Wednesday, December 11, 2013

‎በዋልድባ ላይ ለሚሰራው የሥኳር ፕሮጀክት ነዋሪዎች መነሳት ጀመሩ


#‎በዋልድባ ላይ ለሚሰራው የሥኳር ፕሮጀክት ነዋሪዎች መነሳት ጀመሩ ‪#‎የቆራሪት_ከተማ በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል በዋልድባ ገዳም ላይ ለሚገነባው የስኳር ልማት ፕሮጀክት በመጀመሪያ ዙር 1800 አባወራዎች ከቦታቸው መነሳታቸው ታወቀ። ለተነሱ አር...ሶ አደሮቹ 127.5 ሚሊዮን ብር የካሳ ክፍያ ተሰጥቷል። ለእነዚህ ተነሺዎች ከወራት በፊት የገጠር ከተማ መልክ በመያዝ በተገነባችው የቆራሪት ከተማ ላይ የማስፈር ስራ ተከናውኗል። ለዚች ከተማ ምስረታ ምክንያት ደግሞ በዋልድባ ገዳም ላይ የሚሰራው የስኳር ልማት ፕሮጀክት መሆኑ ታውቋል። በአሁኑ ሰዓት ከቦታው የተነሱት 1800 ነዋሪዎች ከወልቃይት ወረዳ ፤ ከቃሌማ እና ፅምሪ ቀበሌ ይኖሩ የነበሩ አርሶ አደሮች ናቸው። መንግሥት እንደሚለው ለእነዚህ የልማት ተነሺዎች ለተነሱበት ቦታ በምትኩ የእርሻ ፤ የመኖሪያ ቤት ፤ ሙሉ የቤት እና የሰብል ካሳ ክፍያ ፈጽሜያለሁ ብሏል። ለአርሶ አደሮቹ ነዋሪዎች መንግሥት 127.5 ሚሊየን ብር ካሳ መስጠቱ ታውቋል ፤ በሁለተኛ ዙር የሰፈራ ፕሮግራሙ ላይ 4ሺህ ሰዎች ከቦታው ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሰፈራው የሚቀጥል ሲሆን ለሚነሱት ከ13 ለማያንሱ አብያተ ክርስቲያናት ምትክ አዳዲስ ቤተክርስቲያን በቆራሪት ከተማ መሰራት መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሏል። የዚህ ፕሮጀክት እሳቤ መነሻው 1991 ዓ.ም ቢሆንም አሁን ላይ ግን ወደ እውነታው እየተቃረበ ያለ ይመስላል ፤ ከዓመት በፊት ብዙ ሲያነጋግር የነበረው ይህ የሥኳር ፕሮጀክት አሁን ላይ የቁርጥ ቀኑ የቀረበ መስሏል ፤ መንግሥት ገዳሙን አልነካሁም በማለት አይኔን ግንባር ያድርገው እያለ ቢምልም መሀላው እውነታው ሊደብቀው አልቻለም። ገዳማውያኑም የሚደርስባቸው መከራ ከቀን ቀን እየጨመረ መምጣቱ ከቦታው የሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ ፤ ጥቂት የማይባሉት መከራውን በመቋቋም የሚመጣውን ነገር ሁሉ በጸጋ ለመቀበል በአቋማቸው ፀንተው አሁንም ድረስ ያሉ ሲሆን ፤ ጥቂት መነኮሳት ግን የመንግሥትን የአምስት አመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ከግብ ለማድረስ ቀን ከሌት ከመንግሥት ሹማምንት ጋር ዳገት ሲወጡ ቁልቁለት ሲወርዱ ተስተውሏል። የ2005 ዓ.ም በጀት ዓመት የሥኳር ኮርፖሬሽን ዓመታዊ አፈጻጸም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀረበበት ጊዜ መንግሥት በበጀት እጥረት የሰፈራ ፕሮግራሙን በአግባቡ ለማስኬድ እንቅፋት እንደሆነበት ሚኒስትሩ ለምክር ቤቱ ማቅረባቸው ይታወሳል ፤ ከዚህ በተጨማሪም ቦታው ድረስ በመሄድ ስራውን የሚያከናውን የተማረ የሰው ኃይል እጥረት እና ቦታው ላይ ረዥም ጊዜ አለመቆየት መቻልን ለፕሮጀክቱ መጓተት እንደ ሁለተኛ ምክንያት አቅርበው ነበር። አንድ አድርገን ከውስጥ ሰዎች ባገኝችው መረጃ መሰረት በአሁኑ ሰዓት ዋልድባ ላይ እየተሰራ ላለው የሥኳር ፕሮጀክት የወራት ዝምታ መንስኤው ባለሙያዎች ቦታው ላይ ይህን ሥራ ለመስራት ፍቃደኛ አለመሆናቸው መሆኑን ለማወቅ ችላለች። በተለያዩ ጊዜም ለሥራ ወደ ቦታው ያቀኑ ባለሙያዎች በራሳቸው ፍቃድ ስራውን ያለደመወዝ እየለቀቁ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ እኛስ የኃያሉን የአምላክን እጅ እጠብቃለን ።

