Monday, October 14, 2013

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰልፍ ክልከላ ቀጭን መስመር

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ መስከረም 24 ቀን 2006 ዓ.ም. ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ለሁለተኛ ጊዜ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በበርካታ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ገለጻ ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ሰልፍ የማድረግ ሕገ መንግሥታዊ መብት ዙሪያ የሰጡት ምላሽ ግን አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ኤልሳቤጥ እቁባይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረበችው ጥያቄ የሚከተለው ነበር፡- ‹‹የትግል እንቅስቃሴአቸውን አገር ውስጥ እያደረጉ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለያዩ ጊዜዎች በተለያዩ ከተማዎች ከመንግሥት ምላሽ ይፈልጋሉ ባሏቸው ጉዳዮች ላይ ሰላማዊ ሰልፎችን አድርገዋል፡፡ ምንም እንኳን ሰልፎቹን አስመልክቶ በመንግሥት ኮሚኒኬሽን በኩል የተሰጡ መግለጫዎች ቢኖሩም ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ከቀረቡ ጥያቄዎች ‹ምላሽ ያሻቸዋል፣ አግባብነት አላቸው› ብለው መንግስትም በተለያየ መንገድ ከሚሰበስባቸው መረጃዎች የወሰዷቸው ጥያቄዎች አሉ ወይ››

ለጥያቄው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጠው ምላሽ ለብዙዎች የሚያረካ ነበር ለማለት ያስቸግራል፡፡ ይልቁንም ምላሹ ሌሎች ተጨማሪ በርካታ ጥያቄዎችን አስነስቷል፡፡ በመልሳቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ሕገ መንግሥታዊ መብት መሆኑን፣ መንግሥታቸው በጫና ሐሳቡን የሚቀይር እንዳልሆነ፣ ተመሳሳይ ጥያቄዎች በተደጋጋሚ ከተጠየቁ መንግሥት አንድ ቦታ ላይ እንደሚያቆመው፣ የፓርቲዎች መብዛት ሰልፉን እንዳበዛው፣ ሰልፉ የሚታወቀው ውጭ ባሉ የእቅዱ ባለቤቶች እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ 
ሰላማዊ ሰልፍ እንደ ሕገ መንግሥታዊ መብት

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ‹‹ተቃዋሚዎች ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው ነው፡፡ ሕገ መንግሥቱ የሰጣቸው መብት እንጂ ማንም በችሮታ የሰጣቸው አይደለም፡፡ እንደ መንግሥት ኃላፊነታችን ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው ስለሆነ ያንን እንዲያስተናግዱ ማድረግ ነው፤›› በማለት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ሕገ መንግሥታዊ የዜጐች መብት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሀገሩን ችግር ሁሉ ለኦሮሞ ልጆች ብቻ እየሰጠ ሆድ የሚስብሰን ተስፍሽ… ተስፋው ምን ይሆን!

OromoWomanየሀገሩን ችግር ሁሉ ለኦሮሞ ልጆች ብቻ እየሰጠ ሆድ የሚስብሰን ተስፍሽ… ተስፋው ምን ይሆን!
መቅድም

ውድ የድረገጻችን ተከታታዮች ራሴን አሻሽላለሁ ብዬ ትምህርት ጀመሬ ስጠፋ ጊዜ ራሴን ያሸሸሁ መስሏችሁ ምነ ነካህ… ብላችሁ መጨነቃችሁን በተለያየ መልኩ አድርሳችሁኛል፤ ለተጨነቃችሁ እንደተጨነቃችሁልኝ አንድዬ ይጨነቅላችሁ!!! ብዬ መመረቅ እወዳለሁ፤ እነሆ ዛሬ በወዳጃችን ተስፍሽ ማስታወሻ ምክንያት ተከስቻለሁ አንብቡልኝማ፤



መብቱን ለማስከበር ታስሮም እንደማያጎበድድ በእስር ላይ የሚገኘው አንዷለም አራጌ አረጋገጠ

ፋሽስት ወያኔ ባቀነባበረው የውሸት ክስ በሽብርተኝነት ተከሶና በወያኔ አሻንጉሊት ዳኞች እድሜ ልክ ተፈርዶበት ቃሊቲ ወህኒ ቤት የሚገኘው የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አንዳለም አራጌ ዛሬም በእስር ቤት ለመብቱ እየታገለ እንደሆነ ተገለጸ። በውጭ ያሉት የተቃውሞ ሃይሎች መሰባሰብና እየተጠናከሩ መምጣት ሰላም የነሳው ፋሽስት ወያኔ በሀገር ውስጥ በቁጥጥሩ ስር ባለው የፓርቲዎች ሰላማዊ ሰልፍ እንቅስቃሴ ላይ ዛቻ እንዲያሰማ እንዳደረገው ይታወሳል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ነው እንግዲህ ፋሽስት ወያኔ ለአቶ አንዷለም አራ...See More

