Ethiopian Uprising
"NO BULLET CAN KILL THE SPIRIT"
የትግራይ ህዝብ ከትግራይ ውጭ “የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን” የማይምን ከሆነ፤ ከጉያው ውስጥ ያሉት “ዓረና ትግራይ” የተባለው ድርጅትስ መነዋ ማመን አቃተው?
www.ethiopiansemay.blogspot.comwww.ethiopiansemay.blogspot.com
( ጌታቸው ረዳ ለአብርሃ ደስታ “የትግራይ ህዝብ ዝምታ ሲተረጎም” ከሰጠው መልስ የተወሰደ :: ሙሉውን ከድረፁ ያንብቡ )… ሁለት ዓይነት የትግራይ ምሁራኖች አሉ። አንደኛው ቡድን ወያኔን በግልጽ የሚቃወሙ፤ ነገር ግን “ዞር አሉ አልሸሹም” ዓይነት አስተሳሰብ ያላቸው በተዘዋዋሪም ሆነ በቀጥታ ከሚያሞቃቸው “የጎሳ ቀፎ” መውጣት የማይፈልጉ ናቸው (ትንሽ ስታካቸው እና ክርክሩ ጠበቅ ሲልባቸውና ሲበሳጩ ወያኔነታቸው በቀላሉ የሚነበብባቸው ማለት ነው)። ወያኔ መቃወም ብቻ አያስፈልግም፤ መልካሙን ነገርም አውሱለት፤ እየተሰራ ያለው ሕንጻ፤ሆቴልና ፋብሪካ አወድሱለት ወዘተ…. የሚሉ ናቸው (ሂትለር ጀርመንን በኢንዱስትሪ በር ከፍቶላታል እና ስለ ሂትለር በጐነት አውሩ አንደማለት)። አንዲህ አይነት የተምታታ አቋም ያለቸው የትግራይ ምሁራኖች ብዙዎቹ ቢሆኑም ለምሳሌ ለምጥቀስ አንደ ዶ/ር ገላውዴዎስ አርአያ እና ዶ/ር ሃይሉ መንገሻ የመሳሰሉት መጥቀስ ይቻላል።
ሌላው
ቡድን ደግሞ በግልጽ የወያኔን ፖሊሲ አቅፎ ደግፎ “እልል” እያሉ የወያኔ ፕሮፓጋንዳ እየተቀበሉ የሚተገብሩ እና
የጥፋት መልእክተኛ የነበረው የመለስ ዜናዊ አወዳሾች አንደ እነ ዶ/ር ተወልደብርሃን ገ/አግዚአብሔር (የደራሲው
የስብሐት ገ/እግዚአብሔር ወንድም)http://youtu.be/f75zPblWSiI
የሕዝቡን መከራ የሚያራዝሙ፤ጠባብ ብሔረተኛነት ሕሊናቸውን ያሰወራቸው “ዑውራን” ምሁራን ይገኙበታል። አነኚህ እና
የመሳሰሉ የትግራይ ምሁራን 1ኛ የሕዝብቻው ስቃይ እያዩም ቢሆን ባድርባይ ጸባይ እና ወያኔ በለገሰላቸው ምቾት
ታውረው ተባበሪ የሆኑ ናቸው።
