮች ገሰሰው/ስሁል የት ሄደ ብለው ሲጠይቁ የተሰጠው መልስ በሥራ
ምክንያት ወደ ሩቅ ቦታ ሄዷል የሚል እንደነበር ይናገራሉ። ኮንፈረንሱ ከመድረሱ በፊት የስብሃት ነጋ ቡድን በአግአዚ
ገሰሰ፣ በጥቂቱም ቢሆን በግደይ ዘርአጽዮን ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ አካሂደዋል። ነገር ግን ውጤት አልባ ነበር።
በዲማ ኮንፈረንስ የተመረጡት 1. አረጋዊ በርሄ፣ የተሓህት ሊቀመንበር 2. ስብሃት ነጋ 3. ግደይ ዘርአጽዮን 4.
ሥዩም መስፍን 5. አግአዚ ገሰሰ 6. አባይ ፀሃየ 7. ሙሴ (መሃሪ) ተክሌ ነበሩ። ምርጫው ጸረ-ዲሞክራሲ ስለነበር
የነበረው አመራር ስብሃት ነጋን መርጦ መለስ ዜንዊን ድምጽ ነሳው። በዚሁ ሁሉም ወደየሥራው ሄደ።
ቀደም ብዬ በአርእስቱ ላነሳሁት ጥያቄ መልስ ለመስጠት፣ የተሓህት – ህወሓት ጸረ-ኢትዮጵያ አካሄድና ዓላማን
በመቃወም ለሁለት መሰንጠቁና የሕይወት መስዋእትነት የከፈሉ አመራር ነበሩ ወይ? ከነበሩስ እነማን ናቸው? ለሚለው
ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት እነሆ ፎቶግራፋቸውን ከዚህ በማያያዝ አቀርባለሁ።
ገሰሰው አየለ አግአዚ ገሰሰ ሙሴ መሃሪ ተክሌ አጽብሃ ዳኛው ዶ/ር አታክልት ቀጸላ
አቶ ገሰሰው አየለ የበረሃ ስሙ ስሁል፣ ተወልዶ ያደገው ሽሬ አውራጃ ነው። ገና በወጣትነቱ የሽሬ አውራጃ ማዘጋጃ
ቤት ዋና ሹም በመሆን አገልግሏል። በ1950 አጋማሽ ለፓርላማ ምርጫ ተወዳድሮ በማሸነፍ የኢትዮጵያ ፓርላማ አባል
በመሆን ሠርቷል። ለሶስት ተከታታይ ምርጫ በማሸነፍ 15 ዓመት ሙሉ የፓርላማ አባል ነበር። በኢትዮጵያ የተቀጣጠለው
አብዮት እየተጠናከረ ሲመጣ በ1966 የማገብት አባል ሆነ።
አቶ ገሰሰው አየለ የማገብትን አላማ፣ ተግባርና ፕሮግራም በጸረ-ኢትዮጵያነት የተሞላ መሆኑን ትኩረት ሳይሰጥ
በየካቲት 11 ቀን 1967 ለተመሰረተው የትጥቅ ትግል ግንባር ቀደም መስራች በመሆን በአመራር ደረጃ ግንባሩን ሲመራ
ነበር። የተሓህትን ፕቶግራምና ዓላማ ካየ በኋላ ፍጹም ጸረ-ኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት፣ ጸረ-ኢትዮጵያ
ሕዝብነትን የጨበጠ ፕሮግራምና በፋሽስት ጣልያን የተዘጋጀ ነው እስከማለት ደረሰ። በህዳር 1968 ከአመራሩ ወረደ።
አቶ ገሰሰው አየለ ያነሳው ተቃውሞ ብዙ ቢሆንም ከተራ ቁጥር 1-4 ያሉትን አንኳር ሃሳቦች አስነስቷል። ታጋዩም
ድጋፍ ሰጠው። ከአመራሩም እንደነ አግአዚ ገሰሰ፣ አጽብሃ ዳኘው፣ ዶ/ር አታክለት ቀጸላና መሃሪ ከጎኑ ተሰለፉ።
በተሓህት ውስጥም ጭንቀትና ሽብር በአመራሩ ወስጥ ተፈጠረ። በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድንም ገሰሰው አየለን በዘዴ
ለማጥፋት እቅዱን ዘረጋ።
የገሰሰው አየለ ደብዛ መጥፋት
ከዲማ ኮንፈረንስ በኋላና ክዛም ትንሽ ቀደም ብሎ ገሰሰው አየለ የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ ሲሉ የት ገባ የሚሉ ታጋዮችም በዙ። በዚህ ጊዜ የተሓህት አመራር እርስ በርሱ የሚጋጭ ወሬዎች በድርጅቱ አሰራጨ።
- በአዲ ነብራኡድ ወስጥ በኢዲዩ ወይም ጠርናፊት ድንገተኛ ጦርነት ከፍተው ጠርናፊት ገደለችው፣
- እኔ ስለሸመገልኩ አልታገልም ገንዘብ ስጡኝና ሱዳን ሄጄ ልኑር በማለት ገንዘብ ከድርጅቱ ተሰጥቶት በመኪና ተሳፍሮ ሲሄድ በመኪና ውስጥ የነበሩ የኢዲዩ አባላት ገደሉት የሚል ነበር። ሁሉም ውሸት ነው።ኢዲዩም ይህንን በተመለከተ ሰፊ መግለጫ በተነ። ገሰሰው አየለን እኛ አልገደልነውም፣ ልንገድለውም አንችልም። የወንድማቻቾች ደም በከንቱ አናፈስም የሚል ሲሆን፣ የገደለችው ተሓህት ናት አሉ።በአዲ ነብራኡድ ተገደለ የተባለበት ምክንያት ሕዝቡ ራሱ ምስክርነቱን በሰጠበት በመጋቢት ወር ጦርነት አልነበረም። የደም መፋሰስ አልታየም አለ። የገደሉት ራሳቸው ወያኔዎች ናቸው ሲል ሕዝቡ ምስክርነቱን ሰጠ። አዲ ነብራኡድ የገሰሰው አየለ ቤት ነው። ጊዜው የአቶ ገሰሰው አየለ ስሁል አሟሟት እውነቱ ግልጽ ሆኖ የወጣበት ጊዜ ነበር። ገሰሰው በስብሃት ነጋ የሚመራው የተሓህት አመራር በማይታወቅ ቦታ ደብቀው ወይም እንደ ግዞተኛ አቆይተው በሰኔ 1968 በጥይት ደብደበው ሽላሎ ቡምበት አካባቢ ተገደለ። በግድያው የተሳተፉትም አውአሎም ወልዱና አሰፋ ማሞ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ግን አልታወቁም። ይህንን እውነታ ተከታትለው ሃቁን ያገኙት በተሓህት ወስጥ ለትግል የተሰለፉት የገሰሰው አየለ የቅርብ ዘመዶቹ ናቸው። በጊዜው ሃቁን አስቀምጠው አለፉ። ላደረጉት ጥረት የሚመሰገኑና ባለውለታም ናቸው። ጥቂቶቹ፣ ማለትም እንደነ አዘናው ገ/ጻዲቅ ታፍነው የት እንደገቡ የማይታወቁም አሉ።