ቅዳሜ ዕለት የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ዛሬ ከሰአት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡

SHARE:

ቅዳሜ ዕለት የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ዛሬ ከሰአት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡
ቅዳሜ እለት በጃንሜዳ ፖሊስ ማዘዣ ጣቢያ ታስረው የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ችሎት አካባቢ ወደሚገኘው ወረዳ 9 ፖሊሰ ጣቢያ ተወስደው 2 ቀን እንዲያድሩ ከተደረጉ በኋላ ዛሬ ጠዋት ወደ ጃንሜዳ ፖሊስ ጣበያ ተመልሰው የተወሰዱ ሲሆን አሁንም በጃንሜዳ ፖሊስ ጣቢያ ይገኛሉ፡፡ በወረዳ 9 የ2 ቀን ቆይታቸውም የፖሊስ አባላት በግዴታ የወንዶቹን ፀጉር የቆረጧቸው መሆኑ ተረጋግጧል፡፡አባላቱ ዛሬ በ8 ሰአት ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ የተነገራቸው ሲሆን በጃንሜዳ ፖሊስ ጣቢያ የፓርቲው አባላትና ከፍተኛ አመራሮች እየጠየቋቸው ይገኛሉ፡፡

ስንቱን አጣን! (ከፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም)

 

Pro Mesfin
እንደኢትዮጵያ ባለ ኋላቀር አገር አገር ውስጥ መሠልጠን ብዙ ችግር አለበት፤ እኔ ራሴ በኮምፒዩተር መጻፍ ከጀመርሁ ሠላሳ ዓመት ሊሆነኝ ነው፤ ታዲያ መብራት ጠፋና የምሠራው ባጣ የቆዩ ወረቀቶችን ሳገላብጥ አንድ እአአ በዲሴምበር 26 1965 ከዱሮ ተማሪዬ የተጻፈልኝን ደብዳቤ አገኘሁ፤ በዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በነበረ ከአንድ በጣም ጎበዝ ወጣት የተላከልኝ ነበረ፤ ከተመረቀ በኋላ በአንድ ኩባንያ ውስጥ ተቀጥሮ ለጥቂት ዓመታት ሠርቶ ትምህርቱን ለመቀጠል ወደአሜሪካ ሄዶ በሎዝ አንጄለስ አካባቢ ከሚገኝ ትምህርት ቤት ገብቶ ነበር፤ ደብዳቤውን የጻፈልኝ ከዚያ ነው፤ ደብዳቤው ሰባት ገጾች አሉት፤ ከሰባቱ ገጾች አምስቱ ስለኢትዮጵያ ያለውን ስጋት የሚገልጽ ነው፤ በሎዝ አንጀለስ አካባቢ ካሉ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት በሚያደርግበት ጊዜ ሁሉ ብዙዎቹ የሚያሳዩት የመንደረኛነት ስሜት እያበሳጨው የተማሩት ሰዎች በእንደዚህ ያለ ማኅበረሰባዊ ኋላቀርነት ውስጥ ሆነው ኢትዮጵያ የምትባለው አገር እንዴት መራመድ ትችላለች? እያለ ይሰጋ ነበር።

ደብዳቤውን ላቋርጥና ስለሰውየው ትንሽ ልናገር፤ ተማሪ ሆኖ ክፍል ውስጥ ምንም ነገር የማያሳልፍ በጣም ተከራካሪ ተማሪ ስለነበረ አደንቀው ነበር፤ አንድ ጊዜ እንዲያውም የዘውድ መንግሥት ደጋፊ ነኝ አልሁና አንዴት በትከሻው ላይ ጭንቅላት ያለው ሰው ዓመቱን በሙሉ የዘውድ አገዛዝ የሚያደርስብንን በደልና ችግር ሲነግረን ቆይቶ አሁን ደግሞ ያንን ደጋፊ ነኝ ይላል ብሎ ወረፈኝ፤ ልጁን ስለማውቀው አነጋገሩ አሳቀኝ እንጂ አላስቆጣኝም፤ ጥያቄህ ይገባኛል፤ ግን እኔን ሳትወርፈኝ መጠየቅ ትችል ነበር በዬ ቢቀበለውም ባይቀበለውም ለጥያቄው መልሱን ሰጠሁት፤ በኋላም ጥሩ ጓደኛዬ ነበር።
 

