Freedom for Ethiopians
Monday, April 15, 2013
በጣም አጭር ወሬ፤ “ፍትህ ናፈቀን!”
ዛሬም ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የፍትህ ናፍቆት እንዳንገላታቸው ጮክ ብለው ለመንግስት ተናግረዋል፡፡ መንግስት መስማት እና አለመስማቱን ለማጣራት ያደረኩት ሙከራ የለም፡፡
ምክንያቱም መንግስታችን የጆሮ ህክምና ላለማድረግ ቆርጦ ስለተነሳ፤ ከዚህም በበለጠ በርከት ብለን አብረን እና ተባብረን ካልጮህንለት በስተቀር እንደማይሰማን ስለጠረጠርኩ መሆኑ ይታወቅ፡፡
በዛሬው የሙስሊም ኢትዮጵያውን ተቃውሞ በይበልጥ ጎልቶ የወጣው “ፍትህ ናፈቀን” የሚል ቃል ሲሆን ነገሩን በጭምጭምታ የሰሙ የመንግስት ቤተዘመዶች “ፍትህ ፍትህ… ፍትህ ምን ነበር…?” ብለው ሲጠይቁ ተሰምቷል፡፡
No comments:
Post a Comment
Newer Post
Older Post
Home
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment