Thursday, October 10, 2013

Ethiopian Government Choking Muslim Unrest

October 10, 2013Independent European Daily Express
ADDIS ABABA, Oct 10 (IPS) – The refusal by the Ethiopian government to redress grievances harboured by the Muslim community here, which comprises about 34 percent of the country’s 91 million people makes this Horn of African nation vulnerable to extremism.Ethiopian Muslims rocked Addis Ababa
“If legitimate grievances are not met there is a risk that extremist violent elements will exploit those grievances to further their own aim,” Mehari Taddele Maru, head of the African Conflict Prevention Programme at the Pretoria-based Institute for Security Studies, told IPS.
Ethiopia’s Muslim community has been taking part in major demonstrations over the last two years against the country’s ruling regime for alleged interference in its religious affairs. The majority of Ethiopians are Christian.

“አንድነት” ፓርቲ የአዲስ አበባ አስተዳደርና ፖሊስን እከሣለሁ አለ

 ባለፉት ሶስት ወራት “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል መሪ ቃል የመጀመሪያ ዙር ህዝባዊ ንቅናቄ ሲያደርግ የቆየው አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ፤ ባለፈው እሁድ የማጠቃለያ ሰልፉን ሲያደርግ ደርሶብኛል ላለው የሞራልና የንብረት ጉዳት የአዲስ አበባ አስተዳደርና ፖሊስን በህግ እንደሚጠይቅ አስታወቀ፡፡ አንድነትና 33ቱ ፓርቲዎች ከትላንት በስቲያ በአንድነት ፅ/ቤት በሠጡት መግለጫ፤ የህዝባዊ ንቅናቄ ማጠቃለያ ሰልፉን መስከረም 19 አዲስ አበባ ላይ ለማካሄድ እንደምንችል የሚያረጋግጥ የእውቅና ደብዳቤ የከተማ መስተዳደሩ የከንቲባ ፅ/ቤት ቢሰጣቸውም፣ በእጅ አዙር ሠልፉ በመስቀል አደባባይ እንዳይደረግ መከልከላቸውን፣ ከህግ ውጪ በፀጥታ ተቋማት አካባቢ ሰልፉ እንዲከናወን መገደዳቸውንና ቅስቀሣ እንዳይደረግ መታገዳቸውን አመልክተዋል፡፡
 

Sunday, October 6, 2013

ሊበሏት የፈለጓትን አሞራ ይሏታል ጅግራ

ሊበሏት የፈለጓትን አሞራ ይሏታል ጅግራ

26351fb59e29fb0a1375427042 October 6, 2013
ባለፈዉ ዐርብ መስከረም 25 ቀን 2006 ዓ.ም. የወያኔዉ ሎሌ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ አዲስ አበባ ዉስጥ ለአገር ዉስጥና ለዉጭ አገር ጋዜጠኞች በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በየእሁዱ ለሚጠሩት ሰልፍ ጥበቃ ማድረግና በየእሁዱ ተመሳሳይ ጥያቄ ማድመጥ መንግስትን ከሚገባዉ በላይ ያሰለቸዉ ስለሆነ እነዚህ አንድ አይነት ጥያቄ ያነገቡ ሰልፎች የሚቀጥሉ ከሆነ የተቃዉሞ ሰልፍ ማድረግ ይከለከላል በማለት ጌቶቹና ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች የመብትና የነጻነት ጥያቄ የሚያነሳ ማንንም ሰዉ ለማሰር፤ ለመደብደብና ለመግደል ያላቸዉን እቅድ በግልጽ ተናግሯል። የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ ባቀረቡ ቁጥር መሪዎቻቸዉ የሚታሰሩባቸዉ፤ አባላቶቻቸዉ የሚደበደቡባቸዉና ቢሯቸዉ ተሰብሮ ንብረታቸዉ የሚዘረፍባቸዉ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ድርጅቶች አንድም ቀን ሰለቸን ሳይሉ ደብዳቢዉ፤ አሳሪዉና የተቃዋሚ ድርጅቶችን ቢሮ እየሰበረ ንብረታቸዉን የሚዘርፈዉ ወያኔ ሰላማዊ ሰልፍ “ሰለቸኝ” ማለቱ ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረግ ምንም አይነት ትግል የሱን የስልጣን “ዘለአለማዊነት” የሚጻረር መስሎ ከታየዉ ምንም ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ የማይመለስ ፀረ ህዝብ ኃይል መሆኑን እንደገና አረጋግጧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ጋዜጣዊ መግለጫቸው (ከፋሲል ግርማ)

