Friday, June 7, 2013

The Anguish of Higher Education Students in Ethiopia

Academic activities such as studying, teaching, inventing, leading, ahttp://ethiopia.ecadf.netdna-cdn.com/wp-content/uploads/2013/01/Addis-Ababa-University.jpgdministrating and other responsibilities in a university or college require at a minimum academic freedom. Unfortunately, however, academic freedom in higher education institutions of Ethiopia is drier than the Sahara desert. Ethiopians who have been part of these institutions as a student, teacher, or any other workers have been grilled by this desert. Although, no one can tell better than we, the victims of this inferno; national and international human rights organizations have documented the absence of freedom of expression, association, and assembly in the colleges and Universities of Ethiopia(1).

፨፨፨የዘራነውን እናጭዳለን!፨፨፨

፨፨፨የዘራነውን እናጭዳለን!፨፨፨
ሰሞኑን አብዛኛው ኢትዮጵያ ፌስቡከኛ ግብፅ ላይ ሲሸልልና ሲፎክር ነው የሰነበተው "አዝምቱን አታስጨርሱንም" ያሉም አልጠፉም። የዛሬዋ "ግብፃችን" ደግሞ "ቤተልሄም አበራ" የተባለች ወጣት ናት "ኢትዮጵያን አዋረደች" ተብላ ውግዘት እየደረሰባት ነው የአገሬ ፌስቡከኛ ሆየ "መብቷ ነው" እንዲሁም "ኢትዮጵያን አትወክልም ይች ሀገር አሰዳቢ" እያለ ይነታረካል።የልጅቷን የብክነት ቪዲዮን እኔም እንዳየሁት ያማል ያበሳጫል ነገር ግን "ኢትዮጵያ መዋረድ" ዛሬ የጀመረች ይመስል "የኢትዮጵያን ውርደት" በሙሉ ቤተልሄም ጫንቃ ላይ ማሳረፍ አግባብ አይመስለኝም ።እጅግ ቢመረንም እንዋጠው "ቤተልሄም የዚህ ማህበረሰብ ውጤት ናት"። አይናችንን ጨፍነንና ጆሮችንን ደፍነን አላይም አልሰማም ካላልን በስተቀር ኢትዮጵያችን "በወሲብ አብዮት" መናጥ ከጀመረች እኮ ቆየች!የግል ኤፍኤሞች ግራ የገባቸው ጋዜጠኞች ከእኛ በተሰበሰበ ቀረጥ የሚተዳደሩት ሚዲያዎች ሳይቀር ሌት ተቀን የሚለፉት ትውልድን ቀራጭ በሆኑ ፕሮግራሞች እኮ አይደለም ሁሌም የሚሰብኩት ስለልቅነት ነው በግልፅነት ሽፋን አፈንጋጭ የወሲብ በሀል ነው ሀገራችንን የወረራት።አዲስአበባ እና ብዙ የክልል ከተሞች ሲናጡ የሚያድሩት በወሲብ ገበያ እንደሆነ እረሳነው!? እለት እለት ሀገሪቷን እያጥለቀለቁ ባሉት ጫት ቤቶች፥ማሳጅ ቤቶችና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እራቁት ዳንስ ቤቶች ምን ሲሰራ እንደሚዋልና እንደሚታደር ለማንም ግልፅ ነው።በገፅታ ግንባታ ስም ሀገራችን እንደ ታይላንድ የአፈንጋጭ "የወሲብ ቱሪስቶች" መናሃሪያ ከሆነች ሰነበተች።ሌላውን እንተወውና ፌስቡክ እንኳን "ልቅ ወሲብ" ያሰከራቸው ስንት የመከኑ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ ለመታዘብ ቀላል ነው አስታውላችው ካያችው ብዙ የፌስቡክ ፍሬንድ ያሏቸው፣ገጻቸው በብዙ ሰው ላይክ የተደረገና ብዙ አባላት ያሏቸው ግሩፖች ቁምነገር የሚያወሩ ስለፖለቲካዊ ለውጥ የሚያወሱት ሳይሆኑ ነፃነትን ሳይሆን ልቅነትን የሚያስፋፉት "አፈንጋጭ የወሲብ አብዮተኛ" የሆኑት ኢትዮጵያውያን ናቸው ።በየውርደታችን ከመጯጯህ ሰከን ብለን ለምን ተዋረድን ብለን እንጠይቅ።በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ለዜጎቹ የሚቆረቆር መንግስት ፤ ለትውልዱ ስብዕና የሚታትር የሀይማኖት አባት፤ ለዜጎቹ ጠቃሚ መረጃ የሚሰጡ የሚዲያ ተቋም ወዘተ የሉንም አንድ ታዳጊ ወጣት ቀና ብላ/ብሎ የምታየው/የሚያው አርእያ በሀገራችን ከጠፋ ሰነበተ።ቆም ብለን ልቦና ሰጥቶን የሀገራዊ ችግሮቻችን ምንጭ ለይተን ካላወቅንና መፍትሄ ካልፈለግን ነገም እንደ ቤቲ ያሉ ኢትዮጵያውያን የዘራነውን ያሳጭዱናል እንደ ሀገርም የያዝነው የቁልቁለት ጉዞ እናጠናክራለን።

