Tuesday, June 25, 2013

አዲስ መጽሀፍ፣ “ድርጅታዊ ምዝበራ” (በአክሎግ ቢራራ)

ዶክቶር አክሎግ ቢራራ በዚህ መጽሃፍ በማያሻማ ቋንቋ የኢትዮጵያን ሕዝብ የፖለቲካ፤ የኢኮኖሚ፤ የሶሻልና በአጠቃላይ የሕብረተሰቡን ከአስተዳደር ብልሹነት የመነጩ ውስብስብ ችግሮች፤ በጥናት፤ በምርምርና በማስረጃ የተደገፈ ትንተና አቅርበዋል።

 
 

አንዲት የኮንትራት ሰራተኛ በጅዳ ቆንስል በር ታንቃ ሞተች

አንዲት የኮንትራት ሰራተኛ በጅዳ ቆንስል በር ታንቃ ሞተች

(ነቢዩ ሲራክ)
ethio maids
በጅዳ መጠለያ አንዲት የኮንትራት ሰራተኛ በጅዳ ቆንስል በር ታንቃ ሞተች
በሪያድ “ኢትዮጵያዊቷ አሰሪዎቿን ለመበቀል የ6 አመት ህጻን ገደለች” የሳውዲ ጋዜጣ ዘገባ


Monday, June 24, 2013

አቶ ገብረመድህን አርአያ የዘማናችን አሉላ አባ ነጋ ተብለው በከፍተኛ ክብር ተሰየሙ

አቶ ገብረመድህን አርአያ የዘማናችን አሉላ አባ ነጋ ተብለው በከፍተኛ ክብር ተሰየሙGebremedhin Araya, awarded in Australia

June 24, 2013 በምእራብ አውስትራሊያ በፐርዝ ከተማና አካባቢዋ ኗሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ጁን 23 ቀን 2013 ባደረጉት ልዩ ዝግጅት ታዋቂውን የነፃነት ተፋላሚና የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጅ አቶ ገብረመድህን አርአያን የዘመናችን አሉላ አባ ነጋ በማለት በክብር ሰይመዋቸዋል። በዚህ ለእርሳቸው ታስቦ በተደረገው ልዩ የእራት ግብዣ ስነ ስርዓት ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን የተገኙ ሲሆን፣ እንግዶቹ ለአቶ ገብረመድህን አርአያ ያላቸውን ልዩ ክብርና አድናቆት በየተራ እየተነሱ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። በዚሁ መሰረትም አቶ ገብረመድህን ህወሓት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ይዞ የተነሳውን እኩይ አላማና ተግባር በማጋለጥ ያደረጉት ጉልህ አስተዋጽኦ፣ በተለያዩ የሚዲያ ዘርፎች በመረጃ የተደገፉ መግለጫዎችን እና ትምህርቶችን በመስጠት የከወኗቸው ሥራዎች፤ እንዲሁም ለእሩብ ምእተዓመታት ያህል በጽኑነት፤ በቆራጥነትና በሕዝብ ወገናዊነት መቆማቸው በምሳሌነት በጉልህ ተጠቅሰዋል።
ለአቶ ገብረመድህን ማህበረሰቡ በጋራ ባዘጋጀው በዚሁ ስነስርዓት ላይ በአረንጓዴ፤ ቢጫና ቀይ ቀለማት በደመቀ የኢትዮጵያ ሙሉ ካርታ ላይ የጀግናው ራስ አሉላ አባነጋ ምስል የተቀመጠበት የታሪክ ማስታወሻ ከታላቅ አክብሮት ጋር ተበርክቶላቸዋል። እንዲሁም ግለሰቦች በራሳቸው አነሳሽነት ያዘጋጁላቸው የተለያዩ ሽልማቶች ተበርክተውላቸዋል።

የትኛው አማራጭ ለአሜሪካ? “ኢህአዴግን ምን እናድርገው? ንገሩን!”

የትኛው አማራጭ ለአሜሪካ? “ኢህአዴግን ምን እናድርገው? ንገሩን!”