የአቶ ገሰሰው አየለ በተሓህት ፕሮግራም ያስቀመጠው ነቀፌታና ሃሳቡን የደገፉት ግለሰቦች በከፍተኛ ዲግሪ ከቀ. ኃ. ሥ. ዩኒቨርሲቲ የተመረቁ እንደነ እቁባዝጊ በየነ፣ አሰፋ ገብረዋህድ የመሳሰሉ ዘጠኝ ምሁራን የተሓህትን አመራር የውሸት ስም በመስጠት የሥልጣን ሱሰኞች ተብለው ሽራሮ ውስጥ በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል። እነዚህም በተሓህት አመራር ቅጥራኛ ባንዳዎች ተገድለዋል። ይሁን እና መልእክታቸውን አስተላልፈው ከዚች ዓለም በግፍ ተገድለው አልፈዋል። ስማቸው ግን አልጠፋም፤ ለዘላለም ይኖራል።2. ዘርኡ ገሰሰዘርኡ ገሰሰ የበረሃ ስሙ አግአዚ ሲሆን፣ በቀ. ኃ. ሥ. ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት የፖለቲካል ሳይንስ ተማሪ ነበር። ማገብትን ከመሰረቱት አንዱ ነው። በአመራርም እስክ እለተ ሞቱ ተሓህትን ከሚመሩት መካከል ነበር። ዘርኡ ገሰሰና አቶ ገሰሰው አየለ በተሓህት ፕሮግራም ጠማማነት፣ ጸረ-ኢትዮጵያና ጸረ-ኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑ በሁሉም ነጥብ አይለያዩም፣ አንድ አቋም ነበራቸው።ዘርኡ ገሰሰ የተሓህትን ፕሮግራም አጥብቆ ያወግዘዋል፣ በታጋዩም ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትና ክብርም ያገኘ አመራር ነበር። ይህች ግን ለነስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየ፣ ስዩም መስፍን እና መለስ ዜናዊ አትዋጥላቸውም። አደገኛ መሪ ብለው ፈርጀው የሚጠበቀው ልክ እንደ ገሰሰው አየለ በዘዴ ማጥፋት ነበር።ዘርኡ ገሰሰ በተሓህት ፕሮግራም በገጽ 8 ላይ የሰፈረውን እና ሌላውን ፕሮግራም ሁሉ አደገኛ ስለሆነ ፈጽሞ መወገድ አለበት በማለት ከብዙ አመራሮች ጋር መነጋገሩ የቅርብ ሰዎች የሚሉት ሃቅ ነበር። ነገር ግን ሰሚ አላገኘም። እነ ስብሃት ነጋ የሚገደልበትን ዘዴ ለማመቻቸት ይሯሯጡ ነበር።አግአዚ ገሰሰ ከግደይ ዘርአጽዮን እና ከአረጋዊ በርሄ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንደነበራቸው የሚያውቁ ታጋዮች በዚሁ ሴራ ሁለቱ ምንም ዓይነት ተሳታፊነት አልነበረባችውም የሚሉም ብዙ ናቸው። የሴራው አካላት ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ፣ አባይ ፀሃየ፣ ስዩም መስፍን፣ አውአሎም ወልዱና ስየ አብርሃ ናቸው በማለት ያረጋግጣሉ።ይህ በእንዲህ እያለ የተሓህት አመራር ስብሃት ነጋና አባይ ፀሃየ ሆነው ዘዴውን አቀነባብረው ከጨረሱ፣ አግአዚን ጨምሮ በአክሱም ከተማ ትልቅ ሥራ እንዳለ አስመስለው ሃሳባቸውን በማቅረብ የሚፈጸመውም በአመራር ደረጃ ስለሆነ አግአዚ ተዘጋጅ ብለው በትንሽ ቀናት እንደሚገናኙ ተወሰነ። ስብሃትና አባይ ፀሃየ ጠላት በብዛት የሚገኝበት ለመንቀሳቀስም ሆነ መንገዱን መጠቀም በማይቻልበት ቦታ ወቅሮ ማራይ መሆኑ በሕዝብ ግንኙነት ጥናት አግኝተዋል። ወቅሮ ማራይ በደርግ ሚሊሺያ የታጠረ ነው። ቀኑ ደረሰ፣ አግአዚ ገሰሰና ነፃነት ሰንደቅ አብረው ከነስብሃት ጋር ሰመማ በሚባል ቦታ ተገናኙ። ስብሃት ነጋ ለአግአዚ በየትኛው ቦታ ለመሄድ አስበሃል ሲለው በመደባይ ታብር በኩል ሲለው የመረጥከው መንገድ አደገኛ ነው በማለት በሕዝብ ግንኙነት አጥንተን ወቅሮ ማራይ ነፃ መሆኑን፣ ሚሊሻም ሆነ የደርግ ሰራዊት የሌለበት ነው ካሉት በኋላ በህሳቡ ተስማምተው መንገዳቸውን ቀጠሉ። ነፃነት ሰንደቅ አብሮት ስለነበረ ሁሉንም ሰምቶታል። ወቅሮ ማራይ እንደገቡ በሚሊሻ ተከበው በተተኮሰ ጥይት አግአዚ ገሰሰ ወዲያውኑ ወድቆ ሞተ። ነጻነት ግን አመለጠ። እንደምንም ብሎ ዘና ወረዳ ገባ። እዛ ላገኛቸው ታጋዮች የደረሰባቸውን ሲነግራቸው፣ ነፃና ጥሩ መንገድ ነው ብለው ስብሃትና አባይ ፀሃየ አግአዚም የተናገሩትን አምኖ በሚሊሻ ተከበን የጥይት ናዳ ወርዶብን አግአዚን ገደሉት፣ እኔ አመለጥኩ። ስብሃት ነጋና አባይ ፀሃየ ባዘጋጁት የግደያ ዘዴ የሚቃወማቸውን አግአዚ ገሰሰውን አጠፉት ብሎ የተናገረው በተሓህት ውስጥ ተሰራጨ። ስብሃትና አባይ ተከታትለው ነፃነትን ለማግኘት የተፈጠረው ነገር ለማንም እንዳይነገር አስጠነቀቁ። ሆኖም ግን ነገሩ ተሰራጭቷል። አመራሩም የአግአዚን ሁኔታ አንዲት ቀንም ሳያነሳ ቆይቶ በ1ኛው ጉበኤ በጠላት ተገደለ ብለው ተናገሩ። የስብሃት የግድያ ሴራም ሰመረለት።