Tuesday, June 4, 2013

ምከረው ምከረው እምቢ ካለ ሞክረው…

945562_456214187800412_886270627_nእኔ እኮ ሁልጊዜ ግራ የሚገባኝ አቶ ሽመልስ ከማልን በእንዲህ ያለው ጉዳ ላይ ለምን እንደሚያጋፍጧቸው ነው፡፡ እርሳቸውስ ቢሆኑ አሁንስ አበዛችሁት ራሳችሁ ተናገሩ አይሉም እንዴ…!

Friday, May 31, 2013

ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋሁን ቤንሻንጉል-ጉምዝ ውስጥ ታስሯል



ቤንሻንጉል-ጉምዝ

ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋሁን ቤንሻንጉል-ጉምዝ ውስጥ ታስሯል

“ኢትዮ-ምኅዳር” ለሚባለው ሣምንታዊ ጋዜጣ ከአማራ ክልል ሲዘግብ የቆየው ሙሉቀን ተስፋሁን በቤንሻንጉል-ጉምዝ ፖሊስ መያዙን የጋዜጣው ምንጮች አስታወቁ።
የቤንሻንጉል-ጉምዝ ወረዳዎች
ቤንሻንጉል-ጉምዝ

“ኢትዮ-ምኅዳር” ለሚባለው ሣምንታዊ ጋዜጣ ከአማራ ክልል ሲዘግብ የቆየው ሙሉቀን ተስፋሁን በቤንሻንጉል-ጉምዝ ፖሊስ መያዙን የጋዜጣው ምንጮች አስታወቁ።

ሃምሳም ሰውም ይውጣ ሃምሳ ሺህ ግን አንድ ፀባይ እሱም “ፍፁም ሰላማዊ!”

935293_421802944584325_731290226_nአቤት የርዕሴ ርዝመት… ደግሞ በዛ ላይ ቀጥሎ የምናገረውን ማሳበቁ! “ቢወዳት ነው ቢጠላት ባሏ በሻሽ አንቆ ገደላት” አይነት ሆነኮ፡፡
ለማንኛውም ቀጥሎ ስለ ሰላማዊ ሰልፉ ጥቂት ልናወጋ ነው፡፡ በአማርኛ፣ በኦሮምኛ፣ በትግርኛ እና በጥቅሉ በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ስለ ሰላማዊ ትግል ስናወራ ስለ ሙስሊም ኢትዮጵያውን በማውራት ብንጀምር የወጋችንን ደረጃ ከፍ ደርገዋል ሞገስም ይሰጠዋል እና  እንቀጥል…

Wednesday, May 29, 2013

“አባይ ይገደብ፤ ኢህአዴግም ይገደብ፤ አባይ ይቀየስ ኢህአዴግም ይቀየስ!”

bereket_simon“የዘመናት ብሶት የወለደው ጀግናው የኢህአዴግ ሰራዊት ከዚህ በፊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የሬድዮ ጣቢያ ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ተቆጣጥሮታል፡፡ ጉንቦት ሃያ ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስት አመተ መህረት!” አለ ታጋዩ…
“የዘመናት ብሶት የወለደው ጀግናው የኢህአዴግ ሰራዊት ከዚህ በፊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የሬድዮ ጣቢያ አሁን ደግሞ ለራሱ ጥቅም ተቆጣጥሮታል፡፡ ቆጣጥሮታልም፤ ግንቦት ሃያ ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስት አመተ መህረት!” አልኩ እኔ…
“ኢህአዴግ ደርግን ደመሰሰ እና ሌላ ቀዳበት”  አለ ልጅ ያሬድ!  ”ኢህአዴግ ደርግን ደምስሶ በደርግ ዜማ ሌላ ቀዳበት” አልኩ እኔ
ዛሬ ግንቦት ሃያ ነው፡፡

