Friday, October 11, 2013

በሐረማያ ዩንቨርስቲ የመንግስት ባለስልጣናትና የዩንቨርስቲዉ አመራር በጠሩት ስብሰባ ላይ ጽኑ ተቃዉሞ ገጠማቸዉ

መስከረም 30/2006) ቢቢኤን ዋሽንግተን ዲሲ፦ አክራሪነትና ጽንፈኝነትን አስመልክቶ ስልጠና ለመስጥት የፈዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከሐረማያ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ዛሬ ያደረገዉ ስብሰባ ያለዉጤት መበተኑ ታወቀ።
የስብሰባዉ ተሳታፊዎች በግልጽ መንግስት ስም እያመጣ አክራሪ አሸባሪ ብሎ መፈረጁ ግዜ ያለፈበት ነው የተማረዉ የዩንቨርስቲዉ ማህበረሰብ ቀርቶ ዛሬ አባቶቻችንም አይቀበሉትም የመረጃ ምንጫችን ኢቲቪ ብቻ ነው ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ ተሳስታችሗል በማለት ተማሪዎችና የዩንቨርስቲዉ መምህራን የመንግስት ባለስልጣናትን መሞገታቸዉ ለማወቅ ተችሏል።
ጽንፈኛ የሚለዉ ቃል በባርያ ፍንገላ ግዜ በባሪያ አሳዳሪዎች ላይ ያምጹ ለነበሩ ግለሰቦች የተሰጠ ስያሜ ነው በማለት የተናገሩት ክርስቲያን ታዳሚ መንግስት የእስልምና ሐማኖት ተከታዮች ጦርነት በክርስቲያኑ ላይ ሊያዉጁ ነው ብሎ ቢናገር ህዝበ ክርስቲያኑ እንደማያምን በመግለጽ ኢትዮጵያ ዉስጥ አክራሪ አለ ማለቱ አለማቀፋዊ እዉቅናን ያላገንኘ ተዓማኒት የለዉ መሆኑን ገልጸዋል።

ዩንቨርስቲዉ ሶላትና ሂጃብን አስመልክቶ እገዳ ለማድረግ እቅድ እንዳለዉ የገለጸ ቢሆንም ታዳሚዎቹ በሐይማኖት ሳይለያዩ ሐሳቡን ዉድቅ ማድረጋቸዉ ም ታዉቋል።ኢትዮጵያን ልክ እንደ አፍጋኒስታንንና ፓኪስታን ችግር ያለባት ማስመሰሉ ተገቢ አይደልም የኢትዮጵያ ህዝብ ተቻችሎ ያለ በመሆኑ ያንዱ ወገን ሐይማኖት መተግበር ለሌላዉ ስጋት አይደለም የሐማኖት አልባሳት ከበር መልስ የሚለዉ የዩንቨርስቲዉ እቅድ ተቀባይነት የለዉም ሰዎች ሐይማኖታዊ አለባበሳቸዉን ከቀየሩ አማለካከታቸዉን ይቀይራሉ ማለቱ ተቀባይነት የለለዉ ነዉ በማለት ሐሳባቸዉን የገለጹም ነበሩ። ሽብር በሌለበት አገር ስለ ሽብር ማዉራቱ ነራሱ ማሸበር ነው ያሉት ሌላ ተሳታፊ ሙስሊም እንደመሆናችን በቀን አምስት ግዜ መስገድ አለብን በዶርም (በማደሪያ) ዉስጥ መስገድ ከተከለከልን ግቢዉ ዉስጥም እንዳንሰግድ ከተደረግን አስቸጋሪ ነዉ የሚሆነዉ ግን ኢትዮጵያዊ ሙስሊም በመሆኔ በጣም እኮራለሁ ስለምን ካላቹህ ኢትዮጵያ የሰላም አገር ናትና! ምን አልባትም ሶማሊያዊ፣ናይጄሪያዊ ካልያም አፍጋኒስታናዊ ብሆን ኖሮ ይህንን ያገኘሁት ሰላማዊነት አለገኝም ነበር በማለት አስተያታቸዉን ሰጥተዋል።

ወደ ኢትዮጵያዉ መዝገበ ቃላት የሚገቡ አዳዲስ የፖለቲካ ቃላቶች እየተፈጠሩ ለስብሰባ እየተጠራን ለምን ግዜ ይባክናል? ለምን አገርን ለማስደግ ለልማት አንሰበሰብም አያዉቁም ብላቹህ አትናቁን እኛ ከናንተ የበለጠ እናዉቃለን በማለት የመንግስት ካድሬዎችን ያሳፈሩ እንደነበሩ ለማወቅም ተችሏል።