ዛሬ ዛሬ ቀዝቀዝ አሉ እንጂ፤ሌሎቹ ደግሞ መጽሔት አቋቁመው የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ተቀብለው በጸረ አማራነት እና በጸረ ኢትዮጵያነታቸው የታወቁ ከኤርትራ ምሁራን ጋር እጅ እና ጓንቲ ሆነው “ጸረ አማራ” (እነሱ ነፍጠኛ የሚሉትን) መስመር በማራመድ፤ የማይገቡ አሳዛኝ ቅስቀሳዎች በመዝራጋት መጥፎ የታሪክ ጠባሳ የተው ናቸው። አንዳንድ አንባቢዎች ከባዶ ሜዳ ተነስቼ ለሃሜት የጻፍኩት እንዳይመስላቸው ከኤርትራ ምሁራን ጋር ግምባር ፈጥረው “ወያኔን እያወደሱ” በነዚህ ምሁራኖች በአማራነት የሚጠሩ አንዳንድ ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን በማይገባ በመዝለፍ (በመጽሔቱ ላይ ለምሳሌ አቡነ መርቀሬዎስን “ዘ አዘር ዶግ/ሌላኛው ውሻ” በማለት በፎቶአቸው ላይ ተጽፏል) ወይንም ዶኩመንቶችን በማዛባት የሕዝቡን አፍ ለማስዘጋት ሲሞክሩ ነበሩ ዝነኚህ የትግራይ ምሁራን እና የኤርትራ ምሁራን ስም ዝርዝር ለማየት ከፈለጉ ለምሳሌ “ኢትዮጵያን ኮመንታተር” የተባለው መጽሄት አዘጋጆች የነበሩትን መጥቀስ ይቻላል። ባንዳንድ ጸሐፊዎች አባባል መጽሔቱን “ሻዕቢያ ወያኔ ፒስ ማውዝ” ሲሉት ነበር።
ስም ዝርዝር፤ ማነጂንግ ሲኒየር ኤዲተር ኤንድ ፓብሊሺንግ ዶ/ር ሃይለማርያም አበበ፤
Editors ዶ/ር ገላውዴዎስ አርአያ (ኒው ዮርክ)፤ ክንፈ አብርሃ (ስቶክሆልም ስዊድን) ፤ዶ/ር ሶሎሞን ዑንቋይ (ካምብርጅ- ዩናይትድ ኪንግዶም) ዘመነ ልብነድንግል(ፎርት ኮሊስ ኮሎራዶ)
አምደኞች (Contributors)፤ መስፍን አርአያ (አርሊንገተን ቨርጂኒያ)፤ ዶ/ር ደስታ በየነ፤ ዶ/ር ተክኤ ፍስሃጽዮን ( ሞርጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ፤ባልቲሞር ኤም ዲ) ሻዕቢያ (ኤርትራዊ)፤ ጆርዳን ገብረመድህን (ኖርዝ ኢስተርን ዩኒቨርሲቲ- ቦስተን) በህይወት የለም- ነገር ግን ሻዕቢያ (ኤርትራዊ)፤ ዶ/ር አሰግድ ሐጎስ (ዩኒቨርሲቲ ዋሺንገተን ዲሲ) ጸጋይ ሃይሉ (ከኢትዮጵያ)፤ዶከተር ግደይ ወለደገብሪኤል (ሎስ አልሞስ ላብ-ኤን ኤም) አማኑኤል አሰፋ (ዋሺንግተን ዲሲ)፤ዑቕባዝጊ ዓባይ (ሰንሰናቲ- ኦሃዮ)
Editorial Advisors ዶ/ር አምሃ አሰፋ (ሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ- ዋሺንገተን ዲሲ (አገር ውስጥ እያለ በወጣትነታችን የቅርብ ጓደኛነት የነበረን አሁንም የወያነ ደጋፊ አንደሆነ ነው የሚነገረኝ)፤ ሐጎስ ካፊል (ካላማዙ ኤም አይ)፤ዶ/ር ገብረህይወት ተስፋጊዮርጊስ (ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ዊስካንሰን)፤ ዶ/ር ፀሃየ ተፈራ (ዳይሬክተር ኢትዮጵያን ኮሚኒቲ ዴቨለፕመንት ካውንስል አለክሳንድርያ -ቨርጂኒያ)፤ዶ/ር ያዕቆብ ፍስሃ (ምቺጋን ዩኒቭርሲቲ)።
