ዓባይና የአሜሪካ ጨዋታ

መስፍን ወልደ ማርያም
ሰኔ 2005
በአሥራ ዘጠነኛው ምዕተ-ዓመት አስተሳሰብ ከዚህ ቀጥሎ የተጠቀሰው ዓላማ ለአውሮፓ ቄሣራውያን ዋና ግባቸው ሆኖ እስከሃያኛው ምዕተ-ዓመት ዘልቆአል፤ አሀን ፈጽሞ በተለየ ዘመን አሜሪካ ይህንን አስተሳሰብ ይዞ የተነሣ ይመስላል።
ኢትዮጵያን የተቆጣጠረ ዓባይን ይቆጣጠራል፤ ዓባይን የተቆጣጠረ ግብጽን ይቆጣጠራል፤ ግብጽን የተቆጣጠረ ኃይል ቀይ ባሕርን ከመግቢያና መውጫው ጋር ይቆጣጠራል፤ ቀይ ባሕርን ከመግቢያና መውጫው ጋር የተቆጣጠረ ኃይል ዓለምን ይቆጣጠራል።
አሜሪካ በግብጽ ላይ የተከለው ጥፍሩ ሲነቃነቅ መነቀሉ አለመቅረቱን ስላወቀው ሌላ የሚተክልበት አገር ይፈልጋል፤ በአካባቢው የግብጽን ነፍስ የሚነካ ከኢትዮጵያ የተሻለ አገር የለም፤ ለአሜሪካ ዓለም-አቀፍ ዓላማ ኢትዮጵያ ስትመረጥ የአሁኑ የመጀመሪያው አይደለም፤ በመሀከለኛው ምሥራቅ የአረቦችን የተባበረ ኃይል ለመቋቋም የተመረጡ ሦስት አረብ ያልሆኑ አገሮች — ቱርክ፣ ኢትዮጵያና ፋርስ (ኢራን) — ነበሩ፤ በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የአሜሪካ ዓለም-አቀፍ ኃይል መሰማት በጀመረበት ጊዜ ኢትዮጵያን ከከበቡአት የአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች ጋር የነበርዋትን የቆዩ ውዝግቦች ለመቋቋም የአሜሪካ ድጋፍ በጣም አስፈላጊ ነበር፤ አሜሪካን ከአውሮፓ አገሮች ጋር እየመዘኑና እያመዛዘኑ የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስከበር የተደረገው ዲፕሎማሲ (ዓለም-አቀፍ የሰላም ትግል) የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን መንግሥት በእውነት ከሚያኮሩት ተግባሮች አንዱ ነው፤ ይህንን ትግል አምባሳደር ዘውዴ ረታ ምስጋና ይድረሰውና የኤርትራ ጉዳይ በሚለው መጽሐፉ ግሩም አድርጎ አሳይቶናል።
ምናልባት ገና ያልተጠና ጉዳይ በዘመኑ ኢትዮጵያ የነበራት ታሪካዊ ክብር ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ታሪክና ዝና ጋር ተዳምሮ በአፍሪካ ተደማጭነት ነበራት፤ ይህንን ኢትዮጵያ በአፍሪካ አገሮች ላይ የነበራትን ጫና (የዛሬውን አያርገውና) በመጠቀም አሜሪካ አፍሪካን በሙሉ ለዓላማዋ ለማሰለፍ ኢትዮጵያን መሣሪያዋ ለማድረግ ትሞክር ነበር።
እየቆየ የኢትዮጵያ መንግሥት የነጻነት መንፈስን በማሳየት ለአሽከርነት አልመች በማለቱና ለአሜሪካም አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች (የእውቀት ጥበቦች) በመፈጠራቸው ኢትዮጵያ ለአሜሪካ ዓለም-አቀፍ ዓላማ አስፈላጊነትዋ በመቀነሱ አሜሪካ ኢትዮጵያን ችላ ማለት ጀመረ፤ የ1966 ግርግር ከዚህ ጋር ተያይዞ የመጣ መሆኑን ጠለቅ ብሎ ማጥናት ያስፈልጋል፤ በዚህ መሀልም የሶቭየት ኅብረት ዓለም-አቀፋዊ ጉልበት እየተሰማ በመሄዱ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የነበረውን ዓላማ ቀስ በቀስ እየለወጠ ሄደ፤ ከዚህም ጋር የሶቭየት ኅብረት ተጽእኖ እያደገ ሄደ፤ የአሜሪካ አያያዝ እየላላ ሲሄድ የሶቭየት ኅብረት አያያዝ እየጠበቀ ሄደ፤ 1966 የአሜሪካ መውጫና የሶቭየት መግቢያ ሆነ ለማለት ይቻል ይሆናል፤ ከዚሁ ጋር አብሮ የሚታየው በኢትዮጵያ የባህላዊው ሥርዓት መሰነጣጠቅና የቆየው ትውልድ መዳከም ነው፤ የአሜሪካ መዳከም ሶቭየት ኅብረትን ሲያጠነክር፣ የአሮጌው ትውልድ መዳከም አዲሱን ትውልድ አጠነከረ፤ ይህ ማለት አሮጌው ትውልድ ከአሜሪካ ጋር የተያያዘውን ያህል አዲሱ ትውልድ ከሶቭየት ኅብረት ጋር ተያያዘ፤ የኢትዮጵያ የውስጥ ሁኔታ ብቻውን ለውጥ እንዳላመጣና ዓለም-አቀፍ ሁኔታዎችና የልዕለ ኃያላኑ ተጽእኖም ምን ያህል እንደነበረ አመላካች ነው።
ኢሳት ዜና:- የአፍሪካ ጉዳዮች ሃላፊ ዶናልድ ያማማቶ፣ በአፍሪካ የዩሴ አይ ዲ ዳይሬክተር ኤሪል ጋስት፣ በአፍሪካ
ጉዳዮች ተመራማሪ ዶ/ር ፒተር ፓሀም፣ የግንቦት7 ሊቀመንበር ዶ.ር ብርሀኑ ነጋ ፣ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ
ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶና የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአሜሪካ ተወካይ ሚስተር አዶቲ አኪዌ እና ሌሎችም ታዋቂ
ምሁራን ፖለቲከኞች የተሳተፉበት ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ አምባሳደር ያማማቶ እና ዶ/ር ጋስት ኢትዮጵያ በመስቀለኛ
መንገድ ላይ እንድምትገኝ ገልጸዋል።
መንግስቱ ንዋይ : መጋቢት 19 ፣ 1953 ዓ.ም የሞት ፍርድ ከተወሰነባቸው በኋላ የተናገሩት ንግግር