መንግስት ፍርሃትንና መፈራራትን በህዝብ ዘንድ ለማንገስ አክራሪነት፣አሸባሪት እና ጽንፈኝነት በማለት በተለያዩ የትምርት ተቋማት በስልጠናና በዉይይት ስም የሚጠራዉ ተከታታይ ስብሰባ መንግስት ኪሳራን የሚጎናጸፍበት ነዉ! ህዝቡ ከፍርሃት ተላቆ ለመብቱ እንዲታገል የሚጋብዝ መሆኑ በገሃድ እየታየ በማለት ሀሳባቸዉንም የሚገልጹ አሉ።

በዛሬዉ እለት በሐረማያ ዩንቨርስቲ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር አክራሪነትንና አሸባሪነትን አስመልክቶ ባዘጋጀዉ ስልጠና ላይ እስከ አስራ ሁለት ሺ የሚጠጉ ተማሪዎች የተሳተፉበት ሲሆን ተማሪዎች የመንግስት ባለስልጣናት የሚያቀርቡትን ሐሳብ በድምጽ እና ስብሰባዉን ረግጦ በመዉጣት ዉድቅ አድርገዉታል። አንደ ታዛቢዎች አገላለጽ ስልጠናዉ በተገላቢጦሽ ለመንግስት የአመራር አካላት ስልጠና የተሰጠበት ነበር።
ቢቢ ኤን በዛሬዉ ፕሮግራሙ ሰፋ ያለ ዘገባ ይኖረዋል።

“የስደተኛው ማስታወሻ” አዲስ መጽሀፍ ከተስፋዬ ገብረአብ

October 11, 2013 ጋዜጠኛና ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ “የስደተኛው ማስታወሻ” መጽሀፉን በነጻ እንዲነበብ ለቆታል። [ሙሉውን መጽሀፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]
እንደማስገንዘቢያ፣ ድረ-ገጻችን ይህንን የተስፋዬ ገብረአብ አዲስ መጽሀፍ “የስደተኛው ማስታወሻ” አስፈንጣሪ ይዞ የሚቆየው አንባቢያን መጽሀፉን አንብበው ከሚሰጡት አስተያየቶች በመነሳት ይሆናል።
yesedetegnaw mastawesha tesfaye gebereab

Thursday, October 10, 2013

ሼኽ አላሙዲ በዕዳ የተያዘውን ካሩቱሪን ለመጠቅለል አስበዋል

“ኢትዮጵያ ከሁለቱም ያተረፈችው እዳ ነው”alamudi-
በኢትዮጵያ ባሏቸው ኢንቨስትመንቶች መልከ ብዙ ችግሮች እንዳሉባቸው የሚነገርላቸው ሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ በዕዳ የተያዘውን የካሩቱሪን የእርሻ መሬት ለመግዛት ከድርድር ላይ ናቸው ተባለ። ድርድሩ በስምምነት ከተቋጨ የሳዑዲን የምግብ አቅርቦት ለመሸፈን የሚንቀሳቀሱት “ባለሃብት” በጋምቤላ ብቻ ከ230 ሺህ ሄክታር በላይ ድንግል መሬት ባለቤት ይሆናሉ። በድርድሩ መሰረት እስከዛሬ ከወሰዱት በተጨማሪ ብድርም ከንግድ ባንክ ያገኙበታል።

የሳዑዲን የምግብ ኮታ ለመሸፈን ታስቦ እንደተመሰረተ የሚነገርለት የሳዑዲ ስታር አግሮ ኢንዱስትሪ በ2001 ዓ ም 10ሺህ ሄክታር መሬት ተረክቦ በጋምቤላ ስራ ሲጀምር ተጨማሪ 500 ሺህ ሄክታር መሬት እንደሚሰጠው ቃል ተገብቶለት እንደነበር በወቅቱ የተለያዩ መገናኛዎች ዘግበው ነበር።

የሪፖርተር ማኔጂንግ ኤዲተር በደቡብ ክልል ፖሊስ ተወሰደ

የሪፖርተር ማኔጂንግ ኤዲተር በደቡብ ክልል ፖሊስ ተወሰደየሪፖርተር ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር መላኩ ደምሴ ዛሬ ሐሙስ መስከረም 30 ቀን 2006 ዓ.ም. እኩለ ቀን ላይ አዲስ አበባ ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ ከሚገኘው የሪፖርተር ቢሮው በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል የፖሊስ ኃይል አባላት ተይዞ ወደ ሐዋሳ ከተማ ተወሰደ፡፡