እነዚህ በሙሉ ዶክተሮች ናቸው። ይታያችሁ የላቸው መዓረግ እና የዘፈቁበት የብሄረተኛ ፕሮፓጋንዳ ስታነጻጽሩት፤ በወያኔ ለተረገጠው የኢትዮጵያ ሉአላዊነት እና የሕዝቡን መብት መረገጥ ተገቢውን መስመር ለማስያዝና ለፍትሕ መቆም ሲ ገባቸው፤ ፀ ረ ኢትዮጵያ ከሆኑት ሻዕቢያ “ኤርትራዊያን” ጋር ግምባር ፈጥረው የጎሰኞች ፕሮፓጋንዳ ለማራገብ በጸረ አማራነታቸው ከታወቁት ከነኚህ ኤርትራኖች ከነ ዶ/ር ተክኤ ፍስሃጽዮን፤ጆርዳን ገ/ብረመድህን ጋር አጅ እና ጓንቲ ሆነው በታሪክ ላይ ጠባሳ ንድፍ ትተዋል።
አነኚህ እና የመሳሰሉ የትግራይ ምሁራንን ዛሬ ምን እየሰሩ እንደሆነ በግምባር ቀደም ከመውቀስና ከመተቸት ይልቅ “የፖለቲካ ተቃወሚዎች” የትግራይን ሕዝብ ወደ ወያኔ እየገፉት ነው ይለናል። አብርሃ ደስታ አንዲህ ይላል፤
“በዚህ መሰረት (የትግራይ ሕዝብ) ህወሓትን እየተቃወመም ቢሆንም የተቃዋሚ ድርጅቶች ግን ከህወሓት ሊብሱ ይችላሉ ብሎ እንዲያስብ ስለሚገደድ ግራ ተጋብቶ ‘የባሰ ኣታምጣ’ ብሎ ኣብሮ ዝም ይላል።ለዝምታው ምክንያት አለው” ሲል በተቃዋሚው ላይ ትችቱን አሹሏል። ይገርማል።
ወጣት አብርሃ ደስታ የትግራይ ምሁራን ምን ያህል በቆሸሸው የወያኔ ፖለቲካ አንደተዘፈቁ እና የሕዝቡን እና የአገሪቱን ሉዓላዊነት ሲደፈር አፋቸው ዘግተው አይተው እንዳላዩ ሲሆኑ፤ አብዛኛዎቹ ደግሞ “ወያኔ የሚያደርገው ጸረ ሉዓላዊ” አርምጃ “እሰየው” እያሉ የወንጀሉ ተባባሪዎች እየሆኑ አንደሆነ ብዙ ያወቀው አልመሰለኝም።
የትግራይ ህዝብ ከትግራይ ውጭ አሻግሮ በወሬ የሚያዳምጣቸው “የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን” የማይምን ከሆነ፤ ከጉያው ውስጥ ያሉት “ዓረና ትግራይ” የተባለው ድርጅትስ መነዋ ማመን አቃተው? እንምራህ ብለው ተነስተዋል፤ ብዙ ዓመት ሆኗቸዋል አመርቂ አንቅስቀሴ ሲያደርጉ አልታዩም። ባለፈው ሕዝባዊ ምርጫ፤ የምርጫው ውጤት ትግራይ ውስጥም አንደተጭበረበረና ተጽእኖ አንደተደረገላቸው የታወቀ ነው። ታዲያ “የትግራይን ሕዝብ እንደ ሌሎቹ “በጠላትነት” የማይፈርጁት፤ “ከወያኔ ጋር የማያደባልቁት” “መረገጡን” የሚያስተጋቡለት፤ የዓረና ተቃወሚዎች ከጉያው ትግራይ ውስጥ እያሉ ለምን ሆ ብሎ አነሱን ደግፎ “ተቃዉሞውን አላጧጧፈም?