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ጋዜጣዊ መግለጫቸው (ከፋሲል ግርማ)

October 6, 2013
ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ከአካላዊ እንቅስቃሴያቸው እና ድምፀታቸው ጀምሮ እስከ ሚቀልዷቸው ቀልዶች እና የሚያስተላልፏቸው መልዕክቶች በሙሉ የቀድሞውን ሟች ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሚያስታውስ መልኩ ያካሄዱት ጋዜጣዊ መግለጫ ባብዛኛው ተቃርኖ የበዛበት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም በጋዜጣዊ መግለጫቸው ከጥያቄ እና መልሱ አስቀድመው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መንግስት ያለውን መረጃ የተናገሩ ሲሆን እንዲሁ በደፈናው አሃዝ ሳይጠቅሱ የሃገሪቱ ምጣኔሃብት እያደገ መሆኑን፤ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ዘርፉ ካለፈው አመት የተሻለ መሆኑን እና በሰላም እና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከጎረቤት ሃገራት ጋር ኢትዮጵያ ያላትን ግንኙነት ለማብራራት ሞክረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ከኤርትራ በስተቀር ከሌሎች ጎረቤት ሃገራት ጋር ያላት ግንኙነት ስትራቴጂካዊ መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለይ የኢትዮጵያ መንግስት ከሶማሊያ መንግስት ጋር ያለውን ግንኙነት ዘርዝረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ቡጂሌው ወያኔ እናት ሀገራችን ኢትዮጵያን ታሪኳን ማንነቷን እያጠፋ የገኛል ስለዚህ ሁሉም የፓለቲካ ድሪጅት አብሮ መስራት ይጠበቅበታል አንድነት ካለ ውጤት አለ አንድነት ካለ ማሸነፍ አለ  አንድነት ካለ ድል አለ አንድነት ካለ ወያኔ ይፈራል  አንድነት ካለ ወያኔ ሀይል  ይለውም አንድነት ካለ  አገራችን ከወያኔ ሥቃይ ትወጣለች ድል ለሀገራችን>

ወያኔን ለማስወገድ አስገዳጅ የትግል ስልት ወሳኝ ነው!!!



      ወያኔን ለማስወገድ አስገዳጅ የትግል ስልት ወሳኝ ነው!!!
ከለምለም አንዳርጌ(ኖርዌይ)
ላለፉት ሁለት አስርተ አመታት ኢትዮጲያና ሕዝቦ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ ይህ ነው የማይባል ግፍና ሰቆቃ ሲፈጽም የኖረው የዘረኛው የወያኔ ስርዓት የእድሜ ዘመኑ ማብቂያ ጠርዝ ላይ ለመሆኑ ኢትዮጲያን ያህል ሃገርና ህዝብ ከሚመራ ስርዓት የማይጠበቁ የማፍያ ተግባራቱ ስርዓቱ ያለበት የዝቅጠት ደረጃ ጠቋሚዎች ናችው፡፡ በእድሜ ዘመን መጀመሪያ በስም እንጂ በተግባር ዴሞክራሲን የማያቀው የአንድ ጎጥ ቡድን ለይስሙላ ባስቀመጠው ህገ-መንግስት የተካተቱትን የዜጎችን መብት በመሻር ሃገሪቱን የምድር ሲኦል አርገዋታል፡፡ በሃገሪቱ ህገ-መንግስት መሰረት መብታቸውን አውቀው የተቋቋሙ የሞያ ማህበራትም ሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶች በራሳቸውም ሆነ በስርዓቱ ተጽእኖ ይህ ነው የማይባል ተግባራት ሳይከውኑ በዘረኛው ስርዓት እየተኮረኮሙ ይፈርሳሉ አልይም በሞኖፖል በተያዘው የፍትህ ስርዓት ተወንጅለው በግፍ በእስር  ይማቅቃሉ፡፡


 

ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ አላደርግም አለች

 