Tuesday, December 10, 2013

የሀረር እስላማዊትነት እንዴት ያለ ነው? (ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የተሰጠ ምላሽ)

ላሊበላን አላየሁትም፡፡ ላየው ግን እፈልጋለሁ፡፡ ፍጹም በሆነ የቀረጻ ጥበብ ከድንጋይ ተፈልፍለው የወጡትን አስራ አንዱንም አብያተ ክርስቲያናት ለመጎብኘት እጓጓለሁ፡፡ ዕድሉን ካገኘሁ እዚያ ያየሁትንና የተሰማኝን ስሜት ለመጻፍ እመኛለሁ፡፡ ይህንን ለማድረግ ደግሞ የግዴታ ክርስቲያን መሆን አይጠበቅብኝም፡፡ ሰው መሆኔ ብቻ በቂ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ የታሪክና የኢትኖግራፊ

ጸሐፊ በመሆኔ ደግሞ ስለ ላሊበላ የማውቀውን የማሳወቅ ግዴታ አለብኝ፡፡
ላሊበላ ክርስቲያናዊ መሬት ነው፡፡ ጠሊቅ የሆነ ክርስቲያናዊ ባህል፣ ታሪክና ትውፊት ይታይበታል፡፡ በዚህ ድንቅ የስልጣኔ ምድር ያሉትን ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት ያሳነጹት የኢትዮጵያ ክርስቲያን ነገሥታት ናቸው፡፡ በአሁኑ ዘመን ግን ላሊበላ የሁሉም

Monday, December 9, 2013

ተከብሮ ያላስከበረ ሕገ-መንግስት

December 8, 2013
ይድነቃቸው ከበደ
ህዳር 29 ቀን 1987 ዓ.ም ሕገ-መንግስቱ የፀደቀበት ቀን ነው፡፡ይህንንም ተከትሎ በመንግስት አሳሳቢነት እልፍ ሲልም አስገዳጅነት ህዳር 29 በየዓመቱ ከተለያዩ ጎሳ የተወጣጡ ሰዎች ተሰባስበው በመንግሰት ሹማምንቶች ፊት በአደባባይ ከበሮ የሚደለቅበት ቀን ነው፡፡ይሁን እንጂ የአብዛኛው ኢትዮጵያዊያን መልካም ፍቃድና ተሳትፎ ባልታየበት የፀደቀው ህገ መንግስት በብዙሃን ዘንድ ተቀባይነቱ ጥያቄ ውስጥ የገባ ነው፡፡በዚህም መሠረት ከቃሉ አጠቃቀም ጀምሮ እስከ አከባበሩ ክብረ በዓል አብዛኛዉ ሰው እኔንም ጨምሮ ግድ አይሰጠንም፡፡Ethiopian political commentator from Addis Ababa, Ethiopia. Ydnekachew Kebede
‹‹ይህ ህገ-መንግስቱን የመነዳ ተግባር ነው!!!›› ከገዢው መንግስት ተደጋግሞ የሚሰማ ለመፈረጅ ወይም ለመከሰስ የሚጠቀሙበት ቃል ነው፡፡ አንድ ወዳጄ እንዲህ አለኝ ‹‹ ይህ ህገ መንግሰት ዝም ብሎ የተደረደረ ብሎኬት ነው እንዴ የሚናደው ?›› በማለት ሲተች ሰምቸዋለው፡፡በመናድ እና ደግፎ በማቆየት ላይ የተመሠረተሁን  ህገ መንግስት እጅግ በጣም ብዙ ነገር ተብሎለታል፡፡
እየተንገዳገደ ያለው ህገ መንግስት ከአፀዳደቁ ጀምሮ የሚቀሩት ድንጋጌዎች መኖራቸው ለማንም ግልፅነው፡፡ ቢሆንም ፀድቆ በተግባር ላይ የሚገኘው ህገ መንግስት ዋጋ እንዳይኖረው እያደረገ ያለው የገዢው መንግስት አካሄድና ተግባር መሆኑ በአጭሩ ለማሳየት እሞክራለው፡፡