ሰለዚህ የትግራይ ሕዝብ ሲጨቆን “ሌላው” በፍርሃት “ዝም” ስለሚል ነው፤ ወይንም ተቃወሚዎቹ “አንደጠላት” ስለሚፈርጁትት ነው፤ የሚለው አንካሳ ምክንያት አንደ ምክንያት ተቀባይነት የለውም፤፡ መጀመሪያ ነገር ወያኔ የሚያወራው ተቃዋሚዎች “የትግራይን ሕዝብ አንደጠላት ያዩታል” የሚለው የወያኔ ፕሮፓጋንዳ አብርሃ ደስታም ሆነ ሌሎቹ የትግራይ ተወላጆች ተቀብለው እያስተጋቡት ነው። የፖለቲካ ተቃዋሚዎች የትግራይ ሕዘብ በጣላትነት የፈረጀ አንድም (በኢትዮጵያ የሚያምኑ ተቃዋሚዎች) በመረጃ የሚያቀርብ ከአብርሃ ጀምሮ እስከ ሺዎቹ የሚቈጠሩ የትግራይ ምሁራን ማስረጃ አስደግፎ የሚያቀርብ እስካሁን ድረስ አላየሁም። መረጃው አለን የሚሉ ከሆነም ይሄው “ቻለንጁ” ግብዣው እና ሜዳው።
ተቃዋሚው በትግራይ ሕዝብ ተቃባይነት አንዳይኖራቸው ለማድረግ ወያኔ ዘርግቶት የነበረው እና አሁንም እየገፋበት ያለው የውሸት ፕሮፓጋንዳ እየተቀበሉ ማስተጋባት አላዋቂነት ብቻ ሳይሆን የሚያስገምት ነው። የመለስ ዜናዊ “ኢንተርሃሙዌ” ፕሮፓጋንዳ ብዙ የትግራይ ተወላጆች ተቀብለውት አንደነበረ የምናስታውሰው ነው፤፡ አሁንም አብርሃ እያለን ያለው፤-
“ስለዚህ ተቃዋሚዎች ከትግራይ ህዝብ ጋር መወያየትና መግባባት ያስፈልጋቸዋል። ምክንያቱም ሳያውቁት (በሚጠቀሙት የፖለቲካ ስትራተጂ) የትግራይን ህዝብ (target የሚያደርጉ ስለሚመስሉ) በህወሓት ቢጨቆን እንኳ ህወሓትን ላለመቃወም እንዲወስን (የባሰ እንዳይመጣ) ያደርጉታል። ስለዚህ የትግራይ ህዝብ ዝምታ ምክንያት ኣለው (ህወሓት ስለሚደግፍ ግን ኣይደለም)።
ምንድ ነው ተቃዋሚዎቹ ሳያውቁት “በትግራይ ሕዘብ ላይ እያራመዱት የሚገኙት “የፖለቲካ ስትራተጂ”? የትግራይን ሕዝብ ‘ታርጌት’ ያደረገ በጣለትንት የፈረጀ የፓቲካ ስተራተጂ የቱ አንደሆነ ወይንም ማን ድርጅት እና ተቃዋሚ እንዲህ ያለ ስትራተጂ እየተከተለ አንደሆነ በመረጃ እስካልቀረበ ድረስ “ለትግራይ ሕዝብ ዝምታ ተቃዋሚው ለዝምታው “ምክንያት” ነው ብየ አልቀበለውም።አብርሃ የቤት ስራውን ከዚህ በተሻለ መስራት ይኖርበታል።
የሕዝቡ ዝምታ ወያኔን ላለመቃወም ምክንያት ብሎ አብርሃ ሲገልጽልን ‘አንድ ጊዜ ተቃዋሚው በሚያራምደው የፖለቲካ ስትራተጂ ነው “ዝምታ ሊመርጥ የቻለው” ይለናል፡ አንድ ጊዜ ደግሞ ከጭቆናው ላላመላቀቅ የመረጠው “ስለፈራ” ነው ይለናል። ‘ፍርሃት’ በተጠቀሰው አባባል፤ በማሕበራዊ ትንተና እንደ ምክንያት የሚያስኬድ ቢሆንም። 21 ዓመት ባነስተኛው “ከፍርሃቱ”በጥሶ መውጣት ካልቻለ፤ ሌላ ያልተመረመረ ምክንያት አለው። ያ ምክንያት ምንድ ነው? (እዚህ ላይ ዝምታው የትግራይ ሕዝብ ብቻ ተወቃሽ ማድረግ ተገቢ እንዳልሆነ በደማቅ ላሰምርበት እሻለሁ። ምክንያቱም ዝምታው በሌሎቹም እየታየ ያለው አሳዛኝ ሲንድሮም ነውና)። ቢሆንም በትግራይ ላይ መተኰር ያለበት ልዩ ምክንያት ስላለ ፤ በዚህ እንቀጥል፤፡ ለትግራይ ሕዝብ ዝምታ መነሻው ምንድ ነው?