3. መሃሪ ተክለመሃሪ ተክለ የበረሃ ስሙ ሙሴ ነው። በቀ. ኃ. ሥ. ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ ሲማር የቆየ፤ ከሻእቢያ ጋር የተሰለፈ የሻእቢያ ታጋይና አመራር የነበረ ሰው ነው። ሻእቢያና ማገብትን በማይበጠስ የብረት ሰንሰለት ያቆራኘው መሃሪ ተክሌ ነው። ማገብትን የመሰረቱት እነ አረጋዊ በርሄ በጥር 1967 ሳህል ኤርትራ በረሃ ወርደው በሻእቢያ ወታደራዊ ትምህርት ሰልጥነው ብረት ታጥቀው ደደቢት በረሃ እንዲወርዱ ትልቅ ሚና የተጫወተው መሃሪ ተክሌ ነው። መሃሪ ተክሌ በሻእቢያ ተፈቅዶለት በተሓህት ውስጥ እንዲታገል ደደቢት በረሃ ከነ አረጋዊ በርሄ ተቀላቅሎ የተሓህት ተዋጊም ሆነ።የሙሴ ያልተጠበቀ የአቋም ለውጥሙሴ የሁሉንም ታጋይ ባህሪ ጥናት ለመውሰድ ጥቂት ወራቶች ቢወስድበትም የተሓህት ታጋይ ለምንም ለውጥ ዝግጁ መሆኑን አወቀ። የእነ ገሰሰው አየለ አግአዚ ወዘተ. በተሓህት ፕሮግራም ላይ ያላቸውን አመለካከት አወቀ። ከአስገደ ገ/ሥላሴም ጋር ጥሩ ግንኙነት መሰረተ። ታጋዩና ሙሴ ውህደት ፈጠሩ፣ ወደዱትም። በዲማ ኮንፈረንስ ለአመራር ብቁ ነው ብሎ ታጋዩ ወደ ተሓህት መሪነት አደረሰው። ም/ወታደራዊ አዛዥም ሆነ። ይህ በወቅቱ ለነበረው ታጋይ ታላቅ ድል ነበር።ሙሴ ባልተጠበቀ ሁኔታ ጸረ-ሻእቢያ አቋም ያዘ። ሻእቢያ ጸረ-ሕዝብ፣ በተለይ ደግሞ ጸረ-ትግራይ ሕዝብ ነው። ሻእቢያ የኔ ጠላት የትግራይ ሕዝብ ነው የሚል አክራሪ ድርጅት ነው፤ የተሓህት አመራር ደግሞ ሻእቢያን እንደፈጣሪ እየቆጠሩ ጠዋት ማታ እግሩን ይስማሉ በማለት በተጠናከረ መልኩ ጸረ-ሻእቢያ ቅስቀሳውን በማቀነባበር በስፋት ቀጠለበት፣ ታጋዩም አብሮት ቆመ።አመራሩም ሙሴ ከመትክል የትግላችን አጋር ሻእቢያ እየለያየን ነው በማለት ሲናገሩ፣ በእንጻሩ ሙሴ ነፃ ሁኑ፣ አሽከር አትሁኑ፣ የሻእቢያ አገልጋይና ታዛዥ አትሁኑ ነው የምላችሁ ሲላቸው የተሓህት አመራር ሙሴን ማውገዙን ቢቀጥሉበተም በታጋዩ ተቀባይነት አላገኘም። ይበልጡኑ የሙሴ ተቀባይነት ከፍ አለ። በዚህ ምክንያት አመራሩ ሙሴ መሃሪ ተክሌ የሚጠፋበትን መንገድ ማጠንጠን ጀመሩ። የግድያ ሴራ በስብሃት ነጋ የሚመራው የመለስ ዜናዊ፣ አባይ ፀሃየና ሥዩም መስፍን በመተባባር እቅዱን አወጡ። ተግባር ላይ የሚያውሉት ደግሞ ስየ አብርሃና ጻድቃን ገብረተንሳይ ሲሆኑ ግድያውን የሚፈጸመው በርሄ ሃጎስ ሆኖ ተመረጠ። በርሄ ሃጎስ አሁን ካናዳ፣ ኦቶዋ በመኖር ላይ ያለ ግለሰብ ነው። በላፈው ግንቦት 2005 አማራው የትግራይ ሕዝብ ጠላት ነው እያለ አማራውን ኢትዮጵያዊ ሲሰድበውና ሲያንቋሽሸው የነበረ ሰው ነው። በገዘ ተጋሩ ፓል ቶክ።ስየ አብርሃ በሚመራት ሃይል 41 አመቺ ጊዜ ሲጠብቅበት የነበረው ሙሴ ጻድቃን ገብረተንሳይ በኮሚሳርነት የሚመራት ጋንታ በርሄ ሃጎስ የነበረባት ጋንታ በመጠባበቅ ላይ የነበሩት ሁለቱ በአጋጣሚ ሓምሌ መጨረሻ 1968 ከሽራሮ ወጣ ብላ የምትገኘው ቁሽት ጫአ መስከበት ስየ አብርሃ ም/ሃይል መሪ በያዛት ሃይል በኢዲዩ ላይ ጥቃት እንደተጀመረ፣ ሙሴ ታጋዮቹን እያስተባበረ ጦርነቱን በመምራት ላይ እንዳለ በስተኋላው የነበሩት ጻድቃን ገ/ተንሳይና በርሄ ሃጎስ ውጊያው እየበረታ ሲሄድ በርሄ ሃጎስ አነጣጥሮ ሙሴ (መሃሪ) ተክሌን ግራ እጁ ላይ ትከሻውን ጨምሮ ቆርጦ ጣለው። ዞር ሲል ጻድቃን ገ/ተንሳይና በርሄ ሃጎስ ከኋላ ሆነው እንደመቱት አወቀ። አይን ለአይንም ተገጣጠሙ። በርሄ ሃጎስ ሙሴን የመታበትን ደምመላሽ ጠመንጃም ለጻድቃን ሲሰጠው አየው። ክፉኛ የቆሰልውን ሙሴን በቃሬዛ ተሸክመውት ሲሄዱ የነበሩትን ታጋዮች ሁሉ የነገራቸው እኔ በኢዲዩ ጥይት አልተመታሁም፤ የመቱኝና የገደሉኝ ጻድቃን ገብረተንሳይና በርሄ ሃጎስ ናቸው እያለ ሲናገር እንደነበረና አንድ ሰዓት ተኩል ያህል ቆይቶ ከዚች ዓለም እንደተሰናበተ ይናገራሉ። አዲ ፀጸር ቀሽት ወስጥ ተቀበረ። ወዲያው በርሄ ሃጎስ ትንሽ ገንዘብ ተቀብሎ ሱዳን ገባ። ሙሴ የተናገረውን ኑዛዜ አውአሎም ወልዱ ሰምቶታል፣ ምስክርነቱን ይስጥበት።4. አጽብሃ ዳኘውአጽብሃ ዳኘው፣ የበረሃ ስሙ ሸዊት ነው። በቀ. ኃ. ሥ. ዩኒቨርሲቲ በሂሳብ ትምህርት የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ነበር። ማገብት እንደተመሰረተም ከወራት በኋላ አባል ሆነ። መጋቢት 1967 ከተሓህት ጋረ ተቀላቀለ። ከጊዜ በኋላም በተሓህትን ፕሮግራም አደገኛነት ሂስ መሰንዘር በመጀመር ፕሮግራሙ ጸረ-ሃገር ሉአላዊነት፣ ጸረ-ኢትዮጵያ ሕዝብና በታኝ፣ ሕዝብን እርስ በርሱ ለግጭት የሚዳርግ በመሆኑ አዲስ ፕሮግራም ማርቀቅ ይጠበቅብናል በማለት ከነ ገሰሰው አየለ – አግአዚ ገሰሰ ጋር በአቋም ተስማሙ። በሚሰነዝረው ሃሳብ በታጋዩ ተወዳጅ ሆነ፣ በድፍረቱም ምክንያት ስሙ ገነነ። በዚህ መልክ ሲቀጥል፣ ሱዳን፣ ካርቱም ለሥራ ሂዶ በነበረበት ወቅት መለስ ዜናዊና ስብሃት ነጋ በአስቸኳይ አስጠርተው ሱዳን ባለህበት ጊዜ ጾታዊ ግንኙነት ፈጽመሃል በማለት በውሸት ከሰው 06-ሃለዋ ወያነ አስገብተው አሰሩት። አረጋዊ በርሄ ይህን እንደሰማ ከነበረበት ቦታ በቶሎ ደርሶ ከእሰር አስወጥቶ ሥራውን እንዲቀጥል አደረገ። ሐምሌ 1968 አመራሩ ወደ አምስት ስለወረደ ገሰሰው አየለ፣ አግአዚ ገሰሰ፣ ሙሴ (መሃሪ) ተክሌ በተሓህት አመራር ስለተገደሉ፤ በአመራር ላይ የቀሩት አረጋዊ በርሄ፣ ግደይ ዘርአጽዮን፣ ስብሃት ነጋ፣ ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሃየ ብቻ ነበሩ። ከላይ በጠቀስኩት ወርና ዓ.ም. አምስቱ አመራር ተሰብስበው የሚከተሉት ወደ አመራሩ ገቡ። መለስ ዜናዊ፣ አጽብሃ ዳኘው፣ አውአሎም ወልዱና ስየ አብርሃ ወደ ተሓህት አመራር ወጡ።አጽብሃ ዳኘው ለስልጣን እና ሹመት እጁን አልሰጠም። የተሓህት ፕሮግራም ጸረ-ኢትዮጵያና ጸረ-ሕዝብ፣ አውዳሚና በታኝ ስለሆነ መወገድ አለበት፣ ተሓህት ጠባብና ዘረኛ ስለሆነ ትግላችን ኢትዮጵያዊ መሆን አለበት። ትግራይ የአማራ ቅኝ ግዛት ናት፣ አማራ ጠላት ነው ማለት ሕገወጥ የፖለቲካ አቋም ነው በማለት ተከራከረ። ክርክሩን እገላ ወረዳ ስብኦ ቁሽት ሲከራከሩ ስብሃት፣ መለስና አባይ ተናደዱ። ሆያ አዲጨጓር የሚገኘው 06-ሃለዋ ወያነ ሃላፊዎች፣ ሙሉጌታ አለምሰገድና ክንፈ ገ/መድህንን አስጠርተው ዛሬውኑ አጽብሃ ዳኘውን እና ጓደኛው መኮንን በዛብህን ግደሏቸው። ስብሃት ነጋ ጸረ-ተሓህት ናቸው የሚል ወረቀት ጽፎና አዘጋጅቶ ሰጣቸው። እነአጽብሃ መኮንን የተሰጣቸውን ወረቀት ይዘው በመሄድ ሆያ ላይ ጉድጓድ ተቆፍሮ በጥይት ተደብድበው በመገደል ከዚህ ዓለም ተሰናበቱ።አረጋዊ በርሄ የአጽብሃ ዳኘውና የመኮንን በዛብህን መታሰር ሰምቶ ከነበረበት ተምቤን አካባቢ ሌት ተቀን ተጉዞ ሕይወታቸውን ለማዳን ያደረገው ጥረት የሚያስመሰግነው ነው። ሆያ እንደገባ እነ አጽብሃ ወደኔ አምጡልኝ፣ ተፈትተዋል፣ ጥፋት የለባቸውም ሲል ከሙሉጌታ አለምሰገድ ጋር ያገኘው መልስ፣ ስብሃትና መለስ አባይ ሆያ እንደገቡ ሳይውሉ ሳያድሩ ይገደሉ ብለው ስላዘዙን ገደልናቸው አለው። የትእዛዝ ወረቀቱም የኸው ብሎ ሰጠው። አረጋዊ በርሄ ይህንን አሳዛኝ ግድያ ሰምቶ እነስብሃት ነጋ ወደሚገኙበት እገላ ሰብኦ፣ ቁሽት በመሄድ ተገናኛቸው። ነገር ግን ምንም አላደረገም። የተሓህት ሊቀመንበር እንደመሆኑ ለምን ይሆን በነስብሃት ነጋ፣ መለሰ ዜናዊ ወዘተ. ላይ እርምጃ ሳይወሰድ የቀረው የሚል ጥያቄ ተነስቶ ነበር። አሁንም እየተነሳ ነው። መልስ መስጠት ያለበትም የወቅቱ የተሓህት ሊቀመንበር አረጋዊ በርሄ ነው።5. ዶ/ር አታክልት ቀጸላዶ/ር ራስወርቅ ቀፀላ የበርሃ ስሙ ዶ/ር አታክልት ቀፀላ የህክምና ባለሙያ ነው። ቀደም ሲል ከግንባር ገድሊ ሓርነት ትግራይ (ግገሓት) አባል ሆኖ በረሃ ሲንቀሳቀስ የግገሓት የትግል ስልት አደገኛ ነው በማለት በሰኔ 1967 ከተሓህት ተቀላቀለ። በተሓህትም ብዙ ስህተቶች እንደሚኖር አልተጠራጠርም ነበር። ነገር ግን ስህተቱን ለማስተካከልና ለማረም ብዙ ታጋዮች ይኖራሉ የሚለው እምነቱን እንደያዘ ቀስ በቀስ ፕሮግራሙን የማየት እድል ገጠመው። ከነገሰሰው አየለ፣ አግአዚ ገሰሰ፣ ሙሴ መሃሪና አጽብሃ ዳኘው ጋር ጥሩ ግንኙነት ስለፈጠረ፣ እነዚህ ሁሉ የተሓህት ፕሮግራምን የሚቃወሙ ናቸው። አጽብሃ ዳኛው በነስብሃትና መለስ እንደተገደለም ዶ/ር አታክለት ቀጸላ በአጽብሃ ፈንታ የተሓህት አመራሩን ጨበጠ። ግን እጁን አልሰጠም።ዶ/ር አታክለት በፕሮግራሙ መጥፎና አደገኛ፣ ሃገርንና ሕዝብን የሚበታተን ነው ብሎ በማመን ከተለያዩ አመራር ጋር ሲነጋገርበት እንደነበር ይታወቃል። ከግደይ ዘርአጽዮን እና አረጋዊ በርሄ መግባባት እንደነበረውም ራሱ የተናገረው ነው።ከመለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየና ከሌሎቹ አመራር ጋር ግን የሻከረ ግንኙነት እንደነበረው ታጋዩ ሁሉ ያውቃል። ሌላው ቀርቶ ስብሃት ነጋ በየቦታው በሄደበት “የኢትዮጵያ ባንዲራ ራሱ ላይ ጠምጥሞ ዶ/ር አታክለት ቀጸላ በድርጅታችን ተሓህት ችግር እየፈጠረብን ነው” በማለት በየቦታው መናገሩን እኔ ራሴ አስታውሳለሁ። ዶ/ር አታክልት ቀጸላ በ1ኛው ጉባኤ የተሓህት የአመራር ምርጫ በከፍተኛ የድምጽ ቁጥር ተመርጦ የህወሓት ማ/ኮሚቴና ም/ወታደራዊ አዛዥ ሆነ። የነስብሃት ነጋ የስም ማጥፋት ዘመቻ አልተሳካም። በነገሩም ተደናግጠው ነበር።ይህ በየካቲት 5 ቀን 1971 በአዲነብር ኡድ ወረዳ ማይ አባይ በተባለው ቦታ የተካሄደው 1ኛ ጉባኤ፣ የተሓህት ውርስ ስብሃት ነጋ ሊቀመንበር የሆነበት ጉባኤ ወርሱን የተረከቡት ስብሃት ነጋና ህወሓት ናቸው። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ቀደም ብሎ የመጣው ፋሽስት ቡድን እውቅና ያገኘበት ጊዜ ነበር።እነስብሃት ነጋ ዶ/ር አታክልትን ለማጥፋት ብዙ ጥናት በማካሄድ የተመቸ ጊዜ አገኙ። ግንቦት 1971 የውጊያው ዓይነት ጥቃት በኢትዮጵያ ሰራዊት፣ የውጊያው ቦታ ተምቤን፣ አብይ አዲ ጎንባስ ሞሞና ነበር። የህወሓት ሰራዊትም ይዘጋጅበት ነበር። ቀኑ ደርሶ ሁሉም የህወሓት ሰራዊት ወደ ውጊያው ቀጠና አመራ። ውጊያው የሚጀምርበት ጠዋት በስተምእራብ በኩል ከውጊያው ቦታ በግምት በ10 ኪ.ሜ. ርቀት ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየና ሳሞራ የኑስ፣ የታጠቀው መሳሪያ ሲሞኖቭ ባለመነጽር ሆነው ዶ/ር አታክልት ቀጸላን የህወሓት ሊቀመንበር ስብሃት ነጋ ስለጦርነቱ ለመነጋገር ብሎ አስጠራው። እነሱም ለግድያው በመዘጋጀት በጠሩት መሰረት ደረሰ። ፊታቸውን ወደ ውጊያው ቀጠና ምስራቅ በማዞር ቀስ እያሉ መንገዱን ቀጠሉ። እኔና ዶ/ር አባዲ መስፍን ከነስብሃት ነጋ ፊት 500 ሜትር ያህል በሚገመት ርቀት ወደ ጦርነቱ ቀጠና እንጓዝ ነበር። ዶ/ር አታክለት ቀጸላ ስብሃት ነጋ እንዳሰናበተው በፍጥነት እየተጓዘ ሳለ ከ250-300 ሜትር ርቀት ከነሱ መካከል ሳሞራ የኑስ በያዘው ሲሞኖቭ ባለመነጽር ጠመንጃ አስተካክሎና አነጣጥሮ በመተኮስ ዶ/ር አታክልት ቀጸላ የጀርባው አከርካሬ ላይ መታው። ‘Special Column’ ተመትቶ ሲወድቅ አዩት። አባይ ፀሃየ በፍጥነት ሩጦ ወደኛ ተጠግቶ አባዲ፣ አባዲ፣ ብሎ በመጥራት በእጅ ምልክት ኑ ሲለን ሄደን አገኘነው። ዶ/ር አታክልት ስለሞተ ቅበሩት፣ ነገር ግን ለማንም እንዳትናገሩ ብሎ ተመልሶ ከነስብሃት ነጋ ጋር ተቀላቀለ። በኋላም ሶስቱም ተያይዘው ሲሄዱ አየናቸው።ዶ/ር አባዲ መስፍን እና እኔ ጉድጓድ ስንቆፍር እሱ እንደ ባለሙያነቱ ሬሳውን መመርመር ጀምረ። ጀርባው ላይ የመታችን ጥይት ሰውነቱን ከፍቶ አወጣት። በሲሞኖቭ ጥይት ሳሞራ የኑስ ገደለው ብሎ እምባውን መግታት አቃተው። ጥይቷን በወርቀት ጠቅልሎ ያዛት። እኔና ዶ/ር አታክልት አፈርና ድንጋይ በመጫን ቀብረን ተሰናብተን ወደ ጦርነቱ ተመለስን። ዶ/ር አታክልት ሞቶ ይቀበር እንጂ ታሪኩ ህያው ህኖ ይኖራል። እነ ስብሃት ነጋ መለስ ዜናዊ ወዘተ. በንጹሃን ደም መታጠብ የጀመሩት ገና ከጥዋቱ ነበር። እነዚህ ጀግኖች በሞት ቢለዩንም ድምጻቸውና የተቀደሰ ተቃውማቸው፣ የህወሓት ፕሮግራም ይውደም ያሉት ድምጻቸው ግን በታጋዩ ዘንድ ተሰራጨ። በዚህም ምክንያት ብዙ ዲሞክራሲያዊ ጥያቄዎችን በማንሳት የተሓህት- ህወሓት አመራርን አስጨነቁት። አመራሩ ተቃውሞውን አጠፍ በማድረግ በድርጅታችን ሕንፍሽፍሽ ተነሳ ብሎ ብዙ ታጋዮችን እና ንጹሃንን መጨፍጨፊያ ምክንያት አደረገው። የዲሞክራሲ ጥያቄው ተዋንያኖች፤ ገሰሰው አየለ፣ አግአዚ ገሰሰ፣ ሙሴ መሃሪ፣ አጽብሃ ዳኘውና ዶ/ር አታክልት ቀጸላ ያቀጣጠሉት ነው። የህወሓት ፋሽስትና አምባገነን መሪዎች የመጥፊያቸው ጊዜ እየቀረበ ነው፣ ተያይዘው በሕዝብ ሃይል ለፍርድ ይቀርባሉ።6. ግደይ ዘርአጽዮንግደይ ዘርአጽዮን ከአረጋዊ በርሄ ጋር በመሆን የማገብት-ተሓህት-ህወሓት የመሰረት ድንጋይ ያስቀመጡ ህወሓትን የፈጠሩት ሁለቱ ናቸው። ሌላ የለም። ግደይ የተፈጸሙ ጥፋትም ሆነ ወንጀል ካሉ ከነበሩት አመራር እኩል ተጠያቂ ነኝ በማለት በግልጽ ተናግሯል። በህወሓት አመራር አስከቆየሁበት በተፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂ ነኝ። ነጻ ነኝ ብሎ ራሱን ያላገለለ በመሆኑ ያስመሰግነዋል።