ፌዴሬሽኑ የፊፋን ክስ አመነ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምንያህል ተሾመ ሁለት ቢጫ ካርድ አይቶ ሳለ ሰኔ 1/2005 ከቦትስዋና ብሄራዊ ቡድን ጋር በተደረገው ጨዋታ መሰለፉ ስህተት እንደሆነ አመነ፡፡
ፌዴሬሽኑ ብሄራዊ ቡድኑ ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር ከመጫወቱ በፊት ችግር ስለመፈጠሩ ፊፋ አሳውቆት እንደነበር ገልጿል፡፡
ሆኖም ይህ ችግር በቡድኑ ተጫዋቾችና በደጋፊዎች ላይ ያልተፈለገ የመንፈስ ጫና እንዳይፈጥር በመስጋት መረጃውን ይፋ ሳያደርግ ቆይቷል፡፡
ፌዴሬሽኑ በፈጠረው ችግር ዙሪያ ለጋዜጠኞች መግለጫ እየሰጠ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎች ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ እናቀርባለን፡፡
No comments:
Post a Comment