በመጪው ህዳር 15 ለሚካሄደው ታላቁ ሩጫ ሁሉም ኢትዮዽያ ጥቁር ጨርቅ በማሰር ብሶቱን ባደባባይ የሚያሰማበትን ቀን 2013 Great Ethiopian Run
ሳዑዲ
አረቢያ መንግስት በወገኖቻችን ላይ ያደረሰውን እልቂት ወያኔ በየቀኑ ምን እየተሰራ እንደሆነ ለማያውቀው
ለኢትዮዽያ ህዝብ ደብቆ እግር ኯስ ተጫዋቾቻችን እንኯን ጥቁር ሻሽ አድርገው መግባትና በሳውዲ የሚደርገውን ሰቆቃ
ማሳየት አለባቸው ተብሎ እንደዛ ሲለፈፍ ሲነገር ቆይቶ በወያኔ መሰሪ ሰራ መሰረት ይህንን ሳይደረግ ቀርቷል። ያ
የፈረደበት የኢትዮዽያም ህዝብ በዛው በውሸታሙ የወያኔ ቲቪ በጣም ብዙ በየቀኑ ከሳውዲዓረቢያ ወድ ሀገራቸው
በመግባት ላይ እንደሆኑ በየቀኑ እየለፈፈ ይገኛል። ውሽታሙ ቴድሮስ አድህኖም ዛሬ በትዊተራቸው 7384
እስከአሁን ድረስ ገብተዋል ተቀብለናል እያሉ ነው። የኢትዮዽያም ህዝብ ልጆቹ ከነገ ዛሬ ይመጣሉ ብሎ በመጠባበቅ
ላይ ነው።
በአሁኑ ሠዓት አብዛኛው ኢትዮዽያዊ ከዓለም ጫፍ እስከ ዓለም ጫፍ በሳዑዲ በመከራና ስቃይ ላይ ላሉት ለብዙ ሺህ
ወገኖቹ በአንድነት ቆሞ እየተንጫጫ ባለበት ወቅት ሳውዲ ዓረቢያ ውስጥ በግምት 45 000 ኢትዮዽያዊ እንደሚኖር
ተገልጿል።እስካሁን ድረስ በውሽታሙ ቲቪ የገቡት ገቡ የተባሉት ገብተዋል ብለን እንኯን ብናስብ በየቀኑ ቢያንስ 1 ወይም 2 ኢትዮዽያዊ ህይወቱን ያጣል ይባስ ብለው በሳውዲ የሚገኘውን ቆንስላ ጽህፈት ቤት ላልተወሰነ ግዜ ዘግተው በድብቅ ፍራንክ ላላቸው ኢትዮዽያኖቹ ብቻ ወደሀገራቸው ለመግባት እንኯን ብር እየከፈሉ እንደሆነ ከስፍራው በየቀኑ በሚደርሰን መረጃ መሰረት ለማወቅ ችለናል ፍራንክ የሌለውን እዛው እንዲበሰብስ ወይም ሀገር እንደሌለው 2ኛ ሞት እንዲሞት እያደርጉም እንደሆነ ማለት ነው ።
ሰለዚህ ይህንን ከኢትዮዽያ ህዝብ የተደበቀ መሪር ሃዘንና ምሬት በአንድ ላይ በመሆን ለኢትዮዽያ ህዝብ የምናሳወቀበት ቀን እንዲሆን በአክብሮት እንጠይቃለን ።
በሳውዲ የሚገኙ የኢትዮዽያ ህዝብ በደልና ጥቃት በአዲስ አበባ በሚገኘው በሳውዲ ኤምባሲ እሁድ ህዳር 08 ቀን ሊያደርገው የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይደረግ እንደሁም በጣም ብዙ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የነበሩትን ስዎች በመደብደብ እና በማሰር በሃገራቸው እንኯን መናገር እንዳይችሉ አድርገው እንደነበር ይታወሳል። በመሆኑም በመጪው ህዳር 15 ለሚካሄደው ታላቁ ሩጫ ላይ ከ35 000 ህዝብ በላይ ስለሚኖር ሁሉም ኢትዮዽያዊ ይህን መልዕክት ላልሰማው በማስተላለፍ ሁሉም ጥቁር ጨርቅ በማሰር ብሶቱን ባደባባይ የሚያሰማበትን ቀን በጉጉት እንጠብቃለን ።
yared elias

No comments:
Post a Comment