
ለሚመለከተው አካል ማመልከቻ ቢያሰገባም ደብዳቤውን አንቀበልም የተባለው ሰማያዊ ፓርቲ በእማኞች ፊት ማመልከቻውን አስገብቶ ለከንቲባ ጽ/ቤትም አቤት ብሎ ነበር፡፡ እኛም ይህንን አስመልክቶ በጠዋቱ ዜና በጨዋታችን እንዲህ ብለን ነበር….
…..የጽ/ቤቱ ሃላፊዎች ለምን ደብዳቤውን አንቀበልም እንዳሉ እንጃላቸው… ምናልባት እነርሱም በመንግስታቸው የተከፉበት ጉዳ ይኖራል፡፡ (ይቺ የግዳጅ ቦንድ ግዢ እኮ ሰራተኞች የስራ ተነሳሽነት ላይ ከባድ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ነው ያላት….) የምሬን ነውኮ… እነዚህ ሃላፊዎች በመንግስታቸው ላይ ቅሬታ ባይኖራቸው ኖሮ ደብዳቤውን ተቀብለው …
ለሰማያዊ ፓርቲ ባሉበት፤
ደብዳቤያችሁን በጥሞና ተመልክተነዋል፡፡ ጥያቄያችሁ ህገ መንግስታዊ እና ተገቢም ነው፡፡ የስብሰባ እና ሰላማዊ ሰልፍ “አዋቂ” ጽ/ቤትም ይህንን አይነት ጥያቄዎችን ያበረታታል፡፡ ነገር ግን በዕለቱ እንግዶች ስለሚበዙ እና የጥበቃ ሃይላችንም ስራ ስለሚበዛበት መልካም ፈቃዳችሁ ሆኖ ሰላማዊ ሰልፋችሁን ለሌላ ግዜ ብታዘዋውሩት ደስታችን ወደር የለውም፡፡
ከሰላምታ ጋር!
አባይ ይገደባል ሰልፍም ይፈቀዳል፡፡
የማይታይ ማህተም እና ፊርማ፡፡
አድርጎ በጨዋ ደንብ መሸኘት ይቻል ነበር፡፡ ነገር ግንብዙዎቹ የመንግስት ሰራተኞች በተለይ ከዚህ የግዳጅ ለአምስት መረባዊ አደረጃጀት እና የግዳጅ አባይ መዋጮ በኋላ አድማ ላይ ናቸው እና ደብዳቤ አንቀበልም ይላሉ፡፡ ይሄ ከስራ ማቆም አድማ ተለይቶ አይታይም፡፡ ይሄ ፈቃድ ካልተጠየቀበት ተቃውሞ ካለይቶ አይታይም፡፡
የሆነ ሆኖ አሁን ሰማያዊ ፓርቲ ደብዳቤውን በእማኞች ፊት ጠረቤዛ ላይ አስቀምጦ ወጥቷል፡፡ በህጉ መሰረት ሰልፉን ከማድረግ ምንም የሚያግደው ነገር የለም ማለት ነው…
እውነትም ታድያ ከንቲባ ጽ/ቤት ብሎጋችንን አንብቦ ፌስ ቡካችንንም ጎብኝቶ ነው መሰል በጨዋ ደንብ ሰላማዊ ሰልፉን ለሌላ ጊዜ አስተላልፉት እና ይፈቀዳል አላቸው ሰማያዊዎችም እሺ አሉ ለግቦት 24 ሰላማዊ ሰልፉ ዕውና አገኘ፡፡ እኛም አልን….
ብራቮ ከንቲባ… ብሎጋችንን ሳታነብ አልቀረህምና….!!! ብራቮ ሰማያዊ… በፅናታችሁ እነ እንቶኔን ሳታስደነግጡ አልቀራችሁምና!
No comments:
Post a Comment