የተቀረው ኢትዮጵያዊ ለምሳሌ አማራው ሕዝብ እና ኦሮሞ፤ጋምቤላ… አንዲሁም ሌሎቹ በደርግ እና በወያኔ ንጽጽር ምርጫ ቢገቡ ከወያኔ ደርግ እንደሚሻላቸው ይምርጣሉ። ኤርትራኖቹም አንደዚሁ (እራሳቸው በየቀኑ የሚያቀርቡት የሕዝቡ ዘገባ መመልከት በቂ ነው)።፡ትግራይ ውስጥ ግን ምርጫው የነዚያ ተጻራሪ እንደሆነ አያጠራጥርም። አሁንም ቀደም ብየ ወደ ገለጽኩት “የባዕድ ጅብ ከሚበላን የኛው ጅብ ይብላን” ወደ ሚለው አብርሃ ቀደም ብሎ ወደ ተነተነው “ደርግ እና ወያኔ” ወደ ማወዳደሩ ስንገባ “የብሔረተኛነት” ስነ ልቦና እዚህ ላይ ትልቅ ሚና አንዳለው መዘንጋት የለብንም።
ሕዝቡ ለ38 ኣመት በትግራይ ብሔረተኛነት ተሰብኮ የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ተቀብሎ እያራመደው አንዳለም አብርሃ ሊገልጽልን ያልቻለበት ምክንያት አልገባኝም። የትግራይ ሕዝብ ከሌለው በተሻለ መንገድ በወያኔ ስርዓት “ተጠቃሚ” መሆኑን ለብዙ ጊዜ ተከራክረንበታል። አብዛኛዎቹ የትግራይ ምሁራን ይህንን እውነታ ሊቀበሉት አልፈለጉም። ሁለት ምከንየቶች አሉዋቸው። አንደኞቹ “ ተጠቃሚ እየሆነ አንዳለ ቢገባንም” ለወደፊቱ በሌሎቹ አካባቢ ሕዝብ ቅሬታ ፈጥሮ ለአደጋ ሊጋለጥ ስለሚችል፤ ይህን ከማስተጋባት መቆጠብ አለብን” ብለው የተናገሩኝ የትግራይ ተወላጆች አሉ። ለዚህ መለስ ካሁን በፊት ጽፌአለሁ።
አልደግመውም።
2ኛው/ሌላኛው ክፍል ደግሞ፡ ጭራሽኑ ከነበረበት ከደርግ ጊዜ ብሶበታል አንጂ አልተጠቀመም የሚሉ አሉ (የትግራይ ተወላጆች ብቻ ሳይሆኑ ይህንን ውሸት የሚያስተጋቡ፤ በተቃዋሚ ጐራ የቆሙ አሁን አስመራ ከተማ የሚኖር የግንቢት 7 ዋና ጸሐፊው አንዳርጋቸው ጽጌም ጭምር-በዴምህት (ዴሞክራሲያዊ ምንቅስቓስ ህዝቢ ትግራይ) አስመራ ውስጥ ቃለ መጠይቅ ተደርጐለት ያስተጋባው አድር ባይ ውሸትን ልብ ይለዋል)። አንዲህ ዓይነቱ የተዛባ ሙግት ማቅረብ ለምን እንደሚጠቅም ግራ ይገባኛል። የምናወራው “ሪል ፖለቲክ” ነው። አገርና ህዘብን የሚመለከት ትንተና እና ዘገባ ነው። ገና ከመነሻው የብሔረተኛ ቀዳሚ ምኞቱ እና እቅዱ ማወቅ ያስፈልጋል። ወያኔ ብሔረተኛ/ጎሰኛ ነው።ብሔረተኛ ደግሞ፤ መጀመሪያ “የራሱን ብሔር” ይብዛ ይነስ ከሌሎቹ ቅድሚያ መስጠት ነው ተቀዳሚ የቤት ስራው። ለዚህም ነው ወያኔዎችና የወያኔ ጀሌዎች (የወያኔ አባሎችም ያልሆኑ ጭምር) በመተባባር “ትግራይ ልማት መረዳጃ ማሕበር” /ልምዓት ዓዲ ብወዲ ዓዲ’ በሚል መርሆ ታቅፈው ፡በትግራይ ላይ ጉልበታቸው፤ገንዘባቸው፤አውቀታቸው በማስተባባር ለጎሳቸው ቅድሚያ በመስጠት፤ ወያኔ ባሰመረላቸው የጎሰኛነት መመሪያ መሰረት እየተመሩ “ትግራይን ወደ ላቀ ደረጃ አድረሰዋት” የሚገኙት።
ወያኔ ትግራይን በማልማት፤ ፋሲሊቴሺኑን በማዘጋጀት እና በተቻለ መጠን አንድ አገር አንደ አገር ሊያቆመው የሚችል መረታዊ ልማቶችን መዋቅሮችን በትግራይ ዘርግቷል።በዝርፍያ፤በገሃድ፤በሕጋዊ እና ሕገውጥ በሆኑ መንገዶች ሁሉ ለራሱ ዘርፎ ከሚተርፈው የዝርፊያ ሃብት ወደ ትግራይ በማፍሰስ ቀዳሚ የልማት ምሳሌ የሆነችበት ምክንያት ወጣት አብርሃ ሊነግረን አልፈለገም። ሕብረተሰቡ ብናምን ባናምንም የወያኔ ትግራይ ዳረጐት እያመሰገነ ከልቡ ተቀብሎታል። ከወያኔ ሌላ ለትግራይ ልማት እና እድገት የሚያስብ ስርዓት አይመጣም የሚል ድመዳሜም እንደሚያስቀምጥ ምንም አያከራክርም። ደግሞ ከወያኔ በላይ ማን ለትግራይ ቅድሚያ ይሰጣል? ስልጣን ላይ ያሉት የትግራይ ተወላጆች ናቸው፤በየውጭ አገሩ እየተላኩ ወታደራዊ እና ሲቪላዊ ስልጠና የሚለኩት ትግሬዎች ናቸው (ከቁጥር አንጻር ስትመለከቱ አብዛኛዎቹ ከትግራይ ናቸው)፤ አምባሲው፤ ስለላው፤ወታደሩ፤ ስልጣኑ፤ንግዱ…..በማን እጅ ነው ያለው? በትግሬዎች!
ወያኔዎች ትግሬዎች አይደሉም? ናቸው። ስንት ናቸው? በጣም ፤ እጅግ በጣም በሚሊዮኖች የሞቆጠሩ። አነኚህ የትግራይ ሕዝብ አካል አይደሉም? ናቸው። ጥቂት እየተባለ የሚነገረው ‘አሃዝ” የፖለቲካ አላዋቂነት ወይንም ሆን ተብሎ የተሸፈነ አባባል አንጂ “ተጠቃሚዎቹ” “ጥቂቶች” በሚያስብል ግምት ውስጥ አይደሉም። አንድ ሕዝብ በታሪክ ምዕራፎች ብንመለክት፤ በየትም ዓለም “ሁሉም” ሕዝብ “ተጠቃሚ” ማድረግ አይቻልም።ግን በዓይን የሚታይ የሚዳሰስ ጠቀሜታ እና ተጠቃሚ እስካለ ድረስ “ግምገማችን” መሰረት አድርገን “ተጠቃሚ ነው” ብለን መመጐት አንችላለን።
ለም መሬቶች እየመረጠ ከጎንደር እና ከወሎ ነጥቆ ለትግሬው እንካ ሲለው “እሺ” ብሎ እየተጠቀመበት ያለው ሕዝብ ማን ነው? አንዲህ ያለ ሥርዓት በጠምንጃ ጉልበት ከሌሎቹ ወንድሞቹ ሰፊ መሬት ነጥቆ ለትግራይ የሚሰጥ ሥርዓት ከቶ ለወደፊቱ ሊመጣ ይችላል? ጐሰኛ ስራው ምንድ ነው? ከመነሻው ማንንሰ ለመጥቀም እና ነፃ ለማውጣት ነው የተነሳው? አንደዚህ ዓይነቱ ጥቅማጥቅም በጉልበትም ሆነ በሕጋዊ መንገድ እየተጠቀመ ቅድሚያ ለራሱ ጎሳ ለማጐናጸፍ ነው። ይህንን ሰፊ መሬት እና የታመጸ አማራ ኗሪ ሕዝብ መብት ሳይጠብቅ ወደ “እራሱ ጐሳ” ወደ ትግራይ እንዲቀላቀል የተደረገው ማንን ለመጥቀም ነው? ትግራይን ለመንጠቅ ካልሆነ ማንንነ ነው? ሑሞራ ላይ ያለው እርሻ ማን ነው እየተጠቀመበት ያለው? ትግሬው ወይስ አማራው (የጎንደር ሕዝብ)?
እየሆነ ያለውም ይሄው ነው። ትግሬው “የሚዳሰስ፤የሚጨበጥ፤የሚታይ” ጠቀሜታ እና ዕድገት በአከባቢውም ሆነ በግል ህይወቱ ከሌላው በተሻለ አግኝቷል። ለዚህም ነው “እንደ ወያኔ” ለኤርትራኖች ነፃነት እና “ለትግራይ ዕድገት” የሚቆረቆር ሥርዓት ከቶ ለወደፊቱ አይገኝም’ የሚል ሙጉት የምሞግተው። ሰለሆነም፤ የትግራይ ሕዝብ ይከፋም ፤ይደግም፤ እጁን አጣምሮ ዝመታ የመረጠበት ምክንያት ከፍርሃቱ ሌላ ያልተመረመረ ስዕል ከፊት ለፊቱ ያገደው ያለ አንደሆነ አብርሃ አሁንም ከሰጠን ትንተኛ ሌላ ወደ ውስጥ መቆፈር ይገባዋል እላለሁ። ሕዝቡን ወደ ጎን ትትን ወደ ምሁራኑ ክፍል ብናተኩር፤ ያ ያልተመረመረው ስዕል አሁንም በትግራይ ምሁራን ዝምታ ታጭቆ ያለው ብሔረተኛነት ነው የሚል አስተያየት አለኝ። የትግራይን ሕዝብ ጸረ ወያኔ ፊት ለፊት እንዳይነሳ ያገደው ጠባብ ብሄረተኛነት ነው።