ግደይ ዘርአጽዮን የተሓህት-ሀወሓት ከፍተኛ አመራር የድርጅቱ ም/ሊቀመንበር በነበረበት ጊዜ አመራሩ የሚፈጽመውን ግድያና ሽብር አውግዞ ከ1969 መጨራሻ ራሱ ነፃ በመሆን የስንት ታጋይና ሰላማዊ ዜጋ ሕይወት ያዳነ ነው። ግን ብቻውን በመሆኑ የህወሓትን አመራር ክሚፈጽሙት ወንጀል ሊያቆማቸው አልቻለም። በሰላማዊው ዜጋና በታጋዩ ግን ሰፊ የታማኝነት፣ አጋርነትና ክብር የተሰጠው ግደይ ዘርአይጽዮን ነው። ግደይ የታጋዩ ጥብቅ ጓደኛ ሆነ፣ ተወደደ። ማንኛውም ታጋይ ችግር ሲገጥመው ለግደይ ያናገራል። ግደይም ችግሩን ይፈታለታል። ግደይ ራሱም የታጋዩን እና የሕዝቡን ፍቅር ጣእሙን ስላወቀው ሁልጊዜም ደስተኛ ነበር።መለስ ዜናዊ የሚመራውን ማርክሲስት ሌሊኒስት ሊግ ትግራይ ለማቋቋም የሃላፊነቱ ተሰጠው። በ1ኛው ጉባኤ በኮሚሽን ደረጃ እንደተቋቋመ በአቋም ልዩነታቸው እነ መለስ ዜናዊ፣ ግደይን እንደጠላት ማየት፣ ግደይ ዘርአጽዮንም በአቋሙ ስለጸና መፋጠጥ የጀመርንበት ጊዜ ነበር። የነበራቸው ልዩነትም የማይፈታ ሆነ። ሁለቱም በተጻራሪ መንገድ ቀጠሉበት።በእነ መለስ ዜናዊና አበሮቹ የሚያቀርቡት፤ብሄራዊ ዲሞክራሲያዊ አብዮት የአብዮቱ መሰረታዊ ሃይሎች ድሃ ገበሬ፤ ላብ አደሩ ሲሆኑ፣ እነዚህን ካሰባሰብን የአብዮቱ ትግል ዓላማው እና ግቡን ይመታል። ሃብታም ገበሬ ከሁለት ጥንድ በሬዎች በላይ ያሉት ሃብታም ገበሬ ስለሆነ በማርክስ ሌኒናዊ ሳይንስ ሃብታም ገበሬ የትግላችን ጠላት ነው፣ በማለት አስረግጠው ተናግረዋል። ሃብታም ገበሬ መደምሰስ መጥፋት አለበት። ለምን የማርክስ ሌኒናዊ ጠላት ሃብታም ገበሬ ነው። መለስ ዜናዊ ይህንን በወይን መጽሔት እያተመ ታጋዩን ያስተምርበት ነበር።ግደይ ዘርአጽዮንሃብታም ገበሬ የማርክሲዝም ሌኒኒዝም ጠላት አይደለም። አሁንም በህወሓት የሚመሰረተው ማርክሲስት ፓርቲ ሃብታም ገበሬ ጠላት ሳይሆን የትግል አጋራችን እና ወዳጃችን ነው ተብሎ በትግሉ እንደ ወዳጅ መታወቅ አለበት። ከሁለት ጥንድ በሬ በላይ ያለው ሃብታም ገበሬ ነው ስለሆነም ጠላት ነው እያላችሁ ምክንያት በመፍጠር ያምታጠቁት የትግራይ ሕብረተሰብ ፍጹም ጸረ-ሕዝብ ነው። ንብረቱ ሁሉ እየተወረሰ ለህወሓት ገቢ ሲደረግ ለተገደለው ሕዝብና ለፈረሰው ቤት ተጠያቂ ናቸው። ይህ የሃሳብ ልዩነት በነመለስ ዜናዊ ቡድን እና በግደይ ዘርአጽዮን መካክል ሰፍቶ በመውጣት ለዓመታት ቀጠለ።መለስ ዜናዊበእኛና በግደይ ዘርአጽዮን መካከል ሰፊ ልዩነት አለ። አብረን መታገልም አንችልም። ግደይ ዘርአጽዮን ሃብታም ገበሬ የማርክስ ሌኒናዊ የትግል አጋር ነው፣ ጠላት አይደለም ብሎ ያምናል። ይህ የሚያመለክተው ግደይ ዘርአጽዮን ጸረ-ማርክስ-ሌሊናዊና በራዥ ነው ሲል በያዘው አቋም የማይነቃነቀው ግደይ፣ አንተና ጓደኞችህ ናችሁ በራዥና ከላሽ ነህ ስለአለው ንትርኩ ሰማይ ወጣ። ግደይ ዘርአጽዮን አሁንም በዚህ ጉባኤ አቀርበዋለሁ። ሃብታም ገበሬ የትግላችን አጋርና ወዳጅ መሆኑ ሙሉ እምነቴ ነው። ሃብታም ገበሬ ጠላት ነው ብሎ ማስቀመጥ ጸረ-ሕዝብ ነው። እነ መለስ ዜናዊ ሃብታም ገበሬ ጠላት ነው ማለታቸው ማንነታቸውን በትክክል ይገልጸዋል።2. በማለሊት ጉባኤ አመራሩ ዳግም ለሁለት መሰንጠቅየማለሊት ጉባኤ በዚህና በሌላውም ጸረ-ዲሞክራሲ ሲካሄድ ሰንብቶ ሐምሌ 21 ቀን 1977 ምርጫው ደረሰ። ይህ ምርጫ ሕገወጥነትን የተከተለና ሁለት ዋና ዋና ዓላማ የያዘ ነበር።
- የሥልጣን ሽኩቻ ዋና ዓላማው ነበር፣
- በዚህ የሥልጣን ሽኩቻ ማገብት-ተሓህት-ህወሓት የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠው በጸረ-ዲሞክራሲና በጸረ-ሕዝብነቱ አብረው እየመሩት የመጡት አንጋፋ አመራሮች ለማባረር በድርቅ የተጠቃው መከረኛው የትግራይ ሕዝብ እያለቀ ከአፉ ነጥቀው በነስብሃት ነጋ፣ በስንት ሚሊዮን ብር የተዘጋጀው ማለሊት ስልጣናቸውን ለማደላደል ነበር።
ምርጫውበሙሉ ድምጽ የመራጭ ብዛት 250 ነበር። ምርጫው በምስጢር ሆኖ በወረቀት የምትፈልገውን መምረጥም ነበር። ምርጫው ተካሄደ። ድምጹ ተቆጠረ። በዝርዝር ተነገረ። 1ኛ. ግደይ ዘርአጽዮን፣ ያገኘው ድምጽ 247፤ 2ኛ. አረጋዊ በርሄ፣ ያገኘ ድምጽ 245፤ 3ኛ. ሃየሎም አርአያ፣ ያገኘው ድምጽ፣ 236፤ 4ኛ. ስየ አብርሃ ወዘተ. እያለ የድምጽ ቆጠራው ቀጠለ። ወደ መጨረሻው ድምጽ ቆጠራ ደረሰ። ይህንን የሚገልጸው ህብሩ ገብረኪዳን ነበር። በጥቁር ሰሌዳ ላይ የተመረጡት ያገኙትን ድምጽ እየጻፈ ሲገልጽ የሚይዘው የሚጨብጠውን አጣ። የጉባኤው ተሳታፊ ቀጥል ብሎ አፋጠጠው። ላብ ፊቱ ላይ እየወረደ ቀጠለ። 