ከአሜሪካ ትምህርቱን ጨርሶ እንደመጣ ተገናኘንና ወደቀድሞ ሥራው ወደወንጂ ተመልሶ እንደሆነ ስጠይቀው ‹‹እንዴት ብዬ! ዕድሜ ልኬን የፈረንጅ አሽከር ሆኜ መኖር አልፈልግም፤ አሁን ደግሞ ያስተማረኝን ሕዝብ ላገልግል እንጂ!›› ነበር ያለኝ፤ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና በወንጂ ባሉት ደመወዞች መሀከል ከፍተኛ ልዩነት ነበረ፤ ቁም-ነገረኛነቱን፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያለውን ታማኝነት፣ የግል ጥቅሙን ቀንሶ ኢትዮጵያን ለመርዳት ባሳየው ተግባራዊ አርአያነት የማደንቀው የወታደር ልጅ ነው።

ይህ ሰው በደርግ ጊዜም አልሸሸም፤ በአንድ ኢንዱስትሪ ውስጥ በሥልጣን ቦታ ላይ ነበር፤ ወያኔ/ኢሕአዴግ ወንበሩን ሲይዝ እንደዚህ ያሉ ሰዎች የማይፈለጉ መሆናቸው ሲታወቅ አገሩን ጥሎ ተሰደደ፤ በትልቅ ዓለም-አቀፍ መሥሪያ ቤት ጥሩ ሥራ አግኝቶ ዕድሜው ለጡረታ እስቲደርስ ቆየ፤ ወደሚወዳት አገሩ ለመመለስ አልቻለም፤ ከአንድ የትምህርት ቤት ጓደኛው ጋር ግንኙነት እንዳለው አውቃለሁ፤ አንድ ቀን ስለዚሁ የጋራ ጓደኛችን ስናወራ ለምን ወደኢትዮጵያ እንደማይመለስ ጠየቅሁ።
 

የዚህ ወጣት አጎት በወታደርነት ኢትዮጵያን ለረጅም ጊዜ በክብር ያገላገለ ነው፤ ይህ ሰው ወያኔና ሻቢያ በተጣሉ ጊዜ ዜግነታቸው በጉልበት እየተገፈፈ ከአገራቸው እንዲወጡ ከተደረጉት ሰዎች አንዱ ነው፤ በዚያን ጊዜ በሌላ የኤርትራ ተወላጅ ላይ የተፈጸመውን ግፍ ራሱ ሰውዬው በአሜሪካ ድምጽ ራድዮ ሲናገር የሰማሁት የሚከተለውን ነው፤– ‹‹ለኢትዮጵያ በአለኝ ሁሉ አገልግያለሁ፤ ኢትዮጵያን ሳገለግል አንድ እግሬን አጥቻለሁ፤ አንድ ሰው ለአገሩ ከዚህ የበለጠ ምን ያደርጋል?›› ብሎ ሲናገር አስለቅሶኛል።

የኔ የቀድሞ ተማሪና ወዳጅም ለምን ወደኢትዮጵያ እንደማይመለስ ሲጠየቅ ‹‹ለጋሼ (ማለት ለአጎቱ) ያልሆነች ኢትዮጵያ ለእኔ አንዴት ትሆነኛለች? በማለት በጥያቄ መለሰ አሉ፤ አባቱ ያገለገላትን፣ አጎቱ የለፋላትን፣ አያት ቅድመ-አያቶች የሞቱላትንና የደሙላትን አገር እንዲህ በቀላሉ ማጣት ነፍስን ያቆስላል፤ የነዚያን ሰዎች ሁሉ መስዋእት ያከሽፋል፤ ያረክሰዋል፤ ይህንን የተገነዘቡና ያዘኑ፣ ያለቀሱ ሰዎች ናቸው –
እናት ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ፣
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ!

የትናንቱን የአዲስ አበባ የፈንጂ ፍንዳታ ያደረሱት ሁለት ሶማሊያውያን አሸባሪዎች መሆናቸውን ፖሊስ ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 4 ፣ 2006 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት በአዲስ አበባ  ቦሌ  ክፍለ ከተማ  የደረሰው የፈንጂ ፍንዳታ በሁለት ሶማሊያውያን  አሸባሪዎች የተፈፀመ መሆኑን የኢትዮጵያ  ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ ።
የኢትዮጵያ  ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል አሰፋ አብዩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስረዱት ፥ በክፍለ  ከተማው ወረዳ 01 ቀበሌ 01 በተለምዶ ሩዋንዳ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ  በአንድ የመኖሪያ ቤት  ውስጥ ነው ፍንዳታው የደረሰው ።
ፖሊስ ፍንዳታው ፈንጂ መሆኑንና ፥  በጥቅም ላይ የዋለው ቲ ኤም ቲ የተባለ  የፈንጂ ዓይነት መሆኑን እንደደረሰበት  ገልፀዋል ።
ፍንዳታውንም  ሁለት  ሶማሊያውያን ማቀነባበራቸውን ፖሊስ እንዳረጋገጠና  ግለሰቦቹ የአሸባሪ ቡድኑ አልሸባብ አባል መሆናቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች እንዳሉም ነው ጀነራል አሰፋ አብዩ ያስረዱት ።
ከሁለቱ  አሸባሪዎች መካከል አንደኛው ወገቡ ላይ የታጠቀና ለአጥፍቶ ጠፊ ተግባር የተዘጋጀ መሆኑን  የሚያሳይ ነው ።