በቆንጂት ተሾመ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን አሁንም ደጋፊዎቹን በደስታ ያሳበደ ውጤትን በአዲስ አበባ ስታዲየም
አስመዝግቧል። እሁድ እለት የደቡብ አፍሪካ አቻውን 2ለ1 በማሸነፍ ለብራዚሉ የአለም ዋንጫ የመጨረሻ ምዕራፍ ማለፉ
ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ከመጠን በላይ አስፈንጥዟል። ለብዙዎችም ውጤቱ ለማመን የሚከብድ ስለነበር ደስታውና ፈንጠዝያው
ልክ አልነበረውም። ዋልያዎቹን ለመደገፍ በአዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያ ተሰልፎ ያነጋው ተመልካች አንገቱን ደፍቶ
አለመመለሱ ራሱ እጅግ የሚያስደስት ነው።


በአዳማ ከተማ የጫት መሸጪያ ሱቆች በከፍተኛ ደረጃ እተስፋፉና የቃሚውም ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው
ተባለ ፡፡
After Betty survivinghttp://www.blogger.com/blogger.g?blogID=3499323826983623926#editor/target=post;postID=7407261887331811910 today’s eviction, it means she will still have
more time in the house and time to spend with her Mr right as per what
has so far happened in the house.Possibly the relationship between Bolt
and Betty was at the verge of collapsing if at all Betty was evicted out
of the house this evening.The fact that she was never evicted implies
that Africa voted the right way and that means we should still wait for
tight romance from these two housemates.

በባህርዳር ከተማ በብሄራዊ ቡድናችን ድል ደስታቸውን ለመግለጽ አደባባይ ከወጡት መካከል በአንድ መኪና ላይ
ደስታቸውን ሆነው ሲገልጹ ከነበሩ ወገኖቻችን መካከል 2ቱ ሕይወታቸው ሊያልፍ መቻሉ ተዘገበ። በሌላ በኩልም –
ኢትዮጵያ ትናንት ደቡብ አፍሪካን ማሸነፉዋን ተከትሎ ምሽት ላይ በነቂስ ወደ አደባባይ ወጥተው ድጋፍ ካደረጉት
የባህር ዳር ነዋሪዎች መካከል በዛ ያለ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች “የኮከብ ዓርማ የሌለውን ሰንደቅ ዓላማ በመልበሳቸው፣
እንዲሁም ‹‹ሰማያዊ ፤ሰማያዊ ደገመው ዋልያዊ››፣ “ኢትዮጵያዊው ለሰንደቅ አላማው ፤ለሰማያዊው ” እያሉ
ደስታቸውን በመግለጻቸው፣ ከፌደራል ፖሊሶች ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተው ማምሸታቸውን የኢሳት ቲቪ በዛሬ ምሽት የዜና
እወጃው ዘገቧል።





የሕወሐት አባልና የአገር ውስጥ ደህንነት ዋና ሃላፊ አቶ ወልደስላሴ ከስልጣናቸው እንዲነሱ መደረጉን የቅርብ ምንጮች
አስታወቁ። ወ/ስላሴ ከስልጣን እንዲነሱ ያደረጉት የደህንነት ዋና ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ መሆናቸውን ምንጮቹ
ጠቁመዋል። የሁለቱ ሹማምንት ፀብ ውስጥ ለውስጥ ሲብላላ ቆይቶ መጨረሻ መፈንዳቱ ታውቋል። በመቀሌ በተካሄደው
የፓርቲው ጉባኤ አቶ ጌታቸው የፓርቲው ማ/ኮሚቴ አባል ሆነው እንዳይመረጡ ሰፊ ቅስቀሳ ሲካሂድ የቆየው ወ/ስላሴ
በመጨረሻም የአባላት ምርጫ ሲካሄድ ባቀረበው ተቃውሞ ላይ « ..ጌታቸው የተሰጠውን የፓርቲና መንግስታዊ ሃላፊነት
በአግባቡ እየተወጣ አይደለም፤ የአልሙዲ ተላላኪና አሽከር ሆኗል…የአላሙዲ አገልጋይ ሆኖዋል…ስለዚህም በማ/ኮሚቴ
አባልነት መካተት የለበትም..» ሲል መናገሩን ያወሱት ምንጮቹ፣ የወ/ስላሴ ተቃውሞ ተቀባይነት ባለማግኘቱ አቶ
ጌታቸው በማ/ኮሚቴ አባልነታቸው እንዲቀጥሉ መደረጉን አያይዘው ገልፀዋል። ..