ሰበር ዜና በግንቦት ሰባት ዋና ፀሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እና የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል አመራሮች ላይ ሊደረግ የነበረው ግድያ ከሸፈ
የግንቦት 7 መሪዎችን ለመግደል የተጠነሰሰው ሴራ ከሸፈ
በኢትዮጵያ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ዋና ሃለፊ በአቶ ጌታቸው አሰፋ እና በጠቅላይ ሚኒስትሩ የብራዊ ደህንነት አማካሪ በአቶ ጸጋየ በርሄ ቁጥጥር የተመራና በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌና በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል መሪዎች ላይ የተቀነባበረው የግድያ ሙከራ ከሸፈ።
ከግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው ለግድያ የተላከው ሙሉቀን መስፍን የተባለው ግለሰብ በትናንትናው እለት በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን፣ በእየደረጃው ከሚገኙ የደህንነት ሀላፊዎች ጋር በስልክ ሲያደርግ የነበረው የስልክ ለውውጥ በህዝባዊ ሀይሉ የመረጃ ክፍል ሲቀዳ ቆይቷል።
ወያኔ-ኦ-ሚሊኒየም በሚል የተመራው የግድያ ዘመቻ -በነገው እለት ጥቅምት 30/2006 ዓም ሊካሄድ ታቅዶ እንደነበር የድምጽ መረጃው ያመለክታል።
የግንቦት 7 ህዝባዊ ሀይል ሰራዊት የምረቃ በአል በነገው እለት የሚካሄድ መሆኑን መነሻ በማድረግ በእለቱ በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል መሪዎችንና የኤርትራ ባለስልጣናትን ለመግደል የታቀደው ዘመቻ ከመነሻው ክትትል ሲደረግበት ቆይቶ፣ በፍጻሜው ዋዜማ ላይ ሲድርስ ሙሉቀን መስፍን የተባለውን ለግድያ የተላከውን ግለሰብ ህዝባዊ ሀይሉ በቁጥጥር ስር በማድረግ ወያኔ-ኦ-ሚሊኒየም የተባለው ኦፕሬሽን ከሽፏል።

http://www.blogger.com/blogger.g?blogID=3499323826983623926#editor/target=post;postID=7301910215740791013





















ምንሊክ ሳልሳዊ

እውነቱን ልንገራችሁ አይደል—-ያሳለፍነው ሳምንት የአግራሞት ነው፡፡ የአሜሪካንን የስልክ ጠለፋና የስለላ ጦስ
ሰማችሁልኝ አይደል? እንዴ — አንድዬን ብቻ እኮ ነው ያልሰለለችው! (የሚጠለፍ ስልክ የለማ!) እኔማ ምን
እንደመሰለኝ ታውቃላችሁ? በቃ — በልጅነቴ እሰማው የነበረው 8ኛው ሺ የገባ ነው የመሰለኝ፡፡ እስቲ
አስቡት—የጀርመኗ ቻንስለር አንጌላ መርከል፤ለአስር ዓመት ስልካቸው እየተጠለፈ ተሰልለዋል፡፡ እሺ— መሪዎቹስ እርስ
በእርስ ይተዋወቁ ይሆናል፡፡ 30 ሚሊዮን የፈረንሳይ ዜጎች፣ 60 ሚሊዮን የስፔይን ዜጎች ስልካቸው ተጠልፎ መክረሙ
ምን ይባላል? ግን አሜሪካ ከስልክ ጠለፋ ውጭ ሥራ የላትም ማለት ነው ? አንድ ነገር ግን ፈርቻለሁ፡፡ ይሄ
የፀረ-ሽብርተኝነት ዘመቻ ዓለምን አካክዶ መተማመን ታሪክ ሆኖ እንዳይቀር! አሁን አንጌላ መርከል ዳግም ለአሜሪካ
ልባቸውን የሚሰጡ ይመስላችኋል? (10 ዓመት እኮ ነው የተሰለሉት!) ወይ አሜሪካ—ሽብርተኝነትን እዋጋለሁ ብላ
ዓለሙን ሁሉ በሽብር ሞላችው! (እሾህን በእሾህ አሉ !)
Posted in 