24ኛ. መለስ ዜናዊ፣ ያገኘው ድምጽ 130፤ 25ኛ. ስብሃት ነጋ፣ ያገኘው ድምጽ 127 በማለት የ25ቱን የማለሊት ተመራጮች የማለሊት ማ/ኮሚቴ ብሎ በጥቁር ሰሌዳው ላይ በማስቀመጥ ተመልሶ ወደ ቦታው ሄዶ ተቀመጠ። መለስ ዜናዊ ራሱን ደፋ። ፊቱ የተጠበሰ ስጋ መሰለ። ስብሃት ነጋ ደግሞ አዳራሹን ለቆ ወጣ። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የጉባኤው ሊቀመንበር የነበረው ሥዩም መስፍን ከሰዓት በኋላ በ11 ሰዓት እዚህ እንገናኝ ብሎ ጉባኤተኛውን አሰናበተ። በዚህ ዓይነት ነበር ታጋዩ እነ መለስ ዜናዊን መሬት ውስጥ የቀበራቸው። ነገር ግን ተመልሰው ታጋዩን አጠቁት። ብዙ ነባር ታጋይ በእነ መለስ፣ ስብሃት ወዘተ. ተገደለ፣ ከሞት የተረፈውም ሸሸ።ልክ በ11 ሰዓት ጉባኤው ተሰየመ። በስብሃት ነጋ አመራር የተመረጡት ማ/ኮሚቴ ማለሊት አሰባስቦ ሹመትና ሥልጣን እየሰጠ እንዲተባበሩት አደረገ። ከአረጋዊ በርሄ ስልጣን አገኛለሁ ብሎ ስየ አብርሃ በከፍተኛ ድምጽ የመረጥነው በግንባር ቀደምትምነት ክህደት ከነ ስብሃት ጋር ተሰለፈ። በዚሁ ጉባኤ የመጀመሪያው ተናጋሪ መለስ ዜናዊ፤ ቀጥሎ ስብሃት ነጋ፤ ቀጥሎ ስየ አብርሃ በመተባበር ግደይ ዘርአጽዮን እና አረጋዊ በርሄ ከህወሓት ከማለሊት ተባረዋል ተባለ። ታጋዩ ተደናገጠ፣ አጉረመረመ አለቀሰ። ከአመራሩ ጻድቃን፣ ሥዩም ገብሩ፣ ወዘተ. በየተራ በሁለት አንጋፋ አመራር አሰነዋሪ የሆነ ስድብ አወረዱባቸው። የተባረሩትም ክኛ ጋር ተቀላቀሉ። እነ መለስ ዜናዊ ተደላድለው በህወሓት-ማለሊት ኮርቻ ላይ ተቀመጡ። የህወሓት ሁለተኛ መሰንጠቅ ይህ ነው።የስየ አብርሃ ክህደትስየ አብርሃ ደፋርና ጎበዝ እንደነበረ አውቃለሁ። ከሃዲነቱን ግን አላውቅም ነበር። በ1969 የሕንፍሽፍሽ ዋና ተዋናይ ነበር ተብሎ በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን እስከ 1977 ድረስ በዓይነ ቁራኛ ሲከታተሉት እንደነበር አውቃለሁ። ከህወሓት ታጋዮች ደግሞ ለሰየ አብርሃ ጥብቅና እና ድጋፍ አልተለየውም ነበር። ከዚህም የተነሳ ነው በማለሊት ጉባኤ በከፍተኛ ድምጽ የመረጥነው። ነገር ግን ከሃዲውና እምነተ ቢሱ ስየ አብርሃ የሥልጣን ጥማቱን ለማርካት የህወሓት-ማለሊት ሙሉ ወታደራዊ አዛዥ ለመሆን ግደይ ዘርአጽዮንን እና አረጋዊ በርሄን በውሸትና በስም ማጥፋት ደበደባቸው። ሲጠብቀውና ሲንከባከበው የቆየውን ታጋይ ለምን መለስ ዜናዊን እና ስብሃት ነጋን በአነስተኛ ደምጽ መረጣችሁ ብሎ ነባሩን ታጋይ እንደ እባብ እራስ እራሱን ቀጠቀጠው። በየቦታው እየሄደ አጠፋው።በህዳር 1980 የህወሓት ታጋይ ባነሳው ተቃውሞ ኤርትራም ሆነ ሌላ ቦታ ሂደን አንዋጋም። ትግራይን ከአማራው ቅኝ አገዛዝ ነፃ አውጥተን የትግራይን መንግሥት መመስረት ነው እንጂ ከዚህ ውጭ የምናውቀው ነገር የለም። ኤርትራ ሄደው በረሃ የበላቸውና ያለቁት የትግራይ ወጣት ሴትና ወንድ እስከ አሁን 130,000 ደርሷል። የኛ ድርጅት ህወሓት ከየት ወረዳና ዞን መጡ የሚል ዝርዝር ስማቸው እንኳን አያውቀውም። እንደ ሰው ሳይሆን እንደ ከብት እየታፈስን ሂደን ሞተን ቀረን። አሁንም ትግራይን ነፃ እናወጣለን እንጂ ሌላ ቦታ አንሄድም አለ። በዚህ ጊዜ እነ መለስ ዜናዊና ስብሃት ነጋ ስየ አብርሃን አነጋግረው በ36,000 ታጋይ ላይ ሞት ፈረዱበት። ይህ ሁሉ ታጋይ የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ። በዚህ ግድያ የተሰማሩት መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየ፣ ሃየሎም አርአያ፣ ሳሞራ የኑስ፣ ጻድቃን ገ/ተንሳይ፣ አበበ ተክለሃይማኖት፣ ስየ አብርሃ፣ ክንፈ ገብረመድህን፣ አርከበ እቁባይ፣ ገብሩ አስራት፣ ዓረጋሽ አዳነ፣ አውአሎም ወልዱ ወዘተ. ነበሩ።የተግባሩ አፈጻጸም በስየ አብርሃና በክንፈ ገ/መድህን ትእዛዝና አመራር ነበር። ገዳዮቹ፣ ብስራት አማረ፣ ሃሰን ሽፋ፣ ወልደሥላሴ፣ ዘአማኑኤል ለገሰ (ወዲ ሻምበል)፣ ተስፋዬ ጡሩራ (መርሳ)፣ ተስፋዬ አፈርሰው (አጽብሃ) ወዘተ. ነበሩ። ከ200 በላይ የሃለዋ ወያነ (06) ታጋዮችን በማሰለፍ ታጋዩን ገደሉት። የሃውዜን ጥቃትም በደርግ ሚግ 21-23-27 በእጅ አዙር ያስደበድቡት እነ ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ ወዘተ. ከዚህ ተነስተው ነው።