ኢ.ኤም.ኤፍ – ከአፍሪካ ለአለም ዋንጫ ካለፉት አስር አገሮች መካከል፤ ኢትዮጵያ እና ግብጽ ይገኙበታል። እሁድ ኦክቶበር 13 ኢትዮጵያ እና ናይጄርያ – ኦክቶበር 19 ግብጽ ከጋና ጋር ይጫወታሉ። ኢትዮጵያ ከናይጄሪያ ጋር ለምታደርገው ግጥሚያ ከወዲሁ ዝግጅት ላይ መሆናቸው ባለፈ፤ ከሌላ አገር ጋር የወዳጅነት ጨዋታ አላደረጉም። ሱፐር ስፖርት ድረ ገጽ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽንን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ ግን፤ ግብጽ ለኢትዮጵያ ያቀረበችውን የወዳጅነት ጨዋታ ውድቅ አድርጋዋለች።
xz ፌዴሬሽኑ በዚህ ጉዳይ ምላሽ ሲሰጥ፤ “አዎ ከግብጽ በኩል የወዳጅነት ጥያቄ ቀርቦልናል። ሆኖም በግብጽ አገር መረጋጋት የለም። በ እንዲህ አይነቱ አለመረጋጋት በሌለበት አገር ጨዋታ ማድረግ አንችልም። ለነገሩ ከዚህ በፊት እኛ የወዳጅነት ጨዋታ እንዲያደርጉ ጠይቀናቸው ፈቃደኛ አልሆኑም። የአሁኑ የኛ ውሳኔ ለተጨዋቾቻችን ደህንነት ሲባል የተደረገ እንጂ፤ ግብጽን ካለማክበር የመጣ አይደለም።” ብለዋል። በ እርግጥም በግብጽ አገር ባለው አለመረጋጋት ምክንያት ኦክቶበር 19 ቀን ከጋና ጋር የሚደረገው ጨዋታ በዝግ ስቴዲየም ውስጥ እንዲሆን በፊፋ በኩል ተወስኗል። የት ሊሆን እንደሚችል ገና አልታወቀም። ቀኑ ሲደርስ ደግሞ ተመልካች በሌለበት ይጋጠማሉ ማለት ነው። ለጋና ተጫዋቾች ደህንነት ሲባል እስካሁን የትኛው ስቴዲየም እንደሚጫወቱ ይፋ አልተደረገም።
EMF

ጥያቄው ሃይመኖታዊ ነፃነት መብት ወይስ ፖለቲካዊ ……(አቶ ይድነቃቸው ከበደ)

October 5, 2013 ‹‹ መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፤ሃይማኖትም በመንግስት ጣልቃ አይገባም፡፡ ›› ሕገ መንግስት አንቀጽ 11 ንዕሱ አንቀፅ 3 ፡፡ ‹‹ መንኛው ሰው የመሰብ፤የሕሊና እና የሃይማኖት ነጻነት አለው ፡፡ ይህ መብት ማንኛውም ሰው የመረጠውን ሃይመኖት ወይም እምነት የመያዝ ወይም የመቀበል ሃይማኖቱንና እምነቱን ለብቻ ወይም ከሌሎች ጋር በመሆን በይፋ ወይም በግል የማምለክ፣ የመከተል፣የመተግበር ፣የማስተማር ወይም የመግለጽ መብትን ያካትታል፡፡››ሕገ መንግስት አንቀጽ 27 ንዕሱ አንቀፅ 1 ፡፡Yidenachew Kebede

‹‹ ማንኛውም ሰው የሚፈልገውን እምነት ለመያዝ ያለውን ነጻነት በኃይል ወይም በሌላ ሁኔታ ማስገደድ ወይም መከልከል አይቻልም፡፡ ›› ሕገ መንግስት አንቀጽ 27 ንዕሱ አንቀፅ 3 ፡፡
የሙስሊሞች ጥያቄ

1ኛ. በስልጣን ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች ያለምርጫ የመጡና ህዝቡን የማይወክሉ በመሆናቸው ህዝቡ በነፃ ፍላጎቱ፤ በገለልተኛ አስመራጮች እና በመስጂድ ደረጃ በሚመርጡ አመራሮች ይተኩልን፡፡
2ኛ. አህባሽ የተባለው እምነት እንደ ማንኛውም እምነት እራሱን ችሎ የመንቀሳቀስ መብት ይኖረዋል እንጂ በሙስሊሙ መስጂዶችና መዋቅር ውስጥ በግድ እንዲጫን ሊደረግ አይገባውም ፡፡
3ኛ. አወሊያ የህዝብ ንብረት እንደመሆኑ መጠን እራሱን በአግባቡ ማስተዳደር ለማይችለው መጅሊስ መሰጠት የሌለበት ሲሆን ህዝብ በሚመርጣቸው የቦርድ አባላት ይተዳደር ፡፡