ኤርትራኖች አሁን ያሉበት እና የትግራይ ምሁራን ያሉበት ስታወዳድሩ ፤ ኤርትራኖቹ አንዲያ በዘምባባና በአበባ የተቀበሉት፤ደማቸውና ገንዘባቸው ያፈሰሱበት “የሻዕቢያ” ድርጅት ገበና በብዙ መጽሐፍት እያሳተሙ በቃለ መጠይቅ በየራዲዮኑ እና በየፓልቶኩ እያገላጡ ሕዝቡ አንዲነሳበት እያደረጉት ይገኛሉ። የትግሬ ምሁራን እና ታጋዮች ግን ፤ ከቆራጦቹ ከነ አስገደ ገብረስላሴ ፤ገብረመድህን አርአያ፤ተስፋይ አጽብሃ/ቸንቶ፤ እና ጓደኞቹ እንዲሁም ጥቂቶች……በስተቀር የትግራይ ታጋዮች እና ምሁራን በብሔረተኛነት ገመድ ስለተበተቡ በጣም በሚያሰዝን ሁኔታ “ዝምታን” መርጠዋል። እነ አብርሃ ደስታ መመርመር ያለባቸው በተቃዋሚው ስትራቴጂ ላይ ምክንያት አድርጎ የተተነተነ የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ከማተኮር ይልቅ በጠቀስኩት ላይ ትኩረታቸው ቢያደርጉ ለጠቃሚ ውይይት በር ይከፍታል።
በመጨረሻ ልለው የምፈልገው ነገር፤ የተማረው የትግራይ ምሁር፤ በራሱ ጠባብ ብሔረተኛነት ስሜት ምክንያት ተተብትቦ የወያኔ ተበባሪ ሆኖ የሕዝቡ መከራ “ጀሮ ዳባ’ ብሎ ከጨቋኙ የወያኔ ቡድን ጋር ከወገነ፤ ሕዝቡ እየደረሰበት ካለው መከራ ራሱን ነጻ ለማውጣት እያገደው ያለው“ፍርሃት” የሚባል አንቅፋት አንደምክንያት ከተወሰደ ፤ የትግራይ ሕዝብ ከራሱ በላይ የተሻለ ነፃ አውጪ ከየት አንዲመጣ ይጠብቃል? ደርግን ያክል የተደራጀ ታላቅ ሠራዊት መክቼ አሸንፋለሁ ብሎ በተግባርም ተቃውሞው አሳይቶ መምታት ከቻለ፤በወያኔ ላይ ሲደርስ ደርግን አንደመታው ወያኔን ላለመምታት ጉልበቱን ተብትቦ ያሰረው “ክር” ምንድነው? ፍርሃት ብቻውን እንደምክንያት በቂ ሊሆን አይችልም። የ21 ዓመት ተባባሪነትና ዝምታ በመካከላቸው የተዘረጋው ‘ገመድ’/ ‘እትብት’ መመርመር ይኖርበታል።
ብሐረተኞች የዘረጉት ፖለቲካ በቀላሉ የሚተነተን ሳይሆን በመስኩ ላይ ጥናት ያደረጉ ምሁራን ለዚህ ተገቢውን መልስ አንደሚኖራቸው አምናለሁ።በትንተናው ላይም አንዲሳተፉበት እጋብዛለሁ። ይህ ጽሑፍ የአብርሃ ደስታ ጽሑፍ በተለጠፈው በኢትዮ ሚዲያ እንዲለጠፍ ተልኳል (ደምቡም መሆን ያለበት ያ ነበር) ሆኖም አዘጋጅ ፖለቲካን ወደ ግል ስሜት እየለወጠ እልህ ውስጥ ገብቶ የምናስተላልፋቸው የሕዝብ ጉዳዮች በድረገጹ ተለጥፈው አንዳይነበቡ ማገዱን ብዙዎቹ የተስማሙበት ችግር መሆኑን የታወቀ ቢሆንም፤ ይህ ጽሁፍ ልኬዋለሁ። ቢያወጣው መልካም፤ባያወጣውም ፤ለሬከርድ/ለትዝብት አንተወዋለን። ሆኖም ጽሑፉ ድንገት ታፍኖ እንዳይቀር ወደ ሌሎቹ ድረገጾች ለሕትምት ተልኳል) አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)