አቶ ሙሐመድ ኢብራሒም ማእከላዊ እስር ቤት ዉስጥ በደረሰባቸው ድብደባ ህይወታቸዉ ማለፉ፤ ሆድ-እቃቸዉ ተከፍቶ ኩላሊታቸዉ መሰረቁ ታወቀ

December 9, 2013

“አስክሬን ምንሊክ ሆስፒታል ሄደን እንድንወስድ ስልክ ተደወለልን፤ ለሞቱ ከደነገጥነዉ በላይ አስክሬኑን ስንመለከት ፍጹም ተረብሸናል፤ ከአዉሬ አፍ የተረፈ አስክሬን ነበር ሚመስለዉ…ሰዉነቱ ተቦጫጭቋል!” ጓደኞች

ዋሽንግተን ዲሲ፤ ህዳር 30/2006 (ቢቢኤን) ፦ በአዲስ አበባ ዉስጥ በቦሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪ የነበሩት አቶ ሙሐመድ ኢብራሒም ቀደም ሲል በጥቅምት 4/2006 በአካባቢዉ ላይ ፈንድቶ ከነበረዉ ቦንብ ጋር በተያያዘ መልኩ ለምርመራ ማእከላዊ እስር ቤት መግባታቸዉ እና በማእከላዊ ቆይታቸዉ ምግብ እንዳይገባላቸዉ ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸዉ መከልከሉም ለማወቅ ተችሏል።TPLF, EPRDF latest victim
እንደ አቶ ሙሐመድ ጓደኛ አገላለጽ ግለሰቡ ለተጠረጠሩበት ወንጅል የሚያበቃቸዉ ጉዳይ ባይኖርም፤ከገቡበት ማእከላዊ እስር ቤት በደረሰባቸዉ ከፍተኛ ድብደባ በህይወት መዉጣት አልቻሉም።

Sunday, December 8, 2013

ተማሪዎች ‹‹የፍትህ ያለህ!›› እያሉ ነው!


ከ2005 አጋማሽ በኋላ የአወልያ ግቢን መሰረት ያደረገውንና 2004 ታህሳስ ወር የተጀመረውን የህዝበ ሙስሊሙን ተቃውሞ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መረከብ እንዳለባቸው የሚያስረዱ ጥሪዎች ከየአቅጣጫው ይሰሙ ጀመር፡፡ ይህ አስፈሪ አቅጣጫ ልቦናው ውስጥ ከፍተኛ ፍርሀት የፈጠረበት የኢህአዴግ መንግስት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በራሳቸው ጉዳይ (በሰላትና ሂጃብ ጉዳይ) እንዲጨናነከትሎ በጥር ወር 2005 መጀመሪያ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሊኖር የሚገባውን የቁ በማድረግ በህዝበ ሙስሊሙ ተቃውሞ እንዳይሳተፉ ለመግታት ማሰቡን ከአንድ ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣን የወጣ መረጃ አመለከተ፡፡ ይህን ውሳኔ ተአለባበስ፣ አመጋገብና አምልኮ ስነ-ስርአት አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስቴር አውጥቶት የነበረውን ኢ-ህገ መንግስታዊ ረቂቅ ደንብ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በቀጥታ ተግባራዊ አደረገ፡፡ ይህ ገና በውይይት ላይ የሚገኝ ረቂቅ ደንብ ምንም እንኳ ሁሉንም የሃይማኖት ተከታዮች የሚመለከት ቢመስልም ቅሉ ግን ያነጣጠረው ድሮም በእናት አገሩ ኢትዮጵያ ፍዳውን እያየ በኖረው ሙስሊም ተማሪ ላይ ነበር፡፡ በውስጡም ሂጃብንና ሰላትን የሚገድቡ ህገ ወጥ ኢህአዴጋዊ ሴራዎች የተጎነጎኑበት ነበር፡፡