እነዚህን ጥያቄዎች ለመንግስት ለማድረስና መፍትሄ ለማፈላለግ ደግሞ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በራሱ ፍቃድ 17 አባላት ያላቸውን ተወካዮች (ከሃገር ሽማግሌዎች፤ ከሃይማኖት ኣዋቂዎች፤ ከምሁራን እና ከሰባኪያን) ጥቆማውን በመቀበል እና ከመላ ሃገሪቱ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የተፈረሙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የድጋፍ ፊርማዎችን በማስረጃነት በመያዝ እነዚህን ሦስት ጥያቄዎች ብቻ በመያዝ ምላሽ ለማፈላለግ ከላይ ታች ሲሉ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሜቴዎች ስምንት ወራት አለፉ፡፡ በሂደቱ ከክፍለ ከተማ እስከ የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት፤ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እስከ ሁሉም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ድረስ እነዚህን ጥያቄዎች በመተንተን በተለያየ ግዜ አቅርበዋል ውጤቱ ግን አራተኛ ጥያቄ ወለደ እሱም፡-
4ኛ. ከላይ ለተዘረዘሩት ጥያቄዎች ለመንግስት ለማድረስና መፍትሄ ለማፈላለግ ሃይማኖታዊ ግዴታቸውን በመወጣታቸው ለእስር የተዳረጉ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሜቴዎች ይፈቱ ፤የሚል ነው፡፡

ሆኖም በምድር ላይ የሚከናወኑ ነገሮች ሁሉ ፖለቲካዊ እንድምታ አላቸው ከሚል የተቆነጠረ ሃሳብ በመነሳት ምክንያቲዊ እና ወቅታዊ ነገሮችን ግምት ውስጥ ሳያስገብ ተቃራኒን ሃሳብ ለማሸነፍ ወይም ድጋፍ ለማግኘት ተብሎ መሰረታዊ የህግ ስእተት እና ፖለቲካዊ ወለምታ ከመዳረግ በፊት በመግቢያነት የተጠቀሱት የህገ መንግስቱ ድንጋጌዎችና የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄ ጎን ለጎን በማስተያየት የተሻለ ሃሳብ እስኪገኝ ድረስ ለድምዳሜ የሚያገለግሉ ናቸው፡፡

በመሆኑም ከላይ የተገለጹት የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄ የመብት ጥያቄዎች ናቸው መብት ደግሞ ከህግ የሚመነጭ ሲሆን የህግ ጥያቄ መጠየቅ በራሱ ፖለቲካዊ ጥያቄ መሆን አይችልም፤የፖለቲካ ጥያቄ መሆን የሚችለው እስላማዊ መንግስት እናቋቁም ወይም ፖለቲካዊ ሥልጣን ይኑረን እና የመሳሰሉት ከሙስሊሙ ማህበረሰብ የተነሱ ሃሳቦች እና በዚህ ምክንያት የደረሰ ጉዳትና እስራት ቢኖር ሂደቱ ፖለቲካዊ ነው ብሎ በመደምድም በጉዳዩ ላይ ከአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት አቋም መያዝ ይቻላል ግን እውነታው የመብት እንጂ ፖለቲካዊ ጥያቄ አለመሆኑ ነው፡፡

በተጨማሪ እነዚህ ግልፅ የመብት ጥያቄዎች በሃይል በመጠምዘዝ ፖለቲካዊ ይዘት ለማላበስ በመንግስት የሚደረገው ጥረት ለማንም ግልፅ ቢሆንም የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄዎች ንፁህ የመብት ጥያቄ ነው፤የፖለቲካ ጥያቄ ነው ለማስባል ተራ አሉባልታ ለማጠናከር ተደጋጋሚ በእውነት ላይ ያልተመሰረተ ዘጋቢ ፊልም በኢቲቪ በማቅረብ ያልተሳካ ጥረት ተደርጓል፤ በቀጣይም ይበልጥ ተጠናክሮ የህዝብን አንድነትን ሊንዱ በሚችሉ መልኩ ተቀነባብሮ ሊቀርቡ እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡

ይሁን እንጂ ከሃይማኖታዊ መቻቻል ባለፍ ሃይማኖታዊ መከባበር ላይ የተመሠረተ ግንኝነትን ባዳበር ህዝብ መካከል አንዳችም አስፈሪ ነገር እንደማይኖር ይገመታል፤ለዚህም ጥሩ ማሳያ የሚሆነው የሙስሊሙ ማህበረስብ ጥያቄ ከእምነት ነፃነት መብት የመነጨ ጥያቄ መሆኑን በመረዳት የሌላ እምነት ተከታይ ለሙስሊም ማህበረሰብ ጥያቄ ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያለሆነ ድጋፍ በመስጠት ላይ ይገኛል ይህ ደግሞ የመንግስትን አፍራሽ ተልኮ ያጋለጠ ነው፡፡

በመሆኑም የሙስሊሞች ጥያቄ ከህገ መንግስቱ ጋራ ሲመሳከር ሙሉ በሙሉ የመብት ጥያቄ ነው ለዚህም ነው ከአንድ ዓመት ከ 6 ወር በላይ ‹‹ ፍትህ ፍትህ ፍትህ ፍትህ………. ›› ሲሉ የከረሙት መንግስት ደግሞ በተቃሪኒው ‹‹ የሃይማኖት አክራሪነት ለማስፋፋት እና ድብቅ ፖለቲካዊ አጀንዳቸውን ለማስፈጸም የሚጥሩ ›› በማለት እየወነጀላቸው ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ የሙስሊሞች ጥያቄ ሃይማኖታዊ ጥያቄ ነው፡፡ ስለሆነም የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄ እና የመንግስት ተሳትፎ በማስተያየት ጥያቄው ሃይማኖታዊ እንጂ ፖለቲካዊ ላለመሆኑ እነዚህን ማስረጃዎችን መመልከት ተገቢ ናቸው፡-

1ኛ. መንግስት በቀጥታ እጁን በማስገባ የመጅሊስ ምርጫ በቀበሌ እና በመንግስት ካድሪዎች እንዲካሄድ አድርጓል፡፡የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄ ደግሞ የመጅሊስ ምርጫ በተቻለ ፍጥነት እና በገለልተኛ አስመራጭ አማካኝነት ምርጫ መካሄድ የሚኖርበት ሲሆን ጉዳዩም ሃይማኖታዊ እንጂ ፖለቲካዊ ባለመሆኑ በመስጂድ ሊካሄድ ይገባዋል፡፡

2ኛ. አህባሽ የተባለው እምነት ሸኽ አብደላ አልሃረሪ በሚባሉ የሚመራ እምነት በመንግስት ልዩ ድጋፍ ተደርጎለት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትሩ በወኑት ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም አማካኝነት ሃምሌ 2003 ዓ.ም በጊዮን ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ‹‹ይህንን አመለካከት በሃገራችን ለማስፋፋት እንዴት ብንሰራ ይሻላል በሚል መንግስት ለረጅም ግዜ ሲመክር ቆይቷል›› በማለት በሰጡት ሰፊ ጋዜጣዊ መግለጫ የአህባሽ እምነት ከመንግስት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ከመኖሩ ባለፈም አስተምህሮቱን መንግስት ለማስፋፋት ፍላጎት እንዳለው የሚያሳይ ነው፡፡ የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄ ደግሞ መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፤ሃይማኖትም በመንግስት ጣልቃ አይገባም፡፡ የሚለውን ህገመንግስታዊ ድንጋጌ ተጥሷል በተጨማሪ አህባሽ የተባለው እምነት እንደ ማንኛውም እምነት እራሱን ችሎ የመንቀሳቀስ መብት ይኖረዋል እንጂ በሙስሊሙ መስጂዶችና መዋቅር ውስጥ በግድ እንዲጫን ሊደረግ አይገባውም ፡፡