ስየ አብርሃ ይህንን ክህደትና አረመኔያዊ ተግባር ከመፈጸሙ ትንሽ ቀደም ብሎ ከነመለስ፣ ስብሃትና አባይ ፀሃየ ጋር ተነስቶ የነበረው አለመግባባት ተጧጡፎ ቀጠለ። ስየ አብርሃ ሁሉንም ያጣ ብቻውን ሆኖ እየተናገረ መሄድ ጀመረ። ታጋዩ ሁሉ ጠላው፣ ራቀው። የፖሊት ቢሮ አባላት በየወሩ በስብሃት ነጋ የተፈቀደውን የኪስ ገንዘብ ብር 1,000 አልቀበልም አለ። ተወልደ፣ ገብሩ አስራትም እንደዚሁ አንቀበልም ብለዋል። ስየ አብርሃ በፈጸመው ክህደት እስከ ዛሬ በህወሓት ታጋይ እየተወገዘ ነው።3. የህወሓት ለሶስተኛ ጊዜ መሰንጠቅወቅቱ ጥቅምት 1980 ነበር። የህወሓት ማ/ኮሚቴን ጨምሮ የማለሊት ማ/ኮሚቴ በአንድነት የተጠራ ስብሰባ ነበር። በዚህ ጊዜ የተነሱት ጥያቄዎች የስልጣን ሽኩቻ ሳይሆን የህወሓት-ማለሊት ፖሊት ቢሮ ዱሮ ከነበረውና ከተፈጸሙት ስህተቶች ያልተማረ፣ ብዙ ስህተት እየፈጸመ ነው። ከዚህ ስህተቱ መማር አለበት ወዘተ. በማለት የቀረበው ጥያቄ አነታራኪ ሆኖ በመቀመጡ፣ ስብሃት ነጋ በሚመራው ስብሰባ የቀረቡትን ጥያቄዎች በሙሉ ውድቅ አደረጋቸው። መለስ ዜናዊም የስብሃት ነጋን ሃሳብ ደገፈ። ጥያቄቆቹን ያነሱት በ1975 በ2ኛው ጉባኤ የተመረጡት የህወሓት አመራር ናቸው። እነሱም፤- ክብሮም ገ/ማርያም የህወሓት ማ/ኮሚቴና የሰራዊቱ የሎጂስቲክ ዋና ሃላፊ የነበረ፣
- ኃ/ሥላሴ መስፍን፣ የህወሓት ማ/ኮሚቴ፣ ጠቅላላ የህወሓት ክፍለ ጦሮች የኮሚሳሮች የበላይ ሃላፊና ተቆጣጣሪ የነበረ፣
- ሰአረ ገብረጻድቅ፣ የህወሓት ማ/ኮሚቴና ጠቅላላ የህወሓት ማ/ኮሚቴና ፖሊት ቢሮ ጽ/ቤት ሃላፊ የነበረ፣
- ተክሉ ሃዋዝ፣ የህወሓት ማ/ኮሚቴና የቀድሞ የድርጅቱ ዋና የደህንነት ሃላፊ የነበረ ናቸው።
ከላይ የተጠቀሱት አራቱ አመራር ባቀረቡት ሃሳብ አፈንጋጩ የእነ ግደይ ዘርአጽዮን እና አረጋዊ በርሄ ደጋፊዎች ተብለው ተወነጀሉ። ወንጃዮቹ፣ መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ ስየ አብርሃ፣ አውአሎም ወልዱ፣ አባይ ፀሃየ፣ ሥዩም መስፍን፣ ገብሩ አስራት፣ አርከበ እቁባይ ናቸው፡ እነዚህ የፖሊት ቢሮ አባላት ተሰብሰበው ተወንጃዮቹን በማስጠራት እርማት እንዲያደርጉ ወሰኑ። በቀረቡበት ጊዜም፣ ያቀረባችሁት ሃሳብ ጸረ-ህወሓት-ማለሊት በመሆኑ፤ ከአመራርና ከሃላፊነታችሁ ተወግዳችሁ በተራ ታጋይነት ቀጥሉ ተብለው በስብሃት ነጋና መለስ ዜናዊ ተሰናበቱ። ይህ ወቅት ህወሓት ለሶስተኛ ጊዜ የተሰነጠቀበት ወቅት ነበር።5. የህወሓት ለአራተኛ ጊዜ መሰንጠቅይህ የህዋሓት ለአራተኛ ጊዜ መሰንጠቅ በ1993 የተፈጠረው ነው። ዋናው ዓላማ የስልጣን ሽኩቻ ነበር። ሌላው አንዱ ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ ሆኖ ሌላው ደግሞ ጸረ-ኢትዮጵያ ሆኖ የተፈጠረ መበታተን አይደለም። በእነ ስየ አብርሃ የሚመራው ቡድንም ጸረ-ኢትዮጵያና ጸረ-ሕዝብ ነው። ሃገራችን ኢትዮጵያን ያፈረሱ፣ የቀይ ባህር የባህር በሯን የሸጡና ያስነጠቁ፣ የዘር ማጥፋት እልቂት የፈጸሙ፣ ሕዝብን ለድህነት፣ ለችግር፣ ለበሽታና ለስደት የዳረጉ እነ መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ ስየ አብርሃ፣ ተወልደ ወ/ማርያም፣ ገብሩ አስራት ወዘተ. ተባብረው በሕዝብና በሃገር ከባድ ወንጀል የፈጸሙ ናቸው። በሁለት የተሰነጠቁበት ቀንደኛ ምክንያት ደግሞ የስልጣን ሽኩቻ ነው። ሌላ ምንም ነገር አልነበረም።6. የህወሓት ለአምስተኛ ጊዜ መሰንጠቅህወሓት ኢትዮጵያን ወሮ በቅኝ ግዛት ከተቆጣጠረ በኋላ መሪው መለስ ዜናዊና የህወሓት አመራር ሁሉም በሃገራችን ከፍተኛውን የሥልጣን ወንበር ላይ ተደላድለው በመቀመጥ ኢትዮጵያን ለ21 ዓመታት በገዙበት ጊዜ በሕዝብና በሃገር ከፍተኛ ወንጀል በመፈጸም የኢትዮጵያን ሃብት ዘርፈዋል። ሕዝብን ያደኸየውን ስርዓት የመሰረተው መለስ ዜናዊ ሰኔ 7 ቀን 2004 ከዚህ ዓለም በሞት ተቀጠፈ። ብስራት አብሳሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ መከታና መመኪያ እንዲሁም ዓይን እና ጆሮ ኢሳት በጥዋቱ የመለስ ዜናዊን ሞት ነገረን። ለወዳጆቹ ሃዘን ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የእፎይታ ቀን ሆነ። አረመኔው መሪ መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት ተቀጥፎ መኖሪያውን ሲኦል አደረገ። በዚህም ምክያት ህወሓት ለአምስተኛ ጊዜ ተሰነጠቀ። ከላይ እስከ ታች በቅራኔና በሥልጣን ሽኩቻ እንደ ዱባ ተፍረከረከ።
No comments:
Post a Comment