የፖሊስ አባላቱ የያዙት የፍርድ ቤት ማዘዣ እንደሚያመለክተው፣ ሪፖርተር ጋዜጣ ረቡዕ ነሐሴ 29 ቀን 2005 ዓ.ም. በጋዜጣው የፊት ገጽ ላይ ‹‹የደቡብ ክልል ሦስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች ከኃላፊነት ተነሱ›› በሚል ባተመው ዜና ምክንያት ጋዜጠኛ መላኩ ለጥያቄ መፈለጋቸውን ይገልጻል፡፡ አዘጋጁ በቅድሚያ አምቼ አካባቢ በሚገኘው በቦሌ ክፍለ ከተማ በፖሊስ ማዘዣ የተወሰደ ሲሆን፣ በኋላም ለክልሉ ፖሊስ አባላት ተላልፎ መሰጠቱ ታውቋል፡፡
የክልሉ ኃላፊዎቹ ተነስተዋል በሚል ሪፖርተር ጋዜጣ የዘገበው ዜና ስህተት መሆኑን በማመን በቀጣይ ዕትሙ እሑድ ጳጉሜን 3 ቀን 2005 ዓ.ም. ላይ ዜናው በወጣበት የጋዜጣው የፊት ገጽ ላይ ማስተካከያ ማውጣቱ የሚታወስ ሲሆን፣ በሐዋሳ የሚገኘው የሪፖርተር ባልደረባም ይህንን ዘገባ በማጠናቀርና በመዘገብ ለሠራው ስህተት ዝግጅት ክፍሉ አስተዳደራዊ ዕርምጃ መውሰዱ ይታወቃል፡፡

የአማራ ክልል የድንበር ከተሞች ለአጎራባች ክልሎች ሊሰጡ ነው፡፡

የአማራ ክልል የድንበር ከተሞች ለአጎራባች ክልሎች ሊሰጡ ነው፡፡
ኢሳት ከአማራ ክልል ባለስልጣናት ባገኘው መረጃ የጃን አሞራ፣ የማይጸብሪ አዋሳኝ፣ ራስዳሸንን ጨምሮ የአዲአርቃይን አካባቢዎች ወደ ትግራይ፣ በመተማ በኩል ደግሞ የተወሰነውን ክፍል ለቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለመስጠት ድርድር በመካሄድ ላይ ነው።

ባለስልጣናቱ ቀደም ብለው የህዝቡን የልብ ትርታ ለማዳመጥ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር የደረሰን መረጃ የሚያመለክት ሲሆን፣ አንዳንድ የወረዳ ባላስልጣናት ጉዳዩን ወደ መድረክ እንድናወጣላቸው ተማጽነዋል።

መንግስት ከአሁን በፊት በአማራ ክልል ስር የነበረውን የመተከል ዞን ለቢኒሻንጉል ጉምዝ ፤ራያና ቆቦ ፤ዳንሻ እና ሁመራ ፤በመተማ በኩል ለሱዳን ፤የመተማ ቀሪው ክፍል ለቤንሻንጉል ፣ በሰሜን ሺዋ በኩል ለኦሮምያ የልማት እገዛ በሚል መሰጠቱን በማውሳት ፣ አሁንም ተጨማሪ መሬት እየተቆረሰ ክልሎችን ለማስደሰት እየዋለ ነው በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

የአንቀጽ 39 ቱርፈቶች የሰጡን ገፀ በረከቶች ናቸው ሲሉ የአማረሩት የድንበር ከተማ ነዋሪዎች፣ ”ጨለምተኛ አባት መሬት እየሸጠ ልጆቹን ከእርስት ይነቅላል፡፡ ጨለምተኛ መንግስት አገርን በመሸጥ ዜጎችን ያስደፍራል፡፤ ምንነታቸውን ያሳጣል መንግስትም ማንነታችን እየነጠቀን ነው ሲሉ” ገልጸዋል።