3ኛ. አስተዳደራዊ የሆነ ጥያቄ ሲሆን እሱም አወሊያ ት/ት የህዝብ ንብረት እንደመሆኑ መጠን እራሱን በአግባቡ ማስተዳደር ለማይችለው መጅሊስ መሰጠት የለበትም ህዝብ በሚመርጣቸው የቦርድ አባላት ይተዳደር የሚለው የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄ ነው ፡፡ ይህን ጥያቄ በሁለት መንገድ ማየት ይቻላል አንድም መጅሊሱ የሙስሊሙ ማህበረስብ ውክልና እንደሌለው ሁለተኛ ደግሞ የአወሊያ ት/ት አስተዳደር ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለው እንዲሆን ካስፈለገ የተለያዩ መመዘኛዎችን መሰረት በማድረግ ህዝብ በሚመርጣቸው የቦርድ አባላት ይተዳደር የሚል ነው፡፡

4ኛ. ከላይ የተዘረዘሩት ችግሮችን ለመግለፅ እና ለችግሮቹሁ መፍትሔ ለማፈላለግ የተመረጡ የኮሜቴ አባላት ከመንግስት ተወካዬች ጋር በተደጋጋሚ በመገናኘት ጥያቄው ሃይማኖታዊ መሆኑ እና መፍትሔም ሊገኝለት የሚችለው ሃይማኖታዊ በሆነ መንገድ ብቻ መሆኑን ሲያስረዱ ሰንብተዋል፤ መንግስትም በጉዳዩ ላይ ከኮሜቴ አባላት ጋር ሲደራደር ቆይቷል፡፡ይሁን እንጂ መንግስት በስተመጨረሻ ካፈርኩ አይመልሰኝ በሚል ተልካሻ አስተሳሰብ በመነሳት የኮሜቴ አባላትን በሽብርተኝነት ስም ከሶ ለእስር ዳረጋቸው፡፡

ይሁን እንጂ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄ ሲመረመር በየትኛውም መመዘኛ የሃይመኖት ነፃነት መብት ጥያቄ ነው ፤ በመንግስት በኩል ደግሞ እየሆነ ያለው ፖለቲካዊ አካሄድ ነው ለዚህም ነው ጥያቄችን ሃይማኖታዊ እንጂ ፖለቲካዊ አይደለም በማለት ከመናገር እና ከመፃፍ ባለፈም ሰላማዊ በሆነ መንግድ በተለያ ቦታና ጊዜ ድምፃቸውን ሲያሰሙ የከረሙት፡፡ የነገሩ አካሄድ እንዲ በሆነበት ሁኔታ የሙስሊሞች ጥያቄ የፖለቲካ ጥያቄ ነው በማለት ከፖለቲካ ፓርቲ መገለጹ ከስእተትም በላይ ስእተት ነው፤ ነገ ደግሞ ከችግሩ ለመላቀቅ በአቻነት አብረን እንስራ ወደሚል ጥያቄ እንዳያመራ ያሰጋል ፡፡ ነግር ግን በህገ መንግስቱ የተቀመጡ መብቶች እንዲከበሩ አደርጋለው ለዚህም ድጋፋቹሁን ስጡኝ ብሎ የፖለቲካ አጀንዳ አድርጎ መታገል እና ጥያቄ ማቅረብ ከፖለቲካ ድርጅቶች የሚጠበቅ ተግባር ነው ፡፡
Yidenachew-Kebede

No Human Rights = No Development

September 26, 2013

Oakland Institute and the Housing and Land Rights Network Submit Human Rights

መሬት የማን ነው?

ክፍል አንድ – ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
land
October 6, 2013 10:53 
አገር ማለት በአባቶች፣ በአያቶችና በቅድማያቶች አጥንትና ደም ተገንብቶ የታጠረ መሬት ነው፤ የዶር. በድሉ ዋቅጅራን ዋይታ እየኮረኮረ የሚያወጣውና የሚያስተጋባው የፍቅር ስሜት ምንጭ ነው።
የተከሰከሰውና ተፈረካክሶ አፈር የሆነው አጥንትና የወረደው የአያቶችና የቅድማያቶች ደም እየፈሰሰ መሬቱ ላይ በሚገኙ ወንዞች ውስጥ ሁሉ ገብቶአል፤ እንዲያውም እነዚህ ወንዞች ወስደው በቀይ ባሕር፣ በሜዲቴራንያን ባሕርና በሕንድ ውቅያኖስ ጨምረውታል፤