Tuesday, November 19, 2013

Ethiopian workers beaten, robbed in Saudi Arabia

e34d90cdNovember 19, 2013, ADDIS ABABA (BD Live) — When Abdallah Awele moved to Saudi Arabia from Ethiopia last year, he thought he would land a good job and earn enough money to send home to his family.

suppert g 7 puper forces anetel get our freedom


support this puper forcest to get our freedom and unit to our ethiopian


we are setand together to our land ethiopian


we have to setand for our freedom


ጭንቁን ቀን እንዴት እንለፍ!?

ጥላቻው እያደገ ሔዷል፣ ሳውዲ አሰሪዎች ኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኞቻቸውን ድሮ ድሮ በአረቦች ዘንድ የተከበርን፣ የታፈርን የእኛን የሃበሻ ልጆች “ጨካኞች ፣ የማይታመኑ!” እያሉ ጥላቻቸውን መገልጽ ጀምረዋል። November 14,2013 የወጣው አረብ ኑውስ Recent clashes make Saudis wary of Ethiopian maids በሚል ርዕስ ስር ሳውዲ አሰሪዎች ኢትዮጵያን ሰራተኞችን ለማባረር እየዛቱ ነው! ይህ የአረብ ኒውስ ዘገባ በሹክሹክታ የምንሰማው ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
የሪያድ መንፉሃን ግጭት ተከትሎ ደም እድገብሮም ለኢትዮጵያን ተሰጠው ወደ ሃገር ቤት የመግባትን እድል ለመጠቀም ከሃያ ሽህ በላይ ኢትዮጵያውያን የሪያድ መጠለያዎችን አጨናንቀዋል። እንዲውም በሪያድ የኢትዮጵያ አምሳደር ቁጥሩን ወደ ሃያ ሶስት ሽህ እንደሆነ ረቡዕ November 14,2013 ለወጣው አረብ ኒውስ አስታውቀዋል። አሁንም በሽዎች የሚቆጠሩ ወደ መጠለያ ለመግባት እየጎረፉ ነው። በመጠለያው የምግብና የሚጠጣ ውሃ እጥረቱ ደግሞ ኢትዮጰያውያኑ አጥር ሰብረው እንዲወጡ እያስገደደ ነው ተብሏል።
በጅዳ እና በተለያዩ የሳውዲ ከተሞች ያሉ ህጋዊ መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያንም የሚይዙት የሚጨብጡት አጥተው በቋፍ ላይ ናቸው ። በሪያድ እና በተለያዩ ከተሞቸ ባሳለፍነው ቅዳሜ በመንፉሃው ሁከት ጭካኔ የተቀላቀለበት በሃገሩ ነዋሪዎች ተወሰደ በተባለው እርምጃ ገና በመሰራጨት ላይ ያለው መረጃ ምስል ህጋዊ ሆነ ህገ ወጥ የሆነውን ሁሉንም እያስጨነቀ ነው። እኔም እዚያው መንፉሃ ሆነውን የአይን እማኝ ከሰማሁ ወዲህ ከ16 አመታት በላይ የማውቃቸው ሳውዲዎች ይህን ፈጸሙ ለማለት ብቻ ሳይሆን በዚህች ሃገር ይህ መሰል ግፍ በሰው ልጅ ይፈጸማል ለማለት ተቸግሬያለሁ። እውነት መሆኑን ደጋግሜ ሳሰላስለው ደግሞ የሳውዲ ኑሮ እየጎረበጠኝና ተስፋየን እየሟጠጠው ሄዷል። ብዙዎች በዚህና በመሳሰለው የማሳደድ ችግር ምክንያት ወደ ሃገር መግባት ይፈልጋሉ፣ በሪያድ ከመንፉሃ በተጨማሪ በኮንትራት ስራ የመጡና ለበርካታ አመታት በሳውዲ ነዋሪ የሆኑት ሳይቀሩ እንደ መንፉሃ ግፉአን በውድ የገዙትን እቃ በርካሽ እየሸጡና መኖሪያ ፍቃዳቸውን አሽቀንጥረው በመጣል ወደ መጠለያው እየገቡ ነው ።

Monday, November 18, 2013

በገዛ ሀገራችን መንግስታዊ ሽፍቶችም ሆነ በተሰደዱበት ሀገር ሰዎች መደፈሩ ፣ መዋረዱ መቼ ይሆን የሚቆመው ?

“… በየምሽቱ ሁላችንንም ወደ ምርመራ ክፍል ይወስዱናል ፡፡ ከዚያም እያንዳችንን ለያይተው ይገርፉናል ፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ስጠራ ሶስት ወንዶች በክፍል ውስጥ ይጠብቁኝ ነበር ፡፡ ወዲያዉኑ ሶስቱም በየተራ እየተፈራረቁ ደፈሩኝ ፡፡ ወደነበርንበት ጉድጓድ ስመለስ በከፍተኛ ህመም እየተሰቃየሁ ነበር ፡፡ አሁን ድረስ ህክምና ማግኘት አልቻልኩም ፡፡ በዚያ እስር ቤት ለሶስት ወራት ስቆይ በ12 ወታደሮች በተደጋጋሚ ተደፍሪያለሁ ፡፡ በግርፊያውና በአስገድዶ መድፈሩ ላይ የአካባቢው ኮማንደርም ተሳታፊ ነበር ፡፡ በዚያ የነበሩ ልጃገረዶችም ሆኑ እናቶች በሙሉ ተደፍረዋል ፡፡ በሶስቱ ወራት ውስጥ ቢያንስ 40 የሚሆኑ ሴቶች የእኔ እጣ ደርሷቸዋል ፡፡ ”

በኦጋዴን አካባቢ ታስረው ከተፈቱ የአካባቢው ነዋሪዎች መካከል ሂዩማን ራይትስ ዎች ካናገራት አንዲት ወጣት ታሪክ የተቀነጨበ፡፡
ምንጭ “ፋክት” መፅሄት ቁጥር 19 ጥቅምት 2006 እትም በገዛ ሀገራችን መንግስታዊ ሽፍቶችም ሆነ በተሰደዱበት ሀገር ሰዎች መደፈሩ ፣ መዋረዱ መቼ ይሆን የሚቆመው ?

የስደት ውርደት በዛ! ኢትዮጵያዊነትም ረከሰ


በሳዑዲ ዓረቢያ በኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ እየተፈጸመ ያለውና እየተስተጋባ ያለው አሰቃቂ ግድያና ድብደባ ይዘገንናል፣ ይሰቀጥጣል፣ ያቅለሸልሻል፡፡ አረመኔያዊ ነው፡፡

ሰላማዊ ታጋይን ማሸማቀቅ አይቻልም

በ1997 ዓ.ም የምርጫ ሰሞን ገዢው ፓርቲ በርካሽ ዋጋ ርካሽ ተግባር እንዲፈጽሙ የላካቸው ግለሰቦች የቅንጅትን አመራሮች የሚበዙት በዕድሜ አንጋፋና በትምህርት አንቱታን ያገኙ የዩኒቨርስቲ መምህራን፣ዳኞችና ሃኪሞች ናቸው፡፡ በዋጋ የተገዙት ግለሰቦች ግን ለማህበራዊ ህይወት ቦታ የሚሰጡ ባለመሆናቸው አመራሮቹን ለጆሮ በሚሰቀጥጥ ስድብ ይሰድቧቸው ነበር፡፡ዶክተር ሃይሉን፣ኢንጂነር ሃይሉ ሻውልን ‹‹አንተ››እያሉ በመደዴ ቃላት ይወርፏቸው ነበር፡፡