ሌላኛው  አሸባሪ በሻንጣ ፈንጂ  የያዘ ሲሆን ፥ የፈነዳውም ፈንጂ በሻንጣው ውስጥ የነበረ መሆኑን ነው ጀነራል አሰፋ ያስረዱት ።
ለአጥፍቶ  ጠፊ ተግባር  ሲዘጋጅ የነበረው ግለሰብ የታጠቀው ፈንጂ  ግን  እንዳልፈነዳ አመልክተዋል ።
አሸባሪዎቹ በአጠቃላይ  ሶስት ፈንጂዎችንም ይዘው ነበር ።

አሸባሪዎቹ ህዝብ ባለበት ስፍራ አደጋ ለማድረስ ተከራይተው በነበሩበት ቤት ውስጥ ሲዘጋጁ ፍንዳታው ደርሷል ብሎ ፖሊስ እንደሚጠረጥር ነው የጠቆሙት ።
ከአሸባሪዎቹ  ጋር ፖሊስ የእጅ ቦምቦችንና ሽጉጥ ከነጥይቱ  አግኝቷል ።

ከዚህ የምንማረው  
ጀነራል አሰፋ አብዩ እንደሚሉት ሶማሊያውያን አሸባሪዎቹ  ቤቱን ከተከራዩ ከ22  እስከ 23 ቀን ይሆናቸዋል ።
እስከ  ስድስት የሚደርሱ  ቤቶችን በከተማዋ  የሚያከራዩት የቤቱ ባለቤቶች  ስለነዚህ  ግለሰቦች ስምን ጨምሮ  ማንነታቸውን  እንደማያውቁ ነው የተደረሰበት ።
በመሆኑም ህብረተሰቡ ቤቱንም ሆነ  መኪናውን ሲያከራይ ስለተከራዩ ማንነት በቂ  እውቀት ይዞ ፥  መታወቂያና ፓስፖርት ተመልክቶ  መሆን  እንዳለበት ነው ያሳሰቡት ።
የሚያገኛቸውን መረጃዎች በአቅራቢያው ለሚገኝ የፖሊስ  ተቋም  መስጠት  ግዴታው መሆኑን በመረዳትም ፥  ሽብርተኝነተን ከፖሊስ ጎን  ሆኖ  እንዲከላከል ጥሪ አቀርበዋል ።
ተያያዥ ዜና

በአዲስ አበባ የፈንጂ ፍንዳታ ደረሰ



Sunday, October 13, 2013

የፖለቲካ ፓርቲዎች ሥር ነቀል የአስተሳሰብና የአቋም ለውጥ አስፈላጊነት

ከእንጉዳይ በቀለ፣ አዲስ አበባ ሕወሐት/ኢህአዴግ ኢትዮጵያን በጉልበትና በግፍ መግዛት ከጀመረ 22ኛ ዓመቱን ይዟል፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ እንደ ሟርትአይታይብኝና ይህ ቁጥር አሁን ካለው እውነታ በመነሣት ወደ ሠላሳና አርባ ብሎም ሃምሳ የማይዘልቅበት ምንም ምክንያት ያለ አይመስልም.. ይህን ለመገመት ውስብስብ ስሌት ወይንም የሂሣብ ቀመር አይጠይቅም፡፡ በአገር ቤት ያለውን አያያዝና በተቃዋሚዎች በኩል ያለውን እንቅስቃሴ በመቃኘት ስህተት ነው ሊባል ከማይችል ድምዳሜ ላይ ሊደረስ ይቻላል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአገራችን ፖለቲካ በእጅጉ ከመሰላቸቱ የተነሣ መፃዒ ዕድል ፈንታውን ከእግዚአብሔር እንጂ ከተቃዋሚዎች ወይንም ከፖለቲካ ድርጅቶች ተስፋ ማድረግ ከተወ ሰነባብቷል፡፡

ESAT DC Daily News Oct 12, 2013


After latest Lampedusa tragedy, Ban calls for action to protect human rights of migrants

Italian coastguards help a group of boat people found floating in a crowded craft near Lampedusa Island.UNHCR/A.Di Loreto
12 October 2013 – Following reports of a second ship capsizing off the coast of the Italian island of Lampedusa, Secretary-General Ban Ki-moon today called on the international community to protect the rights of migrants and take action to prevent such tragic incidents.