ማንዴላ በመጨረሻዋ የፍርድ ቀን ለዘረኞች ያለው

ኢትዮጵያን በቁጥጥሩ ስር ያዋላት የትግራይ ዱር አራዊት ቡድን ዛሬ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየጫነ ያለውን የአፓርታይድ አይነት ስራት እነ ኒልሰን ማንዴላ ከደቡብ አፍሪካ ምድር ከስሩ መንግለው ለመጣል እጅግ ብዙ መስዋእትነትና ምእተ አመት የሚጠጋ ጊዜ ነበር የወሰደባቸው።Former South African president Nelson Mandela
የደቡብ አፍሪካውን የጥቂት ነጮች አፓርታይ መንግስት ለማስወገድ ኤ ኤን ሲ በ1912 ዓም ኢ ኤ አ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ከአርባ አመት በላይ ሰላማዊ የትግል ስልት ነበር ሲከተል የቆየው። ህዝባዊ እንቢታ፤ እቤት የመዋል አድማ፤ የሥራ ማቆም አድማ፤ ይለፍ ወረቀት ሳይዙ በጅምላ ሆ ብሎ የተከለከለ ቦታ ሄዶ መታሰር፤ ወዘተ…. ያሁሉ ግማሽ ምእተ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ የተካሄደው ሰላማዊ ትግል የህዳጣኑን መንግስት ጭቆናና ጭካኔ አባባሰው እንጂ ለደቡብ አፍሪካ ህዝብ የፈየደው ነገር አልነበረም።
ኋላ ላይ ግን እነማንዴላ ሀሳባቸውን ለመቀየር ተገደዱ። ሰላማዊው ትግል በትጥቅ ትግል መደገፍ እንዳለበት አመኑ። ይህንንም ወሰኑ። የሽምቅ ውጊያ ለመጀመር በርካታ የ ኤ ኤን ሲ ታጋዮች ማንዴላን ጨምሮ ወደተለያዩ ሀገሮች ለወታደራዊ ስልጠና ተሰማሩ። ማንዴላም ወደ ኢትዮጵያ አቀና። እናም እ ኤ አ በ1961 ዓም የ ኤ ኤን ሲ ወታደራዊ ክንፍ በማንዴላ መሪነት ተመስርቶ በመንግስቱ የኢኮኖሚና ወታደራዊ ተቋማት ላይ አደጋ መጣል ጀመረ።

Sunday, May 26, 2013

የሰበሩ ዝርዝር፤ ብራቮ ከንቲባ…. ብራቮ ሰማያዊ!!!

968802_418767841554502_16363769_nየሰበሩ ዝርዝር፤ ብራቮ ከንቲባ…. ብራቮ ሰማያዊ!!!
ለሚመለከተው አካል ማመልከቻ ቢያሰገባም ደብዳቤውን አንቀበልም የተባለው ሰማያዊ ፓርቲ በእማኞች ፊት ማመልከቻውን አስገብቶ ለከንቲባ ጽ/ቤትም አቤት ብሎ ነበር፡፡ እኛም ይህንን አስመልክቶ በጠዋቱ ዜና በጨዋታችን እንዲህ ብለን ነበር….
…..የጽ/ቤቱ ሃላፊዎች ለምን ደብዳቤውን አንቀበልም እንዳሉ እንጃላቸው… ምናልባት እነርሱም በመንግስታቸው የተከፉበት ጉዳ ይኖራል፡፡ (ይቺ የግዳጅ ቦንድ ግዢ እኮ ሰራተኞች የስራ ተነሳሽነት ላይ ከባድ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ነው ያላት….) የምሬን ነውኮ… እነዚህ ሃላፊዎች በመንግስታቸው ላይ ቅሬታ ባይኖራቸው ኖሮ ደብዳቤውን ተቀብለው …
ለሰማያዊ ፓርቲ ባሉበት፤