 
 
አሜሪካ ከመቼውም ጊዜ በላይ ደንግጣለች። ኦባንግ እንዳሉት ለህዝባቸው “ሬት” ለምዕራባውያንና “ማር” (የቤት ቀጋ፤ የውጭ አልጋ) የነበሩት አምባገነን በድንገት እንደ ተነቀለ ቡሽ ተስፈንጥረው ከሲስተም መውጣታቸው አሜሪካንን አስጨንቋታል። በተለይም እሳቸው አፍነው የያዙት የስርዓቱ “ክፉ ጠረን” አሁን እነርሱ (አሜሪካውያኑ) ደጅ የደረሰ ያህል መፍትሄ ለመፈለግ የወሰኑ ይመስላሉ። አውቀውና ፈቅደው ሲታለሉ የቆዩበትን ጊዜ አስልተው መንገዳቸውን የማስተካከል ስራ የጀመሩት ዛሬ አይደለም። አንዳንድ ምንጮች እንደሚሉት ከመለስ ሞት በኋላ አሜሪካ በምስራቅ አፍሪካ ላይ ሚዛኗን ሊያስታት የሚችል ውድቀት የሚደርስባት ኢትዮጵያ ላይ ያላትን አቋም ማስተካከል ሲያቅታት ብቻ እንደሆነ ይናገራሉ።

 

Sunday, June 23, 2013

ኮረዳይቱ ወደ ሀገሯ ልትመለስ ነው!

ኮረዳይቱ ወደ ሀገሯ ልትመለስ ነው!

ኮረዳይቱ ወደ ሀገሯ ልትመለስ ነው!
994174_561097347267400_570836208_n
 “አለን” የምን
ለው ካርቶኒስት አሌክስ እንዲህ ስሏል!
እኛም ለጊዜው እንዲህ ለጥፈነዋል፡፡ ጭማሪ ካለን ተመስጦ አድርገን እንመለሳለን!

ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. እና ኢትዮጵያ

ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. እና ኢትዮጵያ

tplf addis
ወደ ግንቦት 20ቀን, 1983 ዓ.ም. ከመግባታችን በፊት ትንሽ ወደ ኋላ መለስ በማለት የደርግ ስርዓትን በትንሹ እንቃኘው::
ደርግ
የካቲት ወር 1966 ዓ.ም. የዘውድ አገዛዙን ስርዓት በመቃወም በአርሶ አደሩ ፣ በተማሪው ፣ በአስተማሪው ፣ በመንግስት ሰራተኛው ፣ በወዛደሩ ፣ በነጋዴው እና በመለዮ ለባሹ ወዘተ ፣ ወዘተ የተቀጣጠለው ህዝባዊ አመጽ ጊዜ ሳይወስድበት በ6 ወራት ውስጥ የተነሳው ህዝባዊ አመጽ ግቡን መታ::

ህዝባዊ አመጹን የሚመራው የተደረጀ ፓርቲ ባለመኖሩ በር የተከፈተለት መለዮ ለባሽ አመቺ ሁኔታ በማግኘቱ በፍጥነት ተደራጅቶ ከተራ ወታደር ጀምሮ የተለያዩ ማእረግ ያላቸው አባላቱን አስመርጦ ወደ 120 የሚጠጉ ተወካዮቹን አዲስ አበባ በሚገኘው አራተኛ ክፍለጦር አሰባሰበ::


ከጦር ሃይሎች ፣ ከክቡር ዘበኛ እና ከፖሊስ የተውጣጡት እንኚሁ መለዮ ለባሾች በሰኔ ወር 1966 ዓ.ም. ተሰብስበው ብሄራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ መስርተው “ኢትዮጵያ ትቅደም ፣ አቆርቋዥ ይውደም” በሚል መርህ ስር ሰፊ ሊባል የሚችል የህዝብ ድጋፍም አግኝተው ነበር::

መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም. የተመሰረተው አስተባባሪ ኮሚቴ ንጉሱን ከስልጣን አውርዶ “ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ” የሚል ስም በመያዝ ኢትዮጵያን ማስተዳደር ጀመረ:: ቀስ በቀስም ደርግ የስልጣን ወንበሩን በማመቻቸት የሃገሪቷ መንግስት ለመሆን ቻለ::


በወቅቱ በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች ሃገራት ሶሻሊዝም ወይም ህብረተሰባዊነት በሚባል ርዕዮተ አለም እድገት እና ብልጽግና የማይገኝበት “ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን የማላይ” ስርዓት በቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት እና ቻይና ፕሮፖጋንዳ አለምን እንደማዕበል ሲወዘውዛት የነበረበው ሁኔታ ሆኖ በደርግ የተመሰረተው መንግስት ግራና ቀኙን ሳይመለከት ሶሻሊዝም በኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈጥረውን ቀውስ እና ችግር ሳያጤን እና ኢትዮጵያውያን ሊቃውንትን ሳያማክር በ1972 ዓ.ም. ኢሰፓአኮን(የኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲ አደራጅ ኮሚሽን) መሰረተ:: ይህንን ምስረታ ተከትሎም ደርግ አንድ እግሩን ገደል ከተተው::
በዚህ ጽሁፍ ሁለት ነገሮችን ለያይቼ በማሳየት ለማለፍ እሞክራለሁኝ፤

የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ከኃላፊነታቸው ተነሱ

የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ከኃላፊነታቸው ተነሱ

 የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ከኃላፊነታቸው ተነሱ

- ከምኒልክ ሆስፒታል ጥገና ጋር በተገናኘ መሆኑ ተጠቁሟል
በቅርቡ የተቋቋመው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙት አቶ ፈለቀ ኃይሌ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ታወቀ፡፡


በአቃቤ ሕግና በፍረድ ቤቱ መካከል አለመስማማት እየነገሰ መሆኑ ተሰማ!

በአቃቤ ሕግና በፍረድ ቤቱ መካከል አለመስማማት እየነገሰ መሆኑ ተሰማ!

ቅዳሜ ሰኔ 15/2005
‹‹ዳኞቹ እናንተ ናችሁ እኛ?›› ከዳኞቹ መካከል አንዱ ለአቃቤ ሕጎቹ ከተናገረው!
የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የክስ ሂደትን ታክኮ በአቃቤ ሕግና በዳኞች መካከል አለመስማማት መፈጠሩ ተነገረ፡፡ አለመስማማቱ የተፈጠረው አቃቤ ሕግ ለተደጋጋሚ ጊዜ በችሎት ውስጥ ከዳኞች ጭምር የበላይ መሆኑን ለማሳየት ጥረት በማድረጉ ነው ተብሏል፡፡ በዚሁ እያገባደድነው ባለው ሳምንት ተሰይሞ ምንም ሳያከናውን ተበትኖ በነበረው ችሎት ላይ አቃቤ ሕግ ቀድሞ ለፍርድ ቤት ሪጂስትራ ገቢ ማድረግ የነበረበትን ሲዲ እዚያው ለችሎቱ ገቢ ለማድረግ መሞከሩና ሲዲውን ገቢ ማድረግ የነበረበት ክሱ በተመሰረተበት ወቅት ማለትም (ከስድስት ወራት በፊት) ሆኖ ሳለ እስከአሁን ሳያስገባ መቆየቱ በዳኞቹና አቃቤ ሕጎቹ መካከል ፍጥጫ ጭምር እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል፡፡
 
 

ፕ/ት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የሌባ ተባባሪነት ለመደባቸው

ፕ/ት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የሌባ ተባባሪነት ለመደባቸው

Posted: June 23, 2013 in Amharic News
0
11
ከጥቂት ሳምንታት በፊት ዘ-ሐበሻ የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ሊቀትጉሃን አስታጥቄ አባተ አቅመ ደካማ ለሆኑ አባት አርበኞች የፈቀዱላቸውን 25 ኮንዶሚኒየም ቤቶች ለግል ጥቅም አውለዋል፣ ከሚያከራዩዋቸው ሕንፃዎች ከሚያገኙት ገቢ ላይ የአከራይ ተከራይ ግብር አለመክፈል፣ ያላግባብ ወጪ ማድረግና በመሳሰሉት ተጠርጥረው መከሰሳቸውን መዘገቧ ይታወሳል። ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ታትሞ የወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ “ፕሬዚዳንት ግርማ የአርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ክስ እንዲቋረጥ ጥሪ ማቅረባቸውን” ያትታል። ዜናውን ለተመለከተ ከዘራፊው የወያኔ ስርዓት ጋር በመተባበር “አበባ የመትከልና አበባ የመቁረጥ ስልጣን” ብቻ ተሰጥቷቸው ቁጭ ያሉት ፕሬዚዳንቱ እኚህን በርከት ያሉ አርበኞች አባቶችን ያስለቀሱትን ሊቀትጉሃንን ክሳቸው ተቋርጦ ይፈቱ ሲሉ በድፍረት መጠየቃቸው የሌባ ተባባሪነቱ ለመደባቸው፤ ወይም ከሌባ ጋር መተባበር ሱስ ሆነባቸው እንዴ? ያስብላል። የሪፖርተር ዜና እንደሚከተለው ነው። አንብቡትና ትዝብታችሁን ጣሉበት።