“The Secretary-General is deeply saddened to hear reports of the loss of lives as another boat carrying migrants capsized yesterday off the coast of Italy, only a few days after the tragic incident near Lampedusa which had already claimed more than 300 lives,” Mr. Ban's spokesperson said in a statement.
According to media reports, at least 27 people died and 221 were saved on Friday after their boat capsized near Lampedusa.

The incident occurred just over a week after more than 300 migrants, mostly Ethiopian, lost their lives when their boat caught fire half a mile from the coast, leading the vessel to capsize in the same area.
“The Secretary-General calls on the international community as a whole to take action to prevent such tragedies in the future, including measures that address their root causes and that places the vulnerability and human rights of migrants at the centre of the response,” the statement said.
News Tracker: past stories on this issue

በ1ኪሎ ቁርጥ ሥጋ እና በ12 ድራፍት ብርጭቆ – እውነትና ከሕደት………(ከ ይድነቃቸው ከበደ)

ooohhhh
(የሰማያዊ ፓርቲ የህግ ጉዳይ ሀላፊ)
ኪነ-ጥበብ ምኞታችን፣ደስታችን፣አዘናችንን እና ክፋታችን የምናይበት እና የምናዳምጥበት የህይወታችን ነፀብራቅ ነው፡፡ ኪነ-ጥበብ ህይወትን ቀለል አድርጎ ከማዝናናት ባለፈ በገለሰብ አስተሳሰብ ላይ የራሱ የሆነ በጎ ወይም በጎ ያልወነ አስታውጾ የሚያበረከት ጥበባዊ ሃይል ነው፡፡ይህ ሃይል በመልካም አስተሳሰብ ላይ ተመስርቶ ወደ ህብረተሰቡ ውስጥ ሲገባ የሚኖረው አገራዊ ፋይዳ እጅግ በጣም የበዛ ነው፤፤ በመሆኑም ኪነ-ጥበብ እንዲህ አይነቱ ጠቀሜታ እንዲኖረው የሚያደርጉት በጥበብ ሙያ ውስጥ የሚገኙ ባለሙያዎች ናቸው ፤እነኚህ ባለሙያዎች ሙያቸው ከመሬት የፈለቀ ሣይሆኖ በልምድና በት/ት የዳበረ ጥበባዊ ተስጥኦ ነው፡፡ ከኪነ-ጥበብ ዘርፎች ውስጥ ከሚመደቡት አንዱ ቴአትር ነው፤ ቴአትር በአገራችን ያለው ተቀባይነት ቀላል የሚባል አይደለም ፤ቴአትር አሁን ያለበት ደረጃ ለመድረስ የቴአትር ባለሙያዎች የከፈሉት ዋጋ ከዕድሜቻው፣ ከገንዘባቸው እና ከዕለት ተዕለት ማህበራዊ ህይወታቸው ላይ ጎምዶ ያስቀረባቸውን የሚያውቁት 

ዋጋውን የከፈሉት እነሱ ብቻ ናቸው፡፡ ቢሆንም በቴአያትር ጥበብ የዝወትር እንቅስቃሴችን መጥፎዉንና የተሸለውን በመለየት ጥበባዊ በሆነ መንገድ እየተዝናናን እንድንማርበት ለሚያደርጉ የቴአትር ባለሙያዎች ስራዎቻቸውን ስንመለከትና ስናደምጥ እውነትም ለሙያው እድገት የተከፈለ ነገር እንዳለ ያስገነዝበናል፡፡
 
ስለሆነም ለቴአትር ባለሙያዎቻችን ከትላንት ዛሬ የምንሰጣቸው ከበሬታና አድናቆት የሚበረታታና የሚያስደነቅ ነው፤ይህ ደግሞ ለቴአትሩም እድገት የሚጠቅም ነው፡፡ይሁን እንጂ በቀርብ በብሔራዊ ቴአትር ቀደምት ባለሙያዎች ላበረከቱት አስታዋጽኦ በማስታወስ የሽልማት ፕሮግራም የተዘጋጀ ቢሆንም ዝግጅቱ እውነትና ከሕደት የተቀላቀለበት ነበር፡፡