ትንሽ ስለ ተስፋዬ ገብረአብ

October 10, 2013
Abraha Desta the facebook
አብረሃ ደስታ
‘የተስፋዬ ገብረአብ ማንነት አጋለጠ’ የተባለውን ፅሑፍ አነበብኩት። ገረመኝም። ረዥም ነው። የአንድ ሰው ማንነት ለማጋለጥ አርባ ምናምን ገፅ? ተስፋዬ ገብረአብን ‘ያጋለጠ’ ፅሑፍ ለኔ ምንም ዓይነት ተጨማሪ መረጃ አልሰጠኝም።
ስለ ተስፋዬ ገብረአብ ትንሽ ለመፃፍ የተገደድኩት ምክንያት አንዳንድ የህወሓት ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች ‘የተስፋዬን መጋለጥ’ ምክንያት በማድረግ እኔ አንድ ነገር እንድልላቸው ስለወተወቱኝ ነው። አንዳንዴ’ኮ ጎበዞች ናቸው። ተፎካካሪያቸውን ማኖ ማስነካት ይችላሉ። እኔ ደግሞ ማኖ መንካት እወዳለሁ፤ (ማኖ ካልነካንላቸው ከስድብ ዉጭ ሌላ የሚያውቁት ነገር የላቸው)።
ተስፋዬ ገብረአብ ጎበዝ የስነ ፅሑፍ ሰው ነው። ፅሑፉን ለመገምገም ማንነቱና ስራው አያገባንም። የፅሑፉ ይዘትና መልእክት መገምገም በቂ ነው። እንደ የስነፅሑፍ ሰው ጥሩም መጥፎም ስራዎች ይኖሩታል። ለምሳሌ ‘የቡርቃ ዝምታ’ ፅሑፉ መጥፎ ዓላማ ያለው መሆኑ የሚያሳይ ነው።

በኖርዎይ የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይልን ለመርዳት በ28 ሴፕቴምበር 2013 በተዘጋጀው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በደማቅና በአስገራሚ ሁኔታና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ

g7pf event2በኖርዎይ የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይልን ለመርዳት በ28 ሴፕቴምበር 2013 በተዘጋጀው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በደማቅና በአስገራሚ ሁኔታና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፥፥ ይህ ዝግጅት ከተለያዩ የኖርዎይ ክፍለ ሃገራት እንዲሁም ከሎንደን ድረስ ኢትዮጵያውያን ህዝባዊ ሃይሉን ለመርዳት የተሰባሰቡበትና አጋርነታቸውን የገለፁበት ነበር፥፥
ይህንን ከፍተኛ አላፊነት በመሸከም ፕሮግራሙ ለዚህ መሳካት ያበቃችሁ ያአብይ ኮሚቴና የተለያዩ የሰብ ኮሚቴዎች አባላት፣ በተለያየ ቡድን ለስራው መሳካት የተሰለፋችሁ ወገኖች፣ በመላ አለም እንዲሁም በኖርዌይ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን፣ ታላቅ ምስጋና ይድረሳችሁ፥፥

በማያያዝም በተደጋጋሚ እዚህ በኖርዌይ ምድር አከርካሪያቸው የተሰበረው የወያኔ ቡችሎች እና ሎሌዎች የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይልን የድጋፍ ፕሮግራም ለማስተጓጎል ያደረጉት ሙከራ በማህበረሰባችን ሙሉ የነቃ ተሳትፎና ክትትል ከንቱ ሊሆን ችሏል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ
ኖርዌይ፣ ኦስሎ ሰፕቴምበር 29፣ 2013

በኦስሎ በተካሄደው የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት የተሳካ እንደነበር ትህዴን ዘገበ

tpdm
በተለያዩ አገራት የሚገኙ የትህዴን ደጋፊዎች ግንቦት-7 እያካሄደው ባለ ስብሰባ መገኘታቸውን የትህዴን የህዝብ ግንኝነት ገለጸ፣ ትህዴን የትጥቅ ትግል በማካሄድ ላይ ከሚገኘው ግንቦት-7 ጋር

ተባብሮ ለመስራት መግባባት ላይ ከመድረሱም በላይ በተግባር በተለያየ መልኩ ሲተጋገዙ የቆዩ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተለያዩ ሃገራት የሚገኙ የትህዴን አባላት የግንቦት-7 አመራር ከአባላቱ ጋር

በተለያዩ ሃገራት እያካሄደው ባለ ስብሰባ በመገኘት አንድነታችንን አጠናክረን እጅ ለእጅ ተያይዘን እንሰራለን ሲሉ ለግንቦት-7 ያላቸውን ድጋፍ መግለጻቸውን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣፥

በስብሰባው የተገኙ የትህዴን ተወካዮች አያይዘው እኛ በዚሁ ስብሰባ ስንገኝ ለይምሰል ሳይሆን የህዝብን ድምጽ በአፈሙዝ ረግጦ ስልጣን የተቆናጠጠውን ከፋፋዩን የኢህአዴግ ስርዓትን በሚገባው ቋንቋ
በትጥቅ ትግል ከስሩ መንግሎ ለመጣል ገና ከመነሻው ትህዴን አምኖበት የተነሳለት በመሆኑ የድርጅቱን ዓላማ ዕግቡ ለማድረስ የሁለቱም ድርጅቶች አባላትና ደጋፊዎች የኢህአዴግ ስርዓት መለያ

