አንዳንድ
ወዳጆቻችን ልክ በህይወት ያሉ እስኪ “መስል ድረሰ መለስ ለልደትህ እንኳን አደረሰህ!… መልካም የልደት በዓል
ይሁንልህ!” ሲሏቸው አይቼ ሳቅቼ ሳቅቼ ሞተውት! (ደግሞ እኮ …አንተ… ነው የሚሏቸው …ወይ ጫማ መለካካት!)እንደ እውነቱ ስለ መለስ የልደት ቀን መታሰቢያ ለማድረግ ከኔ የሚቀድም አካል መኖር አልነበረበትም፡፡ ያ ሁሉ ወዳጅነታችን ከግባ መሬቱ ጋር አብሮ የተቀበረ አስመሰልኩት እኮ!
በነ እስክንድር ነጋ … የእስር ፍርድ ምክንያት በማድረግ ስለ ጉዳዩ አስተያየት እንድሰጥ የተለያዩ የፌስቡክ
ጓደኞቼ ሲወተውቱኝ ከርመዋል (የቅርብ ጓደኞቼ ግን ዝምታን መምረጥ እንዳለብኝ መክረውኛል)። አስተያየቴን እንድገልፅ
የገፋፉኝ ጓዶች በቁጥር ብዙ ቢሆኑም ምክንያታቸው ወይ ዓላማቸው ግን የተለያየ ነው።