በሌሊት እርቃኔን ሆኜ ቀዝቅዛ ውሃ እየተደፋብኝ ምርመራ ይካሄድብኛል” – ወ/ሮ አልማዝ
በሌሊት እርቃኔን ሆኜ ቀዝቅዛ ውሃ እየተደፋብኝ ምርመራ ይካሄድብኛል” – ወ/ሮ አልማዝ

የፀረ ሙስና ኮሚሽን ባለፈው ወር ወደ ፍ/ቤት ባቀረባቸው ተጠርጣሪዎች ላይ የጀመረውን ምርመራ እንዳላጠናቀቀ
በመግለፁ፤ ለሦስተኛ ጊዜ የ14 ቀናት ቀጠሮ ተፈቅዶለት ተጠርጣሪዎች በእስር እንዲቆዩ ታዘዘ፡፡ በአምስት የምርመራ
መዝገቦች የተካተቱት ከአርባ በላይ ተጠርጣሪዎች ሰሞኑን እንደገና ፍ/ቤት የቀረቡ ሲሆን፤ ከተጠርጣሪዎች አንዷ
የሆኑት ወ/ሮ አልማዝ ከበደ በውድቅት ሌሊት ራቁታቸውን ቀዝቃዛ ውሃ የተደፋባቸው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን
ለፍ/ቤቱ ገልፀዋል፡፡ ፍ/ቤቱ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በተለያዩ መዝገቦች የቀረቡት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣
ነጋዴዎች፣ ትራንዚተሮችና ደላላዎች እንዲሁም የገቢዎችና ጉምሩክ ሠራተኞች የጠየቁትን የዋስትና መብት በመከልከል
የምርመራ ቡዱኑና አቃቤ ህግ ለ3ኛ ጊዜ የጠየቁትን የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል፡፡ ሁሉም ተጠርጣሪዎች
በጠበቆቻቸው ለፍ/ቤቱ ባቀረቡት አቤቱታ፣ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ካሁን በፊት ተጠርጣሪዎቹን የያዝኳቸው በበቂ ማስረጃ
ነው ማለቱን ጠቅሰው፣ ምርመራዬን አልጨረስኩም እያለ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መጠየቅ አልነበረበትም ብለዋል፡፡
የፀረ ሙስና ኮሚሽን ሁለቴ የ14 ቀን የቀጠሮ እንደተሰጠው የተጠርጣሪ ጠበቆች ገልፀው፤ ኮሚሽኑ ምርመራዬን
አላጠናቀቅኩም ብሎ እንደገና ጊዜ ይሰጠኝ ማለቱ ስራውን በትጋት እየተወጣ አለመሆኑን ያመለክታል ብለዋል፡፡ የፀረ
ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን በበኩሉ፣ እስካሁን ያከናወናቸውን ስራዎች ለፍርድ ቤቱ ሲዘረዝር በተጠርጣሪዎች መኖሪያ
ቤትና ቢሮ በብርበራ የተገኙ ሠነዶችን ሲያጣራ መቆየቱን ጠቅሶ፣ ዲጂታል ማስረጃዎችን ለሙያተኛ በመላክ ውጤቱን
እየተጠባበቀ መሆኑን ገልጿል፡፡ ከአዲስ አበባ ውጪ በሞጆ፣ በአዳማ፣ በሚሌ እና በአዋሽ የገቢዎችና የጉምሩክ
ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች የምርመራ ቡድን ተልኮ ምርመራ እያከናወነ መሆኑን ለፍ/ቤት ተናግሯል፡፡ ቀረጥ ሰውረዋል ተብለው
በተጠረጠሩት ድርጅቶች ላይ የተጀመረው የኦዲት ስራ አለመጠናቀቁን የገለፀው ኮሚሽኑ፤ ስራው ከተጠናቀቀ በኋላ
የኦዲተሮችን ቃል እቀበላለሁ ብሏል፡፡
ምንጩ ያልታወቀ ሃብትን ህጋዊ አስመስሎ ከመያዝ ጋር በተገናኘ የተጀመሩ ምርመራዎችም እንዳልተጠናቀቁ ኮሚሽኑ
ገልፆ፤ ፍ/ቤቱ የምርመራውን ስፋት እና ውስብስብነት በማገናዘብ የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ይፍቀድልኝ ሲል
ጠይቋል፡፡
ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን አይቶ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል፡፡ ካሁን በፊት በርካታ ተጠርጣሪዎች የተለያዩ
በደሎች እና ድብደባ ጭምር እየተፈፀመባቸው መሆኑን በመግለፃቸው ጉዳያቸው እንዲመረመር በፍርድ ቤት የተሰጡ ትዕዛዞች
የት እንደደረሱ ባይታወቅም፣ በዚህ ሳምንትም ከተጠርጣሪ ለቀረበ ተመሳሳይ አቤቱታ ተመሳሳይ የምርመራ ትዕዛዝ
ተሰጥቷል፡፡ ከተጠርጣሪዎች አንዱ የሆኑት ወሮ አልማዝ ከበደ፣ በምርመራ ወቅት ሰብአዊ ክብራቸውን የሚነካ ነገር
እየተፈፀመባቸው መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ገልፀው፣ ከምሽቱ 6 ሰዓት ራቁታቸውን ቀዝቃዛ ውሃ እየተደፋባቸው ምርመራ
እንደሚካሄድባቸው ተናግረዋል፡፡ ወ/ሮ አልማዝ አቤቱታቸውን ለፍርድ ቤቱ ሲያቀርቡ ቤተሰቦቻቸው ያለቀሱ ሲሆን፤ የፀረ
ሙስና ኮሚሽን የምርመራ ቡድን ድርጊቱን ተቃውሟል፡፡ ተጠርጣሪዎች ያቀረቡት አቤቱታ “ሃሰት ነው” ሲል ተቃውሞ
ያሰማው የፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ የተጠርጣሪዋ አቤቱታ የተቋሙን ስም ለማጉደፍ ታስቦ ቤተሰቦቻቸው ጭምር የተሣተፉበት
በምክክር የተደረገ ነው ብሏል፡፡ በሌላ ትዕዛዝም የህክምና እና ከሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር ተያይዘው ከተጠርጣሪዎች
የቀረቡ አቤቱታዎችን በተመለከተ የኮሚሽኑ የምርመራ ቡድን እንዲያጣራና ክትትል እንዲያደርግ ፍርድ ቤቱ ማሳሰቢያ
ሰጥቷል፡
- 16 የኢትዮዽያ ከፍተኛ ባለስልጣን በሙስና ተጠርጥረው ታሰሩ (freedom4ethiopian.wordpress.com)
No comments:
Post a Comment