ከሆነው በዘር የመከፋፈል አባዜ በመውጣት በሙሉ ልብ ድርጊቱን በማውገዝ ከሃገር ውስጥ ይሁን ከሃገር ውጭ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ከመቸውም ጊዜ በላይ ግንኝነታችንን አጠናክረን ተባብረን መስራት ይጠበቅብናል በማለት ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፣፥
የግንቦት-7 አመራርና አባላት በቡኩላቸው የትጥቅ ትግል በማድረግ ላይ ካሉት ተቃዋሚ ድርጅቶች በመሳሪያ ፤ በሰው ሃይልና በዓላማ ሲታይ ትህዴን ጠንካራ መሆኑን በመግለጽ እንዲህ ካለው አስተማማኝ
ድርጅት ጋር ተባብሮ ለመስራት ከመግባባት አልፈን አብረን እየሰራን ነው፣ ይህ መልካም ጅምር አጠናክረን እንቀጥልበታለን ሲሉ መግለጻቸውን የደረሰን ዘገባ ያስረዳል፣፥
ምንጭ፥ http://www.tpdmonline.com/news/NEWS_2013/OCTOBER_2013/ARTICLE_NEWS/abalat_demhit_ab_nay_gunbet-7_akheba_tesatifom.pdf

 
 

The Total Domination of the Ethiopian Army by Ethnic Tigrean Officers

Ginbot 7 Report
Originally Posted May 30th, 2009
Since day one of its active political life, Ginbot 7 has repeatedly informed the international community that the ethnocentric political and economic policies of the TPLF regime are the primary sources of violence and instability in Ethiopia and the Horn of Africa at large Despite the different masks that this crafty regime wears to dupe donor nations and other stakeholders, Ginbot 7 has delved deep into the inner workings of the TPLF regime and exposed the toxic ethnic policies that consumed the life of many Ethiopians, and forced many others to seek refuge in neighboring countries.

ይድረስ ለፕሬዚደንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ

October 10, 2013 ይሄይስ አእምሮ
ክቡር ፕሬዚደንት ግርማ ሆይ፣
ኢትዮጵያንና “ሕዝቦቿ”ን የሚወዱ ከሆነ ቀጥዬ የምነግርዎትን ከልብ እንዲሰሙኝ በሚያምኑት እለምነዎታለሁ፡፡
ሰሞኑን በጡረታ ሊሰናበቱ እንደሆነ ከተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ዜና ዘገባ ሰማሁ፡፡ በመጀመሪያ ሥራዎን ጨርሰው ለዚህ በመብቃትዎ እንኳን ደስ ያለዎ፡፡ ቀጥዬም በሥራ ዘመንዎ ምን እንደሠሩና እኛ በምናውቅልዎም ሆነ እርስዎ በሚያውቋቸው ምክንያቶች የተነሣ ምን ምን መሥራት ፈልገው ሊሠሩ እንዳልቻሉ “ፕሬዚደንታዊ የሥልጣን ዘመን”ዎን የኋሊዮሽ በማሰብ  ከራስዎ ጋር በምልሰት ለመነጋገር የሚያስችል የማሰላሰያ ጊዜ በማግኘትዎ አሁንም በድጋሚ እንኳን ደስ ያለዎ – መልካም ዕረፍት፡፡ ነገር ግን ከስንብትዎ ጋር በተያያዘ የሰማሁት፣ ክፉኛ ያስደነገጠኝና ማመንም ያቃተኝ አንድ ጉዳይ ስላለ ይህን ማስታወሻ ልጽፍልዎ ተገደድኩ፡፡ President Girma Wolde-Giorgis
ጡረታ ሲወጡ እንዲኖሩበት መንግሥት የተከራየልዎት ቤት በነዚሁ ሚዲያዎች እንደሰማሁት በርግጥም በወር ብር አራት መቶ ሺ ነው እንዴ???…(የመጀመሪያውና ባለ530 ሺው ቤት ምናልባትም “ስለተወደደ” ሊሆን ይችላል እንደተሰረዘ ሰምቻለሁ፡፡)
የሰማሁት ጉድ እውነት ከሆነ አሁኑኑ ተግባራዊ ሊያደርጉት የሚገባዎ አንድ ምክር ልለግሰዎ፡፡ ይህን የምለው በብዙ ምክንያቶች ነው፡፡ ዋናው ግን የራሴው ምክንያት ነው፡፡ ቤቴን ቢጎበኙ – እርግጠኛ ነኝ – “ይቅርብኝ በራሴው ቤት እኖራለሁ” ይላሉ፡፡
ውድ ፕሬዚደንት ግርማ፣