በሩሲያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አጠገብ የተገኘው ጥቅል ቦምብ መሆኑ ተረጋገጠ

በሩሲያ ሞስኮ ከተማ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አቅራቢያ በፖሊስና አነፍናፊ ውሻ አማካይነት የተገኘው ጥቅል፣ ቤት ሠራሽ ቦምብ መሆኑን የአገሪቱ የደኅንነት አገልግሎት ማረጋገጡን ዘገባዎች አመለከቱ፡፡
ዘ ቮይስ ኦፍ ራሺያ (የሩሲያ ድምፅ) የተሰኘው የአገሪቱ ሬዲዮ በድረ ገጹ እንዳለው፣ ባለፈው ሳምንት ዓርብ በፖሊስና በአጋዥ
አነፍናፊ ውሻ አማካይነት በኢትዮጵያ ኤምባሲ አቅራቢያ ተቀምጦ የተገኘው ጥቅል ዕቃ ወደ ላብራቶሪ ተወስዷል፡፡
በሞስኮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አካባቢ ከሚገኝ የቆሻሻ መጣያ አቅራቢያ ወድቆ ከተገኘውና በኋላም በቤት ውስጥ እንደተሠራ ከተረጋገጠው ቦምብ ጋር አብሮ የሞባይል ስልክ ተያይዞ መገኘቱን የአገሪቱ የደኅንነት አገልግሎትን የጠቀሰው ዘገባ ያመለክታል፡፡
በሩሲያ የአገር ውስጥ ደኅንነት አገልግሎት ላብራቶሪ የተመረመረው ጥቅል ዕቃ፣ በሦስት የፕላስቲክ ብልቃጦች ውስጥ በግምት 400 ግራም የሚሆን ፓይሮ ፓውደርና ሮው ቦልትስ የተሰኘ ተቀጣጣይና የፈንጂ ዱቄት ተሞልቶ ታሽጐ ነበር፡፡ የታመቀ ተቀጣጣይ ዱቄት ከተሞሉ ብልቃጦች ጋር ተያይዞ የተቀመጠው የሞባይል ስልክም ከርቀት ፍንዳታውን ለመቆጣጠር ያለመ መሆኑን ምርመራው አረጋግጧል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ ተጨማሪ ማብራሪያ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለማግኘት ያረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡
ethiopian reporter


















Written by ኤልያስ, AddisAdmassNews.com






ሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ግፍና በደል በሰላማዊ ሰልፍ ለመቃወም ፓርቲያችን በወሰነው መሰረት
ለሚመለከተው ክፍል አሳውቀን ነበር፡፡መቸም ህዝባችን በጭቆና ውስጥ ስለኖረ በመብቱና በግዴታው መሀል ያለውን
ድንበር በውል ካለመረዳቱ የተነሳ ሰልፉ እንዲደረግ ስለመፈቀዱ በተደጋጋሚ ስንጠየቅ ነበር፡፡ህጉ የሚለው ግን
ማስፈቀድ ሳይሆን ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡በተቃራኒው መንግስት በተለያዩ ጉዳዮች ሳቢያ በእለቱ ለሰላማዊ ሰልፉ የደህንነት
ከለላ መስጠት የማይችልበት ሁኔታ ከገጠመው ሰልፉን ለጠራው አካል ችግሩን ገልጾ ቀኑ እንዲተላለፍለት
ይጠይቃል፡፡በመሆኑም ይህን መሰል ጥያቄ ከሚመለከተው መስሪያ ቤት ለፓርቲያችን ባለመቅረቡ በሙሉ ልብ ቅድመ-ዝግጅት
ማድረጉን ተያያዝን፡፡
ሁሌም ቢሆን መንግስት ሰበብ ፈልጎ ሊወነጅለንና ከመስመር ሊያስወጣን እንደሚፈልግ በሚገባ እናውቃለንና በጥቃቅን
ጉዳዮች ላይ ሳይቀር ጥንቃቄ እናደርጋለን፡፡ለሚመለከተው መስሪያ ቤት ባሳወቅን በአስራ ሁለት ሰአታት ውስጥ ምላሽ
ስላልመጣ ሙሉ በሙሉ ህጋዊነታችንን አረጋግጠናል ማለት ነው፣እነሱ ደግሞ ጠብ-መንጃ በእጃቸው አለና የፈለጉትን ሁሉ
ማድረግ ይችላል፡፡
ነገሩ የተፈፀመው የተማራቂ ተማሪዎች “ጌት
ተጌዘር” አዘጋጅተው ያንን ፖሮግራም ጨርሰው ከምሽቱ ሁለት ሰአት ተኩል አካባቢ ወይም ከዛ ረፈድ ብሎ በቁጥር ወደ
(ዘ-ሐበሻ) ከሳዑዲ አረቢያ 13 ግዛቶች ውስጥ በሰው ብዛት 7ኛ እንደሆነች በሚነገርላት አል ቃሲም ከተማ
ስደተኞችን ማፈስ ተጀመረ። ከትናንት ጀምሮ ፖሊስ በየቤቱ እየሰበረ በመግባት ስደተኞችን እያፈሰ መሆኑን ከአካባቢው
የዓይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ በላኩት መረጃ ዘገበዋል።
